uk
Feedback
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Відкрити в Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Показати більше
8 843
Підписники
+824 години
+237 днів
-3530 днів
Архів дописів
​ኢማም ኢብኑል ቀዪም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ ​«ከሸይጣን ታላላቅ ተንኮሎች መካከል አንዱ፡ ለአሽራኮች (ለአጋሪዎች) ሰዎች የሚያከብሩትን የተከበረ ቀብር ያቆምላቸዋል። ከዚያም ከአላህ ውጭ የሚመለክ ጣዖት ያደርገዋል። በመቀጠልም ወደ ወዳጆቹ (እንዲህ ሲል) መመሪያን ያስተላልፋል (ያጠናውታል)፦ “ይህን ቀብር ከመመለክ፣ (በዓል ተደርጎ) መፋሰሻ ከመደረግና ጣዖት ሆኖ ከመያዝ የከለከለ ሰው፤ እርሱማ የሟቹን ደረጃ አሳንሷል፣ ሐቁንም በድሏል (አጉድሏል)” ይላቸዋል። ​በዚህም ምክንያት እነዚያ መሃይም የሆኑት አሽራኮች ያንን ሰው ለመግደልና ለመቅጣት ይጣጣራሉ፣ ያከፍሩታልም። እሱ በአጋሪዎች ዘንድ ያለበት ወንጀል፡ አላህና መልክተኛው ያዘዙበትን ማዘዙ፣ እንዲሁም አላህና መልክተኛው የከለከሉትን መከልከሉ ብቻ ነው፤ ይኸውም ቀብሩን ጣዖትና (የአምልኮ) በዓል ከማድረግ፣ በላዩ ላይ መብራት (ሻማ) ከመለኮስ፣ በላዩ ላይ መስጊዶችንና ጉልላቶችን (ቁባዎችን) ከመገንባት፣ በኖራ ከመለሰን፣ ከፍ አድርጎ ከመገንባት፣ ከመሳም፣ (በረካ ለመፈለግ) ከመሻሸት፣ እርሱን (ቀብሩን) ከመለመን፣ ወይም በርሱ (በሟቹ ጃህ) ከመለመን፣ ወይም ወደ እርሱ (ለዚያ ተብሎ) ጉዞ ከመጓዝ፣ ወይም ከአላህ ውጭ ከእርሱ እገዛን ከመጠየቅ (ኢስቲጋሣ ከማድረግ) መከልከሉ ነው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች አላህ መልክተኛውን የላከበትን አላማ — ይኸውም ተውሒድን ለአላህ ብቻ ማጥረትንና ከአላህ ውጭ ሌላ እንዳይመለክ የተላኩበትን መሰረት — የሚፃረሩ መሆናቸው ከእስልምና ዲን በግልጽና በግድ (በአስገዳጅ እውቀት) የሚታወቁ ጉዳዮች ናቸው። ​ተውሒድን አጥባቂው (ሙዋሒዱ) ሰው ይህንን በከለከለ ጊዜ አሽራኮች ይቆጣሉ፣ ልቦቻቸውም ይሸበራሉ (ይጸየፋሉ)። እንዲህም ይላሉ፦ “እርሱማ የከፍተኛ ማዕረግ ባለቤቶችን (ደረጃ) አሳንሷል፤ ለእነርሱ ምንም ክብርና ደረጃ እንደሌላቸውም ሞግቷል!” ይላሉ። ይህም (የሸይጣን ማታለያ) በመሃይማን፣ በዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችና ወደ እውቀትና ዲን በሚያስጠጉ በብዙ ሰዎች ነፍስ ውስጥ ይሰርጻል። በዚህም ሳቢያ የተውሒድ ሰዎችን ጠላት ያደርጋሉ፣ ታላላቅ (የሃሰት) ወንጀሎችንም ይለጥፉባቸዋል፣ ሰዎችንም ከእነርሱ ያሸሻሉ። በአንጻሩ የአሽራኮችን (የአጋሪዎችን) ወገን ይወዳሉ፣ ያከብሯቸዋልም፤ እነርሱ ራሳቸው የአላህ ወዳጆች (አውሊያኦች)፣ የዲኑና የመልክተኛው ረዳቶች እንደሆኑም ይሞግታሉ (ያምናሉ)! ​አላህ ግን ይህንን እምቢ ይላል! እነርሱ ፈጽሞ የእርሱ ወዳጆች አይደሉም፤ የእርሱ ወዳጆች እኮ እነዚያ አላህን የሚፈሩት (ሙተቁን)፣ እርሱን የተከተሉት፣ ከእርሱ (ትዕዛዝ) ጋር የተስማሙት፣ እርሱ ይዞት የመጣውን ያወቁትና ወደ እርሱ የሚጣሩት ብቻ ናቸው። እነዚያ ባልተሰጣቸው ነገር ተለባብሰው (የሌላቸውን ትልቅነት አውርተው) የሐሰት ልብስን እንደለበሱት፣ ሰዎችን ከነቢያቸው ሱና እንደሚያግዱትና (መንገዷን) ጠማማ ለማድረግ እንደሚፈልጉት፣ እነርሱም መልካም እየሠሩ ይመስላቸዋል (እንደነዚህ ያሉትማ የአላህ ወዳጆች ሊሆኑ አይችሉም)!» ​📚 ኢጋሠቱል ለህፋን [1/384]

Голосове повідомлення00:16

↪ አንድ አማኝ ለአላህ የሚገባው ማላቅ ቢያልቀው ኖሮ ወንጀልን ባላቀለለ ነበር ! አላህን በምናቀው ልክ ነው የምናልቀው . ሸይኽ ዓዲል

🌸فَإِذَا جَآءَتْهُمُ ٱلْحَسَنَةُ قَالُوا۟ لَنَا هَٰذِهِۦ ۖ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌۭ يَطَّيَّرُوا۟ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ ۗ أَلَآ إِنَّمَا طَٰٓئِرُهُمْ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ~እነሱጋ መልካም (ምቾት ፣ድሎት ፣ጤንነት) በመጣቻቸዉ ጊዜ ይች የመጣችዉ የኛ ነች ይላሉ።ህመም ፣ማጣት ችግር ፣የመሳሰለ ችግር ብትነካቸዉ በሙሳ እሱጋ ባሉት ገደቢስ ይሆናሉ።አዋጅ!መጥፎ ገድአችሁ አላህ ዘንድ ብቻ ነዉ።ነገር ግን አብዛሐኞቹ አያዉቁም።

🔖እህቴ ነገ የልጆቼ አባት የቤተሰቤ ሃላፊ ይሆናል ብለሽ ያሰብሽውን እሽ በይና አግቢው !።በመርህ ተጓዥ ድንና መልካም ስነምግባር የሌለው ነገ ልጆችሽን በተርቢያ የማያሳድግ ባል ከወድሁ ቢቀር ይሻል
🔖እህቴ ነገ የልጆቼ አባት የቤተሰቤ ሃላፊ ይሆናል ብለሽ ያሰብሽውን እሽ በይና አግቢው !።በመርህ ተጓዥ ድንና መልካም ስነምግባር የሌለው ነገ ልጆችሽን በተርቢያ የማያሳድግ ባል ከወድሁ ቢቀር ይሻልሻል ~!

🗂 የክረምት የቋንቋ ስልጠና  በኦንላይን 1️⃣ስልጠና አንድ ✅ለሁለቱም ፆታ የተዘጋጀ   የ English ቋንቋ ስልጠና 2️⃣ስልጠና ሁለት ለሁለቱም ፆታ የተዘጋጀ የዓረብኛ ቋንቋ ስልጠና ... ኢሕሳን የቋንቋ ትምህርት መማርያ ማዕከል ✅ ሙሉ ማብራሪያ ✔️ t.me/Ihsan_language/303 ❤️ t.me/Ihsan_language/303

እውነተኛ የሴት ልጅ ነፃነትና ጥበቃ ሊረጋገጥ የሚችለው ክብሯን ከፍ ባደረገው፣ ከውርደትና ከብልሽትም ጠብቆ በማኅበረሰቧ ውስጥ የተከበረችና ውድ ዕንቁ እንድትሆን ባደረጋት የኢስላም ሸሪዓ ጥላ ስር ብቻ ነው። 📌 قـ✑ــال العلامــة صـالح الفــوزان حفظــہ اللـہ تعـالـﮯ : ☜ المــرأة لا تڪـون حــرة إلا بالتــزام الأحڪـام الشــرعية ⇦ الشــر؏ حــررها مـن الهــوان حــررها مـن الفســاد حــررها مـن ڪـل رذيلـة ❀ ◄ ضبطها ✿ ◄ ڪرمها ❀ ◄ عززهـا ✿ ◄ صانهـا 📑 شـرح ڪـتاب الفتـن والحـوادث [ صـ 34 ] "አንዲት ሴት ነፃ ልትሆን የምትችለው የሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን (አህካሞችን) ሙጥኝ ብላ ስትይዝ ብቻ ነው። ​⇦ ሸሪዓ ከውርደት ነፃ አውጥቷታል፣ ከብልሽት ነፃ አውጥቷታል፣ ከማንኛውም መጥፎ ምግባር (ርኩሰት) ነፃ አውጥቷታል። ​❀ ◄ ስነ-ስርዓት አስይዟታል ✿ ◄ አክብሯታል ❀ ◄ ልዕልናን ሰጥቷታል ✿ ◄ ጠብቋታል ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን ​📑 [ሸርሕ ኪታብ አል-ፊተን ወል-ሐዋዲሥ — ገጽ 34] t.me/durusuabihizam t.me/durusuabihizam

ጥሩ ሷሊሕ የሆነች ሚስት ከየት ላግኝ? የብዙ ወንዶች ጥያቄ ነው። ምላሹን ቁርኣን ይነግረናል። አላህ የነቢዩ ዘከሪያን ዱዓእ ተቀብሎ ሚስቱን ያስተካለበትን ምክንያት አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦ (فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ یَحۡیَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥۤۚ إِنَّهُمۡ كَانُوا۟ یُسَـٰرِعُونَ فِی ٱلۡخَیۡرَ ٰ⁠تِ وَیَدۡعُونَنَا رَغَبࣰا وَرَهَبࣰاۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِینَ) "ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ።" [አል-አንቢያእ: 90] ታላቁ የማሊኪያ ፈቂህ ኢብኑ-ል-ዓረቢ እንዲህ ብለዋል፦ «መልካም (ሷሊሕ) የሆነች ሚስት በጥረት አትገኝም። አላህን ለፈራ ሰው አላህ የሚሰጠው ሪዝቅ ናት።» ስለዚህ ወንድሜ ለአላህ ትእዛዛት እጅ ስጥ አላህንም በመተናነስ ለምነው። በዚህ እንጂ በመጠናናትም ይሁን ባልተፈቀደ መንገድ መልካም ሚስትና ጣፋጭ ትዳር አይገኝም። ©: ተንቢሃት

🔖ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ "وقـد ضمـن اللَّـه سبحانـه لڪلّ مـن عمـل صالحـا أن يحييـه حيـاة طيبـة وهـو صـادق الوعـد لا يخلـف وعـده". አላህ መልካምን ለሰራ ሰው ሁሉ ያማረ ህይወት እንደሚያኖረው ዋስትና ሰጥቶታል የእሱ ቃል እውነት ነው ቃሉን አያፈርስም። 📚[አዳእ ወደዋእ] t.me/https_Asselfya

4_5789441247278021073.mp32.76 KB

Repost from TewhideAcadamy
አዘጋጅ ወንድማችሁ ሳዳት ከማል አቡ መርየም። አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ ወንድም እና እህቶች ሆይ! ይህ ቻናል ከጀማሪ ጀምሮ የኪታብ ቂርኣት በድምፅ፣ ከዛም ጎግል ላይ ለእያዳንዱ ትምህርት በጥያቄ እና መልስ የሚለቀቅበት ነው፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ የደርሱ ፔዲኤፍ አብሮ ይለቀቅለታል፡፡ በአላህ ፍቃድ በተሸለ መንገድ ካሉበት ሆነው ይማሩ፡፡ አላህ ኢኽላስ ይስጠን፡፡ https://t.me/TewhideAcadamy

4_5814305929646050898.mp310.22 KB

ሰውን መጥቀም ካልቻልክ... አትጉዳው፣ ማስደሰት ካልቻልክ... አታስከፋው። ማሳቅ ካልቻልክ... አታስለቅሰው። ልትጠግነው ካልቻልክ... አትስበረው፣ ልታወድሰው ካልቻልክ... አታማው። ዱኒያ በራሷ ከባድ ናት፤ ለሰዎች የሸክም ማቃለያ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ሸክም አንሁን። ለሁሉም ሰው መልካም መሆን ባንችል እንኳ፣ ክፉ ከመሆን እንቆጠብ። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
"እውነተኛ ሙስሊም ማለት ያ እጁና ምላሱ ከሰዎች ላይ ሰላም የሆኑለት ሰው ነው።" (ቡኻሪ)

4_5927120005954016851.mp39.70 MB