uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 529 підписників, посідаючи 5 408 місце в категорії Релігія і духовність та 2 215 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 529 підписників.

За останніми даними від 26 вересня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -11, а за останні 24 години на -10, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 16.67%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 9.90% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 2 589 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 538 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 17.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 27 вересня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 529
Підписники
-1024 години
-157 днів
-1130 днів
Архів дописів
፨ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ ፨ ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ ፨የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ #መናገሻ_ገነተ_ጽጌ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፨ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ ፨ ኮከበ ክብር፥ *
+3
፨ ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ ፨ ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ ፨የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ #መናገሻ_ገነተ_ጽጌ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

"በጣሊያን ወረራ ወቅት አስተዋጽዖ ካደረጉት መካከል ዐበይቶቹ ገዳማትና አድባራት" "…ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገደልና ዱር አላገኝ ስትል፤ ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤ 300 ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤ 2ሺ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣ በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡ "…ይህንን እኩይ ተግባሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማእታት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም መሐል አዲስ አበባ ላይ በ8 ጥይት ያረፉት)ና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት) ፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው ታላቁ ሊቅ አቡነ ክፍሌ፡፡ ፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ የደብረ ሊባኖስ መነኰሳት፡፡ ፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 የአቡነ ዜና ማርቆስ መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 የዝቋላ መነኰሳት፡፡ ፠ በጥቅምት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ 2116 የሆኑ የደብረ ዳሞ መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 3/1929 ዓ.ም 60 የታረዱ የምድረ ከብድ መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 15/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ በዚህም አንበሶች ከጫካ ወጥተው ያለቀሱላቸው፤ 91 የሚሆኑ የአሰቦት መነኰሳት፡፡ ፠ በኅዳር 25/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ ሲታረዱም ብርሃንም የወረደላቸው፤ 143 የአዲስ ዓለም ካህናትና መነኰሳት፡፡ ፠ በየካቲት 12/1929 ዓ.ም ከ30 ሺ በላይ በአካፋ ሳይቀር የተጨፈጨፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፡፡ ፠ በመጋቢት 16/1929 ዓ.ም. ከላይ በቦንብ የውሃ ገንዳውን ጭምር፣ ከታች በመትረየስ የተፈጁት 515 የማኅበረ ሥላሴ ገዳም መነኰሳት፡፡ የበቁ አባቶችም በጸሎታቸውም አውሮጵላኗን የከሰከሷት፡፡ ፠ በመጋቢት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ ብዛታቸው በውል ያልታወቁ የደብረ ዓባይ ገዳም መነኰሳት፡፡ ፠ በሚያዝያ 18 ና ሚያዝያ 20/1929 ዓ.ም የታረዱ 363  የመርጦ ለማርያምና የተድባበ ማርያም ካህናትና መነኰሳት፡፡ ፠ በሐምሌ 29/1929 ዓ.ም. እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ግማሾቹ የተሰፉትና ግማሾቹ ደግሞ በግዞት የተወሰዱት ጎንደር ሊቃውንት፡፡ ፠ በየካቲት 18/1929 ዓ.ም የተሠዉት የአዲስ አበባ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካህናት አባቶች፡፡ ፠ በየካቲት 20/1929 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት ተለቅመው እንዲሰበሰቡ ከተደረገና ከተደበደቡ በኋላ እጅና እግራቸውን አስረው እሳት አጉርሰዋቸዋል፡፡ ፠ የትግራይ ጨለቆት ሥላሴ አገልጋዮችና (ርዕሰ ደብር የነበሩትን አስተዳዳሪውን ጨምሮ) አስረው ‹‹በሮማ ካቶሊክ ታምናላችው ወይስ በረሃብ ትሞታላችሁ?›› እያሉ በረሃብ አሠቃይተዋቸዋል፡፡ እምቢ ቢሏቸው ጽኑ ግርፋት ገርፈው ከለቀቋቸው በኋላ በመኪና ገጭተው ገድለዋቸዋል፡፡ ፠ ይደመቆ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/ ፠ አፈር ባይኔ ተክለ ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ ፠ አክርሚት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ ፠ ጎበጥ አገር ገብርኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ እመ ምሕረት/ ፠ አንኮበር ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. ፠ ደረፎ ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/ ፠ ጎንቻ መድኀኔ ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/ ፠  አንኮበር ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ ከብዙ በጥቂቱ ናቸው። #ጀግናውና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡  ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤ እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡ ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤ ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡  ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ ደግሞ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤ አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤ ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤ ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤ በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡ መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤ ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡ ፠ ከ1927-1934 ዓ.ም ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀገራችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤ *በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤ *ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤ **የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ ከ30,000 በላይ ሰማዕታት፤ *በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤ *በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤ *ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤ *በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤ *ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤ *ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡ *ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣ *350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡ **ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡  (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

"ሲሳያ ለነፍስ ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ" /ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundayScho
"ሲሳያ ለነፍስ ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ" /ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ። ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ
አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ። ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት  ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት  የተለያዩ መመሪያዎች  መተላለፋቸው ተገልጿል። ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ  የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ  የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም  ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ  ለማወቅ ተችሏል። በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት  ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው። በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና  ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም  ተገልጿል። ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ  መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

ከ1978-1988ዓ.ም. ከዓድዋ በፊት የነበሩ 8ቱ አድዋዎችና የዓድዋ ሶሎዳ ውጊያ፤ 1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡ 2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ 3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ መንደር ውጊያ፡፡ 4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት ከጥር 13 -15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡ 5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡ 6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡ 7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡) 8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡ 9ኛ)  #አድዋ #ሶሎዳ፡፡ ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ ተራራ ላይ ነው፡፡ "የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት መነሻ" ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡ መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ(እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡ ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ  (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጠርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ዘወረደ_ወይም_ሕርቃል_ወይም_ሙሴኒ     ጾም ማለት፤ ፨ ከእህልና ከውኃ እንዲሁም ከሥጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው። ፨ ጾም ማለት በጾም ወቅት ሥጋ ነክ ምግቦችንም ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ ዓይነቶችን ጥሉላትነት በሌላቸው ምግቦች መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ማለት ነው። ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው። ፨ ጾም ለእግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዐቢይ ጾም ስንጾምም፤ ዐይናችን ትጹም (ክፉ ከማየት)፤ ጆሮም ትጹም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤ እጅም ትጹም (ከመስረቅም ሆነ ሰውን ከመደብደብ)፤ አግርም ትጹም (ወደ ኀጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤ ….. ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንጹም። ዐቢይ ጾም ማለት ታላቅ ጾም ማለት ነው። ታላቅ ጾም የተሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቊጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው። የዐቢይ ጾም  የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ወይም ጾመ ሕርቃል በተጨማሪም ሙሴኒ በመባል ይታወቃል፤ ለምን እንደተባለ በዝርዝር ስንመከለከታቸው፤ ፩ኛ. #ዘወረደ_ይባላል፤ ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ፤ ወሚመ ኢያእመሩ፤ እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ፡፡›› ‹‹ዘወረደ እምላዕሉ እመልዕልተ ኵሉ››፡፡ «ዘወረደ» ማለትም በቀጥታ፣ ቃል በቃል ሲተረጐም «የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም በምሥጢሩ አምላክ፥ ወልደ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም፥ እኛን  ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን፤ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና መውረዱን፥ ከድንግል ማርያም መወለዱን፥ የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ይህ እንዲታወስበት፣ እንዲወሳበት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን ሳምንትን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ ‹‹ዘወረደ›› ብሎ ሰይሞታል፡፡ /ዮሐ.3፥13፣ ጾመ ድጓ፡፡/       ፪ኛ. #ጾመ_ሕርቃል_ይባላል፡፡ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ሌላ መጠሪያ ስሙ ‹‹ጾመ ሕርቃል›› ነው፡፡ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም. ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ንግሥቲቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ካህናትን አሸክሞ፥ ሌላውን ንዋያተ ቅድሳት ዘርፎ፥ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ፥ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ፥ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፤ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርግ? አላቸው; እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን ፩ ሱባኤ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉ ያለበትን አጥቶ ሲቸገር ኪርዮስ መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ፤ ይህንን ለማሰብ፥ ለማስታወስ የምንጾመው ሲሆን፤ ዛሬም እኛ በመስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን እያልን፥ ለሕርቃል በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳትን፥ መንፈሳዊ ኃይልን እንዲበዛልን እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡    ፫ኛ. #ሙሴኒ የመጀመሪያው ሳምንት ሙሴኒ የተባለበት ምክንያትም፤ በዚሁ ሳምንት መጀመሪያ የሰኞ ዕዝል «ከመዝ ይቤ ሙሴ ፀዓቱ እምትእይንት (ሙሴ ከከተማ መውጣቱ እንደዚህ ነው አለ») ስለሚል እንደዚሁም የዚሁ ዕለት ማለት የሰኞ አቡን «ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት ምድር ሰናይት» እያለ የሙሴን ታሪክ ስለሚጠቃቅስ ሳምንቱ ሙሴኒ ተባለ፡፡ ነቢያትም አርባ አርባ ቀን ጾመው ካለፉ በኋላ የሙሴ ሕግና ትንቢተ ነቢያት ፈጻሚ የሆነው አምላካችን እንደ እነሱ 40 ቀንና 40 ሌሊት መጾሙን  የሚያስታውስ ነው፡፡  /ዘፀ.24፥18፤  1ኛ.ነገ.19፥8፤  ማቴ.4፥1-4/፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሳችሁ! ጾሙ የካቲት 17 ይገባል #የዐቢይ_ጾም_ሳምንታት_ስያሜዎች ፩ኛ)የመጀመሪያው እሑድ(ሳምንት)፥ #ዘወረደ (ሙሴኒ፣ ጾመ ሕርቃል) ይባላል፡፡ በመጽሐፉ መጀመሪያ አምላክ ከሰማይ መውረዱን፣ ሰው መሆኑንና መስቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡ ፪ኛ. የሁለተኛው እሑድ፥ #ቅድስት ይባላል፤ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው ፫ኛ. የሦስተኛው እሑድ፥ #ምኲራብ ይባላል፤ በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኲራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ ፬ኛ. ዐራተኛው እሑድ፥ #መፃጉዕ ይባላል፤ ድውያንን መፈወሱን፣ ዕውራንን ማብራቱን፣ የሚያነሣ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፭. አምስተኛው እሑድ፥  #ደብረ_ዘይት ይባላል፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሁኖ ያስተማረው ትምህርት፥ የዳግም ምጽአትን ነገር የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፮. ስድስተኛው እሑድ፥ #ገብርኄር ይባላል፡፡ የጌታውን ብር ተቀብሎ ያተረፈበት፣ በጌታውም ፊት ምስጋናን ያገኘው ሰው ታሪክ ይዘመርበታል፡፡ ፯. ሰባተኛው እሑድ፥ #ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ እየመጣ ይማር የነበረውን የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፰. ስምንተኛው እሑድ፥ #ሆሣዕና ነው፡፡ ጌታ በአሕያ ውርንጭላ ሆኖ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡ ፨ ከሠርክ ሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ያለው ሰባት ቀን #ሕማማት ይባላል:- የጌታን መከራና ስቃይ እንዲሁም ሞት የምናስታውስበት ሳምንት ነው ፡፡ #የዐቢይ_ጾም_ሌሎች_መጠሪያ_ስያሜዎች ፩. ዐቢይ ጾም ይባላል፤ ፪. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤ ፫. የካሣ ጾም ይባላል፤ ፬. የድል ጾም ይባላል፤ ፭. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፤ ፮. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፤ ፯. የቀድሶተ ገዳም ጾም፤ ፰. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፤ ፱. የሥራ መጀመሪያ ጾም፤ ፲. ጾመ አርብዓ ይባላል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

እንኳን ለእመቤታችን ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤ ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ፡፡ (ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡) እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች የካቲት አሥራ ስድስት ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡ ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም የሚያጠጡ(በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ) ፣ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16፤ #በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ በሃገራችን በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመው፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ነው፡፡ እነዚህም፤ 1ኛ) የላይ ቤት፤ የደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት 2ኛ) የታች ቤት አብነት፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ 3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡ እኛም ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ የዐቢየ እግዚእንና የበዓታን ይትበሃል አንድ ላይ በቅደም ተከተል አድረገን አዘጋጅተንላችኋል፤ የደፈጫ ከላይ ከተጠቀሱት ከ2ቱ በጥቂት ቀለም ብቻ የሚለይ በመኾኑ አላካተትነውም፡፡ ስለዚህ እንደ የደብራችሁ ይተበሃል የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ) የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡ መልካም ማኅሌት፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958