uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 640 підписників, посідаючи 5 373 місце в категорії Релігія і духовність та 2 216 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 640 підписників.

За останніми даними від 09 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 72, а за останні 24 години на 0, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 8.45%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 4.64% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 1 319 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 725 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 12.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 10 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 640
Підписники
Немає даних24 години
+907 днів
+7230 днів
Архів дописів
#በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤ ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን
+9
#በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ፤ ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ታቦቷ የመጣው) ✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች) ✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ) ✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች ፥ ሰሜን ተራሮች) ✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር) ✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ) ✣ ደብረ ጽዮን ማርያም (ነቀምት) ✣ ደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም (ባሕርዳር) ✣ አርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ማርያም ✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ ፥ ለንደን) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት: ኅዳር 21 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ ) ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/ share እና like ያድርጉ #ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_፤ ፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6) ፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23) ፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/ ፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/ ፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....) ፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡ ፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡ ፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡ ፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡ ———— #ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_፤ ፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤ ✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት) በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/ ፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች ✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡ ፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤ ✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/ ——- **** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤ «ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤ ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡ አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤ ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤ ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡ ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/

ኅዳር 13 በዓለ እግዚአብሔር አብ ወአእላፍ መላእክት ፤ በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል በድምቀት ይከብራል። የዚህ ደብር ታሪክ እነዲህ ነው፤ በደብሩ የሚገኝው የእግዚአብሔር አብ ታቦት በደብራችን በቀጨኔ ደብረሰላም ይገኝ ነበር፡፡ በታላላቅ አባቶችም ይህ ታቦት ወጥቶ ወደ አሁኑ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ሥፍራ እንደሚሄድ የበቁ አባቶች አስቀድመው ይናገሩ ነበር፡፡ እንደተናሩትም ሐምሌ 29 ፤1969 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ወጥቶ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ቤት አረፋ፣ ቤተክርስቲያኑም እራሱን ችሎ እስኪቆም ድረስ የደብራችን የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም አገልጋዮች በቅዳሴ በማኀሌት በሰዓታት ያገለግሉ ነበር :: ከዚህም በኃላ ጥር 19 ቀን 1971 ዓ.ም የመጀመሪያው ቤተክርስቲያኑ አልቆ ተመርቋል፡ የቤተክርስቲያኑ ዲያቆናት ፣ ቀሳውስት እና መሪጌቶችም በጊዜያዊነት ተቀጠርው ነበር ሆኖም የአገልግሎት ፍቅር ያደረባቸው የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሊቃውንት አልግሎታቸውን አላቆሙም ነበር። ለታሪክ ያህል ታላቁ ሊቅ አለቃ ኤልያስ ነቢየ ልዑል ከመኖርያ ቤታቸው ቀጨኔ ድረስ በምጣት ለደብሩ ታላቅ አሰተዋጾዖ አድርገዋል። እሁን ያለው ሕንፃ ቤ.ክ የደብተራ ኦሪት እና የኖኀ መርከብን ቅርጽ ይዞ በቅድስቱ አካባቢ ያለው አሠራር ደግሞ ክቧን ቤ.ክ ሆኖ ተሰረቶ በ2009 ዓም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ተመረቋል፡፡ የቅዱሰ እግዚአብሔር አብ ታቦትም ኅዳር 13 እልፍ አእላፋት መላእክት በሚከሩበት ዕለት ይከብረል። በዚሁ ደብር ኅዳር 25 የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በዓልም ይከበራል ( ታቦቱ በድርብነት አለ) የእግዚአብሔር ቸርነት የአእላፍ መላእክት ተራዳኢነት አይለየን! አሜን ። #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#አንኳን_ለቅዱስ_አግዚአብሔር አብ በዓልና_ለአእላፍ_መላእክት_በዓለ_ሢመት እንዲሁም #ቅዱስ_ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 ጀምሮ እስከ 13 ድረስ ከአምላኩ ምሕረትን ለሚለምንበት) በዓል በሰላም አደረሳቹህ፡፡ ፨ ፨ ፨ #ኀዳር_13 ቀን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሊቃውንት #አእላፍ መላእክት እየተባለ ይጠራል ፤ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከብሩብት ቀን ነው እንዚህም ሥጋ የሌለቸው ረቂቃንና ለዓለም ሁሉ የሚማልዱ ናቸው ፡፡ #Share ያድርጉ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ 100 በክፍለ ነገድ 10 አድርጓቸዋል ፡፡ በ3 ሰማያትና በ10 ዓለማት ላይም ይገኛሉ፡፡ መላእክት ያሉባቸው ከተሞች #ኢዮር #ራማ #ኤረር ይባላሉ ፡፡ አሥሩ ነገዶች ከነአለቆቻቸው አንዲህ ናቸው 1. #አጋዕዝት (ቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል የነበረ ፤ አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ስር ናቸው) 2. #ኪሩቤል (አለቃቸው ቅዱስ #ኪሩብ ፤ ለበለጠ ኀዳር 7 የጻፍነውን ይመልከቱ) 3. #ሱራፌል (አለቃችወ ቅዱስ #ሲራፊ ፤ ለበለጠ ኀዳር 24 ይጠብቁን) 4. #ኃይላት (አለቃቸው ቅዱስ #ሚካኤል ) 5. #አርባብ (አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ) 6. #መናብርት (አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል) 7. #ሥልጣናት (አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ) 8. #መኳንንት (አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ) 9. #ሊቃናት (አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል) 10. #መላእክት (አለቃቸው ቅድስ አናንኤል) ናችው፡፡ ከእነዚህም ፨ አጋዕዝት ፣ኪሩቤል ፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖርያቸው በኢዮር(3ኛው ሰማይ ) ነው ፡፡ ፨አርባብ ፣መናብርትን ሥልጣናት መኖርያቸው በራማ ነው ፡፡ ፨መኳንንት ፣ሊቃናት ፣ መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር ነው (1ኛው ሰማይ ) ———- (ከእልፍ አእላፋት አለቃዎች ስሞች በጥቂቱ)፡፡ ጸሎትነ ትብጻሕ (ሰላም ለክሙ) ለመላእክተ ምሕረት፤ #ሚካኤል_ወገብርኤል፥ #ሱራፌልወኪሩቤል/፬ቱ እንስሳ/፥ #ዑር(ራ)ኤል_ወሩፋኤል /፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ/፥ #ሱርያል_ወፋኑኤል፥ #አፍኒን_ወራጕኤል፥ #ሳቁኤል_ወአቅናኤል፥ #ብርናኤል_ወሱባኤል፥ #ፍናኤል_ወሰላታኤል፥ #ሰዳካኤል_ወኤልናኤል፥ #አናንኤል_ወኢየሩማኤል፥ #ግርማኤል_ወድርማኤል ፥ #ድማህኤል_ወአድማኤል፥ #ሙራኤል_/ምናቴር_አብያቴር/፥ #ሱታ(ስቱ)ኤል_ወሱርያል፤ ……. ፨ ፨ ፨ ፨ የመላእክት ተፈጥሮ እመኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደመኖር ) ነው ፡፡ አይራቡም አይጠሙም ፤አይዋለደሙ ፣ አይሞቱም ፣ ዕረፍት የላቸውም ፤ምስጋናቸው እረፍታቸው ፤እረፍታቸው ምስጋናችው ነው አንጂ(አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ) እንዲል፡፡ ተፈጥሯቸው እጅግ ረቂቅ ነው፡፡ ተግባረቸውም ዘውተር እግዚአብሄርን ማመስገን ነው፡፡ —— #መላአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ፤ ለመዓትም ይላካሉ፡፡ ምሕረትን ያወረዳሉ ፡፡ ልመናን ያሳርጋሉ ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ አንዲዚሁም ሁሉ ወቅትንም የሚቆጣጠሩ አሉ ፤ ስለ ሰው ልጆች ይማልዳሉ (ዘካ 1÷12 ) ምሥጢርም የሚገልፁም አሉ(ዳን 9÷21) መላእክት ተራዳኢም ናቸው (ኢያ 5÷13)፣ እነዳንሰናክል ይጠብቁናል (መዝ 90÷11 ) ፣ያድናሉ ( መዝ 33÷7 ) ፣የፀጋ ስግደትም ይገባቸዋል (መሳ 13÷20) በፍርድ ቀንም ኀጥአንን ከጻድቃን ያለያያሉ (ማቴ 25 ÷31) እነሆ እግዚአብሄር ይፈርድዘንድ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል እንዲል ፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ፨፨፨ እልፍ አእላፋት ወትእልፊት ቅዱሳን ንጹሐን መላእክት ቆሙ በአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አምላክ በማለት፡፡ ምልጃቸው እና ጠብቆታቸው አይለየን አሜን ፡፡ —————— ኀዳር 13 ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ቦታዎች ጥቂቶቹ፤ ከፎቶ ጋር …. 1. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (መስቀሉ የሚገኝበት)፤ 2. ጠዳ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (ጎንደር፤ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ)፤ 3. ጎርዶማ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን (በሰሜን ሸዋ)፤ 4. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (አዲስ አበባ)፤ 5. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) 6. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#አንኳን_አደረሳቹህ ኅዳር ፲፪፤ በዓለ ሢመቱ ለቅዱስ ሚካኤል "በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና #ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_፨ "እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡" ፨፨፨ #Share ያድርጉ ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ ፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ ፨፨፨ ፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ #Share ያድርጉ ሥርዓተ ማኀሌቱ እስመ ለዓለሙን የሰንበትን በማድረግ ተጠቀሙ(ሰርዓ ለነ) በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1) *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2) *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3) *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4) *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5) *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6) *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7) *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8) *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9) *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10) *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11) *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12) *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13) *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14) *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 15) *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 16) *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 17) *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 18) *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 19) *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ ) (ሰሜን ሆቴል አካባቢ)

#የክርስቶስ_አያት ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ፣ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን አያት የሆነች ፣ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያምም እናቷ የሆነች የተመሰገነች እና የከበረች ቅድስተ ሐና ዐረፋቷ ነው፡፡ #share ያድርጉ #ቅድስት_ሐና በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሚልኪ ልጅ ለሆነው የማጣት ልጅ ናት፡፡ ____ #ማጣትም 3 ልጆች አሉት እነርሱም ፤ #የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ነው፤ አዋላጅ የነበረች ስትሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች ፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችንን ከወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡ #ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ነዉ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡ #ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም ከሆነ ጋር ተጋብታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡ ሰሎሜና ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን እናት ለሆነች ለቅድስት ሐና እኀትማማች ናቸው፡፡ _ ቅድስት ሐና መካነ እያለች አምላክን ልጅ እንዲሰጣት እጅግ አብዝታ ትለምን ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኀነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችን የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፡፡ ጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል እነርሱም ሐና እና ኢያቄብ ናቸው:: አምላካችንን የልጅ ልጅቻችን ነው ለማለት ተገብተዋልና፡፡ ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ አባቶችም ታጋድሎዋ እጅግ ብዙ እንድሆነ ነግረውናል፡፡ ---ምልጃዋ አይለየን ፡፡ ሃገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን አሜን! አርኬ ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ፡፡ ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ፡፡ ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ፡፡ እስመ ረከብኪ ምገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ፡፡ እምሔውተ አምላክ ትኵኒ በሥጋ፡፡ በቦታው ሄዳቹ በዓሉን ማክበር ለምትፈልጉ👇🏼 ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. እና በሌሎች የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያተ ክርስቲያናት ... ፠ ኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ ፡ ፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና:: ፠ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በደብረ መንክራት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን በደባልነት ትገኛለች ሌሎች በዓሉ የሚከብሩባቸውን ቦታዎች ኮሜንት ላይ ያጋሩን /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like