uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 951 підписників, посідаючи 5 316 місце в категорії Релігія і духовність та 2 234 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 951 підписників.

За останніми даними від 21 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 408, а за останні 24 години на 1, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.79%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.92% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 4 113 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 742 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 29.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 22 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 951
Підписники
+124 години
+1627 днів
+40830 днів
Архів дописів
‹‹አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ፤ በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ›› (ዕን ፫፥፪) *አስቀድምን መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስ
‹‹አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ፤ በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ›› (ዕን ፫፥፪) *አስቀድምን መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረስዎ፡፡ የዚህ አመት የአገልግሎት ምዕራፋችን እስከ በዓለ ልደት መልካም የሚባል ሲሆን ከዚህም የተሻለ እንድንሰራ ፈጣሪ ይርዳን እያልን በሃገር ቤት ለማትገኙ ወንድም እና እህቶቻችን፤ ምንም እንኳን በዓሉን በሐገር ቤት ተሰባስበን በአንድነት ማክበር ባንችልም በአካባቢ ተለያይተን በመንፈስ ግን አንድ ሆነን የምናከብረውን በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉን በሰላምና በደስታ እንዲሁም በታላቅ ፍስሐ የምናከብረው በዓል ስለሆነ ከብርሃነ ልደቱ ረድኤት በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን ፡፡ በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንልዎ ሰንበት ት/ት ቤታችን መልካም ምኞቱን ይገልጽሎታል፡፡ ——ዲ/ን ታምራት ሙሉነህ ——-የስንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ

#ታኅሣሥ_29_ልደታቸው_ከጌታችን_ልደት_ጋር_የተባበረላቸው_ቅዱሳን (በድጋሚ ) ፤ እንዲሁም #አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር እንዲሁም የተባበረላቸው አባት #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕናና የቆብ ልጃቸው #አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ፤ #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #አቡነ ዳንኤል ዘገርዓልታ፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ ————- #አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና #አቡነ_አብሳዲ_ዘደብረ_መጒና_፤ #ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር ከተባበረላቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ፠ #የበረሃው_ዕንቊ_ገዳም_መንበረ_ልዑል_ጽርሐ_አርያም_ደብረ_መጕናን_የመሠረቱ፡፡ ፠ አብርሃም ቅድስት ሥላሴን እንዳስተናገደ፤ #አቡነ_አብሳዲ_ደግሞ_ጌታችንን_ተቀብለው_እግሩን_ያጠቡ_ናቸው፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ፠ #ደቀ_መዛሙርቶቻቸው_በተሰየፉበት_አንገረብ_ወንዝ_ላይ_ #44ት #የፍል_ውኃ_ፈዋሽ_ጠበል_አንገረብ_የሚባል_ያላቸው፤ በሃገራችን ብዙሃን ሕዝብ ከሚጠመቅባቸው ጠበሎች ዋነኛው ከተጠማቂው ሕዝብ ብዛት የተነሣ #ቀንና_ሌሊት_ጥምቀት_የሚካሄድበት፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ፠ ከብቃታቸው የተነሣ ወደ ላይ ጽርሐ አርያምን ወደ ታች በርባሮስ ድረስ የሚደረገውን የሚመለከቱ፤ ፠ #ወላዴ_አእላፍ ፥ #ወላዴ_ቅዱሳን_ሊቃውንት፥ #አበ_ብዙኃን፥ #ወላዴ_ሰማዕታት የሆኑ፤ ፠ በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት የሚያስተምሩት፤ ፠ 470 ዓመታትን የኖሩት፡፡ ፠ ታኅሣሥ 29 የጌታችንና,ን የጻድቁን የልደት በዓል፤ ሙሉ አርማጭሆ እንዲሁም የትክል ድንጋይ፣ የዳንሻና አካባቢው ምዕመናን በ10ሺዎች የሚቈጠር ሕዝብ የሚያከብርላቸው፡፡ * ምንኵስናን የተቀበሉት ከአቡነ ዮሐንስ ከማ ነው፡፡ * በማንዳባ ገዳም ከ7ቱ ከዋክብትና ከ7ቱ ከዋክብተ ጣና አንዱ ከኾኑትና ደንጊያን እንደ ጀልባ ከሚጠቀሙት ከአቡነ ያሳይ ጋር ብዙ የጽድቅ ሥራና የትሩፋት ተጋድሎን ፈጽመዋል፡፡ * ቀድሞ በኤርታ ደብረ ማርያም ነበር የሚኖሩት፤ ኋላ ታቦተ ማኅበረ በኵርንና ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ይዘው ብዙ ቅዱሳንን ወዳፈለቁበት መሥዋዕተ ኦሪት ይሠዋበት ወደነበረው ገዳመ መጕና መጡ፤ ገዳሙ የሚገኘውም በጎንደር ታች አርማጭሆ ነው፡፡ ‹‹በሬ ሜዳ›› የሚባለው ቦታ ላይ የጌታችን ልደትና የጻድቁ ልደት ዝክር የሚዘከርበት ምርፋቅ ነው፡፡ ጻድቁ የተጓዙባቸው ምዕራፋት ከቁርባኔ ወንዝ እስከ መታጠቂያ በር 13ት ሲሆኑ የ13ቱ ሕማማት ምሳሌ ሲሆኑ፤ የመታጠቂያ በር ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ በ1407 ዓ.ም. በአፄ ይስሐቅ ዘመን ‹‹ዳሩ እሳት ፥ መሐሉ ገነት፡፡›› ተብሎ ተገድሟል፡፡ ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን ዐምዳ ወብርሃና ለደብረ መጒና በቆብ የወለዷቸው በርካታ ቅዱሳን ቢኖርም፤ #ገዳማትን_የመሠረቱ_ለአብነት_ዋናዎቹ_፤ ፠ #አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ሥልጣነ ክርስቶስ (አመራ ቊስቋም ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ልብሰ_ክርስቶስ_ (ዳውጨና አማኑኤል ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ማቴዎስ (ያይራ ተክለ ሃይማኖት ገዳምን የመሠቱ) ፠ #አቡነ_ዮሐንስ_ዘመረባ (ጊዮርጊስ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ ሰማዕቱ አቡነ ጽጌ ድንግል (እንኮ ድብ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ዘወልደ_ዳዊት (ጐረፍ ተክለ ሃይማኖትን የመሠረቱ) ፠ አቡነ መቅደሰ ክርስቶስ (ሳይኮ ኪዳነ ምሕረትን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ህላዌ_ክርስቶስ (አምስትያ ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ ተላዌ ክርስቶስ ( ገዳምን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ከናፍረ_ክርስቶስ (ገዳምን የመሠረቱ) ፠ አቡነ የማነ ክርስቶስ (ገው ጊዮርጊስን የመሠረቱ) ፠ #አቡነ_ዕደ_ክርሰቶስ (የኢትዮጵያና የግብፅ ሐዋርያ ፥ የደብረ መጕና 3ኛ መምህር /አበምኔት/) ፠ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ (በትግራይ ገዳምን የመሠረቱ፤ ልደታቸው ከአባታቸው ጋር በታኅሣሥ 29 የተባበረላቸው) ፠ #ሰማዕቱና_በአባታቸው_ወንበር_የተተኩት_አቡነ_አምኀ_ጊዮርጊስ፡፡ (የደብረ መጕና 2ኛው መምህረ /አበምኔት/) ሲሆኑ፤ #ቅዱሳን_ደራስያን_ሊቃውንት_ከሆኑት_መካከል_ለአብነት_፤ ፠ #አባ_ገብረ_ኢየሱስ_ (የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ) ፠ #እጨጌ_በትረ_ጊዮርጊስ_ (በአፄ ፋሲል ዘመን የኢትዮጵያ ሊቃውንት አፈ ጕባኤ የነበሩና የቅባት ሃይማኖት መሪዎች እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን የረቱ …. በዚህም ሊቃነታቸው በዐይኑ ያየ ባለቅኔ፤ ‹‹ወረከብናሁ ለበትር ዘያደክማ ለሮሜ፤ ቅሩጸ በንባብ ወጽሩበ በትርጓሜ፡፡›› ብሎ የተቀኘላቸው የሊቃውንት ዋልታ፡፡ ፠ #አባ_ስብሐት_ለአብ_ (የመልክ ሥላሴ፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ዘይነግሥን የደረሱና 14ቱን ቅዳሴ ያመሠጠሩና በአንድምታ የተረጐሙ፣ በጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ ከብዙ ሊቃወንት ጋር በመሆን የቅኔና የመጻሕፍትን ምሥጢር ከነሙሉ አገባቡና እርባ ቅምሩን እንዲሁም የአቡሻኽርን ሁሉ የቀመሩ፤ የንጉሡ የአድያም ሰገድ ኢያሱ መምህረ ንስሐ የነበሩ) ፠ #አባ_ዳንኤል_፤ (ብዙ መጻሕፍትን ያሰባሰቡና የጻፉ፤ ንዋያተ ቅድሳትን የሚሠርቅ ‹‹ቢዘራ ለበረድ ፥ ቢወልድ ልጁን ለጕጓድ፡፡›› ብለው ከ8000 በላይ ሊቃውንትን በማሰባሰብ እንዲወሰን ያደረጉ፡፡ #ከላይ_ያሉትን_ለአብነት_የጠቀስናቸውን_ቅሳንና_ሊቃውንት_አስተምረውና_ወልደው_፤ ለ90 ዓመታት ፍሬና ቅጠላ ቅጠል ተመግበው፤ ራቁታቸውን በጋ ከክረምት በበረሃው መንነው፤ ሳማ (አበርባራን) ለትሩፋትና ለተጋድሎ ለብሰው፤ በፀሐይ ሰረገላ፥ በብርሃን መንኰራኵር እየተጫኑ እንደ ሐዋርያት በማስተማራቸው፤ የጸጋና የቅብዐት ተካተዮችን እያስተማሩ ወደ እናት ቤ/ክ በመመለሳቸው፤ ** የሚያምረውን ሥጋዊ ደም ግባታቸውንና ሰውነታቸው እንደ ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብና እንደ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ወደ ቁስል በመቀየራቸውና ሥስቃዩንና መከራውን በመቻላቸው፤ ቁስላቸው ተልቶ ትሎቹን የገዳሙ አእዋፋት እስኪመገቡት ድረስ በመታገሣቸው፡፡ *** በርካታ ቃል ኪዳን አምላካችን ሰጥቷቸው በተወለዱ በ470 ዓመታቸው ዐርፈዋል፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

<<ተዘከሩ መኳንንቲክሙ.... ፤ የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መምህራኖቻችሁን አስቡ ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታቸሁ በእምነት ምሰሏቸው ፡፡ >>/ዕብ 13፥8/ ፨፨፨ ፨ተኅሣሥ
<<ተዘከሩ መኳንንቲክሙ.... ፤ የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መምህራኖቻችሁን አስቡ ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታቸሁ በእምነት ምሰሏቸው ፡፡ >>/ዕብ 13፥8/ ፨፨፨ ፨ተኅሣሥ 27 ቀን በሕፃናት ክፍል የመድኀኔዓለም እና ዝክረ አበው ላይ በተደረገው የምስጋና መርኀ ግብር ላይ ለምንወዳቸው መምህራችን #ለርዕሰ_ደብር_ጥሩነህ_ኃይለ_ጊዮርጊስ ፤ የጌታችን ልደት ወቅት እንደሚያዝው ፤ከቅዱስ ኒቆላዎስ(ገና አባት ) እንዳየነው፤ ሳባውያን (ኢትዮጵያውን) ከሆኑት ከሰብዓ ሰገል እንደተማርነው ፤ ሰ/ት/ቤታችን ስጦታን አበርክቷል :: ስጦታውም የካባና የስዕል ሲሆን ፤ በሕፃናት ክፍል የስዕል መምህር በሆነው #በሰዓሊ_ፈቃደ_ሥላሴ ተስሏል ፡፡ ስጦታውን ያበረከተውም የሰ/ት/ቤቱ ሕፃናት ክፍል ነው፡፡ ፨ መምህራችን ርዕሰ ደብር ጥሩነህ የሰንበት ት/ቤቱን የወጣትና የሕጻናት ክፍል መዘምራን የቅዱስ ያሬድን ውብ ዜማ በማስተማር ልጆቹ የአባቶቻቸው ፈለግ እንዲከተሉ በትጋት እያገለገሉ ያሉ አባታችን ናቸው፡፡ ለመምህራችን ርዕሰ ደብር ጥሩነህ ኃይለ ጊዮርጊስ ፤ ረጅም የአገልግሎት ዕድሜ ከ ጤና ጋር አምላከ ሊቃውንት ይስጥልን፡፡አሜን! †

#የጌታችን ልደት በዋናነት የሚከበርባቸው ዐበይት ገዳማትና አድባራት፤ ፠ በኢየሩሳሌም ቤተ ልሔም፤ ጌታችን በተወለደባት ፠ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ በተወለደባት ዕለት የጌታችን መወ
+3
#የጌታችን ልደት በዋናነት የሚከበርባቸው ዐበይት ገዳማትና አድባራት፤ ፠ በኢየሩሳሌም ቤተ ልሔም፤ ጌታችን በተወለደባት ፠ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ በተወለደባት ዕለት የጌታችን መወለድ የተበሠረባት /ቋራና መተማ/ ፠ ሰረባር በዓለ እግዚአብሔር፤ ቅዱስ ላሊበላ ከሕንፃዎቹ ሁሉ መጀመሪያ ያነጸው ውቀር ቤ.ክ. /ስሜን፤ ደረስጌ አጠገብ/ ፠ ደብረ ሮሐ ላስታ ላሊበላ ፠ ርዕሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ ቤ.ክ. /እጅግ ጥንታዊ ታሪክ ያለው ጽላቱ ከደበቡ ኢትዮጵያ የሄደና ኋላ ቊጥሩ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነ፤ ጎንደር ከተማ/ ፠ ደብረ ስብሐት ቀሃ ኢየሱስ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ፤ ጎንደር ከተማ/ ፠ ቂልጠፋት በዓለ ወልድ፤ (ጉራጌ ፥ እንደጋይ ወረዳ) ፠ ጉንችሬ በዓለ ወልድ፤ (ጉራጌ ፥ እነሞር ወረዳ) ፠ አሸዋ ሜዳ ቤሮ ደብረ ምህረት ቅዱስ ላሊበላ ቤተክርስቲያን፤ (በምዕራብ ሸዋ ፥ ወልመራ ወረዳ) በአዲስ አበባ ደረጃ የሚገኙ፤ ፠ አዲስ አበባ መካነ ሥላሴ ቅዱስ በዓለ ወልድ /በ1883ዓ.ም. የተመሠረተ፤ 4ኪሎ፤ አዲስ አበባ/ ፠ ፊሊዶሮ መድኀኔዓለም ቅዱስ ላሊበላ፡፡ (ሌሎችም ካሉ ከነፎቷቸው ላኩልን፡፡)

ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ትንቢት የተናገረላት ናት፡- ‹‹እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች፣ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ /ት.ኢሳ. 7፥14/ **ነቢይ ሕዝቅኤል ‹‹እግዚአብሔርም አለኝ ‹ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች፣ አትከፈትም፣ የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር››› አለ፡፡ **ነቢዩ ዳንኤልም ‹‹ሌሊት በራእይ አየሁ ‹እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ፤ ዘመኑን ወደሚያስረጅ ደረሰ፣ ከፊቱም አቀረቡት፣ የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት ተሰጠው፡፡ ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል፤ አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው፤ መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው››› አለ፡፡ **ዳግመኛም ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔር እንደ እኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጠልኝ›› አለ፡፡ አሁንም ደግሞ ‹‹አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ›› አለ፡፡ ሁለተኛም ‹‹በእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፣ ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው፣ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ይባላል›› አለ፡፡ **ነቢዩ ኤርምያስም ስለ እግዚአብሔር ‹‹በዚያን ወራት ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ፣ በምድርም የቀና ፍርድን ያደርጋል፣ እግዚአብሔርም ያመኑትን ያድናቸዋል›› አለ፡፡ **ኤልሳም ‹‹እግዚአብሔር ከሰማይ ይወርዳል፣ በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ ዕውነትን ያስተምራቸዋል፡፡ ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆኑ ወገኖች በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል›› አለ፡፡ **ናሆምም ‹‹እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል፣ ልብሱም እንደልብሴ ነው›› አለ፡፡ **ኢዩኤልም ‹‹የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ፣ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር፡፡ ስለእርሷ ‹ይህች ማናት/› ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ‹ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይህች ድንግል ናት፣ በእርሷም የተጎሳቆሉ አሕዛብ ይድናሉ፤ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት› ብሎ ነገረው፡፡›› **ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፣ ዛሬም በተዋሕዶ ወለድኩህ አለኝ፡፡ ለምነኝ አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ፣ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው፡፡›› ዳግመኛም አብ አለ ‹‹ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ካንተ ጋራ ሳለሁ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ፣ እንደ መልከ ጸዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለሙ አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ፣ ከማለም አይፀፀትም፡፡›› ዕንባቆምም ‹‹አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ፤ በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ›› (ዕን ፫፥፪) **ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ‹‹በበረት ውስጥ የዓለም ገዢ መተኛት እጅግ ድንቅ ነው፤ በበረት ከጽርሐ አርያም ይልቅ ረዘመ፤ ከምድር ዳርቻም ሰፋ፤ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ (ሕዝ 1፡18-23፣ ዳን 7፡9) ብለው ተናገሩላት፡፡ #ኢትዮጵያና ግብፅ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ልደት በዓልን ታኅሣሥ 29 (በ4ት ዓመት 1ዴ ታኅሣሥ 28) ቀን ያከብራሉ፤ ለምን የሚለውን ከባሕረ ሓሰብ ሊቃውንትና ከመጻሕፍት እንድታነቡ እየጋበዝን ይህን ሁኔታ በጥልቀት ካጠኑት ዐበይት ሊቃውንት መካከል ዋናዎቹ #ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ፤ #ሰዒድ ወልደ በጥሪቅ፤ #መበንጋዊ/ማኅቡብ/፤ #ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ/አልአሚድ/፤ #ወልደ መነኰስ፤ #ሐዋርያት በዲድስቅልያ አንቀጽ 29 ገጽ 37፤ ሊቃውንት ወመምህራን ዘኢትዮጵያ ወግብፅ /ለአብነትም ከኢትዮጵያውን ደብረ ቢዘንና የጕንዳጒንዶ ሊቃውንት፣ አለቃ አሥራስ የኔሰው፣ አለቃ ሰዐት ከብቴ … እንዲሁም ቅዱስ ድሜጥሮስና ዮሐንስ አቤልሄሬም(ዮሐንስ አቡሻኽር) ከግብፅ ሊቃውንት/ ይጠቀሳሉ፡፡ #ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር የተባበረላቸው ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕና #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ጌና_እና_ልደት ጌና እና ልደት ዋዜማና ክብረ በዓል /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡ #ጌና፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን አይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡ #ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ #‹‹#ቤዛ_ኩሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ::›› /#ቅዱስ_ያሬድ/ ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 በ1ዓ.ም. (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ! ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ ሉቃ2፡10-12፡፡ ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ ሉቃ 2፡13-19፡፡ መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡ #ይህም_ሊታወቅ_አንድ_ባሕታዊ_በቋራ_/_ኋላ_ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም/_ቋርፍ_ሲምስ_ቶራ_ሚዳቋ_ዮም_ተወልደ_ መድኀኔ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ከሣቴ_ብርሃን፡፡ እያለች ስትዘል አይቷል። በጌታችን በልደቱ የባሕር ውኃ ወተትና ማር ተራሮች እንጀራ እንጨቶችም የበረከት ፍሬ ሆነዋል፡፡ ልደቱንም በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ስማቸውም ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ከገነት የተገኘ ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው ገብረውለታል፡፡ /ዘኅ 20፡17፡፡ ‹‹ሰው ሆይ! ፈጽመህ ደስ ይበልህ፣ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡›› ‹‹በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፤ ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ፤ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት፡፡ የማይታወቅ ተገለጠ፣ የማይታይ ታየ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ፡፡›› ‹‹ከቅድስት ሥለሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም እንደ እኛ ሰው ሆነ፡፡ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ፤ ፈጽሞ አዳነን፣ ወገኖቹም አደረገን፡፡›› ይህችም ዕለት፤

ወዳጆቼ ሆይ #ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ፡፡ /1ኛ ቆሮ. 10/ /ይሁዳ 1፥4/ #የጥድ (#የገና) #ዛፍ #በቤተ_ክርስቲያንና_በመጽሐፍ_ቅዱስ_እይታ_ ፠#የጌታችን_ልደት_December_25 #ወይስ_ታኅሣሥ_29 _(በ4ት ዓመት በ28) ፠ #የጥድ_ዛፍ_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_ወይስ_የአውሮፓውያን_ባህል_? ፠ #የጥድ_ዛፍን_ምዕራባውያን_የሚቀበሉበት_ምክንያትና #_ለምን_ልደትን_በጥድ_ዛፍ_ያከብራሉ? ፠ #ሳንታክሩዝ (#የገና_አባት?) #ማነው? #የጌታችን_ልደት_December_25 #ወይስ_ታኅሣሥ_29 _(በ4ት ዓመት በ28) ፠፨፠ ምዕራባውያን የጌታችንን ልደት የሚያከብሩበት ምክንያት፤ 1ኛ) በ December 25፤ የጥንታውያን የግብጽ የፀሐይ አምላክ ‹‹ራ›› የተባለው ጣዖት የተወለደበትና በዘንባባ ዛፎች መሃል የሚመለክ፤ ከታች የሰው ሰውነት ራሱ የአሞራ ጭንቅላቱ ላይ ፀሐይን የከበበ ዘንዶ ያለበት ጣዖት የሚያመልኩበት ነው፡፡ 2ኛ) በDecember 25፤ ሚትራስ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚታወቅ ባዕድ አምልኮ የሚመለክበት በመሆኑ፤ 3ኛ) በ December 25፤ ሳተርን ሊያ፤ የጥንት የሮማ የእርሻ አምላክ በመባል የሚታወቅ ነው፡፡ በራቁት ጭምር ብዙ ኃጢአት የሚገበርለት ነው፡፡ በ3ኛውና በ4ኛው ይህን ጣዖት አንቀበለም በማለታቸው በርካቶች ሰማዕትነት ተቀብለውበታል፡፡ (ካቶሊካውያን ከላይ የጠቀስናቸውን የባዕድ አምልኮ እናስተዋለን ሲሉ ነው ዲሴምበር 25 የደነገጉት) ፠፨፠ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን የነቢያትን ትንቢት ፥ የአበውን ቀመር (የ15ቱ ሱባኤያትን ቀምረን)፤ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረትነት ነው፡፡ #ምዕራብውያን_ለምን_ልደትን_በጥድ_ዛፍ_ያከብራሉ? በምዕራቡ ዓለም ሰዎች በአንድ ዓመት ውስጥ የሚመጣ ሁለት/፪/ ክስተቶች አሏቸው፡፡ 1ኛ) የዘጠኝ ወር ክረምት ሲሆን 2ኛ) ለሦስት ወራት የሚቆይ የበልግ ጊዜ ነው፡፡ በዘጠኝ ወር ክረምት ሲሆን ለዘጠኝ ወር ያህል መሬት ልምላሜ አትሰጥም፡፡ ዛፎች ይሰባበራሉ፡፡ ቅርንጫፎች ቅጠሎች ይወድቃሉ፡፡ ፍሬዎች ይረግፋሉ፡፡ በክረምት ወራት በሚዘንበው ዝናብ በረዶ የቀላቀለ በመሆኑ የበረደው ክምር መሬቱን ስለሚሸፍን መሬት በረከቷን አትሠጥም በእዚህ የተነሳ ለዘጠኝ ወራት ያህል ይራባሉ፡፡ ይጠማሉ፡፡ ታዲያ በእነርሱ አመለካከት ይህንን የክረምት ወቅት የጨለማ እና የክፉ አምላክ ዘመን በመሆኑ ነው እንጂ ደግ አምላክ ቢሆንማ እንደዚህ አያሰቃየንም ብለው ያስባሉ፡፡ በሁለተኛው ክስተት ማለትም ለሦስት ወራት ያህል ፀሐይን የሚያዩበት አርሰው ፥ ዘርዘርተው የሚያመርቱበት ለዘጠኝ ወራት የሚሆናቸውን ቀለብ የሚሰበስቡበት ነው፡፡ በአጠቃላይ የልምላሜ፣ የጥጋብ እና የተስፋ ወራታቸው ነው፡፡ በዚህም እንደ እነርሱ አመለካከት ይህን የበጋ ወቅት የብርሃን የደጉ አምላክ ዘመን ይሉታል፡፡ #ምዕራብውያን_ለምን_ልደትን_በጥድ_ዛፍ_ያከብራሉ? በእነርሱ ፍልስፍና ምንታዌ/ሁለት/ አማልክት አሉ ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በክረምቱ የዘጠኝ ወራት ውስጥ ብዙ ዛፎች ሲገነደሱ፣ ሲቈረጡ ፣ ፍሬያቸው ሲረግፍ አንድ ዛፍ ግን ፍሬው ሳይረግፍ ሳይገነደስ የዘጠኝ ወር ክረምቱን ያሳልፋል፡፡ ይህም ዛፍ ጥድ ነው፡፡ ጥድ ዛፍ ከሌሎች ዛፎች ሁሉ ጠንክሮ ፀንቶ የሚቆየው በተፈጥሮ ፅኑ ጠንካራ በመሆኑ እንጂ ሌላ ተአምር ኖሮት አይደለም፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ አውሮፓውያን ለገዛ ሓሳባቸው ሲሉ ጥድ ምንም አለመሆኑ ደጉ አምላክ ያንን የክፉ አምላክ ዘመን የሚያሳልፈው በጥድ ዛፍ ውስጥ ስለተሸሸገ ነው፡፡ የጥድ ዛፍ ለደጉ አምላክ ቤተ መቅደስ ነው ይላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ የጥድ ዛፉን በዓመት በዓመት ክረምቱ አልቆ በጋው ሲገባ የደጉ አምላክን መቅደስ እያስጌጡ በጥድ ያመልኩ ነበር፡፡ የክርስትና ሃይማኖት ሲስፋፋና ሲቀበሉ ይህን አምልኮታቸውን አዲስ ከተቀበሉት ሃይማኖት ጋር በማስተሳሰር ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት አዲስ ስም ሰጥተው ይጠቀሙበት ጀምረዋል፡፡ ከጌታችን ልደት ጋር ያስተሳሰረው ይህ ብቻ ሳይሆን የደጉ አምካቸውን መቅደስ የሚስጌጡበት ማለትም ክረምቱ አልቆ በጋው የሚገባበት /የዘመን መለወጫው/ እና የጌታችን የመድኃኔታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በጊዜ አቈጣጠራቸው መገናኘቱ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የድሮ ባህሎቻቸውን እንዳይረሱ ቀናቶቻቸውንም ጭምር ስማቸውን በአማልክቶቻቸው ሰይመውታል፡፡ ለምሣሌ፤ ቀኑ ስያሜውን ያገኘው *Monday (ሰኞ) --------------------------- Moon day ጨረቃን የሚያመልኩበት ቀን *Sunday (እሑድ) ----------------------- Sun day ፀሐይን የሚያመልኩበት ቀን *Saturday (ቅዳሜ) ----------------------- Star day ኮከብን የሚያመልኩበት ቀን *Tuesday (ማክሰኞ) -------------------- Tues day (“Tues” የተባለ ጣኦታቸውን የሚያመልኩበት ቀን) ** የX MASS tree (የገና ዛፍ) የተጀመረው ከሳተርን ሊያ (የጥንት የሮማ የእርሻ አምላክ) ሲሆን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤቱ ያስገባው የጀርመኑ ሃገር የመናፍቅ ሰባኪ ማርቲን ሉተር ነው፤ ወደ አሜሪካ ደግሞ በ1830ዎቹ ከጀርመን ወደ አሜሪካ የተሰደዱ ፔንሲልቫንያዎች ናቸው ከክርስቶስ ልደት ጋር እያያዙ ማክበር የጀመሩት፤ በ1940ዎቹ በአሜሪካና በሌሎቹም ዓለማት እየተስፋፋ መጣ፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የእነርሱን ተከትለን እንዴት ወደ ስሕተት አንዴት እንገባለን!!፡፡ ነገር ግን ከአንድም ሁለቴ ተሳስተናል፡፡ ፠ አንደኛ ሁለት አምላክ አለ ብለን የምናምን አይደለንም ፠ ሁለተኛ እግዚአብሔር ይህችን ቅድስት ሃገር ስለባረካት ክረምቱ ፪ ወራት ብቻ መሆኑ ነው፡፡ በክረምቱም ይህንን ያህል የበረዶ ግግር የለብንም፡፡ ስላደረገልን ነገር ሁሉ ማመስገን አለብን እንጂ፡፡ #ሳናታክሩዝ_፤ አንዳንዶች በ4ኛው ክ/ዘመን ከተነሣው ቅዱስ ቅዱስ ኒኮላስ ጋር አገናኝተው ለልጆች ስጦታ ከሚሰጠው ጋር ለማገናኘት ይሞክራሉ ግን ይህ ሐሰት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ አስተሳሰብ፤ *ሳንታክሩዝ መጥቶ ሌሊት ስጦታ ይላል በሚል ሕፃናቱ፤ ሐሳባዊ በሆነ (በስዕል ነጭ ረዥም ጢም ያለውን ሰው አለ ብለው ሐሰት እንዲማሩ) ያደርጓል፤ ስጦታውን የሚሰጡ ቤተሰቦች ሆነው ሳለ፡፡ *ሰዎች በጌታ ልደት መወለዱን ሳይሆን ሳንታክሩዝ ይመጣል ብለው እንዲያስቡ አድርጓል፤ * ከማንኛውም ነገር ነላይ የጌታ ልደት ይበልጣልና መታሰብ ያለበት የጌታ ልደት እንጂ ሳንታክሩዝ መሆን የለበትምና፡፡ እንግዲህ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምንም ኅብረት እንደሌለው አውቀን የምናደርገውን ከማድረጋችን በፊት ልንጠይቅ ልንሰማ ልንማር ያስፈልጋል፡፡ አባቶቻችን የልደትን በዓል እንድናከብር ያስተማሩን ዛፍ ቆርጦ በማቆም ሳይሆን የተደረገልንን ድኅነት እያሰብን(አምላክ ሰው ሆኖ እንዳዳነን) ፥ እንደ መላእክት እንደ እረኞች በስብሐተ ለእግዚአብሔር ፥ እጅ መንሻ አምሃ በመስጠት ፥ በመረዳዳት ፥ የታመመን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል፡፡ ስለ ቅዱስ ኒቆላዎስ (የገና አባት) በቀጣዩ ጽሑፋችን ይጠብቁን ወዳጆቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ፡፡ /1ኛ ቆሮ. 10/ /ይሁዳ 1፥4/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ /ምንጭ፤ የፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔትና የመ/ር ለማ ‹ወዳጆቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ› የሚል ስብከት፡፡)

የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡

የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡
የ2013 ዓ.ም የታኀሣሥ ወር ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማስታወሻዎች ፤ከፍቶ ማሕደራችን፡