uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 336 підписників, посідаючи 5 643 місце в категорії Релігія і духовність та 2 190 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 336 підписників.

За останніми даними від 13 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -75, а за останні 24 години на 2, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 22.35%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.54% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 428 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 616 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 25.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 14 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 336
Підписники
+224 години
-47 днів
-7530 день
Архів дописів
መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት #‹‹እኔ በሕመም የምሠቃይ በሽተኛ ነኝና አቤቱ ይቅር በለኝ!፤ #አጥንቶቼም ታውከዋልና ፈውሰኝ፤ ከዚህ የተነሣ ነፍሴ እጅግ ተጨነቀች››፡፡ አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱንና ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18 በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡- ፨ በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡ ፨ ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡ ፨ መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ 38 ዓመታት መጽናት እንጂ ስሙ አይደለም፡፡    በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡ ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡ አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡ በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡ #በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡ ፨ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9 ፨ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13 ፨ ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ ፨ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡ ፨ የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡ ፨ ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ /ምንጭ፦ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 አንድምታ/       ፨፨፨ወስብሐት ለእግዚአብሔር፨፨፨ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፨ ቅዱስነትዎ እንኳን አደረስዎ ፨ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundayS
፨ ቅዱስነትዎ እንኳን አደረስዎ ፨ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

አገር ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ስዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣ ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጐች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል፤ በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል፡፡ የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች፡፡ በመጨረሻም ስለስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸልያለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቋሚ ሲኖዶስ የካቲት 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ ‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት›› (ማ
+4
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ ‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት›› (ማቴ 5÷51 ፤ ቅዱስ ያሬድ) ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት፣ በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ h10 የሚበልጡ አባውራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡

#በጣሊያን_ወረራ_ወቅት_አስተዋጽዖ_ካደረጉት_መካከል_ዐበይቶቹ_ገዳማትና_አድባራት፤ #ከካህናት፡፡ ፋሽስት ኢጣሊያ በ5ቱ ዓመት ወረራዋ ጀግኖች አርበኞችን ስላልቻለቻቸው ንጹሐን ዜጋዎችን በመግደል፤ እንዲሁም የተደበቁበትን ገድልና ዱር አላገኝ ስትል፤  ገዳማትንና አድባራትን አቃጥላለች፡፡  እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት 460,770 (በጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጽሐፋቸው ደግሞ 746,800 ሰዎችን በግፍ ገድላለች፤  300ሺህ ሰዎች ደግሞ በስደት ሲንከራተቱ በረሃብ አልቀዋል፤  2,000 አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥላላች፣  በርካታ ንዋያተ ቅድሳትንም ዘርፋ ለካቶሊኳ ቫቲካን ሰጥታለች፡፡ ፠ይህንን እኩይ ተግሯን በግንባር ቀደምትነት የተፋለሟት፤ ዐበይቶቹም፤ ፠ የ፳ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕታት #ብፁዕ_አቡነ_ጴጥሮስ_(ሐምሌ 22/1929 ዓ.ም. መሐል አ.አ ላይ በስምንት ጥይት ያረፉት)ና #ብፁዕ_አቡነ_ሚካኤል_ (ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም በኢሉባቦር ጎሬ ላይ በግፍ የተገደሉት) ፠ ጣሊያንን አውግዘው በታኅሣሥ 7/1928 ዓ.ም ሲሰየፉ፤ ከአንገታቸው ደም፥ ወተትና ውኃ የወጣው #ታላቁ_ሊቅ_አቡነ_ክፍሌ፡፡ ፠ በግንቦት 28/1929 ዓ.ም. ቊጥራቸው 2,200 የሚሆኑ በግፍ የተጨፈጨፉ #የደብረ_ሊባኖስ_መነኰሳት፡፡ ፠ በግንቦት 29/ 1929 ዓ.ም በቅዳሴ ላይ እንዳሉ የታረዱና ደመና የሸፈናቸው 43 #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ_መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 12/ 1929 ዓ.ም በማስታኮት ላይ እያሉ የተገደሉ አስከሬናቸውን ሳይቀር በአካፋ የተሰቃየው 211 #የዝቋላ_መነኰሳት፡፡ ፠ በጥቅምት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ 2116 የሆኑ #የደብረ_ዳሞ_መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 3/1929 ዓ.ም 60 የታረዱ #የምድረ_ከብድ_መነኰሳት፡፡ ፠ በሰኔ 15/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ በዚህም አንበሶች ከጫካ ወጥተው ያለቀሱላቸው፤ 91 የሚሆኑ #የአሰቦት_መነኰሳት፡፡ ፠ በኅዳር 25/ 1929 ዓ.ም የታረዱ፤ ሲታረዱም ብርሃንም የወረደላቸው፤ 143 #የአዲስ_ዓለም_ካህናትና_መነኰሳት፡፡ ፠ በየካቲት 12/1929 ዓ.ም ከ30 ሺ በላይ በአካፋ ሳይቀር የተጨፈጨፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፡፡ ፠ በመጋቢት 16/1929 ዓ.ም. ከላይ በቦንብ የውሃ ገንዳውን ጭምር፣ ከታች በመትረየስ የተፈጁት 515 #የማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም መነኰሳት፡፡ የበቁ አባቶችም በጸሎታቸውም አውሮፕላኗን የከሰከሷት፡፡ ፠ በመጋቢት 17/1929 ዓ.ም የታረዱ ብዛታቸው በውል ያልታወቁ #የደብረ_ዓባይ_ገዳም መነኰሳት፡፡ ፠ በሚያዝያ 18 ና ሚያዝያ 20/1929 ዓ.ም የታረዱ 363 #የመርጦ_ለማርያምና_የተድባበ_ማርያም ካህናትና መነኰሳት፡፡ ፠ በሐምሌ 29/1929 ዓ.ም. እየተለቀሙ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ ግማሾቹ የተሰፉትና ግማሾቹ ደግሞ በግዞት የተወሰዱት #የጎንደር_ሊቃውንት፡፡ ፠ በየካቲት 18/1929 ዓ.ም. የተሠዉት የአዲስ አበባ #የካ_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና ካህናት አባቶች፡፡ ፠ በየካቲት 20/1929 ዓ.ም #በአ.አ ከተማ ያሉ በተለያዩ ገዳማትና አድባራት የሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት ተለቅመው እንዲሰበሰቡ ከተደረገና ከተደበደቡ በኋላ እጅና እግራቸውን አስረው እሳት አጉርሰዋቸዋል፡፡ ፠ የትግራይ #ጨለቆት_ሥላሴ አገልጋዮችና (ርዕሰ ደብር የነበሩትን አስተዳዳሪውን ጨምሮ) አስረው ‹‹በሮማ ካቶሊክ ታምናላችው ወይስ በረሃብ ትሞታላችሁ?›› እያሉ በረሃብ አሠቃይተዋቸዋል፡፡ እምቢ ቢሏቸው ጽኑ ግርፋት ገርፈው ከለቀቋቸው በኋላ በመኪና ገጭተው ገድለዋቸዋል፡፡ ፠ #ይደመቆ_ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን /ሰሜን ሸዋ/ ፠ #አፈር_ባይኔ_ተክለ_ሃይማኖት ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ ፠ #አክርሚት_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ/ ፠ #ጎበጥ_አገር_ገብርኤል ቤ.ክ /ሰሜን ሸዋ እመ ምሕረት/ ፠ #አንኮበር_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ. ፠ #ደረፎ_ቅድስት_ማርያም ቤ.ክ. /ሰሜን ሸዋ ደረፎ/ ፠ #ጎንቻ_መድኀኔ_ዓለም ገዳም /ምሥራቅ ጎጃም/ ፠ #አንኮበር_ቅዱስ_ሚካኤል ቤ.ክ.፡፡ #ጀግናውና_የቅኔው_አዝመራ_አለቃ_መርሻ_ወልደ_ማርያም ከዚህ በታች የቀረበውን ግጥማዊ ቅኔ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ሊገድሏቸው የመጡትን ጣልያኖች አብዛኛውን ፈጅተው በሐምሌ 12/1928ዓ.ም. በሰማዕትነት ያረፉት የ70 አዛውንቱ ጀግናና የቅኔው አዝመራ አለቃ መርሻ ወልደ ማርያም ከመሞታቸው ከ8 ቀን ቀድመው እንዲህ ብለው ተቀኙ፡፡  ተምሮ ተምሮ ካልሰበሰቡት፤ እንዴት ያሳዝናል ሲባክን ዕውቀት፡፡ ሂጅ ተመለሽ ግቢ አገርሽ ቅኔ፤ ወንዶች ከዋሉበት መዋሌ ነው እኔ፡፡  ለጀግንነታቸውም መታሰቢያ ደግሞ የሚቀጥለው ግጥማዌ ቅኔ ቀረበላቸው፤ አለቃ መርሻ አይፈራም እጁ፤ ጠላት ሲጋበዝ እንደ ወዳጁ፤ ገሥግሠው ሄደው እንደ ጐመጁ፤ በሽጉጥ ጠርሙስ ፩ድ ፩ዱን ፈጁ፡፡ መርሻ ቢያጠጣው የሽጉጥ ጠላን፤ ወዲያው ወደቀ ግብዙ ጣሊያን፡፡ ፠ ከ1927-1934 ዓ.ም. ለ7ት ዓመታት ጣሊያን በሀገራችን ላይ ያደረሰችው ጥፋት፤ *በኢትዮጵያ ሰሜንና ደቡብ በየቀለቡና በማደሪያው ከዘመተው የሞቱ፤ *ጠላት አዲስ አበባ በገባ ጊዜ ዓረቦችና ዓርመኖች ግሪኮች ተዘርፈናል በማለታቸው ምክንያት የሞቱ፤ **የካቲት ሚካኤል (የካቲት 12) ዕለት በአካፋ በዱላ በእሳት ያለቁ ከ30,000 በላይ ሰማዕታት፤ *በአርበኝነት በየጊዜው በጠላት እጅ የሞቱ፤ *በደኅንነት አገር ቤት ላይ ሳሉ ሳያስቡት በጠላት እጅ የሞቱ፤ *ወደ ስደት ሲሄዱ በችግር ምክንያት በየመንገዱ የሞቱ፤ *በፌርማቶሪ አመልካችነት በየቀኑ የሞቱ፤ *ጠላት ከኢትዮጵያ ሊወጣ ሲል በተደረገው ጦርነት የሞቱ፤ *ከጠላት ወገን ሆነው (ባንዳዎች) ሆነው ከተዋጉ ባንዳ የሞቱ፡፡ *ሞሶሎኒ ባነሳው ጦርነት በየቀኑ በሚደረገው የግፍ ሥራ ያላግባብ የሞቱ (በሆለታ ተማሪ ቤት የነበሩ ወጣቶች፣ *350 የሚጠጉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ሮምና ሞቃድሾ እስር ቤት ተላኩ፤ ከ2500 በላይ ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው እንዲማቅቁ ተደረጉ፡፡ በእስረኞችና በምርኮኞች ላይም አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽማለች፡፡ **ኢጣሊያ ላደረሰችው ጥፋት 326 ቢሊዮን ሊሬ ቢወሰንባትም የሰጠችው ግን 105 ቢሊዮን ሊሬ ብቻ ነው፡፡  (እንደ ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ዘገባ ደግሞ 175 ሚሊዮን ስተርሊንግ ተወስኖባት የከፈለችው 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው)፡፡ በከፈለችው ገንዘብም የቆቃ ግድብ ብቻ ተሠርቶበታል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡ #9ኛው #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት፡፡ 9ኛ  #አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡ ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ_ ተራራ ላይ ነው፡፡ #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት_መነሻ ፠ ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡ ፠ መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ (እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡ ፠ ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ  (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጦርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡  ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ #ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ /የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡/  ከ1878-1888ዓ.ም. #ከዓድዋ_በፊት_የነበሩ_8ቱ_አድዋዎችና_የዓድዋ_ሶሎዳ_ውጊያ፤ 1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ_ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡ 2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ 3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ_መንደር_ ውጊያ፡፡ 4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት_ ከጥር 13-15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡ 5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ_ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡ 6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡ 7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡) 8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡ --- /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

ምኵራብ፤ ሦስተኛው የአቢይ ጾም ሳምንት ምንት ሦስተኛው ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡ በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡ በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡ በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡ ፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16 ፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52 ፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1 ፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem