uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 526 підписників, посідаючи 5 408 місце в категорії Релігія і духовність та 2 214 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 526 підписників.

За останніми даними від 29 вересня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -30, а за останні 24 години на -5, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 22.76%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 4.01% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 534 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 623 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 21.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 30 вересня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 526
Підписники
-524 години
-157 днів
-3030 днів
Архів дописів
• ይህን ችግር ለመቅረፍ የተነሡት የዘመኑ ፓትርያርክ ከሀቢብ ጊዮርጊስና ከሌሎች ሁለት ምእመናን ጋር በመሆን ሐዋሪያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ሀቢብ በውጪ የሚገኙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶችን የሚሰበስብበትን ዘዴዎች መመልከት የቻለው፡፡ ወዲያውኑ ከጉዞው መልስም ህጻናትና ወጣቶች ተሰብስበው የሚመሩባቸውን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማደራጀትና የሚመጥናቸውን ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ መንፈሳዊ መዝሙራትንም ለማዘጋጀት አቅዶ ሥራውን ጀመረ፡፡ በዚህ ሥራውም በሌላ እምነት ተማርከው የነበሩትን መመለስ ችሏል፡፡ ሀቢብ ጊዮርጊስ #ጸሐፊነትን፣ #አስተዳዳሪነትን እና #ሰባኪነትን በእኩል ደረጃ አሳክቶ መያዝ የቻለ ሰው ነው፡፡ በአጠቃላይ #ሠላሳ_መጽሐፍትን አዘጋጅቷል፡፡ በመጨረሻ ዕድሜው ሲገፋ #ጤናውም_እየታወከ_መጣ፤ ቤቱም በደቀ መዛሙርቱ መሞላት ጀመረ፡፡ ለእርሱም የነበራቸውን ፍቅር ለመግለጽ መኝታን ከበው አብረውት ጸሎት በማድረግ ራሱ የደረሳቸውን #መዝሙራትም_ይዘምሩለት ነበር፡፡ በመጨረሻ ሀቢብ ጊዮርጊስ ነሐሴ 15 ቀን 1951 ዓ.ም (በ75 ዓመቱ) አረፈ፡፡ ዜና እረፍቱም በሀገረ ግብፅ ከዳር እስከ ዳር ተሰማ፡፡ ቀብሩም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት መስከረም 17 ቀን 1951 ዓ.ም ተፈጸመ፡ ምንጭ፡-ሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ እና ሥራዎቹ፣ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/Finotehiwott

#ሊቀ_ዲያቆናት_ሀቢብ_ጊዮርጊስ #ለግብጽ_ቤተ_ክርስቲያን_የንጋት_ጎህ (ነሐሴ 15 እረፍቱ) #ሀቢብ_ጊዮርጊስ_ማነው? ሀቢብ ጊዮርጊስ በ1976 ዓም #በካይሮ_ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ በሕጻንነቱ ስለሞተበት እናቱ ለብቻዋ በፍቅረ ቤተ ክርስቲያን አንጻ አሳደገችው፡፡ ትምህርቱን የተከታተለው አቡነ ቄርሎስ አምስተኛ በመሠረቱት ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ በዚያውም #ዲቁና ተቀብሎ ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው #አሥራ_ሰባት ብቻ ነበር፡፡ በወቅቱ ፓትሪያርኩም በኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የተከሰቱትንና የቤተክስቲያኒቱን አገልግሎት እጅጉን የጎዱ እንቅፋቶች በማስወገድ ወደ ለውጥ መንቀሳቀስ የጀመሩበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሆኖ የተገኘው #የሰለጠኑ_ካህናትን_የሚያፈራ_ተቋም_መክፈት ስለነበር ለዚህ ወሰኝ ተልዕኮ የሚመጥን ይሆናል የሚሉትን ሰው ሲፈልጉ ምርጫቸው ያረፈው በወጣቱን አገልጋይ ሀቢብ ጊዮርጊስ ላይ ሆነ፡፡ ሀቢብ ጊዮርጊስ ኃላፊነቱን እንደተቀበለ ትኩረቱን ያደረገው ለተቋሙ ግንባታ የሚያስፈልገውን ገቢ ማሰባሰብ ላይ ነበር፡፡ በውጤቱም ከሀገር ሀገር እየተዘዋወረ ባደረገው ቅስቀሳ የምእመኑን የታመቀ ፍቅር ማቀጣጠል የቻለ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ የተገኘው ድጋፍም በቂ ሆኖ ስለተገኘ ኮሌጁ እንደታሰበው ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡ ኮሌጁ ተከፍቶ ማስተማር ሲጀምር ደግሞ ሀቢብ ጊዮርጊስም ከመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች አንዱ ለመሆን የቻለ ሲሆን በወቅቱ የተከሰተውን የመምህራን እጥረት መቅረፍ ግድ ሲሆን ደግሞ ተማሪ በሆነበት ዓመታት መምህርነትንም ደርቦ ያዘ፡፡ የሀቢብ አስደናቂ አገልግሎት በስፋት የተገለጠው ከተመረቀ በኋላ ሲሆን በሰባኪነት ተሰማርቶ የሰበካቸው ስብከቶች በወቅቱ ሰማዕያኑን የመሰጡ ብቻ ሆነው አልቀሩም፡፡ ይልቁንም ብዙዎች ከሞተ በኋላ እንኳ ሳይቀር የሚያስተውሷቸው እንዲሁም ታትመው የብዙዎችን ሕይወት ሲለውጡ የሚኖሩ ሆነዋል፡፡ ለመሠረተው ኮሌጅ ማደግ ከፍተኛ ራእይ የነበረው ሀቢብ ጊዮርጊስ በዚያ ወቅት ከሠራቸው ሥራዎች መሀከልም ጉልህ የነበረው በኮሌጁ ዙሪያ የነበሩ ቦታዎችን ባገኘበት አጋጣሚ ሁሉ በግል ገንዘቡ እየገዛ ለኮሌጁ ማስፋፊያ ይሆን ዘንድ ማበርከቱ ይጠቀሳል፡፡ በዚህና መሰል ወደር የለሽ ተግባራቱና ከፍ ያለ ትጋቱ የተደሰቱት ፓትሪያርኩ አቡነ ቄርሎስ #የሊቀ_ዲያቆንነት_ማዕረግን_ሰጡት፡፡ የሀቢብ ጊዮርጊስ ቀጣይ የአገልግሎት ምዕራፍ የኮሌጁ ርዕሰ መምህር በሞት በተለየ ጊዜ እርሱን በመተካት የርዕሰ መምህርነትን ኃላፊነት ሲጨምር የሚጀምረው ነው፡፡ በዚህ ወቅት ከሠራቸው ተግባራት መሀከልም ዋነኛው ኮሌጁን ከውጪ ተጽእኖ የተጠበቀ እንዲሆነ ማድረጉ የመጀመሪያው ሲሆን በመከላከል ብቻ ላይም ሳይወሰን ተቋሙ #የኦርቶዶክሳዊት_ቤተ_ክርስቲያንን_ትምህርት_በምልዓት_የሚያንጸባርቅ መብራት ማድረግ መቻሉ ደግሞ ሌላው ዘለዓለማዊ ስኬቱ ነው፡፡ በተለይ ኦርቶዶክሳዊያን ደቀመዛሙርት ወደ አንግሊካን የትምህርት ተቋማት ሄደው የከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተሉ የሚል ግፊት ሲነሳና እንዲሁም የአንግሊካን ምሁራን በኮፕቲክ የሥነ መለኮት ኮሌጅ እንዲያስተምሩ ሐሳብ ሲመጣ ይህን በመቃወም ግፊቱ ከሐሳብ አልፎ በተግባር እንዳይውል ማድረግ መቻሉ ነበር፡፡ የሀቢብ ልዩ ችሎታ የነበረው በመቃወምና በመከላከል ላይ ብቻ አለመወሰኑ ይልቁንም ከተቃወመው ሐሳብ የተሻለ አማራጭ እንዲኖር መሥራቱ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ በኦርቶዶክሳዊው የትምህርት ተቋም ውሰጥ የአንግሊካን ሊቃውንት እንዳያስተምሩ በማለት አጥብቆ ሲቃወም በምትኩ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊውያን አስተምህሮ በጥልቀት የተረዱ ቀሳውስት እንዲኖሩ አጥብቆ ይሠራ ነበር፡፡ ሌላው የሀቢብ ጊዮርጊስ ጅምር የነበረውና ባለፉት ቅርብ ዓመታት ውሰጥ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን መነቃቃት መንስኤ የሆነው ተግባር ደግሞ ኮሌጁ የማታ የትምህርት መርሐ ግብር እንዲጀምር ማድረጉ ነው፡፡ የዚህ አዲስ መርሐ ግብር መከፈት በርካታ ምሁራንና ወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡና በትምህርተ ሃይማኖት እንዲታነጹ እድል ከመስጠቱም በላይ በዚህ ምክንያትነት #የግብጽ_የትምህርት_ሚኒስቴር_ለኮሌጁ_እውቅና_ሊሰጠው_ችሏል፡፡ በማታው መርሐ ግብር ተካፍለው ከነበሩ ወጣት ምሁራን መካከል #ፖፕ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ አንዱ ናቸው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ለኮሌጁ እድገት ዕድሜውን ሁሉ የተጋው ሀቢብ ጊዮርጊስ ኮሌጁን በማሳደግ ዓለም አቀፍ ደረጃውን እንዲጠብቅ ማድረግ የቻለ ሲሆን መደበኛው የሥነ መለኮት ትምህርት በፍልስፍናና በሥነ ልሳን ትምህርቶች የታጀበ እንዲሆንና እንዲሁም በብቁ መምህራን የተሞላ በማድረግ የምርጥ አገልጋዮች መፍለቂያ እንዲሆን ስላደረገው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በቤተ ክርስቲያን ክህነት የሚቀበሉ ሁሉ የኮሌጁ ዲፕሎማ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ ሕግ ተሠራ፡፡ ሀቢብ ጊዮርጊስ በሕይወት ኖሮ የኮሌጁን አርባኛ ዓመት ለማክበር የበቃ ሲሆን በዚያው ዓመትም ‹‹#የነገረ_መለኮት_ኮሌጅ_ትናንትናና_ዛሬ›› የሚለውን መጽሐፉን ለሕትመት አብቅቷል፡፡ #የሰንበት_ትምህርት_ቤት_ጅማሮ ሀቢብ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ሰንበት ትምህርት ቤት በማቋቋም ሥራውን ሲጀምር የ24 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ ጊዜውም 1900 ዓም ቦታው ካይሮ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የኮፕቲክ አብያተ ክርስቲያናት፡፡ ጅማሮው ሕጻናትን ሰብስቦ በማስተማር ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት አገልግሎቱ ተባርኮለት ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረጽ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቋቋመ፡፡ ይህም ውጥን በሀገሪቱ በሞላ ተስፋፍቶ አገልጋዮች እጅግ የበዙ ሆኑ፡፡ በሀቢብ ጊዮርጊስ የተቋቋሙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በወጣቶች ልቡና ውስጥ መተከል እንዲችል ሕያው ምስክር ሆኑ፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በግብጽ የመጻሕፍትና የበራሪ ጽሑፎች ስርጭት፣ ዐውደ ርእያት፣ ሴሚናሮች፣ ኮንፈረንሶች፣ ወደ አብያተ ክርስቲያናትና ወደ ገዳማት የሚደረጉ መንፈሳዊ ጉዞዎችንና የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የመነጩት ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ነው፡፡ #የሰንበት_ትምህርት_ቤቱ_መስፋት_ምን_ጠቀመ? ሀቢብ ጊዮርጊስ የመሠረተው የሰንበት ትምርት ቤት እንቅስቃሴ ከተስፋፋ በኋላ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያንን ይፈታተኑ የነበሩ ችግሮችን በእግዚአብሔር እርዳታ መፍታት የሚችል ሊሆን በቅቷል፡፡ ከነዚህም መሀከል የሚከተሉት ዐበይት ተግባራት አይዘነጉም፡፡ • መጽሔቶችን በማሳተም ስብከተ ወንጌልን የማስፋፋት ሥራ በብዛት የተሠራው በዚህ ዘመን ነው፡፡ • ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳይመጡ የቀሩ ወጣቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲቀርቡ አድርጓል፡፡ • በዘመኑ የነበሩ እንግሊዛውያን ሚስዮናውያን የቅኝ ገዢዎችን አካሄድ በመከተል ኦርቶዶሳውያንን ከእምነት ለማስወጣት ይጥሩ ነበር፡፡ • ሚስዮናውያኑ በተለይ የትምህርት ዕድል በመስጠትና በመሳሰሉ ዘዴዎች በመጠቀም ወጣቶችን ለማማለል ይሞክራሉ፡፡ ቤት ለቤት እየዞሩ ማራኪነት ባላው ጽሑፎችና ባሸበረቁ ሥዕላት ያዘጋጁዋቸውን ብሮሹሮች በመበተን የሚሠሩት የቅሰጣ ተግባር አልበቃ ብሏቸው የእናት ቤተ ክርስቲያንን ስም ጥላሸት እስከ መቀባት ደርሰው ነበር፡፡ በዚህም ተግባራቸው ብዙዎች ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጠፍተዋል፡፡

#እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ በ485 ዓ.ም በንጉሥ አልአሜዳ ዘመነ መንግሥት ባቀኑ ጊዜ የተሰባሰቡባት ቦታ ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር) ሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባ፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ዘአብየ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ በዚህች በተቀደች ቦታ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡ ይህች ሐመረ ኖኅ፤ በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡ በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም #ታቦተ_ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው #በእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነምሕረት_ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሳት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡ በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ #ከንጉሥ_ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ #አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹#ዳሯ_እሳት_መሐሏ_ገነት_ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ #አፄ_ልብነ_ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየ ቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ #በንግሥት_ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም #ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡ ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም #ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ ከዋልድባ ያሉ አባቶች በተለያየ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት #ጥንተ_ርስታቸውም ናት፡፡ ይህች ቦታ በርካታ ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት እንደመኾኗ፤ ጸበሏ #የአጋንንት_ድል_መንሻ፤ #የብዙ_መነኮሳት_መጠጊያ፤ #የሕሙማን_መፈወሻ፤ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/  ꔰ    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/Finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot #ኪዳነ_ምሕረት #ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም #ቅዱሳን  #Saints  #ክብረ_በዓላት #Feasts   #Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም

#እንኳን_አደረሳቹሁ ፡፡ በዓለ ፍልሰታ ወዕርገታ ለማርያም ወፍልሰተ አጽሙ ለሊቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለ መኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው። ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። በዚህችም ዕለት ከፋርስ ወደ ልዳ የሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍለሰተ አጽም ሆኗል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ ፠፠፠ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot #Share #like

መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ -ሐምሌ 24 1962 ዓ.ም. ዕረፍታቸው ነበር፡፡ -እውነተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን ሊቅ (Doctor of the Church) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ (1885-1962 ዓ.ም) ትምህርትን ከሕይወት ጋር ያስተባበሩ የቀለም ቀንድ ከድል ነሽዋ ቤ/ን ኅብረትን የፈጸሙ ቤተ ክርስቲያንን ስሟን ሲያጠፏትና ሲያክፋፏት የብዕር ዘገራቸውን ያነሱ፣ ቤ/ን ራሷን እንድትችል የታገሉ፣ ልጃቸውን ምኅርካ ክርስቶስን ከሞት ያስነሱ እውነተኛ ጸሎተኛ አማኝ ትሑት ናቸው፡፡ ከሞት የተነሳውን ልጃቸውን ምስክርነት ማንበብ የፈለገ 1990ዎቹ ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ፈልጎ ማንበብ ይችላል፡፡ -አለቃ አያሌው “ጥያቄዎቸን ሁሉ የማጣራባቸው፣ መድሎተ አሚንና ኰኲሐ ሃይማኖት ሲዘጋጅ አብሬያቸው የነበርኩ፣ ሲበሉም በአንድ እጃቸው መጻሕፍትን ይዘው ነው ዓይነዎ ይጎዳል ይደክማል ሲባሉ ለማንበብ ካላገለገለ ይፍረጥ ይሉ እንደነበር መስክረውላቸዋል፡፡” (ሐዲሰ ሰውነት በሚለው የመልአከ ብርሃን አድማሱ መጽሐፍ የመግቢያ ጽሑፍ ላይ የመሰከሩት) -አብዛኛዎቻችን የዚህ ትውልድ አባላት የተቸገርነው ነገር ቀደምት ሊቃውንትንና ሥራዎቻቸውን አለማወቅና ለማወቅ ጥረት አለማድረግ ይመስለኛል፡፡ ጠንከር ያለ ነገር መስማትም ማንበብም የምንፈልግ አይመስልም፡፡ ለዚህም ይመስላል የማንንም አጥማቂና ሰባኪ ነኝ ባይ ገለባ መልእክት ስንሰማ፣ ስናደንቅና ስንከራከርላቸው የምንውለው፡፡ አብዛኛዎቻችን ሃይማኖታችንና ዋኖቻችን ስለማናውቅ ማንም አጥማቂ ሲነዳንና አድርጉ የሚለንን ስንፈጽም የምንታየው፡፡ -ለመሆኑ ስንቶቻችን የሊቁ አድማሱ ጀንበሬን ታሪክና ሥራዎቻቸውን እናውቃለን? ኦርቶዶክሳዊያን ካላነበብነው የሊቁን አድማሱ ጀንበሬን ታሪካቸውንና ሥራዎቻቸውን ለማንበብ መነሳሳት ይገባሀል/ይገባሻል፡፡ ሊያነሳሱና ወደ ዋናው ምንጭ ሊገፉ ከሚችሉ ሥራዎች መካከል በሥስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን መምህራን የተዘጋጀውንና በ2011 ዓ.ም. የታተመውን “አድማሱ ጀንበሬ ሕይወቱ፣ ወሐተታ መጻሕፍቱ” የሚለውን መጽሐፍ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ስለ ሊቁ በድምጫ የሰማንና ፈጽሞ ስለ ሊቁ ሰምቶም ሆነ አንብቦ የማያውቅ ሰው ይህ ድንቅ መጽሐፍ በደንብ ያስተዋውቀዋል፡፡ በብዙ ድካም ላዘጋጃችሁልን መምህራን ምስጋናየ ይድረሳችሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ -መጽሐፉ በ352 ገጽ የተሰደረ ሲሆን በአራት ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ የመ/ር ብርሃኑ አድማስን መቅድም ማንበብ በራሱ በእውነቱ ብዙ ትምህርት መቅሰም ነው፡፡ በምዕራፍ አንድና ኹለት የሊቁን አድማሱ ጀንበሬ ታሪካቸውን በአጭሩ ሳያንዛዛ በጥሩ ሁኔታ ይተነትናል፡፡ እንዲሁም ስለ ቅኔዎቻቸውም ያስረዳናል፡፡ ለምን ለምን አላማ ቅኔዎቻቸውን እንደተጠቀሟቸው ከዕቅበተ እምነት እስከ ነገሥታቱን እስከማሞገስና ማክበር ድረስ ያሉትን ቅኔዎች ያስቃኘናል ከቅኔ ጋር ትውውቅ ለሌለን እንድንረዳውና እንዲገባን አደርጎ ደብተራ በአማን ነጸረ ይተነትነዋል፡፡ ቅኔዎቹን ስታነቡ ትደነቃላችሁ ትገረማላችሁ፡፡ የሊቁ አድማሱ ጀንበሬንም ሆነ የሌሎቹ ባለቅኔዎችን የእውቀት ጥልቀት ያስገርማል ያስደንቃል፡፡ ነገረ ሃይማኖት በቅኔ ሲነገር በቅኔ ምላሽ ይሰጥበታል፡፡ የአድዋ ጦርነት ከመምጣቱ በፊት ትንቢታዊ ቅኔ የተቀኙትን ስማቸው የማይታወቅ አንድ ሊቅ እንደነበሩ ያውቃሉ? ካላወቁ መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡና ይወቁ፡፡ -በምዕራፍ ሦስትና አራት መ/ር ሳሙኤል ፍቃዱ “ኰኲሐ ሃይማኖት” እና መ/ር ያረጋል አበጋዝ "መድሎተ አሚን" የሚለውን የአድማሱ ጀንበሬን የዕቅበተ እምነት ሥራዎች ማንበብ ያላቸውን ጠቀሜታና እንዲሁም እንዴት መጽሐፍቱን እንደጻፏቸው በጥሩ ሁኔታ ያስረዳሉ ይተነትናሉ፡፡ የሁለቱን መምህራን ጽሑፍ ማንበብ የመልአከ ብርሃን አድማሱን መጻሕፍት ያነበበው ሳይቀር እንደገና እንዲያነበው የሚያነሣሡ ናቸው፡፡ ፈጽሞ ላላነበበውም ሊያነሣሣውና እንዴት ማንበብ እንዳለበት ሊያግዘው የሚችል ነው፡፡ መጽሐፉን ገዝተን እናንብብ እናስነብብ እንወያይበት፡፡ -ስጦታም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ለተመራቂዎች መስጠት ካሰቡ ይህን መጽሐፍ ለስጦታ ቢመርጡት ምናለበት? ከዲ/ን ዮሴፍ ፍሥሐ ገጽ የተወሰደ Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

-ነሐሴ 14 1999 ዓ.ም. ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ(1915-1999 ዓ.ም.) ያረፉበት ቀን ነበር፡፡ ሊቁን ሥራዎቻቸውን በማንበብና በማስነበብ እናስታውሳቸው፡፡ እሳቸው ዐይነ ሥውር ሁነው ይኽን ያኽ
-ነሐሴ 14  1999 ዓ.ም.  ሊቁ አለቃ አያሌው ታምሩ(1915-1999 ዓ.ም.) ያረፉበት ቀን ነበር፡፡  ሊቁን ሥራዎቻቸውን በማንበብና በማስነበብ እናስታውሳቸው፡፡ እሳቸው ዐይነ ሥውር ሁነው ይኽን ያኽል መጻሕፍት ከጻፉልን ዐይናማ ነን የምንለው መጻሕፍታቸውን ለማንበብ ለምንስ እንሰንፋለን? -ከጻፏቸው መጻሕፍት መሀከል  1.) መች ተለመደና ከተኲላ ዝምድና (፲፱፻፶፫ ዓ∙ ም∙) 2.) የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት (፲፱፻፶፫ ዓ∙ ም∙) 3.) ምልጃ እርቅና ሰላም(፲፱፻፺፪ ዓ∙ ም∙) 4.) ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ (፲፱፻፸፱ ዓ∙ ም∙) 5.) የኑሮ መሠረት ለሕፃናት (፲፱፻፶፫ ዓ∙ ም∙) 6.)  መልእክተ መንፈስ ቅዱስ(፲፱፻፺፭ ዓ∙ ም∙) 7.) የጽድቅ በር  (፲፱፻፸፱ ዓ∙ ም∙) 8.) ተአምርና መጽሐፍ ቅዱስ። (፲፱፻፺፫ ዓ∙ ም∙) 9.)  ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ። (፲፱፻፺፱ ዓ∙ ም∙) ከዲ/ን ዮሴፍ ፍሥሐ ገጽ የተወሰደ በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤   ꔰ  Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/Finotehiwott

ደብረ ታቦር ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “#ታቦርና #አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው /መሳ. 4፥6/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ #አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም #ሙሴና #ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ #ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ #ሦስት ዳስ እንስራ አንዱን ለአንተ አንዱን #ለሙሴ አንዱን #ለኤልያስ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምፅም ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡ ፠፠፠ #አዕማደ_ሐዋርያት_(#ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ )#ለምን_ተመረጡ አዕማደ ሐዋርያት "አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት #ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ #ሰማያዊ #ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ #ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት ሲል፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡ ፠፠፠ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::  ꔰ   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/Finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት . Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

#ነሐሴ_፲፪ #ቅዱስ_ሚካኤል_ንጉሥ_ቆስጠንጢኖስን_ረደቶ_በድል1ያነገሠበት_ዕለት ንግሥት ዕሌኒም በ272ዓ.ም ታላቁ ቆስጠንጢኖስን ወለደችለት፤ ቆስጠንጢኖስም ገና በወጣትነቱ የአባቱ እንደራሴ ሆኖ እንደሠራ አባቱ ሞተ፡፡ የአባቱ ባለሟሎችና ህዝቡ ተስማምተው የ፲፰ ዓመቱን ቆስጠንጢኖስን በአባቱ ቦታ ሐምሌ ፳፭ ቀን ፫፻ ዓ.ም በሮም ምዕራብ ክፍል በገላትያ አነገሡት፡፡ በጦር ሜዳዎች ብዙ የጀግንነት ሥራዎች ስለሠራ በሠራዊቱ ዘንድ ይወደድ ነበር፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ልጅዋን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለክርስትና ሃይማኖትና ስለክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ በተለይም በ፫፻፲፪ ዓ.ም ከጠላቱ ከመክስምያኖስ ጋር ለመዋጋት "ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት" ብሎ ለዘመቻ እንደተሰለፈ በራእይ በሰማይ ላይ "በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ; የሚል መስቀልና ጽሑፍ ስላየ ለሠራዊቱ ሁሉ #የመስቀል_ምልክት በመሣሪያቸውና በሰንደቅ ዓላማው ላይ እንዲያደርጉ አዘዘ፡፡ ወደያው ጦርነት ቢገጥም #በቲቤር_ወንዝ_ድልድይ ላይ ጠላቱን ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግስት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ሆነ፡፡ ይኸውም የሆነው በመላእክት አለቃ #በቅዱስ_ሚካኤል ረዳትነት ነው፡፡ #ሚካኤል ማለት #መኑ_ከመ_እግዚአብሔ "እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?" ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› (ዳን.፲፪፥፩) በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› (ዳን. ፲፥፲፫) በማለት ያስረዳል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው #ቅዱስ_ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድ መልአክ ነው፡፡ ‹‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም፡፡›› ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ኃይል ዲያብሎስን ድል የነሣ መልአክ ነው፡፡ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፡፡" ራእ ፲፪፥፯-፱፡፡ #ታላቁ_ቆስጠንጢኖስ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ጠላቶቹን ሁሉ ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግሥት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ከሆነ በኋላ በ፫፻ ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ተባለች፡፡ ንግሥት እሌኒም በተፈጠረላት አመች ሁኔታ በመጠቀም #የጌታችን_መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ፫፻፳፯ ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ዕሌኒ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማነጽ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ #ቆስጠንጢኖስ_አምኖ በ፫፻፴፯ ዓ.ም #ተጠመቀ፡፡ ቅድስት ዕሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች ከእርሷም ጋር ብዙ ሠራዊት ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በጸሎቱ የምንታመን ሁላችንን የመልአክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን፡፡ በጸሎቱ ይማረን፡፡ ስንክሳር ዘወርሃ ነሐሴ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/Finotehiwott

#አጋፋሪ_ይደግሳል ፩ኛ ትርጕም አጋፋሪ፤ አሁን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ደረጃ የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር አጋፋሪ ሲባል፤ ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡ ፪ኛ ትርጕሙ፤ አጋፋሪ፤ በቀድሞ ዘመን በሃገራችን በተለይም በቤተ መንግሥት ያለ ሹመት ሲሆን፤ (በጎንደር ፥ በሸዋ ፥ በወሎ ፥ በኢሉአባቦር፥ በሐረርጌ፥  በትግሬ ፥ አጋፋሪ ተብሎ ሲጠራ በጎጃም መጨኔ ይባላል/ ሁለቱንም በቀድሞ ዘመንም ሆነ አሁን ባለው ሁኔታ ትርጕሙን እናያለን ፤ ፠፠፩ኛ ፠፠ አሁን ካለው የቤ/ክን አገልግሎት አንጻር፤ አጋፋሪ ማለት የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር ሲሆን ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡ ይህ አጋፋሪ በደብረ ታቦር በዓል ላይም በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ፤ ‹‹ሆያ ሆዬ›› ይባላል፡፡ ይኸውም ‹‹#ሆያ_ሆዬ_ሆ_››፤ ማለት ጌታው ሆዬ ፥ እሜቴ ሆዬ ለማለት ነው፡፡ ‹‹#እዚያ_ማዶ_ጢስ_ይጤሳል_›› የተባለው፤ እስራኤላውያን በበረሃ ለ40 ዓመታት ሲጓዙ ደመና እየጋረዳቸው (እየጤሰ) ስለመራቸው ነው፡፡ ‹‹#አጋፋሪ_ይደግሳል_››፤ የተባለው አጋፋሪው /አለቃው/ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፤ ይደግሳል መባሉ እስራኤላውያንን ‹‹በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ ፥ ሰላመ ዚአሁ የኀበነ›› እንዲል፤ በአምላክ ትዕዛዝ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከደመናን ፥ ውኃን ከጭንጫ ዓለት እያፈለቀ (እየደገሰ) መርቷቸዋልና ነው፡፡ ****እንዲሁም የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች በክረምት ሲለምኑ የቆዩትን አጠራቅመው፤ የደብረ ታቦር ዕለት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ ለኛም እንዲገልጥልን ብለው፤ ደግሰው ለሕዝቡ ያበላሉ ፥ ያጠጣሉ፡፡ /ይህ ሥርዐት በደብራችንም የሚከናወን ድርጊት ነው፡፡/ ‹‹#ያችን_ድግስ_ውጬ_ውጬ_››፤ የተባለውና በድግስ የተመሰለው መና ሲሆን፤ በደጋሹ ቅዱስ ሚካኤል አማካይነት እስራኤል 40 ዓመታት መመገባቸውን (መና መዋጣቸውን) መናገር ነው፡፡ ‹‹#ከድንክ_አልጋ_ተገልብጬ_›› ፤ ድንክ አልጋ የምትመች እንደሆነች ሁሉ ፥ በድንክ የምትመሰለውንና የምትመቻቸውን ተስፋዪቱ ምድር ኢየሩሳሌምን መውረሳቸው መናገር ነው፡፡ ‹‹#ያቺ_ድንክ_አልጋ_አመለኛ_፥ #ያለአንድ_ሰው_አታስተኛ_››፤ መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን፤ ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት ሴትና ሕፃናት ሳይቈጠሩ፤ አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብ ናቸው ለማለት ነው፡፡ ፠፠፪ኛ ፠፠ #አጋፈረ፤ግስ ሲሆን በቤተ መንግሥት ፥ በግብዣ ቦታ፥ …. በር ላይ ቆሞ የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው አስተናበረ አስተናገደ፡፡ *አጋፋሪ፤ ቅጽል ሲሆን፤ ቃሉ የቀድሞ አማርኛ ሲሆን አስተናባሪ (ብዙውን ጊዜ በግብዣ ወይም በቤተ መንግሥት በር ላይ በመቆም ሥርዐት የሚያስከብር ማለት ነው፡፡ *አጋፋሪ፤ የድግስ አለቃ ፥ አስተናጋጅ  ነገሥታት ግብር ሲያገቡ (ግብዣ ሲጋብዙ ፥ ድግስ ሲደግሱ) ወደ አዳራሹ (ወደ ድግሱ) እንዲገቡ የሚፈቅድ ፥ የማይገባቸውንም የሚከለክል፤ ከገቡም በኋላ እንደ የክብራቸውና እንደየማዕርጋቸው አንተ በዚህ ሁን ፥ አንተ በዚህ ተቀመጥ እያለ የሚያስቀምጥ፤ ኋላ የድግሱ ምግብና መጠጥ መታደል ሲጀምርም፤ እንጀራና ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያዝና የሚቈጣጠር ትልቅ ሹም ነው፡፡ *አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር፡፡ #ቡሄ_፤ ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ  እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤  በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታን ያደርጋል፡፡ ምንጭ፤ የቃል ትምህርት /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ Facebook  https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/Finotehiwott