uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 613 підписників, посідаючи 5 374 місце в категорії Релігія і духовність та 2 203 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 613 підписників.

За останніми даними від 07 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 51, а за останні 24 години на 11, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 7.91%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 4.59% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 1 235 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 716 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 10.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 08 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 613
Підписники
+1124 години
+707 днів
+5130 днів
Архів дописів
#ምኵራብ ፤ ሦስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ምንት ሦስተኛው ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡ በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡ በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡ በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡ ፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16 ፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52 ፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1 ፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የካቲት ፳፭/፳፻
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፩ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የካቲት ፳፭/፳፻፲፬ ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ ይታወቃል።

በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ባለበት ሰዓት ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በተወረወረ አስለቃሽ ጭስ የበዓሉ ስነ ሥርዓት ሳይጠነቀቅ ታቦታተ ህጉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል። በተወረወረው አስለቃሽ ጭስም በርካታ ምዕመናን ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን በቦታው የተገኙ የተ.ሚ.ማ ሪፖርተር ገልጸውልናል። ተሚማ

#አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡ #9ኛው #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት፡፡ 9ኛ #አድዋ፥ #ሶሎዳ፡፡ ዓድዋ የሚለውን ስም የሠየሙት ከተሰዐቱ ቅዱሳን በገቢረ ተአምራታቸው ገሪማ ገረምከኒ የተባለላቸው አባ ገሪማ ሲኾኑ፤ ዓድዋ ብዙ ተራሮችን የያዘች ሃገር ስትሆን፤ ከጣሊያን ጋር የመጨረሻው ፍልሚያ የተደረገው ከዓድዋ ተራሮች በግዙፉ #ሶሎዳ_ ተራራ ላይ ነው፡፡ #የኢጣሊያና_የኢትዮጵያ_ጦርነት_መነሻ ፠ ለአድዋ ጦርነት መነሻው፤ የአውሮፓ ኃያላን ሃገር ነን ብለው ራሳቸውን የሰየሙ አፍሪካን ሊቀራመቱ በተስማሙት መሠረት ጣሊያን ከሚስዮኖቿ አንዱና ተኩላ በሆነው አባ ማስያስ ሰላይነት ያጠኗትን ኢትዮጵያን ልትቀራመት መወሰኗ፡፡ ፠ መጀመሪያ በ1861ዓ.ም. እግሯን ወደ ኢትዮጵያ በአሰብ በኩል አስገባች፤ በ17ዓመታት ቆይታ (እስከ 1878ዓ.ም.) ምጽዋን፣ የዳህላክ ደሴቶችንና የኤርትራን ቀይ ባሕር ያዘች፡፡ ምጽዋን በያዘች በ3ት ዓመታት ኤርትራን ያዘች፤ ኤርትራን በያዘች በ7 ዓመት መረብን ተሻግራ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመግባት ጦርነት ከፈተች፡፡ ራስ አሉላ አባነጋም ድባቅ መትቶ መለሳቸው፡፡ ፠ ይህ አልሆን ሲላቸው በተወካያቸው በአንቶኔሊ በሚያዝያ 25/1881ዓ.ም. በውጫሌ (ወሎ ቦሩ ሜዳ የምትገኝ) ላይ የተፈረመውን የውል ስምምንት አንቀጽ 17 በአማርኛና በጣሊያንኛ ቅጂው የተሳሰተ (የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጭ ሃገራት ጋር የሚያደርገውንግንኙነት በኢጣልያ በኩል ማድረግ ይገባዋል!!፡፡›› በሚል ሰበብ ሌሎች ጦርነቶች ተቀሰቀሱ፡፡  ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ #ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ /የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡/  ከ1878-1888ዓ.ም. #ከዓድዋ_በፊት_የነበሩ_8ቱ_አድዋዎችና_የዓድዋ_ሶሎዳ_ውጊያ፤ 1ኛ) ራስ አሉላ ነጋ (የዐፄ ዮሐንስ ጦር አበጋዝና የሐማሴን ባላባት)፤ #ዶጋሊ_ ላይ ጠላትን ድባቅ በመምታት ወደ ምጽዋ የመለሰበት፡፡ 2ኛ) ደጃች ደበብ፤ #ሰገነይቲ ላይ የተደረገ ውጊያ 3ኛ) ደጃች ባሕታ ሀጐስና ወንድማቸው አዝማች ሰንጋል፤ ከጄነራል ሳጎናይቲና ከተከታዩ ታንቲ ጋር ያደረጉት ውጊያ፡፡ ቀጥሎም ደጃች ባሕታና ዘመዳቸው ባሻይ ምስጉን የተሰዉበት #የሐላይ_መንደር_ ውጊያ፡፡ 4ኛ) ራስ መንገሻ ዮሐንስ #በኰዓቲት_ ከጥር 13-15 የተዋጉበት፤ ጦርነቱ የተራዘመና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት፤ የሟች ቊጥር በመበርከቱ አሸናፊና ተሸናፊው ሳይለይ፤ የራስ መንገሻ ጦር ወደ ሰነዓፌ የተበተነበት፡፡ 5ኛ) የራስ መንገሻ ዮሐንስ የጦር አዝማቾች (እነ ተስፋይ ህንጣሎ አጋሜ፥ ወልደ ማርያም፥ ቀኛዝማች ኃይለማርያም ወምበርታ፥ ቀኛዝማች አብርሃ፥ ደጃች ረዳ አባ ጉብራ /የራስ አርአያ ልጅ/) መሪያችንን ራስ መንገሻን አናስነካም ብለው #በደብረ_አላ_ ላይ የተዋጉት ውጊያ፡፡ 6ኛ) ልዑል ራስ መኰንን (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ጦር አዛዥና የሐረርጌ ገዥ /የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት/)፤ #አምባ_አላጌ ላይ ጣሊያንን እንደ ንብ ወረው ትልቅ ጀብድ የሠሩበትና ለአድዋውም ወኔ ቀስቃሽ ውጊያ፡፡ 7ኛ) ልዑል ራስ መኰንን፤ መቀሌ #እንዳ_ኢየሱስ (ዛሬ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ የሚገኝበት) ላይ፤ ቀድሞ በቦታው ላይ ጠላት ሸምቆ ስለበረ ዙሪያውን ከበው ስንቅ በማሳጣት መሪው ማጆር ጋሊያኖ ማሩኝ ለጄነራሌ ለባራታሪ ሂጄ ዕርቅ ይሆናል አስማማለሁ፤ ብሎ በዕርቅ ያለቀበት፡፡ (ኋላ ግን ማጆር ጋሊያኖ ቃሉን በማጠፉና ጣሊያንን ለጦርነት በማነሳሳቱ የአድዋ ጦር ሁኗል፡፡) 8ኛ) ራስ ስብሐትና ደጃች ሐጐስ ተፈሪ (ቀድሞ ባንዳ ነበሩ) ማጆር ጋሊያኖ ለጄነራሉ ከማስማማት ይልቅ ጠብን በመምከሩና የጣሊያን ጦር በእንትጮ በኩል ከኢትዮጵያ ጋራ ሊዋጋ ሲገሰግስ የአካለ ጉዛይን ባላሃገር በማስተባበር #እንትጮ ላይ ደጀን ሁነው መክተው የተዋጉት ውጊያ፡፡ --- /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/finotehiwotee

ዜና ዕረፍት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም
ዜና ዕረፍት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

#ቅድስት፤ #ኹለተኛው_የዐቢይ_ጾም_ሳምንት ኹለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ #share ፠ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡ ፠ ‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡ ፠ ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡ ፠በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_ክብር፤ 1. በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8 2. በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡ 3. ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡ ‹‹ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና›› ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/finotehiwotee http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

#መልካም_ዜና በወቅታዊ ጉዳይ ለቤተ ክርስቲያነችን ድምፅ በመኾን ታስሮ የነበርው የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ አበበ ሞቅያለው ከእሥር ተፈትቷል ፡፡
#መልካም_ዜና በወቅታዊ ጉዳይ ለቤተ ክርስቲያነችን ድምፅ በመኾን ታስሮ የነበርው የሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋይ አበበ ሞቅያለው ከእሥር ተፈትቷል ፡፡