uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 16 123 підписників, посідаючи 5 232 місце в категорії Релігія і духовність та 2 221 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 16 123 підписників.

За останніми даними від 01 листопада, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 598, а за останні 24 години на 74, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 23.12%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.46% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 729 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 686 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 29.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 02 листопада, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

16 123
Підписники
+7424 години
+847 днів
+59830 днів
Архів дописів
4ኛ) ክብረ በዓል፤ ፨፨በቦታ ርቀት ላልተገኛችሁ፤ የጥቅምት 27 ክብረ በዓልን በአጭሩበፎቶ እናስቃኛችሁ፡፡ ** በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በሰሜን አሜሪካ የሚኒሶታ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፥ ከብዙ ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ ከልጅነት እስከ እውቀት በዲቁናና በቅድስና ባገለገሉበት ደብራችን ኪዳንና ቅዳሴው መርተዋል፥ ትምህርት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፨ ፨፨፨ በነገራችን ላይ ደብራችን ፬ት ሊቃነ ጳጳሳትን አፍርታለች። እነርሱም፤ ፩ኛ. ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፤ የትግራይ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፪ኛ. ብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት፤ የወሊሶ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፫ኛ. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፤ የቀድሞው በመኪና አደጋ አምላክ የጠራቸው ፬ኛ. ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፤ የሚኒሶታ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፠፠ በክብረ በዓሉ ላይም የቤተ ክህነት ኃላፊዎች፥ የ4 አድባራት አስተዳዳሪዎችና የ3 አድባራት ጸሓፊዎች፥ የደብራችን የቀድሞ አገልጋዮች፥ በርካታ የአ.አ. አድባራት ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት ዕፁብ ድንቅ በኾነ ኹኔታ ተከብሯል፨

3ኛ) ዑደትና ወረብ፤ በቦታ ርቀት ላልተገኛችሁ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት (ቅኝት) በፎቶ እናስቃኛችሁ፡፡ማኅሌቱንም በዚሁ በታላቁ ደብር ከቀድሞዎቹ ዐበይት መምህራን (ከመምህር ገብረ ማርያም የላይ ቤት አቋቋምንና ከመምህር መንግሥቱ ቅኔን አብረው የተማሩትና በውጣትነት ጓደኞች በኾኑት በመሪነት 2ቱ ሊቃነ ጠበብት፤ 1ኛ. ሊቀ ጠበብት ዘሚካኤል አየነው፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሊቀ ጠበብት 2ኛ. ሊቀ ጠበብት ኀይለ መሰቀል፤ የእንጦጦ ማርያም ሊቀ ጠበብት መርተውታል፡፡ ሃሌ ሉያ በአማን በአማን ቃልከ አዳም፤ በእንተ ኀጥኣን ዘተሰቀልከ መድኀኔዓለም፡፡ (ስለ ኀጥአን ብለህ የተሰቀልክ መድኀኔ ዓለም፤ እውነት በእውነት ለአዳም የገባህለትን ቃል ኪዳንን እውን አደረግህ ፡፡)

2ኛ) ወረብ፤ በቦታ ርቀት ላልተገኛችሁ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት (ቅኝት) በፎቶ እናስቃኛችሁ፡፡ (በነገራችን ላይ በአ.አ አድባራት ያሉ ዐበይት መምህራን ከየደብሮቻቸው የተሰባሰቡበት ማኅሌት ነበር፡፡) ማኅሌቱንም በዚሁ በታላቁ ደብር ከቀድሞዎቹ ዐበይት መምህራን (ከመምህር ገብረ ማርያም የላይ ቤት አቋቋምንና ከመምህር መንግሥቱ ቅኔን አብረው የተማሩትና በውጣትነት ጓደኞች በኾኑት በመሪነት 2ቱ ሊቃነ ጠበብት፤ 1ኛ. ሊቀ ጠበብት ዘሚካኤል አየነው፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሊቀ ጠበብት 2ኛ. ሊቀ ጠበብት ኀይለ መሰቀል፤ የእንጦጦ ማርያም ሊቀ ጠበብት መርተውታል፡፡ ሃሌ ሉያ በአማን በአማን ቃልከ አዳም፤ በእንተ ኀጥኣን ዘተሰቀልከ መድኀኔዓለም፡፡ (ስለ ኀጥአን ብለህ የተሰቀልክ መድኀኔ ዓለም፤ እውነት በእውነት ለአዳም የገባህለትን ቃል ኪዳንን እውን አደረግህ ፡፡)

1ኛ) የወረብ ቅኝት፤ በቦታ ርቀት ላልተገኛችሁ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት (ቅኝት) በፎቶ እናስቃኛችሁ፡፡ (በነገራችን ላይ በአ.አ አድባራት ያሉ ዐበይት መምህራን ከየደብሮቻቸው የተሰባሰቡበት ማኅሌት ነበር፡፡) ማኅሌቱንም በዚሁ በታላቁ ደብር ከቀድሞዎቹ ዐበይት መምህራን (ከመምህር ገብረ ማርያም የላይ ቤት አቋቋምንና ከመምህር መንግሥቱ ቅኔን አብረው የተማሩትና በውጣትነት ጓደኞች በኾኑት በመሪነት 2ቱ ሊቃነ ጠበብት፤ 1ኛ. ሊቀ ጠበብት ዘሚካኤል አየነው፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም ሊቀ ጠበብት 2ኛ. ሊቀ ጠበብት ኀይለ መሰቀል፤ የእንጦጦ ማርያም ሊቀ ጠበብት መርተውታል፡፡ ሃሌ ሉያ በአማን በአማን ቃልከ አዳም፤ በእንተ ኀጥኣን ዘተሰቀልከ መድኀኔዓለም፡፡ (ስለ ኀጥአን ብለህ የተሰቀልክ መድኀኔ ዓለም፤ እውነት በእውነት ለአዳም የገባህለትን ቃል ኪዳንን እውን አደረግህ ፡፡)

እርማት፤ ነግሡ ከነዚቁ፤ በቀጨኔ የሚለውንና በመ.መ.መ. ከሚለው ጋር ማቀያየር፨ የነግሡ ዚቅን ብለህ የሚከተለውን ወረብ ወርብ፨ ወረብ ፩፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤፪) ተንሥዒ ወንዒ ቅርብተ ዚኣየ ዘበእንቲአኪ ተረግዘ ገቦየ።(፪)

እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✤፨✤ አቡነ መብዓ ጽዮን አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት 27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የፃድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ! አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡ በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡ መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡ በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ #ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡ የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡ ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣ ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡ ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡ የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣ በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣ ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤ እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡ ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡ በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ$ በማለት የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡ ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት 27 ነው፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ የጻድቁ የአባታችን የአቡነ መብዓ ጽዮን በረከት ከእኛ ጋር ትሁን!!! የመስቀሉ ፍቅር በልባችን ይኑር አሜን!!!

፨፨ ሌሎች በሃገራችን የሚገኙ የመድኀኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት፤ (ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ✤መቅደላ መድኀኔዓለም ✤ባሕር ዳር ድባንቄ መድኄኔዓለም ✤አዴት መድኃኔዓለም ✤አዲስ አምባ መድኃኔዓለም ከ1600 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ሙሴ የተፈለፈለ የዋሻ ገዳም ✤በቅሎ አግት / ዝንጀሮ አስጨብጭብ/ ጨጨሆ መድኃኔዓለም ገዳም ✤ወንጪት መድኃኔዓለም በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግስት ተመስርቶ እስካሁን ድረስ ነብር በቤተ መቅደሱ እየኖረ በሚጠብቀው በታላቁ ወይን እንጨት ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ውስጥ የተሰራ ✤መቀሌ መድኃኔዓለም ✤አድግራት መድኃኔዓለም ወቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ብዙ ድንቅ ታሪክ ያለው ✤ደባርቅ መድኃኔዓለም ✤የሽረት መድኃኔዓለም እጅግ ተደንቀውና ተደምመው ምስጋናዎ ኢምንት ሆናብዎት የሚመለሱበት ✤ኮሶ በር መድኃኔዓለም ✤ሐረር መድኃኔዓለም ✤ምስካበ ቅዱሳን ጻድቃኔ ዋሻ መድኃኔዓለም ገዳም ✤እመኪና መድኃኔዓለም ገዳም በመናኔው ጻድቅ ንጉሥ በአጼ ካሌብ ልጅ በጻድቁ ንጉሥ በአጼ ገብረ መስቀል በ6ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረተ ታሪካዊ ገዳም ✤በሬ አገር መድኃኔዓለም ገዳም 1000 ሜትር ፍልፍል ዋሻ ገዳም ✤ተከዜ መድኃኔዓለም ገዳም በ11ኛው መ.ክ.ዘ. የላስታ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም /ታላቁ ሐርቤይ/ ደቀመዝሙር እንደነ ነቢዩ ኤልያስና ወንጌላዊው ቅ.ዮሐንስም ሞትን ሳያይ እስከ ምጽዓተ ሐሳዊ መሲህ /ዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ዋዜማ/ ድረስ የተሰወረው ጻድቁ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ከሰማይ ተቀብሎ የመሰረተው ንዑድ ክቡር የሆነ መካነ ጸሎት ወአርምሞ ወትኅርምት ✤ሬማ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፦ በ1414 በአባ ኖብ የተመሰረተና የብዙ ቅዱሳን መካነ ጸሎት የነበረ በዘመነ ሱስንዮስ ሰማእትነትን የተቀበለቺው ጻድቅት ወሰማእት ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አጽሟ ያለበትና የከበረና የማይሻር ቃልኪዳኑን ከአምላከ ቅዱሳን የተቀበለችበት እፁብ ድንቅ ሥፍራ ሲሆን የሰማእቷን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን አጽማቸው የሚገኝበት ጥንታዊ ገዳም ✤ደብረ ታቦር መድኃኔ ዓለም ✤ናዝሬት መድኃኔዓለም

በኢትዮጵያና በአሜሪካ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 7፤ 1. ✤ላፍቶ ሌንቃ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ 2. ✤መድኃኔዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ 3. ✤የቲሊሊ ደብረ ገነት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን 4. ✤ሚዛን ተፈሪ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን 5. ✤ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም 6. ✤ኒውዮርክ መድኀኔ ዓለም

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 6፤ 7. ✤ደጀን አበ ብዙኃን አብርሃም ወመድኃኔዓለም፤ ደጀን ጎጃም 8. ✤አርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ አርባ ምንጭ ከተማ 9. ✤ቦራራ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን 10. ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ወቅዱስ ላሊበላ ቤ.ክ፤ ጎንደር 11. ✤ጌቴ ሴማኔ ፈረስ ቤት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ደብረ ማርቆስ 12. ✤ወልዲያ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 5፤ 1. ✤ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም 2. ✤አርብዓሐራ ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም(ምስካበ ቅዱሳን መድኀኔዓለም ገዳም)፦ ደመ ክርስቶስን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል የተቀበለበትን የብርሃን ጽዋ የሚያጥኑና ሌሎችንም ቅዱሳንን አጽም በንሥር አሞራ የተመሰለ የጌታ መልአክ በቀስተ ደመና ተከብቦ በቀን የሚያመጣበት እልፍ ታሪክና ብዙ የብዙም ብዙ ገቢረ ተአምራት የሚፈጸሙበት ለተፈቀደላቸውና እንደሚገባ ሆነው በቦታው ላይ በበጎ ኅሊና ለሚጸልዩ ምዕመናን ሥውራኑ እየተገለጡ ጥያቄያቸውን የሚመልሱበት ግርማ ያለው ክቡር ንዑድ የ40ዎቹ ቅዱሳን ሰማእታት መካነ ጸሎት የአቡነ ሐራ ግብፃዊ የቃልኪዳን ሥፍራ 3. ✤ጨጨሆ መድኀኔዓለም፤ ወሎና ጎንደር ድንበር ላይ 4. ✤በደሌ ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፤ ከ100 ዓመት በላይን ያስቈጠረ ጥንታዊ ቤ.ክ. 5. ✤ደሴ መድኃኔዓለም 6. ✤ወዘም ባሕታዊ መድኃኔዓለም፣ ፍቼ አጠገብ ሰሜን ሸዋ

፨፨ በአዲስ አበባ የመድኀኔ ዓለም ክብረ በዓል ያለባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንጠቁማችሁ፤ (ስብስብ 4) (ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ ✤ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምወደ.ት. ቅ. ገብርኤል ቤ.ክ ✤ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔዓለም፤ (ታቦተ ሕጉ ባይወጣም በሰዐታትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡)፤ 6 ኪሎ ✤አቃቂ ጋራው መድኀኔዓለም፤ ✤ረጲ መካነ ጎልጎታ መድኀኔዓለም፤ረጲ ✤መንበረ ሕይወት መድኀኔዓለም፤ አቃቂ ክ/ከተማ ✤ደብረ ቅዱስ ደብረ ቀራሜሎስ ካራአሎ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ፤ የካ ክ/ከተማ ✤መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም፤ የካ ክ/ከተማ ✤ቦሌ ቡልቡላ ደብረ ገነት መድኀኔ ዓለም፤ቦሌ ቡልቡላ ✤ድልበር መድኀኔዓለም፤ ጉለሌ (ቶታል) ✤ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ.ክ ልደታ ሜክሲኮ ✤ደብረ ሳሌም ቦሌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን (የመድኀኔዓም ታቦት በድርብነት ይገኛል)፤ ቦሌ ✤ምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔዓም ቤተክርስቲያን፤ቀበና ✤አያት መድኃኔዓለም፤ አያት ✤ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔዓለም፤ደቡባዊ አ.አ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል ፡፡ ጎተራ ✤የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ወኢሉጣ ቤ.ክ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፤ ለገሃር ✤ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ፤ የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብት ይገኛል፡፡ ✤ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም ቤ.ክ (የመድኀኔዓለምና የመብዓ ጽዮን ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ ኮተቤ(ሲምሲ) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብነት ይገኛል)