uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 366 підписників, посідаючи 5 620 місце в категорії Релігія і духовність та 2 191 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 366 підписників.

За останніми даними від 22 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -33, а за останні 24 години на -2, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 22.71%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 7.98% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 489 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 226 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 22.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 23 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 366
Підписники
-224 години
+317 днів
-3330 день
Архів дописів
ግንቦት 12፤ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም ። ብድጋሚም ግንቦት 12 ፤ የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ፦። የሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን መታሰቢያ ነው ። ።። ✤ ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራ ሰይጣንን ልታስታርቅ በሄደች ጊዜ ከሲኦል ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳት ብዙ እልፍ ነፍሳትን ያወጣችበት ዕለት ነው።ራሷ ባነጸችው በጣና ገዳሟ ይከበራል። -------- ፠ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ፤ በፍልሰቴ ቀን በገዳሜ ይገኝ እኔም ልጄ እለዋለው ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጄ ፊልጶስ ጋር እባርከዋለው።›› /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/ ፠ አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠ ግንቦት 12 በደብረ ሊባኖስ ትልቁ በዓል ነው፡፡ ጥንተ መሠረቱም፤ 12ቱ እጨጌዎች ከያሉበት ቦታ እየመጡ 1ድ 1ድ ወር ሙሉ በፈረቃ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቅዱስ አጽም ተራ ገብተው ያጥኑ ነበር፡፡ ግንቦት 12 ግን ሁሉም ከያሉበት ተሰባስበው በአንድነት ያከብራሉ፡፡ #የጻድቁ_ዋና_ዋና_የታሪክ_ሂደቶች፤ ፠ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በእቲሣ ተወለዱ፡፡ ፠በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡ ፠በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡ ፠እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብ ዘንድ እየተማሩ ፠በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከቄርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡ ፠በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ቄርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡ ፠በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡ ፠በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ ፠በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ ፠በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡ ፠በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡ ፠፠፠አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡ #የጻድቁ_ክብረ_በዓላቶቻቸውም፤ #ኅዳር 24፤ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት #ታኅሣሥ 24፤ የአባታችን ልደት #ጥር 24፤ የአባታችን ስባረ አጽም #መጋቢት 24፤ የአባታችን ጽንሠት #ግንቦት 12፤ የአባታችን ፍልሰተ አጽም #ነሐሴ 24፤ የአባታችን በዓለ እረፍት ናቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ .....share ፠ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአጽሙ፡፡ Facebook  https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

#በአዲስ_አበባ_የሚከብርበት_ #፩_ብቸኛው_ደብር፡፡ ፩ኛ).  #አዲስ_አበባ_ደብረ_ይባቤ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ (ወ/ሮ ደስታ ሞላ በሚባሉ እናት በ1948 የተሠራ፤ ፈዋሽ ጠበልም አለው፡፡) አድራሻው፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፥ መስቀል ፍላወር (ጎተራ /አጎና ሲኒማ/፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (ቦሌ/መገናኛ) → ሳሪስ በሚለው ታክሲ መስቀል ፍላወር ጋራ፤ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፲፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩ኛ).   #ደብረ_ሐዊ_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ (እመቤታችን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት፤ ጃንደረባው ባኮስ የተሠወረበት፤ ቅዱስ ያሬድ ለ22 ዓመታት የመነነበት፥ ያስተማረበትና የተሠወረበት፤ በሀገራችን ትልቁ የሱባዔ መግቢያ ቅዱስ መካን፤ በዓለም ላይ በሃገራችን ብቻ፤ ከሀገራችንም በአብዛኛው በሰሜን ተራሮች ላይ ብርቅዬ ኾነው የሚገኙት ዋልያና ጭላዳ በአብዛኛው የሚገኙበት ቦታም ነው፡፡ በዚህ ቦታ ቅዱስ ያሬድ ያስተማረበትና የተማሪዎቹ ወንበር ጕባኤ ቦታና የደንጊያ ወንበር፤ ጽዮንን ከሩቅ እያየ ያለቀሰበት ቦታ ላይ የፈለቀ ጠበልና በዘንጉ ያፈለቀው ፈዋሽ ጠበል፤ የተሠወረበት የዋሻ ቤተ ክርስቲያን፣ እንዲሁም አበውና እማት የሚኖሩበት ገዳም ይገኛል፡፡) አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጸለምት፥ በየዳ ወረዳ፤ ራስ ደጀን ተራራ አጠገብ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → በየዳ (ባኂት/ አርቋዝዬ/ጭሮ ለባ/) →  በእግር፡፡ ፪ኛ). #በየዳ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ፤ (በደብረ ሐዊ ተራራ በስተጀርባ የሚገኝ ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ በደብረ ሐዊ በምናኔ እንደመኖሩ መጠን በተራራው ጀርባ በገጠሩ መንደር የሚገኙ ምዕመናን እኛም ቅዱስ ያሬድን ልንዘክረው ይገባል፤ የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ደብረ ሐዊ ላይ ብቻ ሳይኾን በኹሉም ቦታ መኖር ይገበዋል በሚል መንፈሳዊ ቅንዓት ተነሣሥተው የሠሩት ነው፡፡) አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጸለምት፥ በየዳ ወረዳ፤ ራስ ደጀን ተራራ አጠገብ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → በየዳ (ባኂት/ አርቋዝዬ/ጭሮ ለባ/) →  በእግር፡፡ ፫ኛ). #ጣና_ቂርቆስና_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ (ከፎገራ ከመንገዱ የ3 ሰዓት መንገድ እንደተጓዙ፤ በመርከብ ደግሞ ከባሕር ዳር፣ ከጎርጎራ፣ ከደልጊ፣ ከቁንዝላ ተሣፍረው ከጣና ክርስቶስ ሠምራ አጠገብ የሚያገኙት ታላቅ ገዳም ነው፤ መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት የነበረ፤ ታቦተ ጽዮን ለበርካታ ዓመታት ያረፈችበት፤ ቅዱስ ያሬድ ምልክት ያለውን ድጓ የጻፈበት ቦታ ነው) አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጸለምት፥ ፎገራ፤ ጣና ዳር፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ፎገራ፡፡ ወይም ከባሕር ዳር /በመርከብ/ ጣና ቂርቆስ፡፡ ፬ኛ). #ወገራ_ደልደሊት_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ፤ (በሰሜን ጎንደር ወገራ አውራጃ አምባ ጊዮርጊስ ወረዳ የሚገኝ ሲኾን፤ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ከብቶች ሁሉ ተመስጠው ሳያርሱ በመቆማቸው ምክንያት ቅዱስ ያሬድ የተገረፈበት ቦታ ነው) አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ወገራ፥ አምባ ጊዮርጊስ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → አምባ ጊዮርጊስ፡፡ ፭ኛ). #ደረስጌ_ወረዳ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ስሜን፥ መካነ ሰላም /ደረስጌ/፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → መካነ ሰላም፡፡ ፮ኛ). #አኵሱም_ደብረ_ዝማሬ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ፤ (ከአኵሱም ዩኒቨርሲቲ አጠገብ የሚገኝ ሲኾን፤ የአኵሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዴት ቅዱስ ያሬድ ተወልዶ ባደገባት፥ ተምሮ ባስተማረባት፤ ሰማያዊ ምሥጢራትና በተገለጡለት፤ የተሰዓቱ ቅዱሳንን የበርካታ ቅዱሳን መናኸሪያ በኾነችው፤ የገዳማትና የአድባራት ራስ፤ የምዕመናን ሁሉ አምባ መጠጊያ በኾነችው ከተማ እንዴት መታሰቢያ ቤተ ከርስቲያን ሳይሠራለት እስካሁን ቀረ ብለው በመንፈሳዊ መነሣሣት በአጭር ጊዜ ውስጥ በዕሥራ ምዕት ማግሥት ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ነው) አድራሻው፤ ማዕከላዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ አኵስም ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → አኵስም፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → በአዲዓርቃይ (በዳንሻ ሁመራ) → ሽረ → አኵሰም፡፡ ፯ኛ). #አኵሱም_ማይኪራህ_ደብረ_መድኀኒት_ወፈለገ_ጥበብ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ፤ (ከአኵሱም ከተማ በ4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በቅዱስ ያሬድ የትውልድ ቦታ አጠገብ በዋናው መንገድ ዳር የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ ቅዱስ ያሬድ ከትሏ መውደቅና መነሳት በመመልከት ማስተዋልን የተማረባት ቦታ ስትሆን ሾላዋ እስካሁንም ድረስ እየተካች ትገኛለች፤ ከሾላው ሥር የሚፈልቅ ፈዋሽ ጠበልም አለ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው የአኵሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደብረ ዝማሬን ቤተ ክርስቲያን ሲሰሩ የሃገሬው ሰው ተመልክቶ እንዴት የትውልድ ቦታው ላይ እኛ ቤተ ክርስቲያን ሳንሠራ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቀድመውን ሠሩ በሚል መንፈሳዊ ቅንዓት ተነሣሥጠው በተፋጠነ ሁኔታ ያነጹት ነው፡፡) አድራሻው፤ ማዕከላዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ አኵስም ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → አኵስም፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → በአዲዓርቃይ (በዳንሻ ሁመራ) → ሽረ → አኵሰም፡፡ ፰ኛ). #ጎንደር_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሩፋኤል_ወአቡነ_ሐራ_ድንግል_ቤ/ክ፤ (ይህ ቤተ ክርስቲያን በጎንደር ከተማ የሚገኝ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ ሲኾን፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ቅዱስ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አራዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡ ፱ኛ). #ጎንደር_ጎሐ_ተራራ_ቅዱስ_ያሬድ_ገዳም፤ አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አራዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡ ፲ኛ). #ባሕር_ዳር_ፈለገ_ጥበብ_ቅዱስ_ማርቆስና_ቅዱስ_ያሬድ ቤ/ክ፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይባብ ካምፓስ አጠገብ የሚገኝ፡፡ አድራሻው፤ ምዕራብ ጎጃም (ባሕር ዳር) ሀገረ ስብከት፥ ባሕር ዳር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር፡፡ ፲፩ኛ). #ዳንግላ_ደብረ_ሣህል_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ፤ (በአዊ ሃገረ ስብከት የሚገኝ ሲሆን በዚህ ደብር ታቦተ ቅዱስ ያሬድ ከ8/10/2008 ዓ.ም. ጀምሮ በድርብነት ይከበራል)፡፡ አድራሻው፤ አዊ ሀገረ ስብከት፥ ምዕራብ ጎጃም፥ ዳንግላ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በባሕር ዳር መስመር /ዳንግላ/፡፡ ፲፪ኛ). #ሐይቅ_ደብረ_ኅሪት_ቅሌንሳ_ማርያም_፤ (ከሐይቅ እስጢፋኖስ ባሻገር የምትገኝና፤ የቅዱስ ላሊበላ አያት መሶበ ወርቅ ያነጸቻት ጥንታዊ ደብር)፡፡ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ሐይቅ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ሐይቅ፡፡ ፲፫ኛ). #ደብረ_ብርሃን_አንሳስ_ማርያም_ቤ/ክ፤ (በደብረ ብርሃን ከተማ የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ስትኾን ፈዋሽ ጠበል ያለባትና፤ የአቋቋሙ ሊቅ፣ የቅዳሴና የሌሎች ዜማ ትምህርቶች መምህር የኾኑት የመምህር አባ ናሁ ሠናይ /መምህር ለምኔ/ ማስተማሪያ ደብር ነች፤ በዚህ ቦታ ታቦተ ቅዱስ ያሬድ ያሬድ በድርብነት ይከበራል) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን ከተማ፤

#ማሕሌቱን_ለማሕሌት_አባት_እናቅርብለት:: ግንቦት 11 በዓለ ሥዋሬው ለቅዱስ ያሬድ በዚህችም ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሰወረበት ቀን ነው። የቅዱስ ያሬድ መጠሪያ ስሞች ሥርዐተ ማኅሌት ዘግንቦት ፲፩ ፠የቅዱስ ያሬድ ልደትና የስሙ ትርጓሜ ፠የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች፤ ፠የቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ነገሮች ፠የቅዱስ ያሬድ የዜማው ይዘት ፤  የዜማው ጠባያት ፤ ከሌሎች ዓለማዊ ዜማዎች የሚለይበት ጠባይና የዜማው ጥቅም ፠፠፠የቅዱስ ያሬድ ሌሎች መጠሪያ ስሞች ፠፠፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ካህን (ካህነ ስብሐት) ፠ ማኅሌታይ፤ ፠ መዘምር ዘበድርሳን፤ ፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት) ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ ልዑለ ስብከት፤ ፠ ሰማዕት፤ ፠ ባሕታዊ፤ ፠ መናኝ ፠ የዜማ አባት፤ ፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ:: ፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ ፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ:: ፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ:: ፠ አእምሮው የመጠቀ፤ ፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤ ፠  እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ ማን እንደርሱ:: …... #ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_፲፩ /ማኅሌቱን በአ.አ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ የምትቆሙ በደብረ ይባቤ የሚለውንና በሰማየዊ ቀለም የተቀባውን እየመረጣችሁ መጠቀም ስትችሉ፤ በሌሎች አድባራት ግን ሰማያዊ ቀለም የሌለበትን (በቢጫና እንዲሁ ያለቀለም የተቀመጠውን) እየመረጣችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡/ #የቅዱስ_ያሬድ_ልደትና_የስሙ_ትርጓሜ ꔰ  ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ፤ እንዲሁም አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ /መምህሩ/ ነው ይላሉ፡፡) ꔰ  የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡ አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡ * አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤ አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡ *** አፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በአፄ ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡ #የቅዱስ_ያሬድ_ድርሰቶች፤ ** ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ፤ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ፤ በከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ፡፡ #፩ኛ) ምዕራፍ (ውዳሴ ማርያም በዜማን፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠለስት፣ ክስተተ አርያምን) ያጠቃልላል፡፡ ፠ የውዳሴ ማርያም ዜማ ቅዱስ ኤፍሬም ሦርያዊ የደረሰውን ለቅዱስ ያሬድ እየነገረው ልብን የሚመስጥ ዜማ ደርሶለታል፡፡ ፠ መስተጋብዕ፤ ስብስብ ማለት ሲኾን፡፡ ከዳዊት መዝሙር (ከ180ው የመስተጋብእ ድርሰት 1ድ ድርሰት በስተቀር) ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የኾነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የኾነው የተቀመረ ነው፡፡ መስተጋብዕ ሲጀምር ‹‹ወለቡ ጽራኅየ (ጩኸቴን ልብ አድርግ›› ብሎ ነው፡፡ በዐቢይ ጾም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ጠዋት ጠዋት ይዘመራል፤ የቀድሞ መምህራን በፍልሠታም ይዘምሩት ነበር፤ ዜማው በዋነኛነት በግዕዝና በዕዝል ሲኾን በአራራይ ከሐሙስ ‹‹አንተሰ እግዚኦ ለዓለም›› የሚለውና ከቅማዴ ‹‹መንግሠትከሰ መንግሥት›› የሚለው ይገኙበታል፡፡ በየእለቱ እንዲደርስ (ከእሑድ በስተቀር) አድርጎ የደረሰው ነው፤ ፠ አርባዕት፤ አራት አራተኛ ማለት ሲን በዳዊት መዝሙር በአራተኛው መሥመር ውስጥ እየገባ የሚዘመር ነው፤ ‹‹ቃልየ አጽምእ እግዚኦ ወለቡ ጽራኅየ፤ ወአጽምአኒ ቃለ ስእለትየ፤ ንጉሥየኒ ወአምላኪየኒ፡፡ ከፈጸመ በኋላ አርባዕት ይገባል፡፡ አርባዕት ሲጀመር ‹‹ቃልየ፤ ከመ ያፈቅርለ ጐሥዓ፤ ዐቢይ፤ ተሣሃለኒ›› ብሎ ነው (በዳዊት መዝሙር ጀምሮ ቀጥሎ በቅዱስ ያሬድ ድርሠት በኾነው በአርባዕት ያጠናቅቃል፡፡አብዛኛው በግጥም መልክ የተቀመረ ሲኾን አልፎ አልፎም በስድ ንባብ መልክ ይገኛል፡፡ ግእዝ ዕዝልና አራራይ ዜማ አለው፡፡ ፠ አርያም፤ አርያም ልዑል፥ ከፍተኛ ማለት ሲኾን፤ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ሰምቶ ‹‹ቀዳሚ ዜማ፤ አንድም ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ›› ስላመጣው ነው፡፡ ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብሎ የግጥም መል ባለው አእያም በተባለው ይጀምራል፡፡ በግጥም መልክና በስድ ንባብ ሲገኝ የግጠም አገጣጠሙ ከፍ ያለ የግጥም አገጣጠምን የተከተለነው፡፡ የሚባልበት ጊዜ በጾም ጊዜ በጾመ ድጓው እየገባ፣ በተለይ ደግሞ በክብረ በዓል ክሥተተ አርያም ሲደርስ ይዘመራል፡፡  ሠለስት፤ ስምዐኒ ብሎ የሚጀምር ባለ ብዙ ሃሌታ ያለው፤ በዳዊት መዝሙር በሦስተኛው መሥመር እየገባ የሚዘመር፤ አንድም 3 መዝሙሮች ብቻ የሚዘመሩለት ብዙውን ጊዜ በግጥም የሚቀርብ ሲኾን፤ ይኽ ዜማ የሚደርሰው በክብረ በዓላት ዋይዜማ፤ በስብሐተ ነግህ፣ በአርያም፣ በጾመ ድጓ ውሎ፣ በአርያም፣ በሰንበት፣ በፍትሐት ጊዜ ነው፡፡ ክስተተ አርያም፤ የሰማይ መከፈት ማለት ሲኾን በታላላቅ በዓል ቀን እንዲሁም ታላላቅ? ሰዎች ሲሞቱ የሚዘመር ነው፤ ክስተትን ቅዱስ ያሬድ ያዘጋጀው ከዳዊት መዝሙራት፥ ከጸሎተ ነቢያትና ከራሱም ጭምር ኀይለ ቃል ያላቸውን ባለሁለት መስመሮች ሐረግ በመውሰድ ሲኾን ዜማው እጅጉን ነፍስና ሥጋን፥ ልብንና ኅሊናን የሚመስጥ ነው፡፡ ፪ኛ) ጾመ_ድጓ፤ በዐቢይ ጾም የሚባል ነው፡፡ ፫ኛ) ድጓ፤ በ4ት ክፍላተ ዘመናት የተቀመረና ጾመ ድጓን በውስጡ የሚያካትት ነው፡፡ ፬ኛ) ዝማሬ፤ ቅዱስ ቊርባን ድርገት ሲወርድ ለቅዱስ ቊርባን ክብር የሚዘመር ነው፡፡ ፭ኛ) መዋሥዕት፤ ሰው ሥጋው ከነፍ ስትለይ ፍትሐት የሚደረግበት ጸሎት ነው፡፡ ፮ኛ) የ፲፬ቱ ቅዳሴያት ዜማ፤ 14ቱን ቅዳሴያት 14ት አባቶች የደረሷቸው ቢሆንም ዜማ የደረሰላቸው ግን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ፯ኛ) አንቀጸ ብርሃንን፤ ድርሰቱ ነው፡፡ /ይቀጥላል……/ በተጨማሪም ደግሞ፤ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ዐይነቶች ግእዝ፣ ዕዝልና ዓራራይ በመባል ይታወቃል፡፡እነዚህ የዜማ ዐይነቶች የአንዱ ድምፅ ከሌላኛው ድምፅ ያልተደባለቀ፣ ወጥ የሆነ ድምፅ አላቸው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ትርጉም ያላቸው በሆኑ የዜማ ምልክቶች (ድፋት፤ ሂደት፤ ቅናት፤ ይዘት፤ ቁርጥ፤ ጭረት፤ ርክርክና ደረት) ደርሷል፡፡ የቅኔ ጀማሪም ነው፡፡ ‹‹ሕንፄሃ …›› የሚለውን ቤት መምቻ ያለውን ቅኔ ልብ ይሏል፤ አንድ ባለቅኔ ግን ይህን ሳይረዳ ‹‹ተትሕተ ያሬድ …›› የሚል ቅኔን ተቀኝቷል፡፡

ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ ማርያም ሥመሪ ወጸሐቂ እንበለ ንትጋ ፤ ለማየ ንጽሕኪ ትረስዩኒ ፈለጋ፤ እስመ ንጽሕ   ይሁብ ምገሰ ወጸጋ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤      የተዘጋጀ ::   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

ꔰ ꔰꔰእንኳን ለእመቤታችን 2029ኛ ዓመት በዓለ ልደት አደረሳችሁꔰ ꔰꔰ ꔰ  #ልደታ_ለማርያም  ꔰ ꔰ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል? ꔰ ሰላም ለልደትኪ እማኀፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ ፠ #የግንቦት_ልደታ_ለማርያም_ክብረ_በዓልና_የእመቤታችን_በዓላት በቀደመዉ ዘመን በዘመነ ብሉይ ‹‹የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል›› ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ. 10፥22/ በሐዲስ ኪዳን እውነተኛ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስ ለሆነችዉ እመቤታችን በስሟ በዓል ሊደረግላት ይገባል፤ ‹‹የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል›› እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ. 111፥7በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 33ት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደዉ በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመዉ እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ፠ #ልደቷ_መጽሐፍ_ቅዱስ_ላይ_ከሌለ_ተቀባይነት_እንዴት_ይኖረዋል?       በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸዉ ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረዉ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ‹‹የንጉሡም የዳዊት የፊተኛዉና የኋለኛዉ ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል›› ይላል፡፡ 1ኛ ዜና 29፥29 ፠ #የእመቤታችን_የልደቷ_ታሪክ የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛዉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ‹‹ሐና››ና ኢያቄም/ዮአኪን በሚለዉ ስም የሚጠሩ ሲሆን ሐና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረዉን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሐና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ እርግብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡ ስለ ሐና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደዉ መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸዉ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከዉና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረዉ ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ፠ #እመቤታችን_የት_ተወለደች? እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሐሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላዉ ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸዉ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸዉ የተለመደ ክስተት ነዉ፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሐሳቦች የሚያነሱ ሲሆን፤ አንደኛዉ ‹‹ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች›› የሚል ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ሐሳብ ደግሞ ‹‹ከሦስተኛዉ ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀዉ ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሐና የክሩሲድ ቤ/ክ በታች ነዉ የተወለደችዉ የሚል ነዉ፡፡ የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ በናዝሬት ነዉ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸዉ ተጠብቀዉ የቆዩ ከመሆናቸዉ አንጻር ተአማኒነታቸዉ የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትዉልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለዉ ተራራማ ሀገር ነዉ፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፊንቄ በስተምስራቅ ይገኛል፡፡ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ›› መኃ. 4፥7 የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምሥጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸዉ የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃዉንት ያስረዳሉ፡፡ ፠ #የልደታ_ለማርያም_በዓል_መቸ_ነዉ? እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነዉ፡፡ በ6ኛዉ ና7ኛዉ መቶ/ክ/ዘመን ነዉ የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደዉና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነዉ ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸዉን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸዉ የሚከበረዉም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅ/ ዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅ/ድንግል ማርያም ልደት ነዉ፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባዉና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነዉ፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬ.ክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀዉልት በማቆም ዐስር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡ #የድንግል_ማርያም_ልደት_ለምን_ይከበራል? * ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅ/ገብርኤል አንደበት‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› በማለት ተነግሯል (ሉቃ 1-14)፤ ምክንያቱም ቅ/ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ፥ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነዉ፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ፤ የድንግል ማርያም ልደትማ ምንኛ የሚያስደስት ይሆን!?፡፡ስለሆነም ከጌታ ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነዉ፡፡ * የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነዉ፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››ብሏል * እመቤታችን  ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፤ በቅድመ አያቶቿ በነ ቴክታና ጰጥሪቃ ሕልም እንደታየችዉ በሌሊት የምታበራ ጨረቃ፤ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰዉ ልጅ ሁሉ ደስታ ነዉ፡፡ * ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት ‹‹መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸዉ››፤ ‹‹ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል››፤ ‹‹ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ››፤ …. ብለዉ የተናገሩላት ቅ/ድ/ማርያም ልደቷ የትንቢታቸዉ ፍፃሜ ነዉና ታላቅ ደስታቸዉ ደስታችንም ነዉ፡፡ (መዝ. 86፥1፣ ኢሳ. 11፥1፣ መኃ. 4፥7)ጂነአ * በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል፤ ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል፡፡ ለሰዉ ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ግን ምንኛ ሊከበር ይገባዉ ይሆን! ፠ #የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር ሐናና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር  እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳውያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ ፣ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ፈንድሻ የሚጥሉ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣  እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡

፥ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን ፥ እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡ --------------- ፠ በፎቶ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ * ሰላ ድንጋይ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ምኒልክና የተሠራና የአቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ በልዩ አሠራር በ42 ቆመ ብእሲ (ዐምድ) የታነጸ፡፡ * መናገሻ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአቡነ ማቴዎስ የተሠራና መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ ውጭው ክብ ውስጡ ግን ከሌሎች ክብ አብያተ ክርስቲያናት ልዩና ድንቅ በሆነ አሠራርና ሥዕላት የተሞላ፡፡ቀ * ጎጃም ደብረ ማርቆስ፤ * መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ከቤተ መንግሥታቸው ላይ ቦታ ቀንሰው ያነጹት ቤ.ክ.፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com  YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ_ሚያዝያ_፴ ማርቆስ የሚለው ስም 3ት ፍቺዎች አሉት ንብ፣ አንበሳና ካህን:: ሀ) *ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ነው፤ ለ) *አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር፤ በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው፡፡ ሐ. *ካህን የሚለው ትርጕም ደግሞ በሐዋ. 14፥13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው:: ፠ ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው፤ ሐዋ. 12፥12፡፡ አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ፡፡ እናቱ ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን (በተነሣ በ50ኛው ቀን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሐዋ. 2፥1 ፤ 12፥12፡፡ ፠ የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር ፥ በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል:: ሐዋ. 12፥25፣ ቈላ. 4፥10፣ 1ኛ ጴጥ. 5፥13 ፠ በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡ እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ:: ፠ ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ፥ ተአምራቱን አይተው አመኑ፥ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም፤ ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው፤ በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፤ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12ኛው ሲጀመር ፥ ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ.ም. ባለው ጊዜ/ ነው:: ፠ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቊጥር በዝተው፥ በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፤ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፤ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም፥ አልሸሽም አለ፡፡ እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ፥ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ፡፡ ወደጌታ ቢያመለክት፤ ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ፤ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት፥ በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥልላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ፤ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ፥ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ፥ የፀሐይም ብርሃን ተሠወረባቸው፤ በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል፡፡ ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው በክብር ሥጋውን በአሌክሳንድርያ ቀብረውታል:: ፠ በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 ዓ.ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት፤ በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የሮማው ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ፤ ቅዱሱ ባረፈ በ1900 ፥ በተወሰደ በ1140 ዓመት አጽሙ ሰኔ 17 ቀን 1960 ዓ.ም. ፈልሶ ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ፡፡ ሲመለስም ጃንሆይም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወ መንግሥት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት ፥ አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ፥ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኰሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ፥ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ፥ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ፥ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን፥ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው፥ ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው፥ በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከ4ኛ ክ/ዘ/ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እስከ አቡነ ቄርሎስ 20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ፥ ሥርዐታችን ከሥርዓታቸው የተስማማ

+ የአባታችን የመጋቤ ሐብታት ታደሰ መልካሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለ 53 ዓመታት ባገለገሉበት በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነገ ሐሙስ ከ 5 እስከ 6 ይፈጸማል ። + ዛ
+ የአባታችን የመጋቤ ሐብታት ታደሰ መልካሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለ 53 ዓመታት ባገለገሉበት በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነገ ሐሙስ ከ 5 እስከ 6 ይፈጸማል ። + ዛሬ ከምሽቱ ዠምሮ በማሕሌት በሰዓታት እና በጸሎተ ፍትሐት በቁመት ይታደራል። #ከአባታችን በረከት ያሳታፈን ።

#ዜና_ዕረፍት መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ ከ1937 - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት ‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38 * የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፡፡ * ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸምበትን ዕለት እና ሰዓት እናሳውቃን። ፨፨ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ መልካሙ በመናገሻ አውራጃ በአዳ በርጋ ልዩ ስሙ ደብረ ጽሙና ገዳም ከአባታቸው ከአቶ መልካሙ ባሻ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ጥሩነሽ የለሙ ሰኔ 12 ቀን 1937 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በዛው በደብረ ጽሙና ገዳም የንባብ መምህር ከነበሩት ከየኔታ ወልደ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የንባብ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው አጠናቅቀዋል፡፡ በመቀጠልም የዜማ መምህር ከነበሩት መምህር መንበሩ ገብረ ሕይወት ጋር በመሄድ የዜማ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በደብረ ጽሙና ገዳም የቅዳሴ መምህር ከነበሩት ከአባ ንዋይ ወልደ ማርያም የቅዳሴ ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ በ1953 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 1959 ዓ.ም ከ ወ/ሮ ትምክህተ ታደሰ ጋር በህገ ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻን በተማሩበት በደብረ ጽሙና ገዳም ፈጽመዋል ከጋብቻውም አንድ የልጅ ፍሬ አግኝተዋል፡፡ ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ በመስከረም 25 ቀን 1960 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ በትውልድ አካባቢያቸው በቅስና ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ ቆይተው መጋቢት 5 ቀን 1962 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከመምሬ መኮንን ወልደ ሥላሴ ጋር በመምጣት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም በዲቁና ተቀጥረው ማገልገል ጀመሩ፡፡ ነገር ግን የመንግስት ለውጥን ተከትሎ መሬታቸው በመወረሱ ምክንያት እን በወቅቱ ይከፈላቸው የነበረው በዓመት 15 ብር የድጎማ ገንዘብ ቤተሰብ ለማስተዳደር በቂ ባለመሆኑ ከአገልግሎቱ ጎን ለጎን በመንግስት መስሪያ ቤት የፍትህ ሚኒስቴር በመቀጠር ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1971 ዓ.ም በደብሩ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በወቅቱ የነበሩት የአጥቢያው ሽማግሌዎች ልጆቻችን ይመለሱ በማለታቸው ከተመለሱትና ዳግመኛ የሙሉ ሰዓት አገልግሎታቸውን ከጀመሩት አገልጋዮች መካከል የያን ጊዜው ሊቀ ዲያቆን የአሁኑ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ አንዱ ናቸው፡፡ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ በደብሩ በሊቀ ዲቁና፤ በዳቦ ቤት ሽያጭ፤ በዳቦ ቤት ተቆጣጣሪነት፤ በደብሩ ገንዘብ ያዢነት፤ ደመወዝ ከፋይነት፤ በቄሰ ገበዝነት ለሁለት ጊዜ፤ በሰበካ ጉባኤ ተወካይነት፤ በልማት ኮሚቴነት፤ እንዲሁም በአሁን ሰዓት በስርዓተ ጋብቻ አስፈጻሚነት ተመድበው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ መጋቤ ሀብታት አባ ታደሰ የንስሃ ልጆቻቸውን እና በጎ አድራጊ ምዕመናንን በማስተባበር ለቤተ ክርስቲያኑ አስፈላጊ የሆኑ ንዋየ ቅድሳትን በማሟላት ለተከታታይ 52 ዓመታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል፤ የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን ! #የሥርዓተ ቀብር ሰዓቱን የምናሳውቅ ይኾናል ። /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ። #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com