uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 394 підписників, посідаючи 5 590 місце в категорії Релігія і духовність та 2 197 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 394 підписників.

За останніми даними від 30 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 21, а за останні 24 години на 1, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 21.61%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.23% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 327 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 576 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 17.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 01 липня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 394
Підписники
+124 години
+307 днів
+2130 день
Архів дописів
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ
+1
#አብርሃ_ወአጽብሃና_4ቱ ቅዱሳን ነገሥታት እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ከነገሡ ነገሥታት የሚለዩበት ነገር አለ ይኸውም፤ ክህነትን ከንግሥና፥ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ (እንደ ካህኑ መልከጼዴቅ፣ አፄ ገብረመስቀል፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ …) እግዚአብሔርንም ሰውንም ያገለገሉ ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ ቅድስናን ከሐናፄ ቤተመቅደስነት ጋር ደርበው የያዙም ጭምር ናቸው፡፡ በዚህም በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሏቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው፤ ጽላት የተቀረጸላቸው፥ ገድል የተጻፈላቸው፤ (ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ የኾኑ) ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 364 ዓ/ም አጽብሐ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ/ም በሞተ ሥጋ አርፈዋል፡፡ ክብረ በዓላቸው በትግራይ ባለ ውቅር ገዳማቸው፤ በአዲስ አበባ ደግሞ፤ * * በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ **በየካ ተራራ ዋሻ ተክለ ሐይማኖት **በአያት ቅዱስ ፋኑኤል ቤተክርስቲያን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ዓመታዊ የንግሥ በዓልና የጉባዔ ጥሪ! አዲስ አበባ ውስጥ የቅዱሳኑ ነገሥታት #አብርሐ #ወአጽብሐ በዓለ ንግሥ የሚከብርበት አጥቢያ ያውቃሉ? ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ጀርባ የቅዱሳኑ ነገሥታት አብር
+1
ዓመታዊ የንግሥ በዓልና የጉባዔ ጥሪ! አዲስ አበባ ውስጥ የቅዱሳኑ ነገሥታት #አብርሐ #ወአጽብሐ በዓለ ንግሥ የሚከብርበት አጥቢያ ያውቃሉ? ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ጀርባ የቅዱሳኑ ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ በዓለ ንግሥ በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የፊታችን ሐሙስ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በልዩ ሁኔታ ይከበራል፤ ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ሕዝቡን ይባርካል፡፡ የምትችሉ ሁሉ ተገኝታችሁ እንድታከብሩና ከቅዱሳኑ ቃል ኪዳን እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤
+1
(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ በቦረና አውራጃ ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

#ጥቅምት_3_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤#_ፅንሰቱ_ነው፡፡ ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል፡፡ እንዲሁም፤ + እንደ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሱን ራሱ ፈልፍሎ ያነፀ #የሕንፃ_ባለሙያ ነው። + ከጓደኛው ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሁኖ የወለቃ ወንዝ ድልድይን የሠራ መሐንዲስ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ድልድዩን ሕዝቡ ይጠቀምበታል፡፡ + እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ መናፍቃንን የረታ #ብርቱ_የቤተ_ክርስቲያን_ጠበቃ ነው። + እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በርካታ መጻሕፍትን የጻፈ (የደረሰ) #ደራሲ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ዙሮ ያስተማረ #ሐዋርያ ነው፡፡ + እንደ ፍጹማን መነኰሳት በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስኖ በተጋድሎ ጸንቶ የኖረ #መናኝ_ጻድቅ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ያሬድ በሰማያዊ ዜማ አምላኩን ያመሰገነ #የዜማ_ሊቅ #የዜማ_ደራሲ ነው። + እንደ ዕዝራ ሱቱኤል ሰማያዊ መጠጥ ጠጥቶ ምስጢራት የተገለጹለት #ድንቅ_ተመራማሪ #የጥበብ_አባት ነው:: (ለምሳሌ፤ በሰዓታት ድርሰቱ ውስጥ ዑደተ ማይን፣ በሌሎች ድርሰቶቹም ስለ አእባንና እጽዋት ቀድሞ ነግሮናል፣ እንዲሁም የውኃ ማቆር ቴክኖሎጂን በዘመኑ ተግባራዊ አድርጓል። + እንደ ሰማዕታት ከነገሥታቱ ስለ ሃይማኖት ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለ #ሰማዕት ነው፡፡ + አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞን፤ አቡነ ኢየሱስ ሞ ሐይቅ እስጢፋኖስን፤ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስን፤ አቡነ ሳሙኤል ዋልድባን፤ አቡነ ዐምደ ሥላሴ ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እንደመሠረቱና የተመሠረተውንም እንዳስፋፉ፤ እርሱም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫን የመሠረተ ቅዱስ ነው፡፡ + በሰዓታት ድርሰቱ ቤተክርስቲያን አምላኳን ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ እንድታመሰግን ያስቻለ ምድራዊ #መልአክ ነው፡፡ + "አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" እስከሚል ድረስ ጸጋ የበዛለት አባት ነውና ስንቱን እንናገረው? አይቻለንምና!!!፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like Facebook (https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool)

እንኳን ደስ አላችሁ ✤ልዩ የምርቃት መርኀ ግብር የ ፳፻፲፪ ዓ.ም እና ፳፻፲፫ ዓ.ም ተማሪዎች፤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ተጋባዥ እንግዶች ፣ መምህራንና ዘማርያን በተገኙበት ይመረቃሉ:: ✤እሑድ መስ
እንኳን ደስ አላችሁ ✤ልዩ የምርቃት መርኀ ግብር የ ፳፻፲፪ ዓ.ም እና ፳፻፲፫ ዓ.ም ተማሪዎች፤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ተጋባዥ እንግዶች ፣ መምህራንና ዘማርያን በተገኙበት ይመረቃሉ:: ✤እሑድ መስከረም 30 ፤ ሰዓት :- 3:30 ✤ የ 560 ተማሪዎች ምርቃት

#የማኀሌተ ጽጌ ፤ የመስከረም 30 3ኛ ማኀሌተ ጽጌ (ሰዊት ሥርናዩ ) ትርጓሜ ✤ #ሰዊት_ሥርናዮ (ትምሕርቱ) ለታዴዎስ ወለበርተሎሜዎስ ወይኑ ፤ እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተከልኪ እደ የማኑ ፡፡ ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ስበኑ፤ ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ ፡፡ ✤ #ትርጉም የታዴዎስ የሥንዴውን የተአምሩ እሸት በቀኝ እጁ የተከለሽ የበርተሎሜዎስ ወይኑ የጴጥሮስ ጥላውና የጳውሎስልብሱ የሆንሽ ማርያም ሆይ ሙታን በአንቺ ሕያውያን ሆኑ ፤ ሐዋርያትም መላእክትን (የምድርን መኳንንትን ) በሰማይ ገዙ ፤ ማቴ 78 .18 (1ኛ ቆሮ 6.2) ✤ #እመቤታቸን #የታዴዎስ_እሸት መባሏ ለዚህ ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያው ታዴዎሰን ወደ ሀገረ ስብከቱ ለማድረስ አብሮ ሲሄድ ፤ በእርሻ ቦታ ላይ አንድ ሽማግሌ አግኝተው የምንበላው ስጠን ቢሉት በሬዎቼን ጠብቁ ብሎ ሄደ ቅዱስ ታዴዎስም ሥራ መፍታት የለበንም ብሎ በተጠመዱት በሬዎች ማረስ ጀመር ቅዱስ ጴጥሮስም ደግሞ ዘርን ይዘራ ነበር የዘራውም ዘር ወዲያው በቅሎ አፈራ ፣ ይህን ታላቅ ተአምር ያየ ገበሬ አደነቅ .፡፡ ጌታ በ ዮሐ. 12 እውነት እላችሁአለሁ የስንዴ ቅንጣት ፍሬ በምድር ወድቃ ብትሞት ፍሬ እንደምታፈራ ፣እኔም ሞቼ ብነሣ ነፋሳትን ከሶኦል ወጥተው ገነት ይገባሉ ››ሲል ከድንግል ማርያም የነሣውን ሥጋ ፣ #በስንዴ ቅንጣት መስሎ ተናግሮ ነበር. ስለዚህ የጌታ ደቀ መዝሙር ይሆነ ታዴዎስ ይህንን ተአምር ሠርቷልና ፣ #እመቤታቸንን #የታዴዎስ #የስንዴው #እሸት አላት ፡፡ ✤ #የበርተሎሜዎስ_ወይን መባሏ ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ ከበርተሎሜዎስ ጋር እልዋህ ወደሚባል ሃገር አብርው በሄዱ ጊዜ ቅዱስ #ጴጥሮስ ቅዱስ በርተሎሜዎስን ለአንድ ነጋዴ ልሽጥልክ ብሎ አማከረው ሙያውም የወይን ጠባቂ እንደሆነ ነገረው ፡፡ ነጋዴውም የወይን ጠባቂ አለቃ አድርጎ ሾሞት 40 ቀን ከቆየ በኃላ የወይኑ ባለቤት ወይኑን ለመጎብኝት ሲመለስ በእባብ ተነድፎ ሞተ ፡፡በርተሎሜዎስም አስነሳው ፡፡ #ስለዚህም ክርስቶስ ከእመቤታችን በነሣው ሥጋ ሞትን ድል አድርጎ ተግልጻልና ፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ ሳትላይ በርተሎሜዎስ፤ የወይኑ ባለቤት የሆነውንና ሞቶ የነበረውን ይህን ሰው አስነሥቷልና የበርተሎሜዎስ #ወይን አላት ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አህዛብን አስተሞሮ ያሳምን ነበር ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በርተሎሜዎስን ለነጋዴው የሸጠውና ነጋዴው ደግሞ የወይን ጠባዊ አለቃ አድርጎ የሾመበት ምክንያት -ወይን በተተከለ በ3 ዓመት ያፈራል ጌታም 3 ዓመት ከ 3ወር ሲያስተምር ያለምሳሌ አለስተማርም ነበር፡፡ ማቴ 13.35 ፡፡ ጌታ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ብሎ ከድንግል ማርያም የነሣውን ደም በወይን መስሎ ተናግሮ ነበረ፡ የሐ 15:: ስለዚህም ቅዱስ በርተሎሜዎስ በራሱ ፈቃድ ተሸጧል ፤ ጴጥሮስም የሸጠበትን ገንዘብ በሥውር ለበርተሎሜዎስ ሲመልስ እርሱ ደግሞ ለነዳያን መጽውቶታል ፡፡ በርተሎሜዎስ አሽዋ በተሞላበት ከረጢት ባሕር ውስጥ ጥለውት መስከረም 1 #ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ ✤ #ማርያም_የጴጥሮስ_ጥላ_መባሏ ደግሞ ጥላ ማለት የሚታይ የአንድ ነገር ግርዶሽ ሲሆን ይህም ብርሃን በሚኖርበት ጊዜ ብቻ ነው ፡፡ እመቤታችን በረድኤት ጌታችን የዓለም ብርሃና ናቹህ ካላቸው ሐዋርያት መካከል ከጴጥሮስ ሳትለይ በጥላው ሕሙማን ተፈውሰዋልና እንዲዚህ አላት ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

እንኳን ለቅድስት አርሴማ ዓመታዊ ክብረ በዓል (በዓለ ዕረፈት) አደረሰን፥ አደረሳችሁ፡፡ በዚህች #በመስከረም 29 ቀን አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት እና የእርሷ ማኅበርተኞች ድል አድራጊዎች 27 ሰማዕታት በሰማዕትነት ያረፉባት ዕለት ነች፡፡ እግዚአብሔር ከእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸውን ይክፈለን፡፡ እነዚህም ቅዱሳን፤ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለፀዐተ ነፍስኪ በጊዜ ኃለፈ ሰይፍ፤ መንገለ ክሣድኪ ድኑን ለአምሳለ መሥዋዕት ውኩፍ፡፡ እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ፤ ረድኤትኪ ትሩፍ በላዕሌየ ያንጸፈጽፍ፤ እስመ አርአየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#የመድኀኔዓለም በዓል ዝማሜ ፤ #ጥቅምት ወር ፤ 2012 ዓ.ም * ኮምጣጤ ከሐሞትና ከከርቤ ጋር ቀላቅለው አይሁድ ላጠጡት ለአፍህ እሰግዳለሁ፡፡ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላቶች የተናገርህ ክርሰቶስ ሆይ አይሁድ ጠቃሚያቸው አንተን ሊወዱህ ሲገባ ለምን ጠሉህ ሙታኖቻቸውን ታሥነሳ ነበርና፡፡ * #መልክአ መድኀኔዓለም እስግድ https://youtu.be/Cx60ZRQ9pUQ