uk
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Відкрити в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 366 підписників, посідаючи 5 646 місце в категорії Релігія і духовність та 2 192 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 366 підписників.

За останніми даними від 18 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -95, а за останні 24 години на 11, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 21.81%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 9.33% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 3 344 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 430 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 22.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 19 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

15 366
Підписники
+1124 години
-67 днів
-9530 день
Архів дописів
#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤  #ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ) #ሰንበት_ዐባይ #ቅዱስ_ቅዳሜ፤ #ቀዳሚት_ሰንበት #ቀዳሚት_ሰንበት፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ያረፈባት ስለሆነች፤ የእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት፤ ቀዳሚት ሰንበት (የዕረፍት ቀን) ትባላለች፡፡ #ሰንበት_ዐባይ (ታላቋ ሰንበት)፤ የመጀመሪያዋ ሰንበት በመሆኗ ታላቋ ሰንበት ትባላላች፡፡ #ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ እግዚአብሔር ሥነ ፈጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሰ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡ ፠ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና ሌሌችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡ ፠ የቻልን ሕዝበ ክርስቲያንም ይህን መነሻ በማድርግ ከዐርብ ጀምረን በማክፈል (በመጾም) እህል ውኃ ሳንቀምሱ ለሁለት ቀናት እናድራለን (እንካፍላለን)፡፡ እንደ ዋልድባና ማኅበረ ሥላሴ ባሉ ገዳማት ያሉ ታላላቅ አባቶችና ወንድሞች ደግሞ ከሆሳዕና አንዳንዶችም ከዕለተ ረቡዕ ጀምረው ለ7ት ቀናት ወይም ለ3ት ቀናት ያከፍላሉ፡፡ #ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ) ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ (በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፥ መሠረተ)›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡ ፠ ቄጠማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምደር በተጠለቀለቀች ጊዜ፤ ኖኅ ወደ መርከብ ይዟቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ልኮ እርሷም ቄጠማ በአፏ ይዛ በመመለስ የምሥራች ምልክት፥ የውኃውን መድረቅ እንደተነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡ ‹‹በክርስቶስ ሞት፤ ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስንል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት ደባትር መዘምራን ዝማሬን ካቀረቡ በኋላ ለልጆቿ ቄጠማ ታድለናለች፡፡ የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማም፤ ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን  ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን፡፡ #ቅዱስ_ቅዳሜ፤ ለ5500 በሲኦል ሲማቅቁ የነበሩ ነፍሳትን ሰላም ለሁላችሁን ይሁን ብሎ ወደ ገነት አስገብቷቸዋልና፤ ይህች ቅዳሜ ቅዱስ (የተለየች) ቅዳሜ ትባላለች፡፡ አውረድዎ፥ አውረድዎ፥ አውረድዎ እምዕፅ፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕዉስ፡፡ ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ፤ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ ስግደት /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSund
+4
ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ ስግደት /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ሥርዓተ_ጸሎተ_ሐሙስ_ወሕጽበተ_እግር ሐዋርያቲሁ ከበበ፥ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤ ኮኖሙ አበ ወእመ፤ ወመሐሮሙ ጥበበ፡፡ (ሐዋርያቱን ሾመ፤ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤ አባትና እናት ኾናቸው፤ ጥበብንም አስተማራቸው፡፡) /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#መልክአ_ሕማማት፤ *መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ነው፡፡ *መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤ 1ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/ 2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/ 3ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/ **በ7ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም  ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ 37፣ ቀሌምንጦስ 1ና 7፣ አቡሊዲስ 25ኛና 27ኛ፣ ባስልዮስ 28ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 21/፡፡ ፠ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ3ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የሥሉስ ቅዱስ፣ የጌታ፣ የማርያም ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤ እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥ በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡ #የ7ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም፤ ፠1ኛ) መንፈቀ ሌሊት(ሌሊት 6 ሰዐት)፤ ጌታችን የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተነሣበትና ዳግመኛ የሚመጣበት ፥ … ሰዐት ነው፡፡ ፠2ኛ) ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)፤ ጨለማን አርቆ ብርሃንን የሚያመጣበት፥ አባታችን ቅዱስ አዳም የተፈጠረበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጲላጦስ አደባባይ ፊት ቁሞ የተመረመረበት፥ …. ሰዐት  ነው፡፡ ፠3ኛ) ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)፤ እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፥ ነቢዩ ዳንኤል ጸሎት ያደረሰበት፥ እመቤታችን  ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ሰምታ የጸነሰችበት፥ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠4ኛ) ቀትር (6 ሰዐት)፤ አጋንንት የሚሰለጥኑበት ሰዐት ስለሆነ እንዳይሰለጥኑብን፥ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሳተበት ስለሆነ እንዳንስት እንጸልያለን፡፡ በተጨማሪም ነቢዩ ሄኖክ ቤተ መቅደስን ያጠነበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠5ኛ) ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)፤ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው የለየበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠6ኛ) ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)፤ ነቢዩ ኤልያስ መሥዋዕት የሰዋበት፥ ዕዝራ ጸሎትን ያቀረበበት፥ ሕዝቅያስ ጸልዮ ፀሐይን ወደ ዐሥር ደረጃዎች የመለሰበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደ በፈቃዱ ወደ አዲስ መቃብር የወረደበት፥ …… ሰዐት ነው፡፡ ፠7ኛ) ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የጸሎትን ሥርዐት ያስተማረበት ፥ እንዲሁም ሌሊቱን በመላእክት ጥበቃ ከርኵሳን አጋንንት እንዲጠብቀን የምንጸለይበት …… ሰዐት ነው፡፡ #ለቡ(ልዩ ማስታወሻ)!! ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡ በሰሙነ ሕማማት የሚባሉትን በአጭሩ ስንቃኛቸው፡፡ /ይህን ጽሑድ ለዐርቡ ጸሎት እንደ ዘማች ስለሚያገለግል በአድካሚ ሁኔታ እንደ ንብ ቀስመንና ሰብስበን አዘጋጅተንላችኋል፤ ላልደሰረሰው አዳርሱ፡፡/ ፠የሰሙነ ሕማማት ጸሎት የሚደረገው በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት መሠረትነት 7ት ጊዜ ነው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ7ቱ ጊዜያት ከፋፍሎ የደረሰው መልክአ ሕማማትም አብሮ በዜማ ይደርሳል፡፡ ፠ደወልና ቃጭል ይመታል፤ ፠ጸሎታት(ሙሉ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት)ና  (የኦሪትና የነቢያት) ምንባባት ይደርሳል፤ ፠የተአምር መቅድምና ምንባብ ይነበባል፤ የተአምራት መርገፍ በዜማ ይባላል፡፡ ፠የወንጌል አቡን በቅብብሎሽ ይደርሳል፤ ፠ምስባክ ይሰበካል ፥ ወንጌል ይነበባል፡፡ #1ኛ_ስግደት፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ›› እያለ ቃጭል ሲያሰማ 22ት ጊዜ ‹‹እግዚኦ ተሣሃለነ›› እየተባለ ይሰገዳል፡፡ #2ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለከ ኀይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን በቅብብሎሽ 6ት ፥ 6ት ጊዜ (በድምሩ 12)፤ 7ኛውን በኅብረት እየተሰገደ ይባላል፡፡ #3ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለአምላክ ይደሉ›› የሚለውን 1ኛውን ዙር በቅብሎሽ፤ 2ኛውን ዙር እያስተዛዘሉ፤ ከስግደት ጋራ ይባላል፡፡ #4ኛ_ስግደት፤ ‹‹ክርስቶስ አምላክነ…›› የሚለውን በመሪና ‹‹ንሰብሖ ..›› ወናልዕል ስሞ የሚለውን በቅብብሎሽ ብለው በዚያው ቀጥለው፤ ‹‹ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን›› የሚለውን በመሪ 21 ጊዜ፤ በተመሪ 20 ጊዜ (በድምሩ 41 ጊዜ) እየተሰገደ ይደርሳል፡፡ ፠የየሰዓቱን (የሌሊት፣ የነግህ፣ የጠዋት 3 ሰዐት፣ የቀትር/6 ሰዐት/፣ የተሰዐት/9ኝ ሰዐት/፣ የሰርክ /11 ሰዐት/፣ የንዋም) መልክአ ሕማማት በዜማ ይደርሳል፡፡ ፠ካህኑ ቡራኬ ሰጥቶ፤ ዲያቆኑ ደግሞ ‹‹ሑር በሰላም›› ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ የአምላክ ስሞችና ትርጕማቸው፡፡ /ምንጭ፤ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m
በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ የአምላክ ስሞችና ትርጕማቸው፡፡ /ምንጭ፤ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች † ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞ:: † ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን:: † ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀ
#የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች † ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞ:: † ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን:: † ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን:: † ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ:: † ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ:: † ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤  ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958