uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

EFF Refereeing Departement (የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፖርትመንት)

Відкрити в Telegram

This is official telegram chanel of Ethiopian football federation refereeing department.

Показати більше
1 674
Підписники
-124 години
-37 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
ማስታወቂያ ለኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ እና ለኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዳኞች በሙሉ፦ የአዲሱ የውድድር ዘመን የዳኞች ኪት አሰጣጥ እና የፎቶ ቀረጻ ፕሮግራም በመጪው ረቡዕ በWosen Gofere Sport Studio እንደሚካሄድ እናሳውቃለን። ስለሆነም ሁሉም የወንዶች እና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዳኞች በተጠቀሰው ቀን በቦታው በሰዓቱ በመገኘት በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ እናሳስባለን። የፎቶ ቀረጻው ለዳኞች የሙያ መረጃ፣ የውድድር አስተዳደር እና ለተለያዩ የዳኞች ማስታወቂያና የሚዲያ አገልግሎቶች ስለሚያገለግል ሁሉም ዳኞች በተገቢው የዳኝነት ልብስ እና መሳሪያዎቻቸው ተዘጋጅተው እንዲመጡ ይጠበቃል። እያንዳንዱ ዳኛ ይዞ መምጣት ያለበት፦ • 🚩 የዳኝነት ባንዲራ • 📣 ፊሽካ (Whistle) • 🟨🟥 ቢጫ እና ቀይ ካርድ • 👟 የዳኝነት ጫማ (Boots) • ለፎቶ ቀረጻው የሚያስፈልጉ ሌሎች የግል የዳኝነት መሳሪያዎች እባክዎ ሁሉም ዳኞች የተጠቀሱትን መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ይዘው እንዲመጡ እና በተመደበው ጊዜ በቦታው ተገኝተው የፎቶ ቀረጻውን እንዲያከናውኑ እናሳስባለን። የፕሮግራሙ ስኬታማ አፈጻጸም የሚወሰነው በሁሉም ዳኞች በሚያደርጉት ተገቢ ትብብር ላይ ስለሆነ፣ የሁላችሁንም ትብብር እና ሙያዊ ተሳትፎ እንጠብቃለን። ቦታ፦ Wosen Gofere Sport Studio (ወሰን አቤም ሆቴል አካባቢ) ቀን፦ መጪው ረቡዕ 27/01/2019 ሰዓት:- 8:00 ከሰዓት ተሳታፊዎች፦ የወንዶች እና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዳኞች ፕሮግራም፦ የዳኞች ኪት አሰጣጥ እና የፎቶ ቀረጻ #ማሳሰቢያ ከአዲስ አበባ እና ዙሪያ ዉጭ በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች የምትኖሩ የወንድ እና ሴት የፕሪሚየር ሊግ ዳኞች ሌሎች ፕሮግራሞች ስለሚኖሩን በቀጣይ እናሳውቃለን ስለዚህ የምጣት ግዴታ የለባችሁም። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ዲፓርትመንት

የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ሙሑር ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ሙሑር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊዜያ
የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ሙሑር ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ሙሑር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊዜያት በማገልገል ያሳለፉ ሲሆን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኮሚሸነር ሙሑር ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል።

የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ብርሃኑ ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ብርሃኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም
የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ብርሃኑ ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ብርሃኑ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊዜያት በማገልገል አሳልፈዋል። የኮሚሽነር ብርሃኑ ሥርዓተ ቀብር በነገው ዕለት መስከረም 24 ቤተል ኮልፌ ክ/ክፍለ ከተማ አጠገብ ባለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6፡00 ይፈጸማል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኮሚሸነር ብርሃኑ ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል።

ለፕሪሚየር ሊግ ኮሚሽነሮች የስልጠና ጥሪን ይመለከታል ለ2019 ዓ/ም የውድድር ዘመን በተሻሻሉ ሕጎች ዙሪያ እና የጨዋታ አመራሮችን በተሻለ መንገድ መገምገም የሚቻልበትን ሁኔታዎች ለመሰልጠን ረቡዕ 27/01/2019 ዓ/ም አትላስ አካባቢ በሚገኘው አዝማን ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በ2018 ዓ/ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሚሽነርነት ተመድባችሁ ስትሰሩ የነበራችሁ ብቻ እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እያስተላለፍን ስልጠናውን ያልወሰደ ኮሚሽነር በውድድር አመቱ የማይመደብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ማሳሰቢያ፦ በቅርቡ በFIFA MA Instructors course ስልጠና የወሰዳችሁ የፕሪሚየር ሊግ ኮሚሽነሮች የስልጠና ጥሪው እናንተን አይመለከትም፡፡ ``ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎችን ለመፍጠር እንሰራለን``

ለወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ አመራሮች ⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከመስከረም 29/2019 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምር መገለፁ ይታወቃል። በመሆኑም ሰኞ በ25/01/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ በ12፡00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም የጤና የምርመራ ውጤት ይዛችሁ በመምጣት ለባለሙያዎች ማረጋገጥ እና በዚያው ቀን 1፡00 ጀምሮ የአካል ብቃት ፈተና በመውሰድ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ሙሉ ቀን ወደፊት በምናሳዉቀው ቦታ ስለተሻሻሉ የጨዋታ ሕጎች እና ቅድመ የውድድር ዝግጅት ገለፃ  ይሰጣል። ስለሆነም በተገለፀው አግባብ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ:- ጥሪዉ የሚመለከታችሁ ብቻ እንድትገኙ እናሳስባለን። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 “አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ያላቸው የዳኝነት ባለሙያዎች ለመፍጠር እንሰራለን”

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መልካም በዓል ይመኛል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መልካም በዓል ይመኛል።

REFEREEING IS NOT ABOUT BEING PERFECT. “Refereeing is not about being perfect. It is about being prepared, focused and fair.”
REFEREEING IS NOT ABOUT BEING PERFECT. “Refereeing is not about being perfect. It is about being prepared, focused and fair.” Pierluigi Collina FIFA chairman of referee committee One of the most iconic referees in football history, Collina’s words capture the essence of the profession: preparation, concentration, courage and fairness. Every match brings pressure. Every decision matters. But the goal remains the same — serve the game with integrity. Be prepared. Stay focused. Be fair #refereeingworld

Dear Ato Isaias Jira, President of the Ethiopian Football Federation, Congratulations on your successful election for a third
Dear Ato Isaias Jira, President of the Ethiopian Football Federation, Congratulations on your successful election for a third term. We sincerely wish you continued success and great achievements as you lead Ethiopian football toward greater progress and excellence. We deeply appreciate your visionary leadership, confidence, and unwavering support for the development and modernization of Ethiopian refereeing. Your trust in our ideas and initiatives has given us the encouragement and opportunity to pursue meaningful reforms and build a stronger, more professional refereeing system. We are honored and pleased to continue working under your leadership and to contribute to the advancement of Ethiopian football. Thank you for your leadership, trust, and continued support. We wish you a successful and transformative third term. National Referees Committee

🌼🌼🌼 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመላው ኢትዮጵያውን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልፃል። 🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት !
🌼🌼🌼 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመላው ኢትዮጵያውን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልፃል። 🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት !

ቀጥታ ስርጭት ! የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 የውድድር ዘመን የሽልማት እና እውቅና መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል (አዲሱ ሆቴል - 7ኛ ፎቅ) ይካሄዳል።
ቀጥታ ስርጭት ! የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 የውድድር ዘመን የሽልማት እና እውቅና መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል (አዲሱ ሆቴል - 7ኛ ፎቅ) ይካሄዳል። ሁነቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን የዩቲዩብ ቻነል (EFF PLAY) በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። https://youtube.com/live/Fup30xMHrCU?feature=share

ታዳጊዎቹ የጨዋታ አመራሮች ዮሴፍ ሰሎሞን እና መዓዛ የኋላሸት በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ላይ ጨዋታዎችን ለመምራት በዛሬው ዕለት ወደ ኪጋሊ አ
+1
ታዳጊዎቹ የጨዋታ አመራሮች ዮሴፍ ሰሎሞን እና መዓዛ የኋላሸት በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ላይ ጨዋታዎችን ለመምራት በዛሬው ዕለት ወደ ኪጋሊ አምርተዋል። የኢ/እ/ፌ ወጣት የጨዋታ አመራሮች ልማት ፕሮጀክት ማናጀር በአምላክ ተሰማ በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፍያ ተገኝቶ ለጨዋታ አመራሮቹ አሸኛኘት አድርጓል። ዳኛ ዮሴፍ እና ረዳት ዳኛ መዓዛ በትናንትናው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ ጨዋታዎችን ከመሩ ታዳጊ ዳኞች መካከል ናቸው።

📢 IMPORTANT ANNOUNCEMENT TO ALL MATCH OFFICIALS AND ASSESSORS Dear Respected Match Officials and Assessors, As we prepare for the start of the new CAF competition season, please be informed that CAF has issued important guidelines regarding the management of competitions and the recent changes to the Laws of the Game. These changes may have a direct impact on matches. Therefore, it is essential that all referees and assessors carefully review the latest instructions and guidance and ensure that they are fully familiar with the updated Laws and their application. We kindly ask all appointed match officials and assessors to read the attached guidelines carefully and ensure full compliance throughout the competition. Your professionalism, preparation, cooperation, and commitment are highly appreciated and will contribute significantly to the successful management of our competitions. Thank you for your continued commitment, and we wish you all a successful CAF competition season. Best regards, Refereeing Department Ethiopian Football Federation

ከቁጭት ወደ ተስፋ: የኢትዮጵያ ዳኝነት አዲስ መንገድ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዳኝነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እየተጻፈ ይገኛል። ለዓመታት በዳኞች ምልመላ፣ ልማትና እድገት ሥርዓት ላይ የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመሠረት (grass root) የጀመረ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ተግባራዊ እያደረገ ነው። የዚህ ትልቅ የለውጥ ጉዞ መነሻ እ.ኤ.አ በ2022 ዩጋንዳ ላይ በተካሄደው የሴካፋ የትምህርት ቤቶች ውድድር ወቅት የተከሰተ አጋጣሚ ነበር። በወቅቱ በስፍራው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ኢትዮጵያ ለውድድሩ የላከቻቸው የፕሪምየር ሊግ ደረጃ ዳኞችን እንደነበር ተመለከቱ። ይህ አጋጣሚ ትልቅ ቁጭት በመፍጠሩ ተተኪዎች ላይ ተግባራዊ ሥራዎች እንዲሰሩ አሳሰቡ። የብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሸዋንግዛው ተባባል ይህን አጋጣሚ ሲያስታውሱ "ያ አጋጣሚ ለዛሬ ሥራችን መነሻ ሆኗል። የተተኪ ዳኞችን ልማት በስትራቴጂ መምራት እንዳለብን ያሳየን ነው" ይላሉ። የዳኞች ኮሚቴው በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ አዲስ ስትራቴጂክ ፕላን ተቀርፆ የዳኛ ምንጮች ትምህርት ቤቶችና ወጣቶች እንዲሆኑ ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀመረ። "ቀደም ሲል በታችኛው እርከን ላይ በሚያጫውቱ ዳኞች እና በፕሪሚየር ሊጉ ዳኞች መካከል የተመጣጠነ የዕድሜ ስብጥር አለመኖር ለዳኝነት ማኔጅመንቱ አስቸጋሪ ፈተና ሆኖ ቆይቷል።" ያሉት የዳኞች ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ምስጋናው ይህንን ችግር ለመቅረፍ አዲስ የዳኝነት ሙያ መመርያ እንዲዘጋጅ መደረጉን ይገልፃሉ። መመርያው አዲስ ወደ ዳኝነት ሙያ የሚገቡ ግለሰቦች ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 22 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ብቻ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ዝርዝር መስፈርት መሠረት ወደ መረጃ ቋት ገብተው ከሥልጠና ጀምሮ በቅርብ ክትትልና እገዛ ወደ ላይ የሚያድጉበት መስመር እነዲዘረጋ ተደርጓል። እንደ አዲስ ፖሊሲ ከተቀመጡት ዋና ዋና አቅጣጫዎች መካከል የፌዴሬሽኑ የዕድሜ ውድድሮች በዕድሜ አቻ ወጣት ዳኞች እንዲመሩ ማድረግ መሆኑን አቶ ሸዋንግዛው ይናገራሉ። "ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ባሉ ወጣት ዳኞች ከ15 ዓመት በታች ውድድሮችን ይመራሉ። ከ17 ዓመት በታች ውድድሮችንም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ወይም በዛ የእድሜ አካባቢ ባሉ ዳኞች ይዳኛሉ። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የትምህርት ቤት ውድድሮች በተማሪ ዳኞች፣ የዩኒቨርሲቲ ውድድሮች ደግሞ በራሳቸው በዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዳኞች እንዲከናወኑ ይደረጋል።" በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮና የዚሁ አዲስ ፖሊሲ ፍሬ ማሳያ ሆኗል። በውድድሩ ላይ የሚገኙት የጨዋታ አመራሮች ሙሉ በሙሉ በዚህ አዲስ የምልመላ መስፈርት ከተለያዩ አካባቢዎች የተመረጡ ታዳጊ ዳኞች ናቸው። ታዳጊዎቹ የጨዋታ አመራሮች እያሳዩ የሚገኙት የአመራርነት ብቃትም ከፍተኛ ተስፋ የሰጠ ሆኗል። ዛሬ የተካሄዱ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ በአካል ተገኝተው የታዳጊ ዳኞቹን እንቅስቅሴ የተመለከቱት የሴካፋ የዳኞች ኃላፊ ዓሊ አህመድ እና የፊፋ ኢንስትራክተር ሁሴን ጋቦኒ ለተጀመሩት ሥራዎች ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል። የሴካፋ የዳኞች ኃላፊ ዓሊ አህመድ በቦታው ተገኝተው ከተመለከቱ በኋላ "ዛሬ እዚህ በመገኘታችን በጣም ደስተኞች ነን። ይህ በእውነት ለኢትዮጵያ ዳኝነት በጣም ጥሩ ተስፋ ያለው ነው። ይህን በመመልከታችን ትልቅ ደስታን ሰጥቶናል። መሰል ፕሮጀክቶች ሁልጊዜ ልናያቸውና ልንደግፋቸው የምንፈልጋቸው ናቸው። ዳኞችን ሁልጊዜ ከመሰረቱ መገንባት አለብን" ብለዋል። የዚህ አዲስ አቅጣጫ ውጤታማነት ቀስ በቀስ እየጎላ መጥቷል። ቀደም ሲል በሴካፋ የትምህርት ቤት ውድድሮች ላይ የተላኩ ታዳጊ ዳኞች ዛሬ ላይ የፊፋ ኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና ደረጃ እስከ መድረስ ችለዋል። ወጣቷ ረዳት ዳኛ ሀና ደመቀ በአንድ ዓመት ውስጥ የሴካፋ ትምህርት ቤቶች ውድድርን ከመምራት ተነስታ በዛሬው ዕለት በተጠናቀቀው የፊፋ ኤሊት የጨዋታ አመራሮች ስልጠና ላይ መካፈሏ የፕሮጀክቱን ትርጉም በሚገባ የሚያሳይ ሆኗል። አቶ ሸዋንግዛው ተባባል በአዳማ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ እያጫወቱ ካሉ ወጣት ዳኞች መካከል የአንድ ወንድና አንድ የሴት ዳኛ በቀጣይ ለሚደረገው የሴካፋ የትምህርት ቤቶች ውድድር መላኩን ገልጸዋል። ፌዴሬሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የጀመራቸውን የስልጠና እንቅስቃሴዎች በመከተል ሌሎች ከተሞች እና ክልሎች በተመሳሳይ መልኩ ተቀብለው እንዲተገብሩት ጥሪ አቅርበዋል። ከቁጭት ተነስቶ በስትራቴጂ ታገዞ አዲስ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳኝነት ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወክሉ ብቁ፣ በእድሜ ለጋ እና በስነ-ምግባር የታነጹ ዳኞችን ለማፍራት ትልቅ መሰረት ጥሏል።

ከቁጭት ወደ ተስፋ: የኢትዮጵያ ዳኝነት አዲስ መንገድ
+9
ከቁጭት ወደ ተስፋ: የኢትዮጵያ ዳኝነት አዲስ መንገድ

በሴፕቴምበር ወር በሚካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ እና ኢንተር-ክለብ ውድድሮች ላይ በካፍ የተመደቡ ኢትዮጵያውያን የጨዋታ አመራሮች
+3
በሴፕቴምበር ወር በሚካሄዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ እና ኢንተር-ክለብ ውድድሮች ላይ በካፍ የተመደቡ ኢትዮጵያውያን የጨዋታ አመራሮች

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መልካም በዓል ይመኛል !
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መልካም በዓል ይመኛል !

የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ሞገስ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ሞገስ ማሞ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊ
የሀዘን መግለጫ ! የጨዋታ ታዛቢ (ኮሚሽነር) ሞገስ ማሞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኮሚሽነር ሞገስ ማሞ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች በኮሚሽነርነት ለረጅም ጊዜያት በማገልገል አሳልፈዋል። የኮሚሽነር ሞገስ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ነሐሴ 18 በፈረንሳይ ሌጋሲዮን ገነተ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 6፡00 ተፈፅሟል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኮሚሸነር ሞገስ ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል።

በትግራይ ፖሊስ ዋልታ እና ጊምቢ ከተማ መካከል የሚደረገውን የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩ የጨዋታ አመራሮች
በትግራይ ፖሊስ ዋልታ እና ጊምቢ ከተማ መካከል የሚደረገውን የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩ የጨዋታ አመራሮች