የጥበብ ማዕድ
📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу የጥበብ ማዕድ
Канал የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 15 932 підписників, посідаючи 5 411 місце в категорії Релігія і духовність та 2 116 місце у регіоні Ефіопія.
📊 Показники аудиторії та динаміка
З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 15 932 підписників.
За останніми даними від 25 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 604, а за останні 24 години на -23, загальне охоплення залишається високим.
- Статус верифікації: Не верифікований
- Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 2.64%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 2.10% реакцій від загальної кількості підписників.
- Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 419 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 334 переглядів.
- Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 10.
📝 Опис та контентна політика
Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 26 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.
በልፋታቸው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው ፤ ገበሬው፥ ጠረፍ ጠባቂው፥ ሀኪሙ መምህሩ ነጋዴው ፤ ሾፌሩ፤ ግንበኛው ፤ አናጢው ወዘተረፈ፥ በአንጻሩ
“ እግዚአብሄር ነገረኝ “ በማለት እየተበረነነ በአማኝ ህዝብ ድጋፍ ደልቶት የሚኖር ሰው ፥ ስለ ስለትጋትና ስለስንፍና የማውራት ሞራል የለውም፤የሀይማኖት መሪዎች ሰባኪዎች ህብረተሰቡ ብዙ መስዋእትነት እንድትከፍሉለት አይጠብቃችሁም! ሀብታሞች ለእናንተ ከሚሰጡት መባና ስጦታ ቆንጥረው በብዙ ምክንያት ለተቸገረ እንዲረዱ ካሳሳባችሁ ትልቅ ውለታ ነው፤
ሹመቴ... ሺ ሞቴ ....
እሱም እንደ ልቡ ... እኔም እንዳሞቴ
ባይልም ዳሞቴ ...
እንደክራሞቴ
ቢፈቅደኝ ... ሊያሞኘኝ ....
ቢያቅደኝ .... ቢመኘኝ .....
እኔ ምን ተዳዬ ...ሁሉም ያሻውን ቢሆን ...
ስንቄን እና ትጥቄን ሳይሰጠኝ ... ላይሸኘኝ
ዓለሜን ብየ ካደርኩ .... ምን አለ የሚሳነኝ
አሀዱ ለፍቅር ... ለሰላም ሽልማት
ምን አለ ልዕልና .. ከጣር ከህማማት
እድሜ እየነገረ ... ልብ እየሰገረ ....
እጅ እየጋገረ ... ቀን እየማገረ ....
ቢሾሙም ..... ጥንስስ ነው
ሲመጡም .... እንጥስ ነው
ቢሄዱም ... ብጥስ ነው
ቢኖሩም ..... ቅንጥስ ነው
አሁ .... ተነፈስኩ
ፈሰስኩ ....
እንደደም ባልረጋም ......
ካልተሾምኩ አልሰጋም
📒 የባለ ቅኔ ምህላየኃይለየሱስ ማሞን ጥበብ ከጲላጦስ የሚለውን መፅሐፍ እየኮመኮምኩ ፅሁፎቹ ጣፍጠው ምላሴን ከረሜላ እንደበላ ሰው "ጣ"! እያልኩ እያነበብኩ ነው ። በጣም! ከጣፈጠኝና ለብቻዬ ከማጣጥም ለናንተም ይቺን ቅንጫቢ ላስኮምኩማቹ ወደድኩ :-
➥ አንድ ቀን የእስራኤል ልጆች ወደ ሙሴ ተሰብስበው መጥተው እግዚአብሔርን እራት ሊጋብዙት እንደሚፈልጉና ይኼንኑም እንዲነግርላቸው ሙሴን ጠየቁት ። በዚህ የድፍረት ጥያቄ የሙሴ ቁጣ ነደደ ። "እግዚአብሔር የሰውን ምግብ አይመገብም ፤ ወደ እናንተ የራት ግብዣም አይመጣም " አላቸው ። የእስራኤል ልጆችም እያዘኑ ተመለሱ ። በነጋታው ምሽት ላይ ሙሴም እንደለመደው ከእግዚአብሔር ጋር ሊነጋገር ወደ ተራራ ወጣ ። ወደ ተራራው ጫፍ ላይ ሲደርስ እግዚአብሔር ቁሟል ።
እግዚአብሔርም " ባሪያዎቼ የእራት ግብዣ አድርገውልኝ ለምንድነው አሳፍረህ የመለስክብኝ ..." በማለት በሀዘኔታ ጠየቀው ። ሙሴም " ጌታ ሆይ የሰው ምግብ አትበላም ብዬ ነበር ። እንዲህ አይነቱን የሞኝ ግብዣም አትቀበልም የሚል እምነት አድሮብኝ ነው ..." አለ ። እግዚአብሔርም አዘዘው " ሂድና ለህዝቤ ንገረው ። ነገ ማታ ለእራት እመጣለሁ ፤ ግብዣውንም ተቀብያለሁ ..."።
ሙሴም በለሊት ወደ ህዝቡ ተመልሶ እግዚአብሔር የእራት ግብዣቸውን እንደተቀበለ አበሰራቸው ። " ማታ እራት ከእናንተ ጋር ነኝ ተዘጋጁ ብሏል " አላቸው ። ህዝቡም ድግሱን ማዘጋጀት ጀመሩ ። በእስራኤል ምድር ታላቅ የተባለው ግብዣም ተዘጋጅቶ መሰናዶው ወደ መጠናቀቁ በተቃረበበት ሰዓት አንድ በረሃብ የከሳና የጠወለገ ሽማግሌ ድንገት ወደ ድንኳኑ ደጃፍ ተጠግቶ " እባካቹ ተርቤአለሁ ... ከድግሱ የምበላውን ትንሽ ስጡኝ " በማለት ልመና አቀረበ ። ህዝቡ ግን እያዳፉና እየጮሁ አስወጡት ... " እኛ የደገስነው ከእግዚአብሔር ጋር ለመብላት ነው ..." በማለት አባረሩት ።
የዚያን ቀን ማታ እግዚአብሔር ሳይመጣ ቀረ ። ሙሴም እጅግ አፈረ ፤ ብዙዎቹም ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሬ መጣሁ የሚለን ውሸት በማለት ጠረጠሩት ። በነጋታው ምሽት ላይ ሙሴ በሲናይ ተራራ ወጥቶ እግዚአብሔርን መጠበቅ ጀመረ ። እግዚአብሔርም በሰዓቱ መጣ ። ሙሴም በሐዘን " ጌታ ሆይ የራት ግብዣቸውን እንደተቀበልክ ለህዝብህ ነግሬ ነበረ አንተ ግን ቀርተኽ አሳፈርኸኝ ..." አለ ። እግዚአብሔርም " ሙሴ በራት ግብዣችሁ ላይ ቀድሜ ነበር የተገኘሁት ነገር ግን ገፍትራቹ አባረራችሁኝ " አለ ። ሙሴም :- " እኛ ያባረርነው ደሃ ሽማግሌ ነው ፤ ሌላ ያባረርነው ሰው የለም " አለው ። እግዚአብሔርም ጠየቀው " ያን ደሃ ሽማግሌስ ማን ፈጠረው ?" ሙሴም " አንተ ነህ ጌታ ሆይ !" በማለት መለሰ። ይኸን ግዜ እግዚአብሔር :- " ታዲያ በፈጠርኩት ውስጥ መኖሬን ትጠራጠራለህ ?" አለው ። ሙሴም አላስተባበለም ። ከታናናሾቹ ለአንዱ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት እቆጥረዋለሁ እንደማለት ነው ።
✍Henokዛሬ ደግሞ እስቲ ስለ Hercules እናወራለን :-
Hercules / Heracles በግሪክ እና በሮማ history ላይ የታወቀ ታላቅና ኃይለኛ ጀግና ነው ። Hercules የአማልክት ንጉስ ዙስ ልጅ ነበረ ። so ከሰዎች ሁሉ በላይ ኃይል ነበረው ።
እሱ አስደናቂ ጦርነቶችንና ጀብዶችን ይሰራ ነበረ በወሬና በቃል ደረጃ ትዕዛዝ መስጠት ሳይሆን በተግባር ፊት ይመራ ነበር ።
ሄርክለስ እጅግ ከባድ የሚባሉትን ነገሮች እንዲሰራ ይጠየቅ ነበረ ለምሳሌ :- አንበሳ መግደል ፣ አስፈሪ የሚባሉትን እንስሳቶችን በነፍስ መቆጣጠር ፣ ከባባድ ተግባሮችን መፈፀም ፣ ሃይድራ መግደል ይሄ ማለት ብዙ ራስ ያሉትን እባቦች አንድባንድ መግደል ፣ የወርቅ እግር ያለው አጋዘን መያዝ ፣ የኤሪማንቶስን አሳማ መያዝ .... ብዙ ጀብዶችን የሰራ ታላቅ ሰው ነው ።
ሄርክለስ አባቱ አምላክ ( ዙስ ) እናቱ ደግሞ የሰው ልጅ ናት ስለዚህ ሄርክለስ ግማሽ አምላክ / ግማሽ ሰው ነበር (demigod ) ይባላል ። ስለ ሄርክለስ በትንሹ ይህን ብያለሁ በቀጣይ ስለ አባቱ ዙስ እነግራችኋለሁ
✍ Henokንቀት ( scorn )
ንቀት ማለት ሌላው ሰው እንደ አንተ እኩል መብት ወይም እሴት አለው የሚባለውን ነገር መከላከል ነው ። ነገር ግን ንቀት ክፉ ነገር ነው ። በውስጠኛው አስተሳሰብ ታስቦ ወደ ውጨኛው ወይም የባህሪ መቀያየርን የሚያመጣ ነገር ነው ።
የውስጥ ባህሪ ያልኩት ሰው ሲናቅ ብዙ ነገሮችን ያስባል ። ለምሳሌ :- " እኔ ከእርሱ እበልጣለሁ " ፣ " ይሄ ለእርሱ አይገባውም " ፣ " ለምን እሱን ብቻ ይወዱታል " ፣ " ማን ስለሆነ " ፣ " እሱ ትንሽና ደካማ ነው " " ይሄ የሚያሳየው ትክክለኛ ክብርን አሳልፎ የራስን ክብርና ዝና ማስጨመር ነው ።
የውጨኛው ደግሞ :- በአሽሙር መሳደብ ፣ መቀለድ ወይም ማሾፍ ( mocking ) ፣ አስቀያሚ የሆነ facial expression ማሳየት ፣ እየተናገረ በመሃል ማቋረጥ .... ። እነዚህ በውጨኛው ባህሪ የሚታይ የንቀት ምልክት ነው ።
Freiderich Neitzsche ንቀትን " ደካማ ስሜት " ይለዋል ይህን ለማለት የፈለገው ሰው ራሱን ሲክብና ሲያተልቅ ሌላን ሰው ያሳንሳል ። አንዳንድ ሰው የራሱን ድክመት የሚሸፍን ሌላውን በመናቅ ወይም በማሳነስ የራሱን ዋጋ ይጨምራል so ይሄ ደሞ የሚያሳየው የስሜትን ደካማነት ነው ።
Arthur Schopenhauer ደግሞ ንቀትን እንደ እውነተኛ ጥላቻ ይመለከታል ። ንቀት በ Arthur እይታ ሰው ሁኖ ሰዎችን የሚንቅ ሰው ክፉም አይደለም መጥፎም አይደለም ግን ትክክለኛ ጠላት ነው ይላል ።
✍ HenokPandora
ፓንዶራ የሚለው ቃል የመጣው ከግሪክ ታሪክ Mythology የመጣ ነው ። ፓንዶራ የሚለው ቃል በብዙ ሁኔታ የሚገለፅ ቢሆንም ቃሉ ከምን እንደመጣ እነግራችኋለሁ ።
Pandora መጀመሪያ ሴት ነበረች ማለትም ተራ የሰው ልጅ ነበረች ተብሎ ይታሰብ ነበረ ። አማልክቶች ሁሎችም ስጦታ ስለሰጧት" Pandora " ተብላ ተጠራች ። pandora ማለት ( ሁሉን ስጦታ ያገኘች ማለት ነው ።)
እሷን አንድ ሳጥን እንዳትከፍት ተነግሯት ነበረ ። እሷ ግን" እምቢ " ብላ ከፈተችው ። በዚያ ሳጥን ውስጥ ያሉ ነገሮች ክፉ ነበሩ። ( ህመም ፣ መከራ ፣ ሞት ፣ ጨለማ ... ) በውስጡ ይዞ ነበረ ግና እሷ ስትከፍተው እነዚያ ክፉ ነገሮች ወደ ዓለም መጡ ። እነዚህ ሁሉ ከወጡ በኋላ ሳጥኑ ውስጥ የቀረው #ተስፋ ብቻ ነበር ።
ከዚያ ግዜ በኋላ ያንን ሳጥን " Pandora's box " በማለት መጠራት ተጀመረ ። ምን አልባትአሁንም ሰዎች ስለ pandora box ሲያወሩ ግራ እንዳይገባቹ ቃሉን ዛሬም ድረስ ሰው ይጠቀማል ። pandora box ዛሬም የሚጠቅመንና የሚያስተምረን ነገር :- ለመክፈት ቀላል የሆነ ግና ለመመለስ የማይቻል ነገር ፣ ለመግባት ቀላል የሆነ ግና ለመውጣት ከባድ የሆነ ፣ ነገሩን ከስሩ ሳናረጋግጥ የምንወስነው ውሳኔ ህይወታችንን ፍዳ ሲያበላው ፣ መጀመሪያ ላይ ለማድረግ ቀላል ሁኖ በመጨረሻ መመለስ ማይቻል ከሆነ Pandora's box እንላለን ።
✍ Henokየመንጋ እሳቤን ለመቅረፍ የምመክራቹ ነገር ቢኖር Dark Psychology መፅሐፍ አነፍንፎ ማንበብ ነው። እናም እነዚህን avoid ለማድረግ የሚረዱትን ግንዛቤ ( awarness) አሳያችኋለሁ :-
1 ( School proof ) የሚባለው :- ጓደኛ ፣ ወንድም ፣ ወይም የሆነ ታዋቂ ሰው በመመልከት እነሱ በሚወስኑት ዉሳኔ ጥገኛ ሁኖ የሚኖር ማለት ነው ። በአጭሩ ሌሎችን በመመልከት የሚወሰን ውሳኔ ይህ ደግሞ በራስ መተማመንን እንደ ብል ምጥጥ አድርጎ ይበላል ።
2 ( Social media ) አንድ ሰው በማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅምም ይሁን የማይጠቅም ነገር post አድርጎ ብዙ view ካገኘ " ብዙ ሰው ስላየው ምርጥ ነው " ብለን እንወስናለን ። ይህ ጥሩ አይደለም አሪፍ ነገር post አረገ ወይም የሚያስጠላ ነገር post አረገ ለማለት አእምሯችን እንዲያስብ postun በራሳችን እንገምግመው ። ኣእምሯችን ይንቀሳቀስ !።
3 ( investment ) አንድን ነገር ስንገዛ ሌላ ሰው የገዛውን ወይም በሌላ ሰው ላይ የሚያምርበትን ነገር አንግዛ ። በራሳችን እንወስን ። ምን ዓይነት ልብስ እንደሚሆነን አውቀን decide እናድርግ ።
ጠቅለል ሳረገው የመንጋ እሳቤ ሁሉ በሮጠበት አትሩጥ ከፊት ለፊት ገደል ሊኖር ስለሚችል ቆም ብለህ አስብ ። በመንጋ እሳቤ ምትመራ ከሆነ የህይወትህን መሪ ሌላ ሰው ነው ሚቆጣጠረው ። Gustave Le Bon ያለውን አስታውስ እሱ እንዲ ይላል " ሰው በቡድን ውስጥ ሲገባ የራሱን አእምሮ ያጣል " ።
✍ Henok
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
