uk
Feedback
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Відкрити в Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Показати більше
2 636
Підписники
+324 години
+187 днів
+5730 день
Архів дописів
ምስጋና ዘፍኖተ ብርሃን የከተራ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓል  በሰላም አክብረን አጠናቀናል !!! ተመስገን     ከሁሉ  አስቀድሞ ለአምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር አምልኮ እና ውዳሴ ይድረስው እናታችን ድንግል ማርያም አሳዳጊያችን እና ጠባቂያችን ቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ይድረሳችሁ !! የሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ ህጻናት (የነገ ተስፍዎች) ማዕከላውያን (ተረካቢዎቻችን) ወጣቶች ( የሰ/ቤቱ ጠበቃዎች) የባለ ትዳር ጉባኤ አባላት ( ጥላዎቻችን )ልዪ ልዪ የአገልግሎት ክፍላት ልብሰ ስብሐት  ልዪ ልዪ አገልግሎት ላይ የተሳተፋችሁ  አባላት  ለእህት ሰ/ት/ቤታችን ለደብረ አሚን ተክለ ሀይማኖት መካዕ ደናግል  ሰንበት ት/ቤት ለደብራችን አገልጋዪች በጠቅላላ ለልዪ ልዪ የጊቢያችን ማህበራት ለምንወዳችሁ እና ለምናከብራችሁ በሶስቱም መውጫ በር ላይ ላላችሁ የአካባቢው ወጣቶች ለል/ክ/ከ ለወረዳ 07 አስተዳደር እና ለጸጥታ ክፍል ስራተኞች በሙሉ ጊዜያችሁን ጉልበታችሁን ሳትሰስቱ እና ሳትቆጥቡ ስትሰጡ ለበዓሉ ድምቀት ለሆናችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት በሙሉ  ዋጋ ከፋይ አስራት ተቀባይ  የለመነቱን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸሩ አምላካችን ዋጋቹሁን ይክፈላችሁ !! ከዓይን ጥቅሻ ይልቅ ፈጥና የምትደርስ እመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማርያም በህይወታችሁ በቤታችሁ ትግባ ስሙ ሲጠራ ልባችን ወከከ እግራችን ሸብረክ የሚለው ጠባቂያችን  ቅዱስ ሚካኤል ከልጅነታችን እስከ ሽምግልናችን በጥባቆቱ አይለየን ከቁጥር ሳያጎድለን አምና ብለን ለማውጋት ያብቃን !! እንዲህ ማማራችን እና መዋባችን በእርሷ ነውና  ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅል !! ሀገራችንን በሰላም እና በፍቅር በአንድነቷ አጽንቶ ያቆይልን የዓመት ሰው ይበለን!!!   ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ከተማ ከጽዮን ልጆች ጋራ መዝሙራችን እንዲሰማ አንድ ሆነን በቀኝ እንድንቆም ከበኩራት ማኅበር ጋራ አንድ ሆንን ዛሬ እናገልገል አንድ ሆነን ዛሬ እንስራ።               ጥር 12/2016ዓ.ም    የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ /ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ          የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት               ጽሕፈት ቤት ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1