ዴር ቶ ጋዳ DERTOGADA
Відкрити в Telegram
ዴር ቶ ጋዳ የመጽሃፍት መደብር። ከተለያዩ የመጽሃፍት መደብሮች የተሠበሠቡ። በድምጽና በጽሁፉ የቀረቡ። አጠር ቀልጠፍ ብሎ የተደረደረ። ማንኛውንም ሠው ያካተተ። ሀሳብ አስተያይት ካለ በዚህ ማውራት ይችላሉ @hassefa ሊንክ https://t.me/joinchat/S15DMRd3cx2ajJAE
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
681
Підписники
-124 години
-27 днів
+930 днів
Архів дописів
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም" ▰ ሉቃ 24፥5 ▰ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። መልካም በዓል 🙏🙏🙏
Repost from Book club
✍ደራሲ ፀጋየ ገብረ መድህን
እሳት ወይ አበባ
...
ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፥
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም...ዝም፡፡
አበባ አንሆን ወይም እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መአት
እድሜአችንን እንዳማጥናት...
እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ-እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን፥ እየቃተትን ስናነባ፡፡ ...
ፈራን፤ አዎን ፍቅር ፈራን፥
የነፍስን አንደበት ዘጋን፥
የእድሜ ጠብታችንን ምጥ፥ የጣር ፅንሳችንን ልሣን፥
ልጅነት የለገሠንን
በመለኮት የቀባንን
በእሳቱ ያጠመቀንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ፥ በሥልጣን ያላበሰንን
ፈራን፥ አዎን እውነት ፈራን
የስሜት እስትንፋስ ነሳን፡፡ ...
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድን
https://t.me/EthioBooksclub
