cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

መንፈሳዊ መንገድ

"ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ራስህን አዛምድ" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ -የተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች -የተለያዩ መንፈሳዊ መፅሐፍት - የተለያዩ መንፈሳዊ ስዕሎችን እና ፎቶዎች - የተለያዩ የአባቶችን ምክር እና ትምህርት የተከፈተ መንፈሳዊ ቻናል

Більше
Рекламні дописи
201
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የመሐረነ አብ ጸሎት @gitsawei ስለ ቤተ ክርስትያን ሰላም ተግተን እንጸልይ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ... የቤተክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ መሰረት ያደረገ እና ሲኖዶሳዊ እውቅና ያለው ነው " - የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ አትሌት ደራርቱ ቱሉ መፈንቅለ ሲኖዶስ የፈጸሙና ከቤተክርስቲያን ተወግዘው የተለዩ ወገኖች ጥፋታቸውን አምነውና ተጸጽተው እንዲመለሱ ለማድረግ የሽምግልና ጥረት እያደረገች ትገኛለች ስትል አሳወቀች። አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፤ የምታደርገው ጥረት የቤተክርስቲያንን ቀኖናና ዶግማ መሰረት ያደረገና ሲኖዶሳዊ እውቅና ያለው መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ገልፃለች። @tikvahethiopia
Показати все...
ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም" እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም። "ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው"  (2 ዜና 30: 19) የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸሩ መድኃኔዓለም ለኛም ለህዝባችንም በምህረትና ቸርነቱን  ይጎብኘን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን 🙏   
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
" ወደ ስፍራውም ደርሶ። ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 22:40) ❤ @gitsawei " ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 22:46) @gitsawei
Показати все...
ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡ በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡ በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።
Показати все...
ስለ ቤተ ክርስትያን ሰላም ተግተን እንጸልይ 💔😥💔😥💔😥 ትኩረት የሚፈልግ ነገር ለሦስት ቀን ነነዌ ላይ እንድናደርገው የታዘዝነው የሐዘንና የሱባኤ ልብስ በንስሐ እና በዕንባ ሆነን የእግዚአብሔርን መልስ ለማግኘት ነው። አስተውሉ የዐለም መንግሥታት እንዲያዩን ሳይሆን የዐለም ፈጣሪ እንዲያየን እና እንዲሰማን ነው። ለአክቲቪዝም ፣ ለፕሮፓጋንዳ እና ለብሽሽቅ ሳይሆን ልብን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ እና ከእርሱ እርዳታን አግኝተን ቶሎ ወደ አንደንታችን ለመመለስ ነው። ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትኩረት የሚፈልግ ነገር ለሦስት ቀን ነነዌ ላይ እንድናደርገው የታዘዝነው የሐዘንና የሱባኤ ልብስ በንስሐ እና በዕንባ ሆነን የእግዚአብሔርን መልስ ለማግኘት ነው። አስተውሉ የዐለም መንግሥታት እንዲያዩን ሳይሆን የዐለም ፈጣሪ እንዲያየን እና እንዲሰማን ነው። ለአክቲቪዝም ፣ ለፕሮፓጋንዳ እና ለብሽሽቅ ሳይሆን ልብን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ እና ከእርሱ እርዳታን አግኝተን ቶሎ ወደ አንደንታችን ለመመለስ ነው። ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ❤️ @gitsawei መልካም ሰንበት እናስተውል
Показати все...
(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2) ---------- 36፤ ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤ 37፤ እርስዋም ሰማኒያ አራት ዓመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር። 38፤ በዚያችም ሰዓት ቀርባ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም ቤዛ ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ እርሱ ትናገር ነበር። 39፤ ሁሉንም እንደ ጌታ ሕግ ከፈጸሙ በኋላ፥ ወደ ገሊላ ወደ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ። 40፤ ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ። 41፤ ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። 42፤ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ❤ @gitsawei ወንጌል ዘሰንበተ ክርስትያን ቅድስት @gitsawei ጥር ፳፰||28 @gitsawei መልካም ሰንበት
Показати все...
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5) ---------- 1፤ ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ 2፤ አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ። 3፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። 4፤ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። 5፤ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና። 6፤ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። 7፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና። 8፤ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና። 9፤ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። 10፤ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። 11፤ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። 12፤ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና። 13፤ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። 14፤ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። 15፤ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። 16፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። 17፤ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። ❤ @gitsawei የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ዘነግህ @gitsawei ጥር ፳፬||24 @gitsawei መልካም ቀን
Показати все...