cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ማኅሌት ሚዲያ

ወደ ማኅሌት ሚዲያ እንኳን በሰላም መጡ፡፡ በዚህ ቻናል የተለያዩ መንፈሳዊ ስብከቶች እና ተከታታይ ትምህርቶች እንዲሁም የመንፈሳዊ መጻሕፍት ዳሰሳዎች ፣ አጫጭር የቤተ-ክርስቲያን አስተምሮዎች እና ዝማሬዎች ይቀርቡበታል፡፡የቻናሉን ይዘቶች ለሌሎች በማጋራትበማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ፡፡

Більше
Рекламні дописи
2 162
Підписники
Немає даних24 години
-67 днів
-1830 днів
Архів дописів
Показати все...
👍 1
Repost from @ነቅዐጥበብ
ይህ ከታች የተያያዘው ምስል የአንድ አክተር (ተዋናይ) ፎቶ እንጂ የጌታችን ሥዕለ አድኅኖ አይደለም!!! በተቻለ መጠን ቅዱሳት ሥዕላትን መጠቀም ያስፈልጋል አባቶቻችን በቅዱሳት ሥዕላት ላይ ያላቸው ጥንቃቄ አስገራሚ ነው! በቅዱሳት ሥዕላት በኩል • ሃይማኖት • ትምህርት • ምድራዊና ሰማያዊ ምሥጢራት • በረከት • ታሪክ ይተላለፉባቸዋል ስለሆነም ስለ ጌታችን ሕማም ስለ ስቅለቱ ስንጽፍ ይህንን ፎቶ ባንጠቀምና በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ቅዱሳት ሥዕላትን ብንጠቀም ለማለት እወዳለሁ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8
Показати все...
👍 3 1
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ፍቅረ ኢየሱስ(ብንያም)ሌላ እህት ማርኮ በማምጣት አስጠመቀ::ሙሉን መረጃ በነገው ጉባኤ ላይ እንገልጠዋለን::ድል ለተዋህዶ::
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መምህር ካሣሁን እንግዳ በአድዋ ጦርነት ጊዜ የአራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ተሸክመው በባዶ እግራቸው የዘመቱ አባታችን ናቸው! በረከታቸው ይደርብን! ዓድዋ የዘመቱ ፈረሶችና የተያዙ ቁሳቁሶች ታሪካቸው ተመዝግቦ በሙዝየም ሲቀመጥ ታቦት ተሸክመው የወጡ ካህናት ታሪካቸው ይካተት ማለት ቦታውን የሃይማኖት ተቋም ለማድረግ ሳይሆን ታሪክ መቀነስ ስለሌለበት ነው!
Показати все...
8👍 4
ቅበላ ማለት ክርስቶስን መቀበል እንጂ ስጋን እንደ አንበሳ መቀበል መብላት አይደለም ክርስቶስን የምንቀበልበት ጊዜ ማለት ነው። መልካም ፆም 🙏
Показати все...
አንድ ሰው ውሃ አቅርቦ በራሱ ላይ በማፍሰስ ምሥጢረ ጥምቀትን መፈጸም እንደማይችል ሁሉ ሥርዓተ ጋብቻንም ከቤተ ክርስቲያን ውጪ መፈጸም አይችልም ምክንያቱም ከ7ቱ ምሥጢራት አንዱ ጋብቻ ነውና።
Показати все...
👍 2
እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በተጨማሪም ዛሬ የቃና ዘገሊላ ትክክለኛ ዕለቱ ነው እስራኤላውያን ሠርግ የሚደግሱት ለሰባት ቀናት ነው ሠርጉ የተጀመረው የካቲት 20 ነው ጌታ የተገኘው በሦስተኛው ቀን ማለትም የካቲት 23 ቀን ነው አባቶች የካቲት ወር ብዙ ጊዜ ዓብይ ጾም ላይ ስለሚውል የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር አብሮ ማክበር ይገባል ብለው እንድናከብር አድርጓል አንድም በአክሱም ከተማ ጥር 12 ቀን ደጋግ ሰዎች ማኅበር በሚጠጡበት ጌታ በአካል ተገኝቷልና ይህችውም ማኅበረ ደጔ ትባላለች። በእነዚህ ምክንያቶች ጥር 12 ቀን እንዲከበር ተደርጓል። ስለዚህ በሦስተኛው ቀን ሲል ከፊት አራት ቀናት ይቀራሉ ግን በሦስተኛው ቀን ማለቱ በዚህ ቀን ወይኑ ስላለቀ ነው። በቃና መንደር የተደረገው ሠርግ ደጋሹ ዶኪማስ ይባላል ሙሽራው ባቲለስ ሙሽራይቱ ዮአጊን ይባላሉ። ዶኪማስ የእመቤታችን ዘመድ ስለሆነ ጠርቷታል እመቤታችን ሠርጉ ቀድማ ተገኝታለች። ቃና ሠርግ ላይ ውኃ ተሞልቶባቸው የነበሩ ድንጋዮች እብነ አልማስ (የአልማስ ድንጋይ) ይባላሉ። ጌታችን ጋብቻን ለመባረክ ወደ ሠርግ ቤት መጥቷል ግን በቃና ሠርግ ጌታ ደቀመዛሙርቱ ብቻ አልተገኙም መላእክትም ተገኝቷል ግን ስለማይበሉ አልተጻፈም። በዚህ ጊዜ ነው ወይኑ ስላለቀ እመቤታችን ምልጃዋ የተገለጠበት ጌታችንም አምላክነቱን ያሳየበት ነው ጌታችን ውኃውን ወደ ወይን የቀየረበት የወይኑም ጣዕም እጅግ በጣም ለየት ያለና ቃና የሚለው ቃል ጣዕምን የሚገልጽ ቃል የሆነበት ነው።
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ለመንፈሳዊ ዩቲዩብ ቻናል (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ጋዜጠኛ ይፈለጋል መንፈሳዊ ትረካዎችን ቃለ መጠይቆችንና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶችን የመስራት በቂ ጊዜና ችሎታው ያላችሁ በተከታዮቹ አድራሻዎች አግኙን ደሞዝ በስምምነት ስልክ:- +251965135434 Telegram:-  @JOEth86
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Показати все...
ሰላም ወዳጆቼ!!! የአበውን አጫጫር አባባሎችን የምትሹ " አንጋረ አበው " የተሰኘ ገጼን ላስተዋውቃችሁ ። አንጋረ አበው ማለት የአባቶች ንግግሮች ማለት ነው ። በዚህ መንፈሳዊ channel የቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ብሒላቸው ይተላለፋል ። እኛም አባቶቻችንን በቃላቸው እንዘክራቸዋለን ። https://t.me/angare_abew
Показати все...
Показати все...
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ መልካም የመስቀል በአል❤️
Показати все...
ደመራ የምትሠሩ ሰዎች እባካችሁን ጫፉ ላይ መስቀል አታድርጉ::  መስቀልን መስቀል በማቃጠል አናከብርም:: (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
Показати все...
Показати все...
Показати все...
፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨፨፨ ፨፨ ፨፨ ፨፨ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ የዚህን ዓለም ጣዕም በመናቅ ....  ‹‹ሞት   ቢሆን፣  ሕይወትም  ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣  ግዛትም ቢሆን፣  ያለውም ቢሆን፣  የሚመጣውም  ቢሆን፣ ኃይላትም ቢሆኑ፣  ከፍታም ቢሆን፣  ዝቅታም ቢሆን፣  ልዩ ፍጥረትም  ቢሆን  በክርስቶስ  ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ››  በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በተግባር በማሳየት ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ ራሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን እስኪፈጽሙ ድረስም ቅዱስ ገብርኤል አልተለያቸውም፡፡ በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ምእመናንም ተጠቅመዋል፡፡ ስሙ በሚጠራባቸው ገዳማትና አድባራት መልአኩ የሚያደርጋቸው ድንቅ ድንቅ ተአምራት ለዚህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ይህም ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ስም መከራ የሚቀበሉ ምእመናንን እንደሚጠብቁና ከልዩ ልዩ ደዌ እንደሚፈውሱ የሚያስረዳ ታሪክ ነው፡፡ (ሮሜ. ፰፥፴፰-፴፱) ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን የተራዳው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ እንዲጠብቀን  ‹‹በተአምኖ ንሴፎ ትንባሌ ዚአከ መዓልተ ወሌሊተ፤ በእግዚአብሔር ታምነን በቀንም በሌሊትም የአንተን ልመና ተስፋ እናደርጋለን››  እያልን ዘወትር ልንማጸነው ያስፈልጋል፡፡ እርሱ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ከሚደርስብን ልዩ ልዩ መከራና ሥቃይ ያድነናልና፡፡  ‹‹የእግዚአብሔር  መልአክ  በሚፈሩት  ሰዎች  ዙርያ  ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፴፬፥፯)፡፡ የቅዱስ ገብርኤል፣ የቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ ጸሎታቸው፣ ምልጃቸው ይጠብቀን፡፡
Показати все...
Показати все...
Показати все...
👍 1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ2ዙር የመጨረሻ ምዝገባ ዛሬና ነገ (25/26) ሲሆን ከ27 ጀምሮ የመማርያ ቻናሉ ማንንም የማይቀበል ይሆናል ። ስለዚህ ላልሰሙ እህት ወንድሞቻችሁ ሊንኩን በማጋራት እንዲመዘገቡ አሳውቋቸው ። 👉  t.me/bahire_hasab2  👈
Показати все...
➕➕➕ ጳጉሜን በባሕረ ሐሳብ ➕➕➕ ✍ የሰው ልጅ ሕይወት ከጊዜ ጋር በእጅጉ የተቈራኘ ፍጥረት ነው፡፡ እያንዳንዱ ማኅበረሰብም የራሱ የሆነና ይህን ከሕይወቱ ጋር የተቈራኘውን ጊዜ የሚቀምርበት የዘመን አቈጣጠር አለው፡፡ ኢትዮጵያም የራሷ የሆነ ሐሳበ ዘመን ማለትም የዘመን አቈጣጠር አላት፡፡ ይህ የዘመን አቈጣጠር (ሐሳበ ዘመን) የዘመናት፣ የዓመታት፣ የወራት፣ የሳምንታት፣ የዕለታት፣ የሰዓታት፣ የደቂቃዎች፣ የቅጽበትና (የካልዒትና) የመሳሰሉት ጊዜያት በሐሳብ የሚመዘኑበት፣ የሚሰፈሩበት፣ የሚቈጠሩበት ምድብና ቀመር ተሰጥቶአቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ እያሰማ የሚጠራበት ትምህርታዊ ውሳኔ ነው፡፡ ✍ ነገር ግን ከግእዝ ቋንቋ በመቀጠል በጣም አስጊ ሁኔታ ላይ ከደረሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ትምህርቶች መካከል አንዱ ይህ ጥንታዊው የባሕረ ሐሳብ ትምህርት ነው ። ለዚህም አንዱ ምክንያት በደፈናው " ትምህርቱ ይከብዳል " የሚል ትውልዱን የሚያሰንፍ ብሂል ነው ። ትምህርቱ ጥልቀት ያለው ቢሆንም ትንሽ ጊዜ ሰጥቶ ለተማረውና ለተረዳው ግን እጅግ በጣም ደስ የሚልና ቀላል ትምህርት ነው ። ✍ ስለዚህ በጥቂቱም ቢሆን በዓላትን ፣ አጿማትን ፣ ዕለታትን በቀላሉ ማውጣት እንችል ዘንድ ዘመኑን በዋጀ ፣ ቀለል ባለና ማራኪ አቀራረብ ትምህርቱን በቴሌግራም ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል ። ነሐሴ 27 ምሽት 3:30 ይጀመራል። ቻናሉን በመቀላቀላ ብቻ መዝገቡ ! 👉 t.me/bahire_hasab2 👈
Показати все...
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌷እንኳን አደረሳችሁ!!! ===================            ✨ሚካኤል አባቴ            ✨ሚካኤል ወዳጄ            ✨ሚካኤል ሞገሴ            ✨ትልሀለች ነፍሴ!! የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት፣ በረከት፣ ጥበቃና ምልጃው አይለየን ሕዝባችንን ከመከራ ሀገራችንን ከጥፋት ይታደግልን💚💛❤️
Показати все...
Показати все...
Показати все...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው? ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ማረግ፣ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። በእዚህ መሠረትም ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን የሥጋዋ ከመቃብር መለየት እና ማረግን ያመለክታል። ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ውስጥ ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው። ፍልሰታ ጾም ለምን እንፆማለን? የፍልሰታ ጾም ከነሐሴ 1 እስከ 15 የሚጾም ሲሆን በቤተ ክርስቲያናችን አስተምሮ መሠረት እመቤታችን ያረፈችው በጥር 21 ቀን ነው። ሐዋርያትም አስከሬኗን ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ በምቀኝነት ልጇ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል። አሁንም እርሷ ገቢረ ተአምር ልታደርግ አይደል? ብለው አስከሬኗን ተሸክመው የሚሔዱትን ሐዋርያትን በታተኗቸው። በዚህን ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስከሬን ከአይሁድ ነጥቀው በገነት አኖሩት። በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ገብተው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት። በዚህ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ የተባለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበር እና መገኘት አልቻለም ነበር። እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ከላይ እንደተጠቀሰው በነቢያት ትንቢት እንደተነገረላት እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት በረከት ቀረብኝ ሲል ተበሳጨ።ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ እራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። በዚህን ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናናችው ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነገረችው።ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች። ሞት በጥር፣በነሐሴ መቃብር ቶማስም ሰበኗን ደብቆ ይዞ ሐዋርያት ካሉበት ደረሰ። ሐዋርያትንም የእመቤታችን ነገር ምን ደረሰ? አላቸው። ሐዋርያትም እመቤታችን ሱባዔ ገብተን ጌታችን አስከሬኗን ከዕፀ ሕይወት አምጥቶ ሰጥቶን በክብር ቀበርናት አሉት። ቶማስም መልሶ ሞት በጥር፣በነሐሴመቃብር?አላቸው።ሐዋርያትም መለሱለት ቶማስ አትጠራጠር። ቀድሞ ጌታችን በተገለጠ ጊዜ ትንሣኤውን ጣቶቼን በተቸነከሩ እጆችህ ካላስገባሁ ብለህ የደረሰብህን ታውቃለህ አሁንም የእመቤታችንን መቀበር አላመንክምን? አሉት። ቶማስ ግን ሐዋርያትን ይዞ ወደ መቃብሯ ሔደ። መቃብሯን ከፍተው ሲመለከቱ ሐዋርያት ደነገጡ። በዚህን ጊዜ ቶማስ አታምኑኝም ብየ ነው እንጂ እመቤታችን አርጋለች። ስታርግም በደመና ከሀገረ ስብከቴ ስመጣ ተገናኘን ለምልክቱም ይኸው የቀበራችሁበት ሰበን አላቸው።ሐዋርያትም ለበረከት ሰበኗን ተከፋፍለው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሔዱ። በዓመቱ ግን ሐዋርያት ተሰበሰቡ እና ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ።በነሐሴ 14 አስከሬኗን ትኩስ በድን አድርጎ አምጥቶ ሰጥቷቸው ከቀበሯት በኋላ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 እመቤታችን ተነሥታ ጌታችን ከመላእክት እና ቅዱሳን ጋር ሆኖ ሐዋርያትን አቁርቧቸዋል።(ውዳሴ ማርያም ትርጉም)። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ እና ሐዋርያት መሠረት ላይ የታነፀችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያትን ግብር ምሳሌ በማድረግ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሐዋርያት የተገለጠ በረከት እና የእመቤታችን ረድኤት እንዲያድርብን እንጾመዋለን።በቤተ ክርስቲያናችን ከአምስቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከልም በመሆኑም ሁሉም ምእመናን እንዲጾም ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች። ነቢዩ ዳንኤል በትንቢተ ዳንኤል ምዕ 10፣21 ላይ እንደተጠቀሰው ”በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ።ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።” እንዳለ ጾሙን ከፅሉላት ምግቦች ከሥጋ እና ወተት ውጤቶች በመጾም እና ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሔድ፣በስግደት፣በምፅዋት እና በጾሎት ይጾሙታል።
Показати все...