cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

Більше
Рекламні дописи
6 275
Підписники
Немає даних24 години
+87 днів
+24130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ከትንሣኤ_እስከ_ዕርገት የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የጌታችን መዋዕለ ሥጋዌ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦ 1. ቅድመ መስቀል፦ ቅድመ መስቀል የምንለው 33 ዓመት ከ 3ወሩን ነው፤ ይህ ጊዜ ኃጢአት ያልሆነ ማንኛውም ነገር በክርስቶስ የተከናወነበት ልዩ ጊዜ ነው፡፡ 2. ጊዜ መስቀል፦ በመስቀል/በጽኑ ስቃይ የቆየበት ሰዓት 3. ድኅረ መስቀል፦ ድኅረ መስቀል የምንለው ደግሞ በአካለ ሥጋ ከመስቀል ወደ መቃብር ፤ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ከሄደበት ቅጽበት ወዲህ ያለውንና 40ዎቹን ቀናት ወይም 1 ወር ከ10 ቀናትን ነው፡፡ *(ከዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ ያሉትን 10 ቀናት ለብቻ እናያቸዋለን)* ✝ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኀላ 40 ቀን በዚህ ምድር ቆይቷል ፡፡ በነዚህ ቀናት ውስጥም በዋናነት 2 ዋና ዋና ሥራዎችን እንደሠራ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ 1. ለሐዋርያት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እና መጽሐፈ ኪዳንን ማስተማር፦ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጉባኤ የተገለጠላቸው 3 ቀናት ቢሆንም ለእያንዳንዳቸው ለየብቻም 2 ወይም 3 ሆነው ግን ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ አልነበረም፡፡ "ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው" እንዲል ሉቃስ ፤ሐዋ 1 : 3፡፡ በተገለጠላቸውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዴትና በምን በማን መተዳደር እንዳለባት አስተምሯቸዋል፡፡ ለምሳሌ ፦ " እርሱም። መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው" ፤ ዮሐ 21 :6 ፤ በማለት ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው መረቡ በቀኝ እንዲጣል ማዘዙ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሁሉ በቀኝ በክብርና በፍቅር እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ ሐዋርያት "እንደቃልህ እናደርጋለን" ብለው እንደ ቃሉ መሠረት ማድረጋቸው ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የምትፈጽመው ሥርዓት ሁሉ መሠረቱ የጌታ ቃል እንደሆነ ይህም በማመን የሚፈጸም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ዓሣዎቹም በየጊዜው የሚያምኑ የሚጠመቁ ምእመናን ምሳሌዎች ናቸው፤ ቀጥሎ በተዘጋጀው ማእድ በአንድነት መመገባቸውም የሁላችን ማእድ የሚሆነውን ከመላእክት ጋር የምናመሰግነውን የምስጋናችንን አንድነት ያመለክታል፦ " ወደ ምድርም በወጡ ጊዜ ፍምና ዓሣ በላዩ ተቀምጦ እንጀራም አዩ"፤እንዲል ዮሐ 21 : 9፡፡ ይህንም ማእድ መላእክት እንዳዘጋጁት መተርጉማነ ሐዲስ ገልጸዋል፦ ትርጉሙ ኅብረተ መላእክት ወሰብእ ነው፡፡ "ወኅብስተ መላእክቲሁ በልዑ እጓለ እመ ሕያው"( ሰዎች የመላእክትን ምግብ በሉ) የሚለው ትንቢተ ዳዊት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜው በዚህ ፍጻሜውን አግኝቷል፤ መዝ 77፡25፡፡ በዓለም መጨረሻም የሚሆነው ይኸው ነው፤ ከመላእክት ጋር ለዘለዓለም ማመስገን!!! ከዚህም ቀጥሎ ደግሞ ለጴጥሮስ በጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነቱን (ክህነትን) አጠንክሮ አደራ ይለዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ ለዚህም መጠበቂያ መመሪያ የሚሆን ጸሎት 7ቱን ኪዳናት አስተምሯቸዋል፡፡ 2. ለነፍሳት አህጉራተ ገነትን ማካፈልና ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ማሳየት/ማስተማር፦ ገነት በ15 አህጉራት እኩል የተከፈለች መሆኗን አበው አስተምረውናል (መጽሐፈ ቀሌምንጦስ)፤ ዓለማችን በሰው ሰራሽ አከፋፈል መሠረት 7 አህጉራት አሏት፤ ገነት ግን የአንዱ አህጉር መጠን ባይታወቅም ቅሉ በ15 አህጉራት የተከፋፈለች ሰፊ መሆኗን ያሳያል፤ ይህች ዓለም የቅጣት ቦታችን ናት (ምድረ ፋይድ/ምድረ ፍዳ) ገነት ግን ጥንተ ርስታችን ናት፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ካወጣ በኀላ ወደ ገነት አሳልፏቸዋል፤ እርሱ ባወቀም ነፍሳት መኖር በሚገባቸው እያመሰገኑ እንዲኖሩ ቦታ ቦታቸውን አስይዟቸዋል፤ ፍጡር ሆኖ ያለ ቦታ መኖር አይቻልምና፡፡ "በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው" እንዲል ቅ.ጴጥሮስ፤ 1ኛ ጴጥ 3 : 19፡፡ ✝ገነት ከገቡ በኀላም ገነት የዘለዓለም መኖሪያቸው እንዳልሆነችና ለዘለዓለም የሚያወርሳቸውን የማታልፈውን የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር አስተምሯቸዋል፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር በዓይነ ሥጋ ማየት፤ በእዝነ ሥጋ መስማት፤ በአእምሮ ጠባዕይ ማወቅ አይቻልም፤ የሚታወቀው በአእምሮ መንፈሳዊ በዓለመ ነፍስ ነውና ለነፍሳት አስተማራቸው፤ ይህም መዓርግ ወይም ደረጃ ነው፤ ምሥጢራትን የምናውቅበት ደረጃ አለ በዓለመ ነፍስ የምንረዳውን በዓለመ ሥጋ አንረዳውም ፦ "ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ፤ እንዳለ ቅ.ጳውሎስ፡፡ 1ኛ ቆሮ13 : 12፡፡ ዳግመኛም፦ "ነገር ግን ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን"፤ ብሏል፡፡ 1ኛ ቆሮ 2 : 9፡፡ እኛም በዚህ በዓለ ሃምሳ ስለ ምሥጢረ ትንሣኤና ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወት አብዝተን የምንማርበትና የምንመረምርበት ሊሆን ይገባል፡፡ 40ዎቹ ቀናት፦ • አዳም ከተፈጠረ በኋላ ገነት ከመግባቱ በፊት 40 ቀን በምድር ቆይቷል፦ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ከዕርገቱ በፊት 40 ቀናትን በዚህ ምድር ቆይቷል፡፡ • የሰው ተስእሎተ መልክዕ በማኅፀን የሚፈጸምለት በ 40 ቀንናት ውስጥ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም የሥርዐቷ ተስእሎተ መልክዕ ተቀርጾ የተጠናቀቀው በ40 ቀናት ነው፡፡ • ሰገኖ እንቁላል ከጣለች በኋላ 40 ቀን ዓይኗን ከአንቁላሉ አትነቅልም፤ ትታው ብትሄድ እንደ ድንጋይ ይደርቅባታል! ጌታችንም ለ40 ቀናት ከቤተክርስቲያን ሐዋርያትን ዓይኑን ሳይነቅል ትክ ብሎ ሲመለከታት ነበር፤ ተለይቷቸው ቢሆን ሐዋርያት በቀቢጸ ተስፋ በደረቁ ነበረና፡፡ (ዛሬም አልተለያትም!) ወነበረ አርብዓ መዋዕለ እንዘ ይሜሕሮሙ ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያት" እንዲል መቅድመ ወንጌል፡፡ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።” እንዲል ሉቃስ — ሐዋርያት 1፥3 ጌታችን 40 ቀናት መቆየቱ እነዚህን ምሥጢራት ያመለክታል፡፡ አምላካችን ምሥጢሩንና ጥበቡን ሁሉ ይግለጥልን!!! ከዕለት እኪት፣ ከዘመን መቅሰፍት ይሠውረን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘቦሌ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን YouTube chanal 👇 https://youtu.be/ajtQIZSCUs4 ከ ኖሮዌይ ትሮንዳሄም
Показати все...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

35👍 12🙏 6👎 1
ይህንን የመሰለ ሕንፃ ቤተ መቅደስ 👇 • መቅደስ ቢኖረውም ይጎበኛል እንጂ አይቀደስበትም • አሁን ምዩዚዬም ነው • ሁሉ ተሟልቶ የተሠራለት ቢሆንም አምልኮ አይፈጸምበትም • መጠመቂያ ቢኖረውም የሚጠመቅበት የለም ምክንያቱም የሀገሩ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ትተዋል ሃይማኖት አልባ ሆነዋል ....ከሃይማኖት ባዶ መሆናቸውን በኩራት ያስጎበኛሉ...የካቴድራሉን ሕንጻ ከአገልግሎት ባዶ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ!!!! እኛም ይህንን አይተን ጎብኝተን ስለ ራሳችን • ሀገር • ሃይማኖት • ቤተ ክርስቲያን • ባህል ...ተነጋግረን ከመቅደሱ ወጣን እኔም ይህንን ቃል አስቤ አዘንኩ 👇 ማቴዎስ 23 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁸ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። ³⁹ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።" 👉እንደ አማኝና አገልጋይ ሁሌም የሚሰማኝ ይህ ነው ! ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ቤተክርስቲያኗን ከነሥርዓቷ በምን ያህል መጠን ይረከባታል? እኛ ስለ ዘርና ስለ ብሔር ስለ ሥልጣንና ሢመት ስለ ገንዘብና ኑሮ ስናስብ ትውልዱን ከእጃችን እየተቀማን ቤተ ክርስቲያንን ዝቅ አድርገን የኛን ልዕልና ብቻ ለማሳየት እየተጋን የት እንደርስ ይሆን?.... የቤተ ክርስቲያን አምላክ ትውልዳችንን በሃይማኖት ያጽናልን ይጠብቅልን ተረካቢ አያሳጣን!!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ከ ኖርዌይ ትሮንዳሂም ግንቦት 5 /2016 ዓ.ም
Показати все...
52😭 26👍 9🔥 6🙏 4😱 2
#እንኳን_ለዳግማይ_ትንሣኤ_አደረሳችሁ! #አግብኦተ_ግብር ፤ #ዳግማይ_ትንሣኤ የቴሌግራም ቻናሌ 👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 "ጊዜው ደረሰ" ዮሐ 17÷1 ✝ዳግማይ ትንሣኤ እና አግብኦተ ግብር፡- ለሐዋርያት በጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት የተገለጠበት ቀን ስለሆነ ዳግማይ ይባላል እንጂ ትንሣኤው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ✝ ዳግማይ ትንሣኤ ከመባሉ በተጨማሪ በሊቃውንት ምሥጢራዊ አጠራር "አግብኦተ ግብር" ይባላል፤ ቀጥታ ትርጉሙ "ሥራን መመለስ" ማለት ነው፤ ምሥጢሩ ግን "ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" ብሎ እንዲያመጣው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥጋ የለበሰበትን ዓላማ በመስቀል የሚያጠናቅቅበት ጊዜው መድረሱን የሚያሳይ ነው፤መስቀሉ ላይ "ተፈጸመ ኩሉ" ብሎ መጮኹም የዚሁ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡ ✝በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ የዮሐንሰ ወንጌል 17÷1-ፍጻሜ ድረስ ሙሉው ይነበባል፡፡ በዓሉ የጸሎተ ሐሙስ ሲሆን በዕለቱ ብዙ የተደራረቡ በዓላት በመኖራቸው ምክንያት "አግብኦተ ግብሩ" ከዳግማይ ትንሣኤ ተደርቦ ይታሰባል፡፡ ✝የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነው፡፡ ✝ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው ይኸውም የመዳን ዘመን ምሕረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን ለማጠየቅ ነው “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤” — ገላትያ 4፥4 አምላካችን ለሁላችንም ምሕረቱን ቸርነቱን አያጉድልብን መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል ከ ኖርዌይ ኦስሎ
Показати все...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

42👍 21🙏 11
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬም የሴቶች ቀን ይከበራል! የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የዛሬው ዕለት #ቅዱሳት_አንስት ወይም #አንስት_አንከራ ተብሎ ይጠራል 👉"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ነገራ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ፤ ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውን ተናገሩ ማለት ነው ለጊዜው የጌታን ትንሣኤ ያበሠሩ ሴቶች መታሰቢያ ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለክርስቲያን ሴቶች ሁሉ መታሰቢያ ቀን ነው። ዛሬም ብሥራተ ትንሣኤውን በዝማሬ በምስጋና በማስቀደስ በመቁረብ በሚዲያ በቃል በተግባር በማብላት በማጠጣት በማስተናገድ በጸሎት....በልዩ ልዩ አገልግሎት የሚፋጠኑ የሚመሰክሩ ሴቶች "ቅዱሳት አንስት" ይባላሉ (የተለዩ የተመረጡ የጸኑ ማለት ነው)። እግዚአብሔር እናቶችንና እህቶችን ይጠብቅልን! ሠናይ ቅዳሜ🙏 መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ከ ኖርዌይ ኦስሎ
Показати все...
👍 48 32🙏 8🥰 6
#የትንሣኤው_ሦስተኛ_ቀን_ቶማስ_ይባላል የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የትንሣኤ ሦስተኛው ዕለት ቶማስ ይባላል፡፡ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን ፣ዲዲሞስ ማለት ደሞ መንታ ማለት ነው፡፡ ማመኑ በፀሐይ ፤መጠራጠሩ በመንታነት ይመሰላል፡፡ ቶማስ ሰዱቃዊ ነው ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ያምናሉ ቶማስም ሰዱቃዊ ስለሆነ ትንሣኤ ሙታንን የማይቀበል የማያምን ሰው ነበር፤ የጌታን ትንሣኤ ለመቀበል የተቸገረው አእምሮውን ገድሎት የነበረው ሰዱቃዊው ሀሳብ ስላልተለየው ነበር፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ጌታ አልዓዛርን ለማስነሣት ሐዋርያትን እንሂድ ሲላቸው "ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" ይላል ዮሐ 11፡16፡፡ የጌታችንን ከሞት መነሣት እርግጥ ሆኖ ሲያገኘው ግን የሞተው አእምሮው/ሀሳቡ ተነሥቷል ፤ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ጠርቶ ሕያውነትን ተቀላቅሏል፡፡ "አንሥአኒ በትንሣኤከ፤ በትንሣኤህ አንሣኝ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ቶማስን በትንሣኤው አንሥቶታል፤ ስለዚህ የትንሣኤው 3ኛው ቀን ለቶማስ መታሰቢያ ሆኗል፡፡ ቶማስም ከ 3 ዓመት ትምህርት በኋላ ከጥርጥር ሞቱ ተነሥቷልና። ቶማስ ጠያቂ ነው፤ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ማየት የፈለገውን ልየው ይላል፡፡ በዚህም ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ ሰውን ይመስላል፤ ፍጥረታዊ ሰው ተነግሮት አያምንም፤ካልጨበጠ ካልዳሰሰ እውነትነቱን አይቀበልም ፦ " ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 2 : 14፡፡ ቶማስ የጌታችንን ድርጊቶች በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ሐዋርያ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን አልዓዛርን ለማስነሣት ሲሄድ ደስተኛ አለመሆኑን በሞት ስጋት ገልጾ ነበር፦ "ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" በማለት እንደተጻፈ፡፡ ዮሐ 11 : 16፡፡ በሌላ ጊዜም ቶማስ መንገዱን የጠየቀው ለዚህ ነበር፤ ያ መንገድ ወዴትና የት የሚወስድ ነው? የሚል ጥያቄ በውስጡ ይመላለስ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው፦ "ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው" ዮሐ 14 : 5፡፡ በዚህ ሁሉ ጥያቄውና ጥርጥሩ ግን ጌታችን አንድም ቀን ሰልችቶት ተቆጥቶት ወይም በጥርጣሬ አትከተለኝ ብሎት አያውቅም ፤ ድካማችንን የሚያውቅ የሚሸከምልን አምላክ ነውና፤ ዛሬም ምንም ያህል ኃጢአት ብንሠራ ተጸጽተን በንስሐ ከተከተልነው አትከተሉኝ አይለንም፤ ከየትኛውም ክህደት ከየትኛውም ሃይማኖት ብንመለስ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት ከገባን በኀላ አልፈልጋችሁም፡ውጡልኝ አይልም፤ "ወደኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም "ብሎናልና፤ ዮሐ 13፡32፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኀላ ለሁሉም ሲገለጥ ለቶማስ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ አልተገለጠለትም ነበር፤ ቶማስም ጌታን በአካል ያዩት ሐዋርያት ሲነግሩት፦ • የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ • ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ • እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ይላቸው ነበር። ዮሐ 20 : 25፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገበት ምክንያትም፦ 1. ቶማስ በውስጡ መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርበት፤ ሁሉም ስለ ትንሣኤው ሲናገር እየሰማ እንዲጓጓ ነው፤ ይህ መጎምጀት ወደ ፍጹም መንፈሳዊነት ይመራልና፤ እኛም ዛሬ ለመንፈሳዊ ነገር ስንጓጓና ስንቸኩል እግዚአብሔርን እናገኘዋለን፤ በውስጣቸው የሚቀጣጠለው ፍቅረ እግዚአብሔር እርሱን ራሱን ይጠራዋል፤ ቀድሞም ለሞት ያደረሰው ፍቅር ነውና፡፡ 2. ጌታችን የአንዲት ነፍስ ጉዳይ ጉዳዩ እንደሆነ ያጠይቃል፡፡ የተገለጠው ለቶማስ ሲል ነበር ለሱም ሲባልም አስቀድሞ በሌለበት የተገለጠበት ፦ • ዕለት • ሰዓት • ቦታ • በተዘጋ ደጅ መግባቱ • ሰላምታው (ሰላም ለሁላችሁ ይሁን) • ሁኔታው /መልኩ አልተቀየረም፡፡ ቶማስ ባለበት የተገለጠበትና ሳይኖር የተገለጠበት ልዩነት ቢኖረው በመጀመሪያ ቀንና በስምንተኛ ቀን መሆኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ፦ • ለሰው ሁሉ ያለውን ክብር/ፍቅር/ግድ • ትንሣኤው እርግጥ መሆኑን • ፍጹም ቸርነቱን • መጀመሪያ ያዩትም መጨረሻ የሚያዩትም በአንድነት እንደሚወርሱት ያጠይቃል፡፡ የቶማስ የመጨረሻ እምነት፦ "ጌታዬ አምላኬም" ፤ዮሐ 20፡28፡፡ ይህ ቃል የመጨረሻው የእምነት ጥግ ቃል ነው፤ የምናምነው ይህን ነው ፤ የምንናገረው ይህን ነው፤ የምንሰብከው ይህንን ነው፤ ከዓለም የምንለየውም በዚህ ቃል ነው፡፡ ቶማስ ብዙ ቢጠይቅም፤ ቢጠራጠርም በመጨረሻ ግን "አምላኬ" ብሎ አመነ፤ ዛሬ "ኢየሱስን አምላክ " ብለው መጥራት የሚከብዳቸው ብዙዎች ናቸው፤ እኛ እንኳን የቶማስን ቃል የወንጌሉን ፍጥጥ ያለ እውነት ስንናገር ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው!!! ቶማስ ጌትነቱን አምላክነቱን ያመነው በመዳሰስና በማየት ከሆነ እኛስ ሳናይ እንዴት እናምናለን እንዳንል ጌታችን " ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" በማለት ወሳኝ መልእክት አስቀምጦልናል፡፡ ዮሐ20 : 29፡፡ ወንጌላዊውም ታሪኩን ሲጠቀልለው፦ " ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል" በማለት ይህን አንብበን፤ ሰምተን ብቻ እንድናምን አስገንዝቦናል፡፡ ዮሐ 20 : 31፡፡ እኛም የቶማስን እጅ እጅ አድርገን ዳሰነዋል የሐዋርያትን ዓይን ዓይን አድርገን አይተነዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም "ክብሩን አየን.." እንዳለ አባ ሕርያቆስም " ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን.." እንዳለ እኛም እንደ ቶማስ " ጌታችን አምላካችን" እንላለን!!!!! በዚህም እኛ "ብፁዓን ነን"!!! እንድናምነው የረዳን አምላካችን ይመስገን!!!! በበጎ ሥራም ደስ እንድናሰኘው ይርዳን!!! በረከተ ሐዋርያት ይደርብን!!! አሜን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል
Показати все...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

37👍 25🙏 12
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትክክለኛው ይህ ነው! በልዩ ሁኔታ የ ነቅዐጥበብ ቴሌግራም ግሩፕ አባላት እንኳን አደረሳችሁ!!! መልካም በዓል ይሁንላችሁ የትንሣው ብርሃን በልባችን ይብራ በአእምሯችን ይገለጥልን!!!!
Показати все...
86👍 15🙏 11
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#እንኳን_ለብርሃነ_ትንሣኤው_አደረሳችሁ -ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን -በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን -አሰሮ ለሰይጣን -አግዐዞ ለአዳም -ሰላም -እምይእዜሰ -ኮነ -ፍሥሓ ወሰላም ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሰይጣንን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20 በዓሉን የደስታ የሰላም የጤና የበረከት ያድርግልን ለሁላችሁም መልካም በዓል🙏 መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
Показати все...
59👍 15🥰 4🙏 4👏 3🤔 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#አገልጋዮች_እንኳን_አደረሳችሁ • በዐቢይ ጾም ሳታቋርጡ ጾመ ድጓ የቆማችሁ • ሰዓታት የቆማችሁ • የቀደሳችሁ • ያስቀደሳችሁ • የጸለያችሁ • በትጋት ጉባኤ የሠራችሁ • ወንጌል የሰበካችሁ • ባጠቃላይ ከቤተ ክርስቲያን ያልተለያችሁ ... • አገልግሎትን እንደ ሥራ ሳይሆን እንደ መጠራት የቆጠራችሁ አገልጋዮች እንኳን አደረሳችሁ!!! በረከታችሁም ይደርብን!!! ለሁላችንም በለመለመ ቄጤማ አምሳል ደስ የሚል ብሥራትን ያሳየን ያሰማን!!! አሜን መልካም በዓል  መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
Показати все...
101🙏 19👍 6
✝ይህ ምሴተ ሐሙስ እጅግ በጣም የተለየና በጭንቀት የተሞላ ጊዜ የነበረ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ጸሎት በዮሐንስ ወንጌል ሰፍሯል፤ ሁኔታውና የነበረው ጭንቀት እንዲሁም ትካዜና ጸሎቱን ያቀረበበት መንገድ ደግሞ በሦስቱም ወንጌላውያን አስገራሚ በሆነ መንገድ ተመዝግቦ እናገኛለን ፤ በማቴዎስ ወንጌል የተገለጸው "ነፍሴ እስከሞት ድረስ አዘነች" በማለት እየተመላለሰ ሦስት ጊዜም ተመሳሳይ ጸሎት "አባ አኅልፋ እምኔየ ለዛቲ ጽዋዕ" በማለት እየሰገደ ይጸልያል(ማቴ 26)፤ በሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ደግሞ "ወኮነ ሀፉ ከመ ነጸፍጻፈ ደም ዘይወርድ ዲበ ምድር" ይላል ከፊቱ የሚወርደው ላብ መሬቱን እስኪያርሰው ድረስ እንደ ደም ይንጠባጠብ ነበር፤ …."ብላዕ በሐፈ ገጽከ" "ደምህ ፈሶ፤ወዝህ ተንጠፍጥፎ፤ወጥተህ ወርደህ ብላ" ብሎ ረግሞት ነበርና ያንን መርገሙን እንደተሸከመለት ለማጠየቅ በዕለተ ሐሙስ ማታ በገነት ጌቴሴማኒ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ወዙን አንጠፈጠፈለት ፤አዳም ከበደለ በኋላ "ራቁቴን ነበርኩና ፈርቼ ተሸሸግሁ …" ሰላለ ፋንታ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ፈራለት፤ፍርሃቱን ተሸከመለት፤እስከመጨረሻውም ፍርሀትን ከሁላችን ያርቅ ዘንድ ጸለየ፤"ሶበሰ ኢፈርሀ እግዚእነ እምኢሰሰለ ፍርሃት እምኔነ" "ጌታ ባይፈራስ ኖሮ ፍርሃት ከእኛ ባልተወገደም ነበር" እንዳለ ሊቁ፡፡ ይህ ቀን ወይም ይህ ምሽት የሰው ልጅ የተፈረደበትን ፍርድ ለመሸከም ወደ መስቀል ከመውጣቱ በፊት የሆነ የመጨረሻው ምሽት ነው፤ የአይሁድ የፋሲካ መታሰቢያ ቀን ነው፤ ጌታ ደግሞ ይህን ፋሲካ ኣሳልፎ እርሱ ፋሲካ ሆኖ ከመታረዱ በፊት የሆነ የመጨረሻው ምሽት ነው፤ ይህ ምሽት የሞትን ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት የሆነ አስጨናቂ ምሽት ነበር፡፡ ስለዚህም ይህ ምሽት በአምስት ቀን ተኩል ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚለው የተስፋ ቀጠሮ ተፈጻሚነት የሚረጋገጥበት ምሽት በመሆኑ " አባ በጽሐ ጊዜሁ ከመ ትሰብሖ ለወልድከ ወከመ ወልድከኒ ይሰብሕከ " (አባት ሆይ ልጅህ ያከብርህ/ያመሰግንህ/ይገልጥህ ዘንድ፣አንተም ልጅህን ታከብረው/ታመሰግነው/ትገልጠው ዘንድ ጊዜው ደረሰ) በማለት ተናገረ፡፡ • ጊዜው ሲደርስ ያዳነን • ኪዳንን የሰጠን • ሐዲስ ሕግ ወንጌልን የሠራልን • ሥጋውን ደሙን የሰጠን • ሥርዓተ ጸሎትን ያስተማረን • ሰማዕትነትን የሰበከልን ...ጌታ ፍቅሩን በልባችን በአእምሯችን ይሣልልን!!! አሜን ! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል
Показати все...
61🙏 25👍 15🥰 1
#ጸሎተ_ምሴተ_ሐሙስ #ትሕትና_ኪዳን_ቍርባን_ሕግ_ጸሎት_ሕማም የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሐሙስ ማታ 3 ሰዓት ጸሎት ነው፡፡ ✝ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው፤ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ "ወአመ ሀሎ በመዋዕለ ሥጋሁ ጸሎተ ወስኢለ አብአ በዐቢይ ገዓር ወአንብዕ ኀበ ዘይክል አድኅኖቶ እሞት" "እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ" (ዕብ 4÷7)፡፡ ✝በዚህ መልእክት ውሰጥ በደንብ ማጤን ያለብን ጉዳይ ቢኖር "በሥጋው ወራት" የሚለውን ሐረግ ሲሆን ይህንም አስተምሕሮ ያቀረበው ከዕለተ ዓርብ፤ ከመስቀል አስቀድሞ ነው፤ ቅድመ መስቀል የነበረውን ጊዜ ሁሉ እንደተመለከትነው ከኃጢአት በስተቀር ማንኛውንም ነገር እንዳከናወነ እንረዳለን፤ ጸሎት ኃጢአት አይደለም ስለዚሀም ከኃጢአት በስተቀር ከተባሉት ትልልቅ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ይህ የዕለተ ሐሙስ ምሴት አስተምሕሮ ነው፤ ከሞቱ በፊት ከመከራው በፊት ይህን ልመና ያቀረበበት ምክንያትም ለሕዝቡ የሚሆነውን የኃጢአት ሥርየት በመስቀል ከማከናወኑ አስቀድሞ ያለ ኃጢአቱ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን ሥርዓተ መሥዋዕት መፈጸሙን ለማጠየቅ ነው፡፡ ✝መተርጉማን ሊቃውንትም "ጸሎትን እንደላም፤ ስኢልን እንደ በግ አቀረበ" በማለት አብራርተዋል (አንድምታ.ትር. ተመልከት)፡፡ ✝ይህም ማለት የቀድሞው ሊቀ ካህናት በበግና በላም ደም መሥዋዕት ስለ ራሱ ኃጢአት ሥርዬት እንደሚጠይቅ ሁሉ ጌታ ግን ያለ ኃጢአቱ ጸሎቱን እንደ ላም ልመናውን እንደ በግ አድርጎ በአባቱ ፊት ያርደዋል፤የሰባ ነው፤ ንጹሕ ነው፤ነውር የለበትም፤ቀንዱ ያልከረከረ ፤ጥፍሩ ያልዘረዘረ፤ነጭ ነው፤ መርገም አላረፈበትም፤ እስከሞት የታዘዘበት ልመናው ነውና ይህም ማለት ደግሞ ለራሱ ለእግዚአብሔር ወልድም ለአግዚአብሔርነቱ ንጹሕ ነው ከአብ ጋር አንድ ነውና "እኔና አብ አንድ ነን" እንዲል፣ አባቱ ጸሎትህን አልሰማም፤ እንባህን አላይም አልቀበልም ይለው ዘንድ ምንም ምክንያት የለም፤ ምክንያቱም ንጹሕ ነው፤ ✞ስለዚህ እርሱ በሥጋው ንጹሕ ከሆነ፤ የባህርይ አምላክ፤ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሥልጣን ጸሎትንና ልመናን በመቀበል አንድ ከሆነ ጸሎቱን ለማን ነው የጸለየው? የሚለውን ጥያቄ ማንሣት ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህንም ሊቃውንቱ መልስ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል "ከሞት ሊያድነው ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ ማለት የምእመናንን ድኅነት ለራሱ አድርጎ ኀበ ዘይክል አድኅኖቶ እሞት አለ፤አንድም ምእመናንን ከሞት ሊያድንለት ወደሚቻለው ወደ አብ አቀረበ" በማለት አብራርተዋል፡፡ ✝ይህም ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሐሙስ ማታ ሲጨነቅ የነበረው ስለ አዳምና ልጆቹ እንጂ ስለራሱ አይደለም፤ ከሞት መዳን ሳይሆን ለመሞት ነው የመጣውና፤ ነገር ግን ለዚህች ሰዓት መጣሁ በማለት ሲናገር አይተናል፤ ✝ዮሐ.አፈ ወርቅም "እመሰ ከመዝ ወእቱ በእፎኬ ዘኢሰአለ በእንተ ትንሣኤሁ፤እስመ ይቤ ንሥትዎ ለዝንቱ ቤተ መቅደስ ወበሠሉሰ ዕለት አነሥኦ አነ፤ ወካዕበ ይቤ ብውሕ ሊተ አንብራ ለነፍስየ ወአልቦ ዘየሀይደኒያ፤በእንተ ምንት ይስእል ዘይቤ ናሁ ነዓርግ ኢየሩሳሌም ወይሜጥውዎ ለወልደ ዕጓለ እመሕያው ለሊቃነ ካህናት ወለጸሐፍት ወይፈትሑ ላዕሌሁ በሞት ወያገብእዎ ለአሕዛብ ወይቀሥፍዎ ወይዘብጥዎ ወይቀትልዎ ወይትነሣእ በሣልስት ዕለት፤ ኢይቤ አብ ያነሥአኒ፤እመሰ ከመዝ ውእቱ ተዐውቀኬ ከመ ኢሰአለ በእንተ ዝንቱ " "እንዲህማ ከሆነ ስለ ትንሣኤውስ ለምን አለመነም?ይህን ቤተ መቅደስ አፍረሱትና በሦስተኛው ቀን እሠራዋለሁ ብሎ ነበርና፤ዳግመኛም ነፍሴን አስቀምጣት ዘነድ ሥልጣን አለኝ የሚቀማኝም የለም ብሎ ነበርና፤እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን የሰውን ልጅ አሳልፈው ለጸሐፍት ለሊቃነ ካህናት ይሰጡታል ፤እነሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ይገርፉታል ይደበድቡታል ይገሉታል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ይነሣል ብሎ ተናግሮ ነበርና፤አብ ያስነሣኛል አላለም፤እንዲህስ ከሆነ ስለ እርሱ ስለሞቱ እንዳለመነ ታወቀ ተረዳ " ብሏል (ድር 8÷104)፤ ሊቁም ይህንን ካስረዳ በኋላ "ወለእመ ትቤለኒ በእንተ ምንት ሰአለ?" (ታዲያ እንዲህ ከሆነ ለምን ለመነ ትለኝ እንደሆነ) "እብል አነሂ በእንተ እለ የአምኑ ቦቱ" (ስላመኑበት ሰዎች ምእመናን ነው እልሃለሁ) ይላል፡፡ ✝ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስም እንዲህ አለ "ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም መጣ ከአብርሃም ባህርይ ሥጋን ነሣ፤የአዳም ባህርይ አስቀድሞ የተያዘባቸው የቀደመ ፍዳንና መርገምን ያጠፋ ዘንድ ወንድሞቹን መሰለ፤መድኃኒታችን እንደ እኛ ነፍስን ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ እርሱን በመክዳታችን እግዚአብሔር ከእርሱ ለይቶን ከነበርን ከእኛ እንደ አንዱ ራሱን ቆጠረና በዚህ አነጋገሩ በአዳም ሕግ ማፍረስ ምክንያት ያገኘንን ፍዳ ያጠፋ ዘንድ ያን ጊዜ ይህንን ቃል አለ እንላለን፤ እርሱ ራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው፤እንደገና ደግሞ እዲያስበን ከእሱም እንዳይለየን ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባህርያችንን ነሥቷልና፤ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለበጎ ሥራ ሁሉ ጀማሪ አብነት ሆነን፤ሰው በመሆኑ ከአብ እርዳታን ያገኝ ዘንድ የሚሻ መስሎ ለእኛ ትንሣኤን አዘጋጀልን፤ለእኛ ባህርይ አስቀድሞ ልጅነትን አዘጋጀ ፤እርሱ ግን በባህርዩ ፍጹም ነው፤በባህርዩ ፈጽሞ ምንም ሕጸጽ የለበትም፤የነሣውም ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ለርሱ ብቻ በእውነት ገንዘቡ ሆነ" (ሃይ.አበ 79÷37-39)፡፡
Показати все...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

23👍 9🙏 4🥰 3