1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የመስከረም ወር የስራ እንቅስቃሴን ያካተተውን የዜና መፅሄት ይከታተሉ።
"ነፁህና ፅዱ ት/ቤት ለትውልድ!" በሚል መሪ ቃል በ2018 በጀት ዓመት የተጀመረው ሳምንታዊው የትምህርት ቤቶች የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የንቅናቄው ዓላማ ተማሪዎች በለጋ ዕድሜያቸው ስለ ቆሻሻ አወጋገድ፣ በተለይም ስለ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ይህንን ግንዛቤ መሠረት በማድረግም የመኖሪያ አካባቢያቸውን ንፅህና እንዲጠብቁ፣ ቆሻሻን እንደገና የመጠቀም (reuse) እና በዑደት ውስጥ የማዋል (recycling) ባህልን እንዲያዳብሩና ትምህርት ቤቶቻቸውንም የንፅህና ተምሳሌት እንዲያደርጉ ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ ላይ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በጋራ በመሆን የትምህርት ቤት ግቢዎችንና አካባቢውን ሲያፀዱ ታይቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከከተማው ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ሁልጊዜ በየሳምንቱ አርብ የሚካሄደው ይህ የፅዳት ንቅናቄ የተማሪዎችን በፅዳት ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ የንፅህና ጉዳይ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን በተግባር ያስተማረ ነበር።
የአካባቢ ንፅህና ለጤናማ ትውልድ ግንባታ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት የኤጀንሲው አስተባባሪዎች ይህ ፕሮግራም ትምህርት ቤቶችን የንፅህና አምባሳደር በማድረግ ተማሪዎች ያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደየቤታቸውና ወደሚኖሩበት ማህበረሰብ እንዲያደርሱ ያግዛል ብለዋል።
ይህ የፅዳት ንቅናቄ የአንድ ጊዜ ብቻ እንቅስቃሴ ሳይሆን፣ በየሳምንቱ ዓርብ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በቋሚነት እንደሚቀጥልም የተገለፀ ሲሆን ይህም የንፅህና ባህልን በተማሪዎች ህይወት ውስጥ ስር የሰደደ ልማድ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ከሰዎች የእለት ተእለት ህይወት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው?
በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ 👉👉👉
ለተ… See more
or Africa, now is not the time to wait and watch.
We have the people, creativity, and natural wealth to build a prosperous and fair future. What we need is to … See more
ላችንን በተግባር ማሳየታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!
ሁሌም በፍጥነት እና በጥራት ፤ በትጋት እና በፅናት ፣ በብቃት እና በውጤት እንራመዳለን ::
በ2018 በጀት አመት የሚጠኑ የጥናትና የምርምር ስራዎች ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በውጤታማነት ለመምራትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚረዱ በ2018 በጀት አመት በዉስጥ አቅምና በዉጭ አቅም የሚጠኑ አምስት ጥናቶች በተመለከተ ላይ ከተጠሪ ተቋማትና ከክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ለተወጣጡ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በዛሬዉ እለት ስልጠና ሰጥቷል።
በዚሁ የስልጠና መድረክ በ2018 በጀት አመት በዉስጥና አቅም እንዲሁም በዉጭ አቅም የሚጠኑ ጥናቶችን የያዘ በተለይም ከመረጃ አሰባሰብ፣ከመረጃ ትንተና አንፃር እንዲሁም የጥናት ምንነት በእነዚህና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችን ያለመ የስልጠና ሰነድ ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተደርጎበታል።
በስልጠና መድረኩ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደስ እንደገለፁት በጽ/ቤቱ በ2018 በጀት አመት በዉስጥ አቅምና በዉጭ አቅም የሚጠኑ አምስት ጥናቶች አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ጥናቶቹ በተለይም የተቋሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከተማችን የደረሰችበት እድገት የሚመጥን ከማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ በበጀት አመት 5 ጥናቶች እንደሚጠኑ እና 2 ጥናቶች በዉጭ አቅም የተቀሩት 3 ጥናቶች በዉስጥ አቅም ለማስጠናት እንዲሁም የሚጠኑት ጥናቶች ከጥናትነት አልፈዉ መፍትሄ እንዲሰጡና ወደ ተግባር ለመግባት እተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ወ/ሮ ይመኙሻል አክለዉም የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን የተገልጋዩን የእርካታ መጠን ከፍ ያለ እንዲሆንና ውጤታማ ለማድረግ ጥናቶችን በምርምር ላይ እና የነበሩ ችግሮች እንዲሁም የአሰራር ክፍቶች ላይ ተመስርቶ ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋትና መፍትሄም አመላካች ጥናቶች ለማካሄድ በጋራ ተቀራርቦ መስራትና ቀድሞ ስልጠና መስጠት መቻሉም ለቀጣይ ስራዎቻችን ከፍተኛ አቅም እንደሚሆንም አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በስልጠና መድረኩ ከሰልጣኞች ሀሳብ አስተያየት የተነሳ ሲሆን የተነሱትን ሀሳቦች ለቀጣይ ስራዎች እንደግብአት በመዉሰድ በተለይም በሚጠኑት ጥናቶች ላይ ሁሉም እየተሳተፈ ጥናቶቹን ከዳር ለማድረስ በቀጣይ በጋራ በትኩረት በመስራት ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
መንግስት ከህዝብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ሰምቶ ዝም አላለም ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል ለዚህም ዛሬ መርቀን ስራ ያስጀመርነዉ የቦሌ አዲስመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ማዕከል ማሳያ ነው ።… See more
ዛሬ በናይሮቢ፣ ኬንያ “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው 24ኛው የCOMESA መሪዎች ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበልን አፅንኦት ሰጥቼ አንስቻለሁ። እንደ አኅጉር የየሀገሮቻችንን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ አለን።
በኢትዮጵያ ዲጂታል ክሂሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል። የጋራ ዲጂታል ነጋችንን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 በአዲስ አበባ እና ሸገር ሲቲ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመልሶ ግንባታ እና የጥገና ሥራ ስለሚከናወን፦
👉ሰሚት ኮንዶሚኒየም ፣ ሰሚት ፍርድ ቤት አካባቢ፣ ወጂ ሰፈር፣ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ፣ ሰንራይዝ ሪል ኤስቴት፣ አራብሳ ኢንዱስት መንደር፣ አይ.ሲ.ቲ. ፓርክ (ለዳታ ማይኒንግ )፣ አይ.ሲ.ቲ. ፓርክ (ለዳታ ማይኒንግ )
👉ቡራዩ ድሬ፣ ኬላ ፣ መናገሻ፣ ቻይና ቱቦ፣ ቆሼ ፊጽለፊጽ፣ ረጲ መድሃኒዓለም ቤ/ክ፣ ፋና ሬዲዮ፣ አየር ጤና ፣ ሳሚ ካፈ ጀርባ ፣ ታቦት ማደሪያ፣ መሐንዲስ ሰፈር፣ ፈመ ሬሲዮ፣ ቴሌ፣ ስልጤ ሰፈር መውጫ፣ ፋኑኤል ቤ/ክ፣ አጃንባ ኮንዶሚኒየም፣ አየር ጤና ፣ናትራን ፣ ለማ ነገዎ ሰፈር፣ አየር ጤና ሞቢል ጋዝ፣ ካራ መድህንዓለም መውጫ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ አየር ጤና ት/ቤት ፣አየር ጤና መስጊድ፣ ኪዳነምህረት ቤ/ክ
እና አካባቢያቸው ላይ የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ስለሆነም በጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን፡ ብሏል።
Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
