1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
"ስማርት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት
ለስማርት አዲስ አበባ !
በቀጣዩ ቪዲዮ ይከታተሉ👉👉👉
ለ… See more
በከተማችን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን ቀጥለናል።
ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማን የመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ስናስጀምር ቅርንጫፎችን በፍጥነት ለማስፋት በገባነው ቃል መሰረት፣ ዛሬ 12 የከተማ አስተዳደር እንዲሁም 3 የፌደራል ተቋማትን በመያዝ 96 የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶች የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ቦሌ ቅርንጫፍን ስራ አስጀምረናል ።
የቦሌ ክፍለከተማ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ስራ ያስጀመርነው ባለ 6 ወለል ህንፃ በ4 ወራት ገንብተን፣ አስፈላጊውን ቴክኖሎጂ እና ግብአት አሟልተን እንዲሁም የሰው ሀይል አሰልጥነን ነው።
ይህንን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በአጭር ጊዜ ግንባታው እንዲጠናቀቅ እና በአስፈላጊው ቴክኖሎጂ እንዲዘምን ለደገፉን አካላት በሙሉ፣ በተለይም የኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ለከተማችን አመራሮች በተገልጋዩ ህብረተሰብ ስም ከልብ አመሰግናለሁ። ተገልጋዩ ህብረተሰብም በማዕከላቱ በመገኘት አገልግሎቶቹን እንድትጠቀሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
Magaalaa keenyatti kenniinsi tajaajila mootummaa sirnasaa kan eeggatee fi si'ataa taasisuuf hojii eegallee cimsinee itti fufneerra.
Kabajamoo Muummicha Ministeera keenya waliin ta'uun tajaajila mootummaa dijitaalawaa giddugala tokkoo Masoob magaalaa Finfinnee yemmuu eegalchiisnu, dameelee saffisaan babal'isuuf bu'uuruma waadaa galleen har'a bulchiinsota magaalaa 12 akkasumas dhaabbilee Federaalaa 3 qabachuun tajaajiloota magaalaa 96 kan kennu giddugala tokkoo Addis Masoob damee Boolee hojii eegalchiisneerra.
Hojii tajaajila dijitaalawaa mootummaa giddugala tokkoo Addis Masoob kutaa magaalaa Boolee kan eegalchiisne gamoo abbaa darbii 6 ji'a 4 keessatti ijaarree, teknooloojii fi galtee barbaachisu guunnee akkasumas humna namaa leenjisneeti.
Tajaajilli dijitaalwaa mootummaa giddugala tokkoo Addis Masoob kuni ijaarsisaa yeroo gabaabaa keessatti akka xumuramuu fi teknooloojii barbaachisuun akka ammayyaa'uu qaamolee nu gargaaran hunda, keessattuu Itoophiyaa Artafishaala Intalajansi Inistiitiyuuti fi hooggantoota magaalaa keenya maqaa hawaasa tajaajilamuutiin onneerraa galateeffadha. Hawaasni tajaajilamaanis giddugalootatti argamuun tajaajiloota akka fayyadaman yaamicha koon dhiheessa.
Waaqni Itoophiyaa Uummata Ishee Haa Eebbisu
Aschalew Mulugeta
መዲናችን አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ለአፍሪካ አገራት ከተሞች የጽዳት ተምሳሌት እየሆነች ትገኛለች።በየቤታችን እኛ አንፈልገውም ብለን የምንጥለው ቆሻሻ በአግባቡ ከተሰበሰበ፣ ከተለዬና ካስተዳደርነው 60 በመቶ የሚሆነው ለመልሶ ጥቅም ላይ መ… See more
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም ራእይ፣ተልእኮና እሴቶችን ያውቃሉ?
በቀጣዩ ስላይድ ይመልከቱ:-👉👉👉
ለተ… See more
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ የተከናወኑ ከተማዊ ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች በተሳካ መልኩ በድምቀት እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በአዲስ አበባ በድምቀት ተከብረዋል፡፡
በተጨማሪም ከ25 ሺህ በላይ አለም አቀፍ ተሳታፊዎች በተሳተፉበት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና የአፍሪካ ካረቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባኤ በስኬት ተጠናቀዋል።
እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት በቅደም ተከተል የተከናወኑ የአለም ፣ የአህጉር እና የሀገር አቀፍኩነቶች፣ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ፕሮግራሞች ለአብነትም የአየር ንብረት ለዉጥ ጉባኤ፣ መስከረም አንድ በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የወንጌል አማኞች የአምልኮ ፕሮግራም ፣ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተካሄዱ ህዝባዊ ሰልፎች ፣የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ ክብረ በዓላት እጅግ ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት በሰፈነበት መንፈስ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መከበሩ የህዝባችንን ጨዋነት ዳግም ያረጋገጠ ነዉ ብለዋል ።
ሁሉንም ሃገር አቀፍና አለማቀፍ ጉባኤዎች እንዲህም ሃይማኖታዊ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ በየደረጃዉ ያለ አመራር ፣ የሆቴል ባለቤቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት አምራቾችን የዋጋ ንረትና የምርት እጥረት እንዳይኖር በማድረጋቸዉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመስግነዋል።
በተለይም የሀይማኖት አባቶች ፣ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች ክብረ በዓላቱ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ በማስተባበር ረገድ ለነበራቸዉ የላቀ አስተዋፆ ምስጋና አቅርበዋል ።
የፌደራል ፣ የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ የፀጥታ አካላት እና አመራሮችንም አመስግነዋል ።
አለም አቀፍ ጉባኤዎቹ ፣ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎቹ ፣ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓላቱ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መከበራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ኩነቶቹ ለነዋሪዉ ህዝባችን የገቢ ምንጭ በመሆን በከተማችን ኢኮኖሚ ላይ አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ከንቲባ አዳነች ትላንት ማምሻዉን በተካሄደዉ የምስጋና ፕሮግራም ላይ አክለው ገልጸዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነሥርዓት ተካሂዷል። በ2010 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ይኽ ሥነሥርዓት የዜግነት የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት የሚፈፅሙ ዜጎችን ለማበረታታት ታቅዶ የሚተገበር ነው። በዘንድሮው መርሃ ግብር 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በ2017 ዓመተ ምህረት እንደነበራቸው አስተዋጽኦ መጠን 105 የፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 የወርቅ ደረጃ፣ 350 ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። የጋራ አስተዋጽኦዋቸው በሥራ ዘመኑ 900.22 ቢሊዮን ብር በግብር እንዲሰበሰብ አስችሏል።
በተጨማሪም የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በግብር እና ቀረጥ አሰባሰብን ብቁ እና ግልፅ የሚያደርጉ የዲጂታል ሥርዓቶችን አስጀምረዋል። ከነዚህም ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት፣ ኤሌክትሮኒክ የጉምሩክ አስተዳደር ሥርዓት እና ኤሌክትሮኒክ የጭነት መከታተያ ሥርዓት ይገኙበታል።
Yesterday marked the 7th Annual Loyal Taxpayers Recognition Ceremony, a tradition established in the Gregorian calendar year 2018 by Prime Minister Abiy Ahmed to foster a culture of appreciation for citizens who diligently fulfill their civic responsibility by paying taxes on time. During this year’s ceremony, 700 loyal taxpayers were honored for their contributions in the 2017 Ethiopian fiscal year, comprising 105 Platinum-level, 245 Gold-level, and 350 Silver-level awardees. Their combined efforts made possible a total tax collection of 900.22 billion Birr for the fiscal year.
In addition, the Ministry of Revenue and the Customs Commission inaugurated several new digital systems designed to enhance efficiency and transparency in tax and customs administration. These include the Electronic Receipts Administration System, Electronic Clearance System, Electronic Customs Management System, and Electronic Cargo Tracking System.
#PMOEthiopia
የውስጥ ባንዳና የውጭ ባዳ” ኃይሎችን በመመከት፣ በመራቅና ድጋፍ በመንሳት የኢትዮጵያን ብልፅግና በጋራ እናረጋግጥ ሲሉ አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ አሳሰቡ
“የውስጥ ባንዳና የውጭ ባዳ” ኃይሎችን በመመከት፣ በመራቅና ድጋፍ በመንሳት የኢትዮጵያን ብልፅግና በጋራ እናረጋግጥ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አሰተዳደር የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ አሳስበዋል
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 'ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና' በሚል መሪ ሀሳብ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከሰራተኞቹ ጋር አካሂዷል።
በዚሁ ውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በተለይ ከለውጡ ወዲህ በጂኦፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስክ የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችን አንስተው አብራርተዋል።
አቶ ገዛኸኝ አክለውም ኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞዋን ስኬታማ ለማድረግ፣ ሁሉም ዜጋ በሙያውና በእውቀቱ ለሀገሩ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ገልፀው የግለሰቦች ጥረት ሲደመር ታላቅ ሀገራዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል።
ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንዳሳካነው ሁሉ፣ የቀይ ባህርን የማሳካት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን በፅኑ እምነት የተናገሩት አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ተሰሚነት አዎንታዊ መሆን መጀመር ብቻም ሳይሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይገባል የሚለው ጉዳይ ዋና አጀንዳ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ እንዳታድግ ያደረጓት የውስጥ ባንዳ እና የውጭ ባዳ ኃይሎች ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህን ጠላቶች መመከት ብቻም ሳይሆን ከአጠገባቸው መራቅና ድንጋይ ከማቀበል መቀጠብ ከሁላችንም እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ በተፃራሪ ወገን ቆመው የነበሩ ኃይሎች በአሁን ጊዜ ኢትዮጵያ ያነገበቻቸውን የረጅም እና አጭር ጊዜ ግቦች ለማሳካት የድርሻቸውን እየተወጡ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ሌሎች አካላትን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት ጉዞ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ እያስተላለፉ ነው ብለዋል፤ ይህም የሆነው ከለውጡ ወዲህ በተሰሩ ጂኦ-ፖለቲካዊ ስራዎች የተገኘ ውጤት መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ አብራርተዋል።
የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው ሀገራችን በፈተናዎች ውስጥም ሆና የተገበረቻቸው መሠረተ ልማቶች፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ተቋም ግንባታ ስራዎች ዘርፈ ብዙ መሆናቸውን በዝርዝር አብራርተዋል።
ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችም ከመድረክ ምላሽ በመስጠትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከጂኦ ስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሠ ቁመና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከፅ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ዉይይት ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት "ከጂኦ ስትራቴጂክ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከፅ/ቤቱ ስራተኞችና አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ዉይይት አካሂዷል።
በዚሁ መድረክ ሀገራችን በጂኦ ስትራቴጂክ ረገድ እንዲሁም ከቀጣናው ጋር ያላት ጂኦ-ስትራቴጂካዊ የሚያሳይ ሰነድ በፅ/ቤቱ ሀላፊ በወ/ሮ መሳይ መርሻ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከሰራተኞቹ ጋር አካሂዷል።
በዚሁ ውይይት ላይ በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት በተለይም ከለውጡ ወዲህ በጂኦፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስክ ሰፋፊ የልማት ስራዎች መከናወን መቻላቸዉን ገልፀዋል።
ወ/ሮ ይመኙሻል አክለውም ኢትዮጵያ የእድገት ግስጋሴዋን የተዋጣለት እንዲሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተሰማራበት መስክ ለሀገሩ ብልጽግና የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እንዳታድግ የሚያደርጓትን የውስጥ ባንዳ እና የውጭ ባዳ ኃይሎች ጠላቶች በጋራ በመሆን ሁላችንም ልንጋፈጣቸዉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ከተሳታፊዎች አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችም ከመድረክ ምላሽ በመስጠትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የሀገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዮች ላይ ዛሬ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ።
ኢትዮጵያውያንን ከዓለም ጋር ከሚያገናኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሳውን እና ማኔጅመንታቸውን የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማትን ካስጎበኘናቸው በኋላ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልክ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረምን ሲሆን፣ ስምምነቱ በዋናነት በከተማችን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት የለሙ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ በዚህም የስቶክ ኦቨር ቱሪዝም ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ የከተማችን አዲስ መለያ የሆነውን new face of Africaን ማስተዋወቅ፣ የአቪየሽን ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በተጨማሪም በከተማው የተለያዩ ማህበራዊና ሰው ተኮር ስራዎችን በጋራ መስራት ላይ ያተኮረ ነው ።
አየር መንገዱ በከተማችን በምንሰራቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች እና በኮሪደር ልማት ላይ ለነበረዉ ድጋፍ ከልብ እያመሰገንን ፣ የከተማ አስተዳደራችን ለስምምነቶቹ ተፈፃሚነት ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ተቀራርቦ የሚሰራ ይሆናል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ በዓለም ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ተርታ መመደብ የምትችል መሆንዋን የውጭ ሀገራት ሙሁራን ተናገሩ
ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የታሪክ፣ የአርኪኦሎጂስቶችና የማህበራዊ ሳይንስ ሙሁራኑ ለኤ አም ኤን እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ መገረማቸውንና ከተማዋንም ከምቹ የዓለም ከተሞች ተርታ የሚያሰልፋት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡት ምሁር ዴቪድ ፊሊፕስ፣ ወደ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2007 ላይ መጥተው እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የመጣውን ለወጥ አድንቀዋል፡፡
ከከተማዋ ንጽህና ጋር በተያያዘ ከአሁን ቀደም የማይመቹ ሁኔታዎች መኖራቸዉ፤ በየቦታው ቆሻሻ እና ደስ የማይል ሽታ እንደነበር ያነሳሉ፡፡
አሁን ላይ ግን ከተማዋ በብዙና በሚደንቅ ሁኔታ ተለዉጣለች፤ በተለይ በከተማዋ እየተከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ስመለከት በጣም ተገርሜያለሁ ብለዋል፡፡
ከእስራኤል የመጡት ሌላኛው ምሁር ጌዲዮን ቦሃክ በበኩላቸው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎችን ስመለከት በጣም የሚደንቁ ናቸው ብለዋል፡፡
ያላለቁ የወንዝ ዳርቻ ስራዎች ሲጠናቀቁ፣ ከተማዋ ይበልጥ የምታምርና የምትዋብ ትመስለኛለች ነው ያሉት ምሁሩ፡፡
በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ ከተማን ልማት በግልፅ ማየት ችያለሁ፡፡ ህፃን እያለሁ በንጉሱ ዘመን አዲስ አበባን የማየት እድል ገጥሞኝ ነበር የሚሉት ደግሞ ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡት ምሁር ስታሊቪን ናቸው፡፡
በጥቂት አመታት ውስጥ በጣም ትልቅ ለውጥ አይቻለሁ፤ እንዲህ አይነት ነገር መስራት ቀላል አይደለም፤ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፤ ለዚህ ደግሞ ብልህነትን ይጠይቃል ብለዋል ሙሁሩ፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
