cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethiopian Digital Library

በዚህ ቻናል 👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን 👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን 👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን 👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን 👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና 👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ! For any comments: @ethiodlbot

Більше
Рекламні дописи
64 407
Підписники
+2024 години
+357 днів
+42330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በሬና አህያ አንድ በሬ ወደ አንድ አህያ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ “በጣም ሰልችቶኛል፡፡ ያለምንም እረፍት ብዙ እሰራለሁ፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” አህያውም “እንግዲያው ነገ እንዲህ አድርግ፡፡ በጀርባህ ተኛና አሞኛል፣ ሆዴ ተነፍቷል፣ እያልክ እህ! እህ ብለህ አቃስት” አለው፡፡ በሬውም ይህንን አደረገ፡፡ በሚቀጥለውም ቀን ጌታው መጥቶ እንዲህ አለ “አይይ! በሬዬ ታሟል፡፡ ስለዚህ አህያው ይረስ፡፡” እናም አህያው የበሬውን ስራ በመስራቱ እጅግ ደከመው፡፡ በሬውም ወደ አህያው ጠጋ ብሎ ተጨማሪ ጥሩ ምክሮችን በደስታ ለማግኘት ካጠገቡ አረፍ አለና “ትናትና በጣም ጥሩ ቀን ነበር፡፡ ዛሬም አርፋለሁ፤ ነገም ስራ አልሄድም፡፡ ስለዚህ ገበሬውን እንዴት ማሳመን እንዳለብኝ ንገረኝ፡፡” ብሎ ጠየቀው፡፡ አህያውም “አዬዬ! እንደዚያ ይሻላል ብለህ ነው? ካልሰራህ እንደምትታረድ ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡” አለው፡፡ በዚህም ምክንያት በሬው ወደ ስራው ለመመለስ ወሰነ፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Показати все...
🤣 72👍 43 8 3🥱 3👏 2😁 1😐 1
የሪሚዲያል ፈተና ከሰኔ 1-7/2016 ዓ.ም ወይም ከሰኔ 8-14/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Показати все...
👍 5 2👏 1💯 1
በየመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው። ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል። ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል። እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል። መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ። e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው። በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Показати все...
👍 18 5🆒 2👏 1💯 1
Показати все...
Crypto Exchange Referral Program | Binance Official

Want to earn more Bitcoin? Join Binance using my referral link and you could get up to 0.018 BTC for free!

የምን " ቤቢ ሻወር " ይልቅ "የአጥር ወፍ አትስማሽ!" በሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጋብቻ ጊዜዋ የተቃረበችን ሴት እና የመውለጃ ጊዜዋ የደረሰችን ሴት "Bridal Shower , Baby Shower " እየተባለ በቅርብ ወዳጆቿ ትጎበኛለች። ለሠርጓ ጊዜ እና በወለደች ወቅት የምትጠቀምባቸውን የተለያዩ ስጦታዎች ያቀርቡላታል ፡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀው ቅርበታቸውን በተግባር ያረጋግጡላታል። እርግጥ ነው በፈረንጅኛ ልሳን መጠራታቸው ባህላዊ መሰረታቸው ከውጭ የተኮረጀ ይምሰል እንጅ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ስያሜዎች በአገራችን የሚተገበሩ ናቸው። እርግጥ ነው ከሳይንስ ዝማኔ ጋር የመጣውና ዘመን አመጣሹ የተረገዘ ልጅን የ" ፆታ ማወቂያ ሸብረብ " ወይም "Gender Reveal Party" በአገራችን ብዙ አልተለመደም። ሌሎቹ ግን በአገራችን ይከወናሉ። እናቶች በተለይ ለእርግዝና ትልቅ ቦታ አላቸው። እኔ ባደኩበት አካባቢ የሰፈር ሴቶች ተሰብስበው የገንፎ እህል ያዘጋጁላታል። ገብሱ ተፈትጎ ፣ ተወቅጦና ተፈጭቶ የገንፎ እህል ማዘጋጀት ፣ ቅንጨ ከበቆሎ ወይ ከስንዴ ወይ ከአጃ እህል ማዘጋጀት ፣ ቆሎና ኑግ ማዘጋጀት ፣ የዳቦ እህል ማዘጋጀት በጥቅሉ ነፍሰ ጡሯ ወልዳ አራስ ቤት ስትቀመጥ ራሷ የምትመገባቸውንና ጠያቂ እንግዳ የሚቀማምሳቸውን ሁሉ ማሰናዳት የወዳጆች ስራ ነው። ታዲያ ተዘጋጅቶ ሲያልቅ ዘመን አመጣሹ "ቤቢ ሻወር" ላይ እንደሚደረገው ልብስ፣ የጨቅላ ማጠቢያ ሳህን ወይም ዳይፐር / በኛ አካባቢ የሽንት ጨርቅ / አይሁን እንጅ ቅቤ፣ እርጎና ሌሎች ባህላዊ መጠየቂያዎችን ከየቤታቸው አምጥተው ይሰጧታል ፣ ይቀቧታል። እንዲሁም የሰሩትን ገንፎ ቅምሻ አዘጋጅተው ይመርቋታል ፡ በሰላም እንድትገላገል ይመኙላታል። ይህ ትዝ ያለኝ Dereje Diressie የረሳሁት የገንፎ ቀመሳ የምርቃት ስያሜ ሮማን ታፈሰወርቅን ዋቢ አድርጎ ቤቢሻወር " የአጥር ወፍ አትስማሽ " መሆኑን ፅፎ አይቼ ነው። "ነፍሰጡር ሴት መውለጃዋ ሲዳረስ እና የገንፎ እህል ተፈጭቶ ወደቤት ሲገባ ሴት ጎረቤቶች፣ጓደኞችና ዘመድ አዝማድ ተጠርቶ ገንፎ ይበሉና "የአጥር ወፍ አትስማሽ" ብለው ይመርቃሉ። አጥር ላይ ያለች ወፍ ከጎረቤትም በጣም የቀረበች ስትሆን ድምፅን ቶሎ ትሰማለች። ምጥ በመጣ ግዜ ነፍሰጡሯ ህመሙ ሳይፀናባት፣እንኳን ጩኸቷን ሌላ ሰው ይቅርና የቅርቧ የአጥር ወፍ እንኳን ሳትሰማት በሰላም ትውለድ ማለት ነው። ባጭሩ ምጧን ቀላል እንዲያደርግላት መመኘት ነው":: እና የከተማ እህቶቻችን የምን " ቤቢ ሻወር " ነው። ይልቅ "የአጥር ወፍ አትስማሽ!" በሉ። እናንተንም የአጥር ወፍ አትስማችሁ !! #ደመቀ_ከበደ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Показати все...
👍 62 18💩 5👏 4😁 3💯 3🤝 2 1
👍 7👏 2💯 1
መልካም የእናቶች ቀን በምዕራቡ ዓለም ሚያዝያ ወር በገባ በሁለተኛዉ ሳምንት እሁድ የእናቶች ቀን በሚል፤ እናትን በማወደስ ለእናት ልዩ ምስጋና በማቅረብ፤ በድምቀት የማክበር፤ የማሰብ ባህልና የተለመደ ነዉ። የእናት ቀን አከባበር መነሻዉ ከዩኤስ አሜሪካ መሆኑና፤ በአሁን ግዜ በበርካታ ሀገሮች ቀኑን የማክበር ባህል መለመዱን ዘገባዎች ያመላክታሉ።
Показати все...
👍 34 21🍾 2💊 2💯 1🆒 1
👍 38 5 3❤‍🔥 3👏 1💯 1🆒 1
👍 14👏 5😭 5💯 3 2 1