uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

Seid Social

Seid Social

Відкрити в Telegram

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Seid Social

Канал Seid Social (@seidsocial) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 23 228 підписників, посідаючи 10 152 місце в категорії Новини і ЗМІ та 1 521 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 23 228 підписників.

За останніми даними від 10 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 26, а за останні 24 години на 0, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 33.00%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 21.30% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 7 661 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 4 945 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 130.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 11 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Новини і ЗМІ.

23 228
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+2630 днів
Архів дописів
አሰብ ቢያንስ በቀናት ቢበዛ በሳምንታት ውስጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ትገባለች። በዛሬው እለት መከላከያ ሰራዊታችን ከቡሬ ተነስቶ ወደ አሰብ የምትወስደውን ስትራቴጂካዊቷን ደባሲማ ን
አሰብ ቢያንስ በቀናት ቢበዛ በሳምንታት ውስጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ትገባለች። በዛሬው እለት መከላከያ ሰራዊታችን ከቡሬ ተነስቶ ወደ አሰብ የምትወስደውን ስትራቴጂካዊቷን ደባሲማ ን መቆጣጠሩ ምን ያክል ፈጣን የመልሶ ማጥቃ እና ማጥቃት እንቅቃሴ ላይ እንዳለ ያሳያል። ደባሲማ በኤርትራ ውስጥ የምትገኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነች። በነገራችን ላይ የመከላከያ ሰራዊት ግዙፉ ሀይል ያለው በዚህ ግንባር ነው። ዛሬ አድዋን መከላከያ ሰራዊት ከተቆጣጠረ በሗላ ሰለኽለኻን ይዞ አዲ ዳእሮን አልፎ ኤስትራ ድንበር ደርሷል። አክሱምም ምናልባት በሰአታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ትውላለች።ይህም ትግራይ ክልልን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠሩ ሂደት በትንሽ ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል። ዛላምበሳና ፋፂም መከላከያ ይዟቸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቀጣይ ሊወስዳቸው ከሚችላቸው እርምጃዎች ውስጥ በአስመራ የሚገኙ የኤርትራ ጦር ተቋማትን ማውደምና አየር ሀይሏን ፓራላይዝድ ማድረግ ይሆናል። ኢትዮጵያ አስመራን ታጠቃለች ተብሎ ስለተፈራ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ዜጎቻቼው ወደ ኤርትራ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂ የሰጡ ሲሆን አስመራ ያሉትም ከኢምባሲ አቅራቢያ እንዳይርቁ አሳስበዋል። መከላከያ ሰራዊታችን በእውነቱ እንደት የሚያኮራ ተቋም ነው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ፋኖ በገባባቸው የቡብ ወሎ ቀበሌዎች ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ምዝበራና ዘረፋ እየፈፀመ ይገኛል። ከዚህም መካከል 👉 ልጆቻቼው አረብ ሀገር ያሉ ወላጆች በልጆቻቼው መጠን በእያንዳንዳቸው ከ 20
ፋኖ በገባባቸው የቡብ ወሎ ቀበሌዎች ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ምዝበራና ዘረፋ እየፈፀመ ይገኛል። ከዚህም መካከል 👉 ልጆቻቼው አረብ ሀገር ያሉ ወላጆች በልጆቻቼው መጠን በእያንዳንዳቸው ከ 20 እስከ 30 ሺህ ብር እየተቀበለ ይገኛል 👉 ከማህበረሰቡ የቀለብ በማለት ጤፍ ስንዴ እየወሰደ ይገኛል! 👉 የሚታረዱ እንሰሳትንም እየወሰደ ይገኛል! 👉 እናቶች የሚጋግሩትን እንጀራ ሳይቀር እየወሰዱ ቤተሰብ ጦም እያሳደሩ ይገኛሉ። ይሄ የሽፍታ ስብስብ ይህንን ካላደረጋችሁ እገታ እንፈፅማለን በማለት እያስፈራሩ ሲሆን ማህበረሰቡ በከፍተኛ እንግልትና ስቃይ ላይ ይገኛል። በመሆኑም የሚመለከተው አካል ሁሉ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በስቃይ ውስጥ ላለው ህዝባችን መፍትሄ ይሻ ዘንድ ጥሪየን አቀርባለሁ! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የሳኡዲን ኤርፖርት ጥቃት አስመልክቶ አጫጭር አዳዲስ መሰጃዎች ፨ በሪያድ ኤርፖርት ላይ የደረሰው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተከትሎ ሳኡዲ አየር ማረፊያውን ሙሉ ለሙሉ ዘግታለች! ፨ በጥቃቱ በደረ
+1
የሳኡዲን ኤርፖርት ጥቃት አስመልክቶ አጫጭር አዳዲስ መሰጃዎች ፨ በሪያድ ኤርፖርት ላይ የደረሰው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተከትሎ ሳኡዲ አየር ማረፊያውን ሙሉ ለሙሉ ዘግታለች! ፨ በጥቃቱ በደረሰው ጉዳት በርካታ ሰው መጎዳቱን ተከትሎ የሪያድ ሆስፒታሎች በከፍተኛ ሁኔታ ለተጎጂዎች ህክምና እንዲያቀርቡ ሳኡዲ አዛለች! ፨ ጥቃቱን ተከትሎ ሁሉም የአለም አየር መንገዶች ወደ ሳኡዲ ዋና ከተማ ሪያድ የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል። ፨ ከጥቃቱ በሗላ አስተያየት የሰጠው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በሁቲዎች ላይ ለሚደረገው ጦርነት ሳኡዲ አረቢያን ልትቀላቀል ትችላለች ብሏል። በኢራንም ላይ ጦርነቱን ዳግም ለመጀመር እያጤንን ነው ብሏል። ፨ የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች ወደ ሪያድ የሚደረግ የሰብአዊና አደጋ ጊዜ በረራ የግድ የነርሱን ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት አሳስበዋል። ፨ አለምአቀፍ እውቅና ያለውና በሳኡዲ የሚደገፈው የየመን መንግስት ጦር ባበል መንደብን ከየመን ሁቲዎች ለመንጠቅ እየተዋጋ እንደሚገኝ ገልፆ በዚህም ድሎችን እያገኘ ወደፊት እየገፋ መሆኑን አስታውቋል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የሳኡዲ አረቢያ ሪያድ አየር ማረፊያ በአሁኑ ሰአት በከፍተኛ ፍንዳታ እየተናወጠ እንደሆነ አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን በስፋት እየዘገቡ ይገኛሉ። የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች የሳኡዲ ዋና ዋና ተቋማትን መ
+1
የሳኡዲ አረቢያ ሪያድ አየር ማረፊያ በአሁኑ ሰአት በከፍተኛ ፍንዳታ እየተናወጠ እንደሆነ አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን በስፋት እየዘገቡ ይገኛሉ። የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች የሳኡዲ ዋና ዋና ተቋማትን መምታትን ኢላማ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥቃቶቻቼው የሪያዱ ንጉስ ኻሊድ አየር ማረፊያ ዋና ኢላማቸው ሆኗል። ከአንድ ቀን በፊት እዚሁ አየር ማረፊያ ላይ በፈፀሙት ጥቃት የሳኡዲውን ፓይለት ጨምሮ ሌሎችም የተገደሉ ሲሆን በጥቃቱ አንዱ የሳኡዲ አይሮፕላን መውደሙ ይታወቃል። ጥቃቱ ዛሬም በከፍተኛ ሁኔታ የተፈፀመ ሲሆን እስካሁን ከ 81 በላይ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተዘገበ ሲሆን የጉዳቱ መጠን ገና አልታወቀም። ይህ ጥቃት የሳኡዲን ኢኮኖሚያ እና ቱሪዝም እንዳይጎዳው አስግቷታል። ጦርነቱ በተኩስ አቁም የማይቋጭ ከሆነ ሁለቱም ሀይሎች የሚከፍሉት ዋጋ እየከበደ ሂዷል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

መከላከያ ሰራዊታችን በዚህ ጦርነት ያሳካው ትልቁ ድል በጦር ሜዳ ላይ ማሸነፉ አይደለም! የመከላከያ ሰራዊትም የመንግስትም ትልቁ ድል የትግራይን ህዝብ ልብ ማሸነፉ ነው። አዎ በዚህ ጦርነት እጅግ የሚ
+3
መከላከያ ሰራዊታችን በዚህ ጦርነት ያሳካው ትልቁ ድል በጦር ሜዳ ላይ ማሸነፉ አይደለም! የመከላከያ ሰራዊትም የመንግስትም ትልቁ ድል የትግራይን ህዝብ ልብ ማሸነፉ ነው። አዎ በዚህ ጦርነት እጅግ የሚያስደስተውና ትልቅ ተስፋ የሚሰጠው ነገር ይህ ነው። በዚህ ልክ መከላከያ ሰራዊትን በደስታና የደስታ ፌሽታ የተቀበለ ህዝብ የለም። ይህም የትግራይ ህዝብ የህወሐትን ክፋት ምን ያክል እንደተረዳ ሰላም ምን ያክል እንደተጠማ ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያዊነት መንፈሱ ተዳፈነ እንጅ እንዳልጠፋ ማሳያ ነው። ይህ ድል የትግራይ ወጣትን ተስፋ ያለመለመ ፤ የትግራይ እናቶችን ሰቀቀን ያቀለለ ፤ የትግራይ ማህበረሰብን ሰላም የማግኘት ተስፋ የዘራ ድንቅ ድል ነው። በተለይም መከላከያ ሰራዊቱ በሚያደርገው ጉዞ ያሳየው ድስፕሊን ፣ ሰብአዊነት ፤ ንፁሀንን መጠበቅና ህዝብን ማስቀደም የትግራይ ህዝባችን ከጠበቀው በላይ በመሆኑ እንዲህ በደስታ ሊቀበለው ችሏል። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ ምእራፍን የሚከፍት ነው። የትግራይ ህዝብ ለምቶ አድጎ የኢትዮጵያ የእድገት ሞተር እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም። ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ስትሆን ደግሞ ከማንም በላይ የትግራይ ህዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ዛሬ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጦርነት እንደምታውጅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳውቃለች ። ለተፈፀመብኝ ሁሉን አቀፍ ወረራ ሁሉን አቀፍ የጦርነት ምላሽ እሰጣለሁ ብላለች። በዚህም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ሊጀመር ቀናቶች ይቀሩታል ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል። የኢትዮጵያ ጦር አሁን ላይ ትግራይን ከህወሓት እና ሸእቢያ ለማፅዳት የሚያደርገውን ዘመቻ ወደ ማጠናቀቅ እየተቃረበ መሆኑን ተከትሎ ኤርትራ ላይ ለሚወስደው እርምጃ ትልቅ መስፈንጠሪያ ሆኖለታል። ወደ ኢትዮጵያ የገባው አብዛኛው የኤርትራ ሰራዊትም ስለተደመሰሰ የኢትዮጵያን ጦር ግስጋሴ በከፍተኛ ደረጃ አፋጥንታል። አሁን ላይ መከላከያ ሰራዊቱ ከትግራይ ሰላም ሀይል ጋር በመሆን ያልተቆጣጠራቸው ትላልቅ ከተሞች አክሱም እና አድዋ ብቻ ናቸው። መከላከያ ሰራዊቱ እየተከተለ ያለው በቴክኖሎጂ እና በከፍተኛ የጦር ስልት ማጥቃት በትንሽ መስዋዕትነት እና መቋቋም ከፍተኛ ድልን እንዲጎናፀፍ አድርጎታል። በዚህም መከላከያ ሰራዊቱ ኤርትራ ሲገባ የሚገባው በአካልም በጦር መሳሪያ አቅርቦትም ምንም አይነት ጉድለት እና ድካም ሳያጋጥመው ነው። የተማረከው የጦር መሳሪያ መአት ሌላ መከላከያ መገንባት የሚያስችል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። እናም ኤርትራ ፀመቺው ስህተት እና የተሳሳተ ስሌት በእጅጉ ተፀፅታለች። ለህወሓት እና ፋኖ የጦር ጥምረት የሰጠቺው የተጋነነ ድምዳሜ ኤርትራን ወደማትወጣው አሮንቃ ውስጥ ከቷታል። አሁን ኢትዮጵያ አልገባሁም ድንበር አልጣስኩምና ጦርነቱን አስቁሙልኝ እያለች እየተማፀነች ነው። ግና የኤረትራን ጦር አለም ሁሉ ስላየው ማስተባበያዋ ውሀ የማያነሳ ነው። አሁን ኤርትራ ያላት አማራጭ አንድ ብቻ ነው እርሱም በ ሗላቀር ጦሯ ዘመማዊውን የኢትዮጵያ ጦር መጋፈጥ! ይህ ጦር ተልእኮውን ለመወጣት እየተመመ ነው። ፍጥነቱም በእጅጉ አስገራሚ ነው። በሳምንት ውስጥ ከቆቦ ተነስቶ አዲግራት መድረስ ማንን ነው ላያስገርም የሚችለው!?? ጦርነቱ ሲደመር ኤርትራ የምታጣው አሰብን ብቻ አይደለም ኤርትራነቷን ጭምር እንጅ! ይህንን ደግሞ የኤርትራ ህዝብ በጉጉት ይጠብቀዋል! የተጋነነ ሊመስላችሁ ይችላል ግና ከኢሳያስ እስርቤት ለመገላገል የኤርትራ ህዝብ የኢትዮጵያን ጦር ይጠብቃል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ደስት ጥዶ ማልቀስ እንዲሉ የሸእቢያ ጦር ሲያቀብጠው ገብቶ በየመንገዱ እንዲህ ከስሎ ቀርቷል! ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የተዳፈሩትን እያደቀቀ ፤ የሚጠሉትን እና የሚንቁትን በብስጭት እያቃጠለ የትግራይን ህዝብ በደስታ እያስቦረቀ ወደፊት ብቻ እየተመመ ነው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የሳኡዲ አረቢያና የየመን ጦርነት ወደለየለት የቀውስ ምእራፍ ሲሸጋገር የሳኡዲ አረቢያ አየር ማረፊያዎች በርካታ እና አስደንጋጭ ውድመቶችን እያስተናገዱ ይገኛሉ። በትላንትናው እለት የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች በሳኡዲ አብሀ አየር ማረፊያ ላይ በፈፀሙት የሚሳኤል ጥቃት 3 ሰዎች ሲገደሉ 37 ደግሞ የቆሰሉ ሲሆን አየር ማረፊያውም ከፍተኛ ውድመትን አስተናግዷል። በዛሬው እለት በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ አየር ማረፊያ ላይ እንዲሁ በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት የሳኡዲው ግዙፉ ኤርባስ A321_200 አይሮፕላን የወደመ ሲሆን ምን ያክል ሰው የጥቃቱ ሰለባ እንደሆነ አልተገለፀም። የሚሳኤል ጥቃቶቹ የአራምኮ የነዳጅ ማእከላትንም አውድሟል። የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ኢንጅነሮችና ሰራተኞችና የተቋም አመራሮች የነዳጅ ማእከላትን እና አየር ማረፊያዎችን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰቡ ሲሆን ከመካ እና መዲና ውጭ የሚደረጉ የሳኡዲ በረራዎችን እንደሚያግዱም አስታውቀዋል። ይህን ተከትሎም የተለያዩ አየር መንገዶች ወደ ሳኡዲ የሚደረጉ በረራዎችን እያቆሙ ሲሆን የሉፍታንዛ አየር መንገድ ቀዳሚው ሆኗል። የህንድ አየር መንገድም ወደ ሳኡዲ የሚያደርገውን በረራ አቋርጧል። ይህን ተከትሎ ሳኡዲ አረቢያ በየመን ሁቲዎች ላይ በብዙ እጥፍ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ የዛተች ሲሆን የሁቲዎችን ኢላማዎች ስትደበድብም ውላለች። ሳኡዲ ከባድ አፀፋ እንደምትመልስ አስጠንቅቃለች። ፈረንሳይና ሳኡዲ አረቢያ የያንቡ የነዳጅ ማጣሪያን በጋራ በሚከላከሉበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ መሆኑን ፈረንሳይ ገልፃለች። ያንቡ በቀይ ባህር የሚገኘው የሳኡዲ ዋና የነዳጅ ማእከል ሲሆን ከሁቲዎች ጥቃት ለመከላከል ሁለቱ ሀገራት እየመከሩ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል። አሜሪካ በሳኡዲ አረቢያ ለሚገኙ ዜጎቿ የማስጠንቀቂያ መልእክት አስተላልፋለች። የየመን ሁቲዎች ጥቃትን መባባስ ተከትሎ የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሜሪካ አሳስባለች። የጦርነቱን መባባስ ተከትሎ ኢራን ሳኡዲ እና ሁቲዎችን ለማደራደር እያደረገቺው ያለው ጥረት ሊከሽፍ እንደሚችል መገናኛ ብዙሀን በስፋት እየዘገቡ ይገኛሉ። የሁለቱ ሀይሎች ጦርነት ቶሎ የማይረግብ ከሆነ ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ሸእቢያ ጦርነቱ ሙሉ እንዲደረግ የፈለገው ትግራይ ውስጥ ነበር። በትግራይ መሬት በትግራይ ህዝብ ላይ በትግራይ ደም እርሱ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ሊመታ! ለበቀልም ለሚዛንም! ህወሐት ደግሞ ጦርነቱ
+1
ሸእቢያ ጦርነቱ ሙሉ እንዲደረግ የፈለገው ትግራይ ውስጥ ነበር። በትግራይ መሬት በትግራይ ህዝብ ላይ በትግራይ ደም እርሱ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ሊመታ! ለበቀልም ለሚዛንም! ህወሐት ደግሞ ጦርነቱ እንዲደረግ ያሰበውና የተዘጋጄው አማራ ክልል ላይ ነበር። እዚህም በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለሙምታት! በአማራ መሬት በአማራ ህዝብ ላይ በአማራ ደም! ከዚያ ክልሉ ይወድማል ማለት ነው። መከላከያ ትግራይ ሳይሻገር አማራ ላይ እየተላለቀ ህወሐት ፍፃሜውን ሊጫወት። ሁለቱም ሲዳከሙለት አማራ ላይ ቀሩኝ ያላቸውን ግዛቶች ወስዶ ሊገነጠል። የአማራ ፋኖ ደግሞ ጦርነቱ እንዲደረግ የሚፈልገው ወሎ ላይ ነው። በወሎ ህዝብ ላይ በወሎ ግዛት ህዝቡን እያደቀቀ ሊበቀል! አሁን መከላከያ ሰራዊት ወደፊት መጓዙን ተከትሎ ፋኖ በወሎ ላይ የያዘውን ቂም ይዞ ወረዳ እና ቀበሌዎችን እየሰረቀ እያወደመ ነው። ይህ ሀይል እንደማያሸንፍ በገባበት ቦታ ቀናት በላይ እንደማይቆይ ያውቀዋል። ስለሆነም የቡድኑ አላማ ባገኘው አጋጣሚ ገብቶ አውድሞ ዘርፎ ገድሎ መውጣት ነው። ይህንን በወሎ ህዝብ ላይ እያደረገ ነው። በከለላ በመቅደላ በመካነሰላም በለገሂዳ ወረዳ በማጀኙ ቀበሌዎች ላይ ይህን እያደረገ ነው። ለፋኖም ሆነ ለአማራ ብሔርተኞች ከወሎነት በላይ የሚጠሉት የለም። እንኳን ህዝቡ ስሙ ይቀፋቸዋል። በመሆኑም አሁን ላይ ያለውን መላቀቅ ተከትሎ በቀረቻቼው ጊዜና አቅም መበቀል የሚፈልጉት የወሎን ህዝብ ነው። የወሎ ህዝብ ደግሞ ያን ያክል ጠንካራ ብሔርተኝነት ስለሌለውና የበርካታ ማንነት ስብጥርም ስለሆነ በአንድነት ይሄን እየዘረፈ የሚሄድ እያወደመ የሚሸሽ ሀይል ለመመከት የሚያስችል ዝግጅትም ንቅናቄም እያደረገ አይደለም። በመሆኑም ሽፍታዎቹ በየጊዜው እየመጡ ዘርፈው ለመሄድ እየቻሉ ይገኛሉ። 👉 t.me/Seidsocial

ኤርትራ ውስጥ ኔትወርክም ኢንተርኔትም ስለሌለለ ከአለምም የተነጠሉ ስለሆኑ የሸእቢያ ወታደሮች ዘመኑ የደረሰበትን የውጊያ መራቀቅ አላወቁትም። የዘመኑን የድሮን የጦርነት መራቀቅና የቴክኖሎጂ ልህቀትም
+1
ኤርትራ ውስጥ ኔትወርክም ኢንተርኔትም ስለሌለለ ከአለምም የተነጠሉ ስለሆኑ የሸእቢያ ወታደሮች ዘመኑ የደረሰበትን የውጊያ መራቀቅ አላወቁትም። የዘመኑን የድሮን የጦርነት መራቀቅና የቴክኖሎጂ ልህቀትም አልተረዱም። ለዚያም ነው በክፍት የጭነት መኪና እየበረሩ መጥተው ከስለው የቀሩት። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የሌላት የድሮን አይነት የለም። ከኢራን ድሮኖች እስከ ቱርኮቹ ባይራክታር ቲቢቱ እና አኪንጂ ድሮኖች ፤ ከሩሲያው ኦሪዮን ድሮኖን እስከ ቻይናው ዊንግሎንግ ድሮን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ስካይዊን እና ነጋሽ ድሮኖችን በአስርሺዎች የታጠቀች ሀገር ነች። እና ሗላቀሩ የኤርትራ ጦር ይሄንን ዘመናዊ ሀይል የመጋጠም አቅሙ ባይኖረውም የድሮ የሽምቅ ውጊያ ብቃቱ ዛሬም ይሰራ መስሎት ወታደሮቹን የእሳት እራት አድርጓቸው አርፏል። የሸእቢያ ጦር ከነ ተሽከርካሪዎቹ ከስሎ ሲታይ ወደፊት ለሚያደርገው ጦርነት ከፍተኛ የሞራል ስብራት የሚፈጥርበት ነው። የሸእቢያ ጦር ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ በይፋ ጥሶ መግባቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስጦታ ተደርጎ ተወስዷል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

በጣሊያን ወረራ ጊዜ በርካታ አርበኞችን ከድተው በጣሊያን ጦር በማስገደል የጎጃሙን ገዢ ራስ ሀይሉ ተክለሃይማኖትን የሚስተካከላቸው የለም ነበር። የጎጃሙ ገዢ ራስ ሀይሉ ታላቁን የአርበኞች መሪ ራስ ደ
+1
በጣሊያን ወረራ ጊዜ በርካታ አርበኞችን ከድተው በጣሊያን ጦር በማስገደል የጎጃሙን ገዢ ራስ ሀይሉ ተክለሃይማኖትን የሚስተካከላቸው የለም ነበር። የጎጃሙ ገዢ ራስ ሀይሉ ታላቁን የአርበኞች መሪ ራስ ደስታ ዳምጠውን ጨምሮ በርካታ የጥቁር አንበሳ አርበኞችን አስበልተዋል። ይሄ ሀገርን መክዳት በነ ኢህአፓም ጊዜ ቀጥሎ ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ የኢትዮጵያን ወታደር ከሗላ በመርዝ ይገድሉ ከሗላም ይወጉ ነበር። እና ባንዳነት እዚህች ሀገር ላይ አዲስ አይደለም። ዛሬም ያ ባንዳነት ያልተፋታቸው እነ ዘመነ ለሸእቢያ እየተገረዱ ብታይዋቸው አትገረሙ! በስልጣን ሲያኮረፉ ሀገርን መክዳት በዚህች ሀገር አዲስ አይደለምና! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ከ October 7 በሗላ በህይወቴ ትልቅ የአመለካከት ለውጥ ከጣሉብኝ ክስተቶች አንዱ ነው። 👉 ሰው በዚህ ልክ ይፀናል ብየ በፍፁም አስቤ አላውቅም። የነብያትና ያለፉ ሷሊሆችን ፅናት ሳነብ እንኳ አ
+2
ከ  October 7 በሗላ በህይወቴ ትልቅ የአመለካከት ለውጥ ከጣሉብኝ ክስተቶች አንዱ ነው። 👉 ሰው በዚህ ልክ ይፀናል ብየ በፍፁም አስቤ አላውቅም። የነብያትና ያለፉ ሷሊሆችን ፅናት ሳነብ እንኳ አሁን ጋዛ ላይ በማየው ልክ ይሆናል ብየ አስቤ አላውቅም ነበር። እንድህ ያለ ፅናት እንድህ ያለ ጀግንነት እንድህ ያለ የቂን ለኔ ሊገባኝ የሚችል አይደለም። 👉 ከሃይማኖታዊ ወንድማማችነት ሰብአዊ ወንድማማችነት በልጦ ያየሁበት አስገራሚ ክስተት ነው ለኔ ይህ ሁለት አመት። ከአረቦች እና ሌሎች ሙስሊም ህዝቦች ይልቅ ክርስቲናኖቹ ስፔይኖች ፤ ኢሪሾች ፤ ጣሊያኖች ፣ ሜክሲኮዎች የስካነዲናቪያንስ ህዝቦች ስለ ጋዛ ሲታመሙ ሲጮኹ ሲታገሉ ያየሁበት ነው። በጣም ልብ የሚነኩ ድጋፎችን ከኒውዚላንድ እስከ ኔዘርላንድ ያየንበት የሰብአዊነትን የእዳ ክብደት ያየሁበት ነው። 👉 እንደ አሮን ቡሽኔል አይነቶቹን ሰዎች በምንም ልገልፃቸው አልችልም። ለፍልስጤማውያን ድምፅ ለመሆን ራሱን እንዴ ሻማ ላቀለጠው ለዚያ የልቤ ሰባሪ! ከዚያ ስንቶቹን አሳየን! ግሬታ ተንበርግ ፤ ጉስታቮ  ፔትሮ፤ ስሪል ራማፎዛ ፤ ጋሪ ሊንከር ፤ፔፕ ጋርዲዮላ ፤  ናሌዲ ፓንዶር ወዘተ 👉 እነ ደቡብ አፍሪካን ፤ ስፔይንን ፤ ብራዚልን ፤ አየርላንድን ፤ ኮሎምቢያ ከሙስሊም ሀገራት ይልቅ የጋዛ ጉዳይ እንቅልፍ የነሳባቸው ክስተት 👉 ከሱኒዎቹ ይልቅ ሺአዎቹ ሙስሊሞች ስለ ጋዛ ወንድሞቻቼው እየታገሉ ከባባድ መስዋዕትነትን የከፈሉበት። እነ ሰይድ ሀሰን ፤ ፉአድ ሹክሪ ፣ የየመን አመራሮች ፤ እነ ሀሺም ሶፊዩዲን ስንቱን እንቁዎቻቼውን ሰው! 👉 እስራኤል ካለ አሜሪካና አጋሮቿ እገዛ አንድም ጦርነት እንደማታደርግ ዳግም ያረጋገጥንበት 👉 ትግስቴ ኢማኔ እጅግ የተፈተነበት ተስፋ የሚያስቆርጡ ስሜቶች ውስጥ የተዘፈቅኩበት 👉 የክህደትን ህመም የኺያናን መሪርነት ያየሁበት!

እንግዲህ ኤርትራ ኢትዮጵያን መውረሯን በአለምአቀፍ ደረጃ ተረጋግጧል። ይህ ለኢትዮጵያ መንግስት ትልቅ ስጦታ ይመስለኛል። ነገሮቹን ሁሉ ያቀልለታል። ግንባሩም አንድ ይሆንለታል። ኤርትራም በራሷ ጊዜ ወ
+2
እንግዲህ ኤርትራ ኢትዮጵያን መውረሯን በአለምአቀፍ ደረጃ ተረጋግጧል። ይህ ለኢትዮጵያ መንግስት ትልቅ ስጦታ ይመስለኛል። ነገሮቹን ሁሉ ያቀልለታል። ግንባሩም አንድ ይሆንለታል። ኤርትራም በራሷ ጊዜ ወረራውን ጋብዛለች። በመሆኑም ከዚህ በሗላ በኢትዮጵያ በኩል የሚደረጉ ጦርነቶች "የኤርትራን ወረራ ተከትሎ" ተብለው ነው በአለምአቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የሚነገሩት። ኤርትራ የባድመ ጦርነት ሽንፈቷን በነ መለስ ሸፍጥ ድናለች። ልትፈርስ የነበረቺውን ኤርትራም መለስ ዜናዊ አድኗት ነበር ያኔ። ዛሬ የሚያድናት አይኖርም! የኢትዮጵያ ጦር አቅጣጫ አሰብን ከመያዝ ሙሉ የሸእቢያ መንግስትን ወደ ማፍረስና የቀጠናውን ካርታ ወደመቀየር ይሸጋገራል። ድል ለጀግናው የሀገሬ መከላከያ ሰራዊት! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የመንደር ሽፍታው ፋኖ የመከላከያ ሰራዊትን ወደ ሰሜን መትመም ተከትሎ ሽፍታዎቹን አሰባስቦ የምእራብ ወሎ ወረዳዎችን ለማጥቃት እየተዘጋጄ መሆኑንና ለዚህም ጥንቃቄ ይደረግ በማለት ማስተላለፌ ይታወቃል።
የመንደር ሽፍታው ፋኖ የመከላከያ ሰራዊትን ወደ ሰሜን መትመም ተከትሎ ሽፍታዎቹን አሰባስቦ የምእራብ ወሎ ወረዳዎችን ለማጥቃት እየተዘጋጄ መሆኑንና ለዚህም ጥንቃቄ ይደረግ በማለት ማስተላለፌ ይታወቃል። ያው እንደታሰበው ፋኖ በከለላ ወረዳ ወመካነሰላም አካባቢ ለዘረፋ እና ሽብር እየታገለ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ አፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን ከባድ ምት እያሳረፉበት ይገኛሉ። ይሄ ከመንደር ሽፍትነት የዘለለ ምንም አይነት አላማና ግብ የሌለው የወያላዎች ስብስብ በርግጥ ፀሀዩ እየጠለቀችበት ትሄዳለች። መንግስት ወጀቡን ካስወገደ በሗላ የመመንጠር ስራ እንደሚሰራ አያጠያይቅም። ጀግኖቹ የከላላ ወረዳ የቦረና ወረዳ ሚሊሻዎች ክብር እና አድናቆት ይገባቸዋል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ሰሞኑን በሳኡዲ አረቢያ የሚደገፈው የየመን ሀይል በበርካታ የሳኡዲ ጦር ጄቶች የአየር ድብደባ ሽፋን ታግዞ ባበል መንዲብን ለመቆጣጠር ተቃርቦ ነበር። በተለይም አል መኻ እና ዙባብ ከተሞችን መልሶ መቆጣጠርን ኢላማ ባደረገው ዘመቻ የሳኡዲ አየር ሀይል 100 የጦር ጄቶችን እንዳሳተፈ ተነግሯል። ውጤቱ ግን ከታች እንደምታዩት ነው የሆነው። በአየር አጀባ የገባው በሳኡዲ የሚታገዘው የየመን መንግስት ጦር ከነ ተሽከርካሪው መልሶ እንዳይመለስ ተደርጎ የድሮኖች ሲሳይ ነው የሆነው። ይህ ዘመን እጅግ እንቆቅልሽ የጦር ዘመን ነው። ከግዙፍ ውድ እና የተራቀቁ የጦር ጄቶች ይልቅ ትናንሽ ድሮኖች ካለምንም ኢላማ መሳት ግዙፍ ጦርን ባዶ እያስቀሩት ይገኛሉ። የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች ጦርም በዚህ መልኩ ከፍተኛ ውድመት በማድረስ ባበልመንዲብን ለመቆጣጠር የመጣውን ሀይል መመከትና መመለስ ችሏል። ጦርነቱ ታኢዝ ላይ በርትቶ የቀጠለ ሲሆን ሁቲዎቹ ታኢዝን መክበባቸው ተገልጿል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የፋኖ አብዮታዊ ትግል የአባታቼውን ቤተመንግስት አራት ኪሎን ለመቆጣጠር በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት የትግሉን ብስራት ማን ሊያበስረን ነው አሳየ ደርቤ የትግል ጫማ የሚሰቅለው🤔 አይ ተጧሪ😂 ይሄ የህ
የፋኖ አብዮታዊ ትግል የአባታቼውን ቤተመንግስት አራት ኪሎን ለመቆጣጠር በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት የትግሉን ብስራት ማን ሊያበስረን ነው አሳየ ደርቤ የትግል ጫማ የሚሰቅለው🤔 አይ ተጧሪ😂 ይሄ የህወሀት ተጋላቢ እስከዛሬ ህወሐት ካምፓላ አስቀምጣ ቀለብ እየሰፈረችለት ነበር በል ያለቺውን የሚለው። አሁን ህወሓት አቅሟን በመጨረሷና የርሱ የመሃይም ፕሮፓጋንዳም ምንም የማይፈይድ መሆኑን አውቃ ቀለቡን ስታቋርጥበት እርሱም ቀደዳውን አቁሞ ቻው ብሎ ተሰናበተ። ባንዳዎች ሳንቲም ሲያስገቡላቸው ብቻ የሚንኳኩ የድሮ ስልኮች ናቸው። ሲያቆም ያቆማሉ። ግና ታሪካቸውም የጥላሸትና የውርደት ሆኖ ይኖራል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ይህ የዛሬው የህወሐት ጦር ምርኮ ነው። የህወሓት ጦር ይሄን ሁሉ መሳሪያ እያስረከበ የሚማረከውና የሚበተነው የመዋጋት ሞራሉ በከፍተኛ ሁኔታ ስለተመታ ነው። ለአንድ ጦር ሀይለኛ ተዋጊነት የሚዋጋበት ኮ
+5
ይህ የዛሬው የህወሐት ጦር ምርኮ ነው። የህወሓት ጦር ይሄን ሁሉ መሳሪያ እያስረከበ የሚማረከውና የሚበተነው የመዋጋት ሞራሉ በከፍተኛ ሁኔታ ስለተመታ ነው። ለአንድ ጦር ሀይለኛ ተዋጊነት የሚዋጋበት ኮዝ አንዱ ወሳኝ ነገር ነው። በአንድ ጦር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቁጭትና የሚሰዋለት አላማ ካለው በፅናት እስከመጨረሻው ይዋጋል። ይህን አሁን የህወሓት ተዋጊዎች ላይ የለም። ብዙዎቹ ተገደው እና ታፍሰው እንዲዋጉ የተደረጉ በመሆኑ አጋጣማውን ሲያገኙ ይፈርሳሉ። የትግራይ ወጣት አሁን ባኗል። ለአርጊት ባለስልጣናት ስልጣን ሲል ህይወቱን የሚገብርበት ምንም ምክንያት የለም። የትግራይ ህዝብ ሰላምና ጥቅምም በጦርነት እንደማይመለስ በሚያስገርም ሁኔታ የትግራይ ህዝብ ተረድቷል። ይህንን ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሀይል ሊያውቅ ይገባል። በጦርነት የሚረጋገጥ የህዝብ ሰላምም ጥቅምም የለም። የትኛውም ሀይልም ከመከላከያ ሰራዊት ፊት ቆሞ ሊዋጋ የሚያስችለው አቅም የለውም። የትግራይ ሰላም በአጠቃላይ የሀገራችንም ሰላም ሙሉ በሙሉ እንደሚረጋገጥ ተስፋ አደርጋለሁ። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

አዘርባይጃን በሀይል የተወሰደባትን ናጎርኖ ካራባኽን ከ 30 አመታት በሗላ እንዳስመለሰቺው ሁሉ ኢትዮጵያም በሸፍጥና ደባ ፤ በውጭ ጠላቶቿ እና የውስጥ መሰሪዎቿ ያጣቻቼውን ግዛቶች ከ 30 አመታት በሗ
አዘርባይጃን በሀይል የተወሰደባትን ናጎርኖ ካራባኽን ከ 30 አመታት በሗላ እንዳስመለሰቺው ሁሉ ኢትዮጵያም በሸፍጥና ደባ ፤ በውጭ ጠላቶቿ እና የውስጥ መሰሪዎቿ ያጣቻቼውን ግዛቶች ከ 30 አመታት በሗላ ታስመልሳለች። ታሪክ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ይቀየራል። ይህ ትንቢትና ምኞት አይደለም። ዘመቻና የትግልም እውነታ ነው። ካለምንም መቋቋም የተመመው ጀግና የመከላከያ ሰራዊታችንም የሚቆመው ቀይ ባህር እንጅ ሌላ አይደለም። እነ ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ ተሰማ መስዋዕትነት የከፈሉላት እነ ጀኔራል ሁሴን አህመድ እስከ መጨረሻዋ እንጥፍጣፊያቸው የታገሉላቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ካለ ጥርጥር ይመለሳሉ። ይህን ድል እናያለን! መቼ ? በቅርብ ጊዜ! ያኔ ባንዳዎች ተቃጥለው ይከስላሉ! ጠላቶቿም ይንበረከካሉ! እንደዚህ አመቺ ወቅት ተገኝቶ አያውቅምና ይህ ጀግና ሰራዊትም አጋጣሚውን ይጠቀማል! ከፊቱ የሚቆምም ሀይል አይኖርም! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

መከላከያ ሰራዊት 2013ስ ላይ ገብቶ አልነበር ወይ አሁንም ተመሳሳይ ነገር እንጅ ሌላ አይገጥመውም የሚሉ አንድም መከላከያ ከጀርባው ይወጋል በሚል ተስፈኝነት ሁለትም መከላከያ እንዳይከዳ በሚል ወገንተኛ አሳቢነት የሚጠይቁ በርካታ ሰዎችን እያየን ነው። በኔ ምልከታ የ 2013ቱ እና ይሄኛው በጣም ይለያያል ነው። ለዚህም የተለያዩ ማሳያዎችን ማስቀመጥ ይቻላል። 1ኛ የመጀመሪያው የአሁኑ መከላከያ ሰራዊት ከያኔው ሰራዊት በጣም የሚለይ መሆኑ ነው። የአሁኑ በጣም የሰለጠነ ፣ በጣም የታጠቀ ፤ በአደረጃጄትም በልምድም በሚገባ የዳበረ ፤ በደህንነትና ስትራቴጂ በከፍተኛ ደረጃ የተዋቀረ በመሆኑ ከፊቱ መቆም የሚችል አማፂ ሀይል የለም። የ 2013ቱ ሰራዊት ጋር የነበረው ቁጭትና መከዳት የፈጠረው በቀል ነበር። ህወሐቶች ከመከላከያ ሰራዊቱ በትጥቅም በልምድ በካበተ ሰራዊትም በጦር መሪዎች ብዛትም ይልቁ ነበር። መከላከያ ያን ጦርነት የተዋጋው ለጡረታ የወጡ ጄኔራሎችን ጭምር አሰባስቦ ነው። ብዙው መሳሪያም ሰሜን እዝ ላይ ተወስዶበት ነው ወደ ጦርነቱ የገባው። እናም ያ እና ይህ ይለያያል ነው። 2ኛው ያኔ መከላከያ ሰራዊቱ የህወሐትን ጦር እንጅ የትግራይ ህዝብ ልብ ማሸነፍ አልቻለም ነበር የትግራይ አክታቪስቶችንም ፖለቲከኞችንም የሀይማኖት አባቶችንም ይሁንታ ማግኘት አልቻለም ነበር። ህወሓት በሰራው የተዋጣለት ፕሮፓጋንዳ የትግራይ ህዝብ መከላከያ ሰራዊትን እንደ ጠላትና ወራሪ እንዲቆጠር ማድረግ ተሳክቶለታል። ህዝብ የጠላው ሀይል ደግሞ ከጀርባው ይወጋል ይከዳል በሞራልም ይንኮታኮታል። እናም መከላከያንም ያጋጠመው ያ ነበር! አሁን ግን ህዝቡ መከላከያ ሰራዊቱ ገብቶ ያረጋጋው ሰላም ይሰጠው ዘንዳ በጉጉት ሲጠብቅ የቆየ ህዝብ ነው። አሁን መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለትግራይ ህዝብ መጤም ወራሪም አይደለም። አብሮ የገባው ከትግራይ የጦር አመራሮች የህወሓት የግፍ አገዛዝ እና የጦርነት አዙሪት የሰለቻቼው የትግራይ ተዋጊዎች አብረውት ነው የገቡት። እነ ጄኔራል ፃዲቃን ፤ አሰነ ጀኔራል ወዲ አንጥሩን ይዞ ነው የሚገባው። እነ ጌታቸው ረዳን ከጎኑ አሰልፎ በርካታ የትግራይ ፖለቲከኞችን ልብ አሸንፎ ነው ወደ ትግራይ ያቀናው። እናም አቀባበሉ የምታዩት ሆኖ ቀጥሏል። 3ኛ የሸእቢያ የአማራ ልዩ ሀይል እና ፋኖ የጦርነቱ አካል መሆን። መከላከያ ሰራዊት ያ ሰቅጣጭ መከዳት ሰሜን እዝ ላይ ከደረሰበት በሗላ የተረፈው መትረፍ የቻለው ወደ ኤርትራ በመሰደድ ነበር። ኤርትራም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ተቀብላ ስታስተናግድ ህወሓት የኤርትራ ጦርም መግባቱ አይቀርም በሚል ኤስትራም ህወሐት ጦርነቱን ካሸነፈ ቀጣይ ተረኛ እኔ ነኝ በሚል ወደ ጦርነቱ ዘው ብላ ገባች። እናም የሻእቢያ ጦር ትግራይ ሲገባ የፈፀመው የጦር ወንጀል ጅምላ ርሸና እና ዝርፊያ የትግራይን ህዝብ በማስቆጣቱ የትግራይ ህዝብ በነቂስ ከህወሓት ጎን እንዲሰለፍ አድርጎታል። የአማራ ሀይሎች መግባትም ነገሩን የብሔር ጦርነት መልክ አላብሶታል። አሁን ያ የለም። ወደ ትግራይ የገባ ክልላዊ ሀይልም ህነ ባእድ ሀይል የለም። አሁን የገቡት የትግራይ ህዝብም ተቋማት የሆኑት መከላከያ ሰራዊቱ እና የትግራይ ሰላም ሀይል ናቸው። በመሆኑም ህዝቡ የሚፈራበት የሚደነግጥበትና የመወረር ስሜት የሚሰማበት ምንም ምክንያት የለም። 4ኛ የአለምአቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍና የዲፕሎማሲ አሰላለፍ መለወጥ። በመጀመሪያው ጦርነት መንግስትን ከፍተኛ ቅርቃር ካስገቡት ነገሮች አንዱ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጫና ነበር አሁን ያ የለም። ከምእራቡ እስከ ምስራቁ አለም ሁሉም ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የግዛት አንድነትና ውህደት ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ የገለፁበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ይህ የመቀሌ ህዝብ መከላከያ ሰራዊት ወደ መቀለ ሲገባ ያደረገው አቀባበል ነው። መከላከያ ሰራዊት በገባበት ከተማ ሁሉ ባልተለመደ መልኩ እየተደረገለት ያለው የሞቀ አቀባበል የትግራይ ህዝብ ምን ያክል ለሰላም እንደተጠማ ማሳያ ነው። በዚሁ ቀጥሎ ህዝብና መንግስት እንዲህ ከተማመኑ የትግራይ ሰላም በመላው ህዝቧ እና በመንግስት ጥምረት ከተረጋገጠ ትግራይ የኢትዮጵያ አዲስ ምእራፍ ትልቅ አብነት ትሆናለች። የትግራይ ህዝብም ለመላው ኢትዮጵያን ትልቅ ትምህርትን የሚሰጡ ይሆናል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial