fa
Feedback
Seid Social

Seid Social

رفتن به کانال در Telegram

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Seid Social

کانال Seid Social (@seidsocial) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 23 161 مشترک است و جایگاه 10 134 را در دسته اخبار و رسانه‌ها و رتبه 1 481 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 23 161 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 17 سپتامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -166 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -8 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 32.06% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 18.40% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 7 429 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 4 264 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 124 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 18 سپتامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته اخبار و رسانه‌ها تبدیل کرده‌اند.

23 161
مشترکین
-824 ساعت
-177 روز
-16630 روز
آرشیو پست ها
አንድ ክርስቲያን ወገናችን "እንደው ከሙስሊሞች አነጋገር በጣም ልቤን የሚነካው " ለአላህ ብየ እወድሃለሁ " የምትዋ ንግግር ነች እና በርግጥ ትርጉሙን ብዙ አልተረዳሁትም ግን ቃሏን ስሰማት ውስጤን በጣም ይሰማኛል " ብሎ ሲናነር ሰማሁት። ከዚያ የርሱን አነጋገር እንደት እንዳጤነው ገረመኝና ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲንና ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ አንድ ላይ ሆነው ስለ ወንድማማችነት ኡኺዋ የሚያወጉበት ጣፋጭ ወግ ገጠመልኝና ላጋራችሁ ወደድኩ። ኡኹዋ በኢስላም ምሰሶ ነው። የማይናወጥ የአኼራም የአዱኒያም መሰረት ነው። የሀቅ ወንድማማችነትን አላህ ይወፍቀን!

ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲንን ስሰማ ነገሮችን የሚገልፁባቸውና ቅልል አድርገው የሚያብራሩባቸው መንገድ ይደንቀኛል። ሸይኻችን ብዙ ጊዜ ብይኖቻቼው ብዙ ጊዜ ከሸይኽ ሙሀመድ ሀሰን አልደደው ጋር ይመሳሰሉብኛል። ማክፈር ሙዝ የመላጥ ያክል የቀለላችሁ ደፋሮች ፤ ሰው ምንም ባለ ቁጥር አቂዳህ ምንድነው እያላችሁ አቃቂር የምታወጡ አቂዳ ያልገባችሁ ወንድሞቻችን ይህቺን ተህዚር እና ተብይን ስሟት! ትክክለኛ ድንበር ያላለፈ መንገድን ለመከተል እድሚያቸውን ሙሉ በኢልም የጨረሱትን ታላላቅ ኡለሞች ስሟቸው። ትጠቀማላችሁ ድንበርም አታልፉም! አለበለዚያ ግን ስድብና ሀሜት ማክፈርና ስለ ሰው መመዘን የበዛበት አስተምህሮ ውስጥ ሰጥማችሁ ከቀራችሁ ልባችሁም ይደርቅባችሗል እዝነትም ታጣላችሁ። አንድ ሰው ሙስሊሙን ወንድሙን በመሰለኝና በደሳለኝ በቀላሉ ከኢስላም ለማስወጣት የሚደፍረው እዝነት ሲያጣ ነው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ኳታር 2015 ላይ የነ ሳኡዲን ግንባር ተቀላቅላ በየመን ላይ ጦርነት ካወጁ የአረብ ሀገራት አንዷ ነበረች። እናም በዚያ ጦርነት ከ 250,000 በላይ የመናዊያን አልቀው ነበር። በሳኡዲ አረቢያ የሚመ
ኳታር 2015 ላይ የነ ሳኡዲን ግንባር ተቀላቅላ በየመን ላይ ጦርነት ካወጁ የአረብ ሀገራት አንዷ ነበረች። እናም በዚያ ጦርነት ከ 250,000 በላይ የመናዊያን አልቀው ነበር። በሳኡዲ አረቢያ የሚመራውና ግብፅን ፣ ኢማራትን ፣ ኩዌይትን ፣ ባህሬይንን ፣ ሱዳንን ፣ ሞሮኮን እንኳን ሌላው ቀርቶ ሴኔጋልን ሳይቀር በያዘውና በአሜሪካ የደህንነትና መሳሪያ ድጋፍ በሚመራው ያ ዘመቻ ኳታርም አብራ በመዝመት በየመናዊያን ላይ ያን ከበባና ጭፍጨፋ ከፈፀሙ ሀገራት አንዷ ሆኖ ነበር። የሚገርመው ታዲያ አብራቸው የዘመተቻቼው ሀገራት አስጠላሽን አሉና ወዲያው ተገልብጠው ከሁለት አመት በሗላ ዙሪያዋን ከበቧት። በባህርም በአየርም በየብስም ቆለፏት። ኳታር ኧረ ድረሱልኝ አዲኑኝ ብላ ለአሜሪካ እና ቱርክ እርዳታ ስታቀርብ ቱርክ በርካታ ጦሯን በመላክና የተቋረጠባትን የንግድ መስመር በመክፈት ታድጋት ነበር። አሜሪካም በሳኡዲና ኢማራት የሚመራው ከበባ ወደ ጦርነት እንዳያመራ በማሳሰብ በከበባ ብቻ እንዳቆም ተደረገ። ታዲያ ኳታር ዛሬም ከነ ሳኡዲ ጎን እያለቀለቀች ነው። ሚዲያዋን አልጀዚራን አቅጣጫ በመስጠት የሳኡዲን ፕሮፓጋንዳ ብቻ እንዲያስተጋባ አዛዋለች። ያኔ ስትከበብ ከቀረቡላት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ አልጀዚራን ዝጊ የሚል ነበር😁 ዛሬ ላይ የየመን ሀይሎች ራሳቸውን ለመከላከል አንድ ሚሳኤል ወይንም ዲሮን ወደ ሳኡዲ ጦር ሰፈሮች እና የነዳጅ ማእከላት ሲተኮሱ ኳታር የውግዘት መግለጫ በመስጠት የሚስተካከላት የለም። አይ የአረብ ሀገራት ነገስታቶች🤔 ኳታር ምን ብታሽቃብጥ የአረብ ነገስታቶች እንደሆነ የኢኽዋን ደጋፊ ናት ስለሚሉ በጎሪጥ ማየታቸውን አያቆሙ። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

አሜሪካ ለሳኡዲ አረቢያ 48 F-35 የጦር ጄቶችን በ24.3 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ ተስማምታለች። ይህም ሳኡዲ ከአሜሪካ ከፈፀመቺው ግዙፍ የመሳሪያ ሽያጭ አንዱ ሆኗል። አሜሪካ 48ቱን የጦር ጄቶች በ
+1
አሜሪካ ለሳኡዲ አረቢያ 48 F-35 የጦር ጄቶችን በ24.3 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ ተስማምታለች። ይህም ሳኡዲ ከአሜሪካ ከፈፀመቺው ግዙፍ የመሳሪያ ሽያጭ አንዱ ሆኗል። አሜሪካ 48ቱን የጦር ጄቶች በ 24.3 ዶላር የምትሸጥ ሲሆን ይህም ሳኡዲ ለእያንዳንዱ የአሜሪካ የጦር ጄት ከ 500 ሚሊዮን ዶላር በላይ የምታወጣ ይሆናል። በዚህም መሰረት አሜሪካ ለሌሎች ሀገራት ከምታስከፍለው ዋጋ ከሁለት እጥፍ በላይ ሳኡዲ አረቢያን አስከፍላታለች። አሜሪካ ከዚህ በፊት ለጃፓን 105 F-35 የጦር ጄቶችን የሸጠቺው በ 23 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ለጀርመን ደግሞ 35 ኤፍ35 ጄቶችን የሸጠችላት በ 8.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። የሆነው ሆኖ አሁን ላይ በየመንና ሳኡዲ አረቢያ መካከል የተከሰተውም ጦርነት አሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጯን እንዲታጧጧጡፍ ረድቷታል። አሜሪካ ከመካከለኛው ምስራቅ የምትዝቀውን የመሳሪያ ሽያጭ ያክል ከየትም አትዝቅም። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ኤርዶጋን በ 2028ም ፕሬዚዳንት ሆኜ እወዳደራለሁ ብሏል። ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገርም ውስጥ በውጪው አለም ተወዳጅነቱ እየቀነሰ የመጣውና እርሱም ከዲሞክራሲያዊ ይልቅ ወደ ፈላጭ ቆራጭ መሪነት የተሸጋገረ
ኤርዶጋን በ 2028ም ፕሬዚዳንት ሆኜ እወዳደራለሁ ብሏል። ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገርም ውስጥ በውጪው አለም ተወዳጅነቱ እየቀነሰ የመጣውና እርሱም ከዲሞክራሲያዊ ይልቅ ወደ ፈላጭ ቆራጭ መሪነት የተሸጋገረው ፕሬዚዳንት ረጄብ ጦይብ ኤርዶጋን የ 25 አመት የስልጣን ጊዜየ አይበቃኝም በማለት 2028 ላይ ዳግመኛ እንደሚወዳደር አሳውቋል። ኤርዶጋን ቱርክን በአለም ላይ ካሉ ሀያላን የጦር ባለቤቶች አንዷ በማድረግ በጦር ቴክኖሎጂ በቀዳሚነት ያሰለፋትና የኢኮኖሚ እመርታ በማስመዝገብ ከፍተኛ እድገትን ማምጣት የቻለ መሪ ቢሆን ባለፉት አመታት ግን የኑሮ ውድነት እና የፖለቲካ ነፃነትን ይገድባል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል። ባለፈው በተካሄደው ምርጫ ኤርዶጋን በጠባብ ልዩነት ሲያሸንፍ ፓርቲ AK ፓርቲ ደግሞ መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ ባለማግኘቱ የደውለት ባህቼሊው የቱርክ ናሽናሊስት ፓርቲ ጋር ተጣምሮ ነው መንግስት የመሰረተው። ኤርዶጋን አሁን ላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና የጦር ቁልፎች በእጇ እንዳስገባ የሚነገር ሲሆን የግዙፉ ድሮን ካምኒ ባይራክታር ባለቤት ሰልጁቅ ባይራክታርም የልጁ ባል ነው። ኤርዶጋን በተለይም ጋዛ እና ፍልስጤምን አስመልክቶ በሚሰጣቸው የማይጨበጡ ማስፈራሪያዎች በብዙዎች እንዲጠላ አድርጎታል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ስለ መከተል ሙከረማ እና ከእነባ እንቆረቆራለን ትላላችሁ። ግና ቢን ሰልማን እነ ጄኔፌር ሎፔዝና የአውሮፓ ራቁተኛ ዘፋኞችን አምጥቶ የከእባንም ከሗላቼው አድርጎ በሚያስጨፍርበት ጊዜ ትንፍሽም አላላችሁ ነበር። የከእባን ቅዱስ ልብስም ለጄፈሪ ኢፕሽቴን ቤተመቅደስ በሰጠበት ጊዜ ትንፍሽ አላሊችሁም ነበር! ዛሬ ይሄ ከእባን ያዋረደው የቢን ሰልማን አገዛዞ በሙስሊሙ አለም እንደተጠላ ስላወቀ የሙስሊሙን ትኩረት ለማግኘት በውሸት ሁቲዎች ወደ ከእባ ተኮሱ ሲል ግን ሙጃሂድነታችሁን መቆጣጠር አቃታችሁ! አሁን ይሄን ሁሉ ማስመሰል የምትፈፅሙት ለአላህ ብላችሁ ነው አ?!! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የ 9/11 የ "ሽብር ጥቃትን" ያክል አሜሪካን የጠቀመ ያደለበ ያንሰራፋ ክስተት የለም። ያ ክስተት አሜሪካ መላ መካከለኛው ምስራቅን እንዲትቆጣጠር በሩን የከፈተላት በርካታ ሙስሊም ሀገራትን እንዲታፈ
የ 9/11 የ "ሽብር ጥቃትን" ያክል አሜሪካን የጠቀመ ያደለበ ያንሰራፋ ክስተት የለም። ያ ክስተት አሜሪካ መላ መካከለኛው ምስራቅን እንዲትቆጣጠር በሩን የከፈተላት በርካታ ሙስሊም ሀገራትን እንዲታፈራርስ ህጋዊነትን የሰጣት ፤ የፈለገቺውን ብታደርግ እንዳትጠየቅም እንዳትወገዝም ምሽግ የሆናት ስራ ነበር። ለዚያም ነው በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመ በሲአይኤና ሞሳድ የተቀናጄ ድርጊት እንጅ እንትና ያቀደውም የፈፀመውም አይደለም ሲሉ የሚሞግቱት። የጀርመኑ ዶይቼቬለ ይዞት በወጣው መረጃ 20% የሚሆነው የአሜሪካ ህዝብ የ መስከረም 11ዱን ጥቃት የፈፀመው የአሜሪካ መንግስት ነው ብለው ያምናሉ። ኒውዮርክን ያክል ግዙፍ ከተማ ደህንነቷ 24 ሰአት በሚጠበቅባት ከተማ ወደ ኒውዮርክ የሚበሩ ሁለት አይሮፕላኖች ተጠልፈው ህንፃ ላይ ተከሰከሱ የሚለው ክስ ብዙዎችን አያሳምንም። ደግሞም ህንፃዎቹ በአይሮፕላን ቢመቱ እንኳ ከላይ እሳት ይቀጣጠላል እንጅ ያን ያክል ከባድ ፍንዳታ ተከስቶ ህንፃዎችን ከስር ነቅሎ እንዳልነበር አያደርጋቸውም ነበር ይህ የሆነው በህንፃዎቹ ውስጥ ከባባድ ፈንጅዎች ተቀብረው ስለነበር ነው ብለው የሚሞግቱት ብዙዎች ናቸው። የሆነው ሆኖ ከዚያ ክስተት በሗላ አሜሪካ ሁሉ ነገር አምሮላታል። የሙስሊም ሀገራትን አፈራርሳ ሀብታቸውን አግዛበታለች። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን ጨርሳበታለች። ኢስላም ከሽብር ጋር እንዲጣበቅ በአሪፍ ተውናበታለች። ኢስላማዊ ነን የሚሉ ግና የርሷን ተልእኮ የተሸከሙ በርካታ ሽብርተኛ ቡድኖችን ፈጥራበታለች። false flag attack እንደ አሜሪካ የጠቀማት የለም። እናም የሞግዚት ልጇ ሳኡዲ አሁን የጠባቂዋን አሜሪካ ሞደል ለመከተል እየተፍጨረጨረች ትመስላለች😊 ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ይህ ሁሉ ፍርስራሽና የጦር አይሮፕላኖች ዲኬይ በአረብ ሀገራት የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እውነታ ነው። ኢራን በሳኡዲ ፣ ኢማራት ፣ ኪዌይት ፣ ባህሬይን ፣ ጆርዳን እና ኳታር የሚገኙ የአሜሪካ ጦ
+5
ይህ ሁሉ ፍርስራሽና የጦር አይሮፕላኖች ዲኬይ በአረብ ሀገራት የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እውነታ ነው። ኢራን በሳኡዲ ፣ ኢማራት ፣ ኪዌይት ፣ ባህሬይን ፣ ጆርዳን እና ኳታር የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን እንዲህ ነው ያወደመቻቼው። በጦርነቱ አሜሪካ ባመነቺው ብቻ 57 የጦር ጄቶችና ድሮኖች በኢራን ወድመዋል። ባህሬይን የሚገኘውና የቀጠናው ግዙፉ ባህር ሀይሏን ጨምሮ ብዙ የጦር ሰፈሮቿ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። እናም አሜሪካ የእስራኤልን ህልም ለማሳካት የገባችበት ጦርነት ቀላል ዋጋ አይደለም ያስከፈላት። አሁን ላይ ወደ ጦርነቱ ቀጥታ ላለመግባት እያቅማማች ያለቺውም ያ ኪሳራ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረባት ነው ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ይህ በዛሬው እለት በሁቲዎች የተመታው የሳኡዲ አረቢያ F-15 የጦር ጄት ነው። የጦር ጄቱ የየመን ታኢዝን ለመደብደብ ሲመጣ ነው ሁቲዎች በአየር መከላከያ ያወረዱት። እስካሁን ፓይለቱ ያለበትና ሁኔታው
+3
ይህ በዛሬው እለት በሁቲዎች የተመታው የሳኡዲ አረቢያ F-15 የጦር ጄት ነው። የጦር ጄቱ የየመን ታኢዝን ለመደብደብ ሲመጣ ነው ሁቲዎች በአየር መከላከያ ያወረዱት። እስካሁን ፓይለቱ ያለበትና ሁኔታው አልታወቀም። ከዚህ በተጨማሪም ዊንግሎንግ የተሰኘውን ግዙፍ ድሮንም የመኖቹ መተው ጥለዋል። በሁለቱ ሀይሎች መካከል ንግግር ተጀምሮ ጦርነቱ ካልቆመ በስተቀር ቀጠናውም አለምም ይናጋልል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የየመን አንሷሩሏህ ሁቲ ቃልአቀባይ የህያ ሳሪእ ሁቲዎች መካን ኢላማ አድርገዋል ተብሎ በሳኡዲ ለቀረበባቸው ውንጀላ መግለጫ ሰጥተዋል። እኛ የኢስላም ምልክቶቻችንን እና ቅዱሳን ቦታዎቻችንን በፍፁም ኢላማ አናደርግም ይህ የለየለት ቅጥፈትና የሀሰት ፕሮጋንዳ ነው። ኢላማዎቻችን ኢላማቸውን የማይስቱና ወታደራዊ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው በማለት በዚህ መልኩ መግለጫ ሰጥተዋል። የተከረበቺዋን መካን የሚያዋርዳት በደለኛው የሳኡዲ አገዛዝ እንጅ የመን ፈፅሞ መካን አትነካም ብሏል በመግለጫው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

እስራኤል ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ተጣምራ ሁቲዎችን በተዘዋዋሪ እየተዋጋች መሆኑን የእስራኤል የአሜሪካ እና የአረብ መገናኛ ብዙሀን በስፋት እየወገቡት ይገኛሉ። CNN ፣ Jerusalem post ፣ አረብ
+2
እስራኤል ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ተጣምራ ሁቲዎችን በተዘዋዋሪ እየተዋጋች መሆኑን የእስራኤል የአሜሪካ እና የአረብ መገናኛ ብዙሀን በስፋት እየወገቡት ይገኛሉ። CNN ፣ Jerusalem post ፣ አረብ ኒውስ እና ሌሎችም መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡት እንዳሉት ከሆነ እስራኤል የደህንነትና ስለላ ሀይሏን ወደ ሳኡዲ አረቢያ ልካለች። እስራኤል ከዚህ በተጨማሪ የባህር ሀይሏ በሁቲዎች ላይ ለሚፈፀም ተልእኮና ጦርነት እንዲዘጋጅ ማዘዟን አናዶሉ ኤጄንሲ ዘግቧል። ሳኡዲ አረቢያ ከግብፅ ጋርም ለመተባበር ንጉሷ ሙሀመድ ቢን ሰልማን ወደ ካይሮ ማምራቱ የሚታወቅ ነው። እንግዲህ አሰላለፉ ይሄን ይመስላል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የህያ ሲንዋር እንዳለው ጋዛ ብዙዎች ትለያለች። ታራግፋለች ታበጥራለች። እና ከጋዛ በሗላ የሚሸወድ መሸወድ የፈለገ ብቻ ነው!
+4
የህያ ሲንዋር እንዳለው ጋዛ ብዙዎች ትለያለች። ታራግፋለች ታበጥራለች። እና ከጋዛ በሗላ የሚሸወድ መሸወድ የፈለገ ብቻ ነው!

ወላሂ በዲን ስም አታጭበረብሩንም! ትክክለኛ መልካችሁንኮ ጋዛ አሳይታናለች። የወርቅ ቅባችሁን ገፋ ቅብ መሆናችሁን አረጋግጣልናለች። በፊት ቢሆን ስታለቅሱ እናለቅስ ስትስቁ እንስቅ ነበር። ስትሸውዱን ሁሉን ነገር ለሚመቻችሁ ብቻ ፈትዋ እየመዘዛችሁ ሙሰቢጥና ሙሰሊጥ ስትሆኑ አሚን ብለን ልንቀበላችሁ ልንታለልችሁ እንችል ነበር። ከጋዛ በሗላማ ንግግራችሁ ራሱ ይቀፈናል። ስናያችሁ ራሱ ደማችን ይፈላል። ንፍቅናችሁ ፤ ሽምጠጣችሁ ፤ መታበያችሁን አይደለም ከአንድ የሀይማኖት መሪ ይቅርና ከተራ አማኝ እንኳ በፍፁም አንጠብቀውም ነበርኮ። ዛሬ ጦርነቱን የዲን አስመስላችሁ አሏሁመ ኢህፈዝ ቢላደል ሀረመይን አሸሪፈይን ብላችሁ ያልተጠቁ ሁሩማቶቻችንን የተጠቁ አስመስላችሁ ለመዋሸትና ለሰላጢኖቻችሁ የፕሮፓጋንዳ ግብአት ለማቀበል ስትሞክሩ ብዙ ሳይጠበቅብን የጋዛ መነፀራችንን ብቻ እናነሳባችሗለን። ጋዛዊያን ተከበው ሲያልቁ በረሀብ ሲሰቃዩ ህፃናቱ ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረው ሞትን ሲጠባበቁ እናንተ ምን የሚል ፈትዋ እየሰጣችሁ ነበር? አላህ ቀብር ውስጥ ስለ ሽንትህን አዳርቀሀል ወይ ብሎ ይጠይቃችሗል ስለ ጋዛ ግን አይጠይቃችሁም ስለ ጋዛ የሚያወሩት ስለ ሽንት ማዳረቅ የማያውቁ ጃሂሎች ናቸው ስትሉን ተፍተናችሗል! እነርሱ እዚያ እያለቁ በጋዛ የሚሞቱት ጀነት ይገባሉ ወይንስ አይገቡም የሚል የፈትዋ አጀንዳ ከፍታችሁ የሞቱት በወንጀል ነው ለማለት 5 ምክንያቶችን ስትደረድሩ በቅታችሁናል! ጋዛዊያን እያለቁ ያሉት በወንጀላቸው ነው ይቶብቱ ስትሉን ከውስጣችን ወጥታችሗል! በመላው አለም ያሉ ሰብአዊያን የሚያደርጉት ቢያጡ በጀልባዎች ሰብረን እንገባለን ብለው ከአንድ አይሉ ሁለት ሶስት አራት ጊዜ ሲታገሉ እናንተ ግን አንዲት አረፍተ ነገር እንኳ መፃፍና መናገር ሲያቅታችሁ ያኔ ጅባት ብለናል! የተወረረቺው የመን ፤ ማእቀብ ተጥሎባት ዙሪያውን ብሎክ የተደረገቺው የመን ፤ በእቀባ ምክንያት በረሀብ የሚሰቃዩት የየመን ህፃናት ፤ በሳኡዲና አጋሮቿ ያለቁት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ንፁሀን የመናዊያን ሆነው ሳለ የመኖች ራሳቸውን ለመከላከል የሳኡዲ ጦር ሰፈሮችና የነዳጅ ተቋማት ላይ አፀፋ ስለሰጡ የበድር ጦርነት የተነሳ ያክል አስጩሀችሁ ጂሀድ ማለታችሁ ራሳችሁን ያስገምታል እንጅ እንኳን እኛን ማንንም አታታልሉም! በፊትም እናውቃችሗለን! ጋዛ ደግሞ የበለጠ አስተዋውቃናለች! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ዘይኑል አቢዲን በምድር ላይ ካለፉ እጅግ ሷሊህ ደግ የአላህ ባሮች አንዱ ነበሩ። የርሳቸው ልቅና ሲወራ አንዱን አንዱ ይበልጠው እየመሰለ ግራ ያጋባል። የሚቀማጠሉበት ስም ብዙ ቢሆንም በአንድ ነገራቸው ግን በህይወት ሳሉ የስራቸውን ያክል አይታወቁም ነበር - በለጋስነታቸው በቸርነታቸው! ዘይኑል አቢዲን ያው መቼስ ስማቸው ራሱ የአላህ ባሮች ጌጥ ነው። የረሱሉ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሽታ የአሊና ፋጢመቱ ዘህራ ፍሬ የሁሰይንም የአብራክ ክፋይ! የርሳቸውን ያክል የሚሰግድ የሌለ የሚመስል ያክል ለሶላት የተፈጠሩ ነበሩ። በዚህም አሊ ሰጃድ ይሏቸውል ( ሰጋጁ አሊ)! ዘይኑል አቢዲንን በህይወት እያሉ መለየት የሚያስቸግረው ስራቸው ታዳ ቸር ለጋስነታቸው ነው። ሲሰጡ እንደ ቅድመ አያታቸው ውዱ ነብይ እጃቸው አይታይም ነበር። ዘይኑል አቢዲን ሀብታም ናቸው። ማታ ሲጨላለም የሸክም ልብሳቸውን ይለብሱና ፊታቸውን ሸፍነው በእያንዳንዱ የመድና ድሀ ቤት በር ላይ ዱቄትና የሚበላ የሚለበስ ነገሮችን እየጣሉ ይሄዳሉ። ይህ የዘይኑል አቢዲን የማታ ሁልጊዜ ስራ ነው። ማንም አያውቃቸውም። የመድና ድሆች "አብደላህ " እያሉ በራሳቸው ስያሜ ይጠሯቸዋል። እንዲህ እያደረጉ የመድና ድሀዎችን እየቀለቡ እስከ እለተሞታቸው ቀጠሉ። ሞት መቼስ ለደጉም ለክፉም አይቀር አይደል። የርሳቸውም ተራ ደረሰ። አያታቸውን ሊገናኙ። የመድና ድሀዎችን የቲም ሊያደርጉ😥 እናም ዘይኑል አቢዲን የመሞታቸው ዜና ተሰማ። ሁሉም የመዲና ህዝብ አሊሙ ፈቂሁ ደጉ ሷሊሁ ሰጋጁ ዛኪሩ ሀቀኛው ጀግኛው ዘይኑል አቢዲን ሞቱ ብሎ በሀዘን ተዋጠ። ግን ያላወቀው ተጨማሪ ነገር ነበር። ያን ጨለማን ተገን አድርጎ ፊቱን ሸፋፍኖ እየተሸከመ ዱቄት በር በር ላይ የሚያስቀምጠውን ዘይኑል አቢዲንን! ዘይኑ የተቀበሩ እለት ያ እርዳታ ቀጥ ብሎ ቆመ። የመድና ድሆች ግራ ገባቸው። በማግስቱም ከማግስቱ ቀጥሎም ከዚያ በሗላ ባሉት አጠቃላይ ቀናት ያ ዱቄት እየተሸከመ የሚያከፋፍል ሰው የለም። አድራሻው ጠፋ። ቢጠበቅ ቢጠበቅ😥 ለካስ ያ ሰው እኛ የደግ ሰው ልጅ የደግ ሰው የልጅ ልጅ የአለማት ሁሉ አይነታ የልጅ ልጅ ልጅ ዘይኑል አቢዲን ሆነው ኖሯል። የመድና ሰዎችም ከቀናት በሗላ የአባታቸውን እውነተኛ ማኝነት አወቁና ይበልጥ ተላቀሱ! መገን ዱኒያ ስንቱ አለፍብሽ 💔 ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

እኔኮ በኢስላም ስም በዲን ስም እንደት ነው ይሄ ሁሉ ተሳዳቢና አክፋሪ ሊበዛ የቻለው? እያልኩ ሁሌ ከራሴ ጋር እሟገታለሁ። ምክንያቱ ሌላ አይደለም ልጆቹ የሚቀረፁበት የአቀራር ሁኔታ ነው። አሁን በዚህ መልኩ ዲንን የተማረ ሰው እንደት ነው አኽላቅ ፣ አደብ ፣ ተዋዱእ ፣ ሀያእ የሚኖረው። እንደ ጎረምሳ እየተሰዳደበ ጭንቅል ጭንቅሉን እየተባባለ እከሌን ካልተሳደብክ ምን የሱና ሰው ነህ እየተባለ ቂርአትን የጀመረ ሰው በርግጥ ራህማም ሀያእም የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው። ደግሞ የሚከፋፍሉት ብዛት። እኛ እዚህ በላኢላሀኢለሏህ ጥላ ስር ያለን ቂብላ የተቅጣጨን ሰው አታክፍሩ ምላሳችሁን ሰብስቡ እንላለን እነርሱ አራቀውት አዘምነውት አወሳስበውት ሀጁሪያ ሱሩሪያ ሙመይአ ሀዳዲያ ማለቂያ የሌለው ክፍፍል! አስባችሁታል ትክኬለኛ ሙሰሰሊም ለመሆን ያላችሁ probability 1/∞ኛ😁 ለማንኛውም ይህ ዲን ነው። ዲናችሁን ከማን እንደምትወስዱ እወቁ። አኽላቅ የሌለው ሰው ጋር ዲን ሲወሰድ ጥፋት ነው የሚሆነው። ለማንኛውም ጀማሪዎ ቀሪ የምመክረው ቂርአትን ህይወታችን በቂርአት ከጨረሱ ከጨመቱ ከበሰሉ ኢልምም እድሜም ካስተማራቸው ራሳችሁ ላይ እንጅ ሰዎች ላይ ምላሳችሁን እንዳትትነዝሩ ከሚያደርጓችሁ ፤ ነፍስያችሁን እንጅ ሰው እንዳትገመግሙ ከሚያደርጓችሁ የአደብ ባለቤቶች ጋር ቅሩ! ያ ከሆነ ከፊትና ትጠበቃላችሁ! ወንድማዊ ምክሬ ነው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ሰሞኑን ቲክቶክ ላይ ስገባ የሸህ ሙሀመድ ሁሰይን አሊ አልአሙዲን የደግነት ስራዎች የሚዘክሩ ተደጋጋሚ ቪዲዮዎች እየመጡልኝ አያቸዋለሁ። ከታላላቅ ድርጅት አመራሮች በርሳቸው ድጋፍ ለቴልቅ ደረጃ እስከደረሱ መሪዎች ፤ ታች በአስተናጋጅነት ጭምር የሚሰሩ ያልጠበቁትን ድጋፍ ከእርሳቸው ያገኙ ሰዎች ፤ በእርሳቸው ድጋፍ የራሳቸውም የቤተሰባቸውም ህይወት እስከመጨረሻው የተለወጡ ኢትዮጵያን እንባ እየተናነቃቸው የተደረገላቸውን ሲያወሩ በእውነቱ ልብ ይነካል። ምንም ቢሆን እንደ ደግነትና ለጋስነት መልካም ነገር የለም። በተለይ ያ ለጋስነት ሀይማኖትና ዘር ፣ ዲሀና ሀብታም ፣ ቀለምና ፆታ ሳይለይ የተደረገ ጊዜ ፍሬው ያመረ መአዛውም ውብ ይሆናል። በቪዲዮዎቹ የገረመኝ ዛሬ ሚሊየነር የሆኑትም ሆነ ታች ልጆቻቼውን ለማሳደግ የሚደክሙ የነበሩትም እኩል በእንባ ተሞልተው ሲናገሩ ማየቴ ነው። የተደረገላቸውን አለመርሳታቸው ደስ ያሰኛል። ከሸህ ሙሀመድ ቪዲዮዎች የተማርኩት ሌላው ነገር ለደግነት ቤተሰብ እንደት መሰረት እንደሆነ ነው። የአልአሙዲ ቤተሰቦች ምንኛ ደግ አዛኝና የሰጡት ፍፁም እንዳይታወቅባተው አድርገው የሚሰጡ እንደነበሩ አሰጣጣቸውም ድህነትን የማይፈራ አሰጣጥ እንደነበር ሲነገር ገርሞኝ ተመልክቼዋለሁ። አልአሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉትን ያክል ያልተነገረላቸው ፤ የሰሩትን ያክል ያልተመሰገኑ ፤ በርሳቸው ልክም ኢትዮጵያን የጠቀመ ባለሀብትም ግለሰብም የሌለ ቢሆንም የእርሳቸውን እገዛ ተመስርቸው ሀገርንም ራሳቸውንም የለወጡ ሰዎች እንዲህ በህይወት ሳሉ ምስክርነት ሲሰጡ ማየት ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ሜድሮክን ያክል ካምፓኒ መስርቸው በስራቸው ለመቶ ሺዎች የስራ እድል ፈጥረው ፤ የህዳሴው ግድብን ጨምሮ ለሀገራቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በቢሊዮን የሚቆጠር ብርን በነፃ እየሰጡ ትልቅ ውለታ የዋሉ የሀገር ባለውለታ ናቸውና ትልቅ ክብር ይገባቸዋል። ባለፈው አመት የሜድሮክ ጠቅላላ አመታዊ ስብሰባ ላይ ከሳኡዲ ሆነው ያስተላለፉት መልእክት አስገርሞኝ ነበር ። ለሜድሮክ ዋና ስራአስኪያጅ ጀማል አህመድ " ጀማል ብዙ ሰው ቅጠሩ ጀማል ብዙ ስራ የሚፈጥር ሶራ ላይ አተኩሩ ሰው እርዱ በቻላችሁት ያክል ሰው አብዙ" እያሉ ከትርፍ ይልቅ ሰው ተቀጥሮ ህይወቱ እንዲደገፍ የነበራቸው ፍላጎት በበኩሌ ምናለ ኢትዮጵያን የሚመራው ብልፅግና የርሳቸውን 1/10ኛ እንኳ ይህን ያክል ሰዋዊነት አስተሳሰብ የተላበሰ ስርአት ቢሆን ያስባለኝ ነው። አላህ ይጠብቃቸው። ሀብታቸውንም እድሚያቸውንም ይባርክላቸው! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ሳኡዲ አረቢያ የእስራኤልን ወታደራዊ እና የስለላ እገዛ መጠየቋን የእስራኤሉ መገናኛ ብዙሀን ኢስራኤል ሀዮም ይዞት የወጣው መረጃ ያመለክታል። ኢስራኤል ሀዮም የእስራኤል ባለስልጣናትን ጠቅሶ ይዞት በወ
+1
ሳኡዲ አረቢያ የእስራኤልን ወታደራዊ እና የስለላ እገዛ መጠየቋን የእስራኤሉ መገናኛ ብዙሀን ኢስራኤል ሀዮም ይዞት የወጣው መረጃ ያመለክታል። ኢስራኤል ሀዮም የእስራኤል ባለስልጣናትን ጠቅሶ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ሳኡዲ አረቢያ የእስራኤልን እገዛ ጠይቃለች። ሙሀመድ ቢን ሰልማን ለዶናልድ ትራምፕ የአየር ሀይል እገዛ ቢጠይቅም ትራምፕ ወደ ጦርነቱ ቀጥታ መግባትን ውድቅ በማድረግ ከ 100 በላይ የአሜሪካ ጦር ጠበብቶችን ለሳኡዲ ድጋፍ መላኩ ይታወቃል። የእስራኤልን የእገዛ ጥያቄ አስመልክቶ ለወጣው መረጃ እስካሁን ከሳኡዲ አረቢያ በኩል የተሰጠ ምላሽም ማብራሪያም የለም። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

"አንተ ጨካኝ የየመን ምድር ምነው ልጆቻችንን በልተህ አስቀረካቸው" የኦቶማ ቱርክ እናቶች ለቅሶ የኦቶማን ሱልጧኔት( ደውለተል ኡስማኒያ) በኢስላም ታሪክ ለረጂም ጊዜ በሀያልነት በመቆየት የሚስተካከለው የለም። በእውነቱ ከኢስላም ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም ኢምፓየሮች በላይ የኦቶማን ኢምፓየር ከ 600 አመት በላይ በሀያልነት በመቆየት ባለሪከርድ ነው። እናም የኦቶማን ሱልጧኔት ያላሸነፈው ሀያል ያላንበረከከው ልእለሀያልም የለው። የአውሮፓ ሀይሎችን ሁሉ አንበርክኮ እስከ ኦስትሪያ የተዘረጋ ከሊቢያ እስከ ኢራቅም የተንጣለለ ከሜድትራኒያን ባህር እስከ ጥቁር ባህር ከዚያም እስከ ህንድ ውቅያኖስ የተዘረጋን ሰፊ ግዛት ተቆጣጥሯል። ከሩሲያ እስከ እንግሊዝ ፣ ከፈረንሳይ እስከ ግሪክ ያላሸነፈው ሀያል ሀይል የለም። የመኖች ሲቀሩ! የኦቶማን ሱልጧኔት የዘይዲያ መዝሀብ ተከታይ በሆኑት የመናዊያን የሚመሩትን የመኖችን ለማሸነፍ ግን ፈፅሞ አቃተው። ለመቶ አመታት ተዋግቶ ተዋግቶ በመጨረሻም ተሸንፎ ወጥቷል። ታዲያ የሚገርመው ወደ የመን የሚላኩ የኦቶማን ወታደሮች እንኳን አሸንፈው ቸሸንፈውም አይመለሱም ነበር። እዚያው ቀልጠው ነበር የሚቀሩት። የኦቶማን ሱልጧኔት ጦሩ ሲሸነፍበት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የቱርክ ወጣቶችን አደራጅቶ ይልካል እዚያው ቀልጠው ይቀራሉ። እናም አንድት እናት ልጇ ወደ የመን ከተላከ እንደማይመጣ እርግጠኛ ነበረች። ወደየመን መላክ ልክ የሞት ፍርድ የመፈረድን ያክል ይቆጠር ነበር። እዚያ በሚጠብቋቸው ሀይለኛ የየመን ተወንጫፊ ተዋጊዎችና አስቸጋሪ መልክአምድር ሰጥመው ተቀጭተው ይቀራሉ እንጅ አይመለሱም። እናም ይህ ሀዘን የቱርክ እናቶችን ክፉኛ ጎዳ። በልጆቻቼው መሄድ ያዘኑና ልባቸው የተሰበረ የቱርክ እናቶች እየተሰባሰቡ እያለቀሱ ይገጥሙ ነው። ግጥሞቹ ልብ የሚነኩና ዛሬም ድረስ በቱርካዊያን ዘንድ በጣም የሚታወቁ የሀዘን ዜማዎች ናቸው። ግጥሙን ወደ አማርኛ ስመልስላችሁ የቱርክ እናቶች እንዲህ እያሉ ያለቅሱ ነበር "በሰማዩ ላይ ደመና በሌለው የሚንቦለቦለው ጭሱ ከየት ነው በጎረቤታችን የለም የሞተ ሰው ምንድን ተፈጥሮ ነው ሰው የሚላቀሰው እናንት የየመን ምድሮች እንደት ጨካኝ ናችሁ ካለምንም ምህረት ልጆቼ በላችሁ! አህ አንቺ የመን አበቦችሽ ለምለም ግን ሂደውብሽ የሚመለስ የለም ውጠሽ አስቀረሽው ለምን እኔ አላውቅም! ቦታው ተዳፋት ነው መንገዱ መሬቱ ጠመዝማዛ ገደል እዚያ የሄዱብን ፈፅሞ አይመለሱም ወይ አለመታደል ምን አይነት ምድር ነው ምን አይነትስ እድል! የወታደር ባንዱ በሰልፍ ይጫወታል ሰርግ ነው እንዳንል ሙሽሮቹ የታል? ቀዩና አረንጓዴው የሚውለበለበው እስኪ ንገሩኛ የሙሽራ ልብስ ነው? ኧረ እስኪ ንገሩኝ የሄዱት ልጆቼ አይመለሱም ወይ የየመን መሬቶች ጨክነው ወስደው አስቆሯየው ወይ? ከወታደር ጩኸት ከአጀባው ጀርባ ድምፃቸው ይጮኻል በአንድነት በአጀባ እስኪ ተመልከቱ ከሰልፉ ባሻገር ከቶ አንድም የለም ከሁለት ጫማዎች ከኮፍያ በቀር💔 እያሉ ያለቅሱ ነበር። ይህ የቱርክ እናቶች የሀዘን እንጉርጉሮ Yemen Türküsü ተብሎ ይጠራል። ዩቲዩብ ላይ ገብታችሁ ብታዩት የጥንቱን አስታውሰው እንደት አዝነው እንደሚያዜሙት። የመኖች ለወራሪዎችም ሆነ ለሚቆጣጠራቸው የትኛውም አካል እምቢ አንገዛም በልቅናችን እንሞታለን እንጅ በማለት የሚታወቁ ፅኑ ህዝቦች ናቸው። ይህንን ማንነታቸውን በዋናነት ከነብያችን ቤተሰቦች ነው የወረሱት። ያኔ የኡመያዎች ስርወመንግስት እነ ኢማም ዘይኑል አቢዲንና ልጆቻቼውን እነ ዘይድ ቢን አሊን ሲያሳድዱ ተቀብለው አብረዋቸው ተሰልፈው ሀያሉን የኡመውዮች መንግስት መክተው አሸንፈው የዘይድን መንገድ ተከትለው መጥተዋል። ከዚያ በሗላ የመን መጥቶ የተቆጣጠረ አንድም ሀያል ስርወመንግስት አልተፈጠረም። እንግሊዝ እንኳ ሀያል በነበረችበት ጊዜ የመንን ለመያዝ ሞክራ ያልጠበቀቺውን መሪር ሽንፈት አከናንበው ነው የመለሷት። ያ የየመኖች ስሪትን ነው ዛሬም በአግራሞት እያየን ያለነው። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

የወንድማማች ጦርነት መሪርነቱ ይሄ ነው። የአንሷሩሏህ ሁቲ ወታደሮች እየተዋጉ በሳኡዲ ከሚደገፈው የየመን ሀይል ወታደር ሲሰግድ ይገጣጠማሉ። እናም ለኢላማ ሲያስገቡት እየሰገደ ነው። ተውት ኦንዳትነኩት እኛ ሙስሊሞች ነን የሚሰግድ ወንድማችንን አንነካም ፣ አንድም ሰው እንዳይነካው ፤ ሶላቱን እንዳትረብሹት ንግግራችሁን አቁሙ ተባብለው ተውት። አያችሁ ግን አ በመካከላቸው ያለው ወንድማማችነት ምን ያክል የውጭ ሀይሎች ቢያጨራርሷቸው እንኳ ጥላቻቼውን እንደት እንደዋጠው! እውነታው ፤ ጣልቃ ባይገባበት ያለው ሀቅ ፤ ለኢስላምም ያላቸው ሁርመት ይሄ ነው። ይሄኔ ነው ኢኺዋና ኢማን የሚፈተነው! ለነዚህ ጀግናና ደግ ህዝቦች አላህ ዘላቂ ፈጣን የሆን ሰላምን መዋደድን ያምጣላቸው። እኔ ቪዲዮውን ሳየው ልቤ ተነክቷል! ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሶሪያን እየተዝናናባት ነው። ካቢኔዎቹን አስከትሎ ሰሞኑን ሶሪያ ነው የከረመው። እዚያም በእስራኤል የተያዙ የሶሪያ ግዛቶች ወደ እስራኤል ሙሉ እንደሚጠቃለሉና የበለጠ ግዛትንም እንደ
+2
ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሶሪያን እየተዝናናባት ነው። ካቢኔዎቹን አስከትሎ ሰሞኑን ሶሪያ ነው የከረመው። እዚያም በእስራኤል የተያዙ የሶሪያ ግዛቶች ወደ እስራኤል ሙሉ እንደሚጠቃለሉና የበለጠ ግዛትንም እንደሚይዙ አሳውቋል። ተራሮቹ ላይ ሆኖ ደማስቆን ቁልቁል እየተመለከተ መጣንላችሁ ብሏል። እስራኤል በሶሪያ ላይ የምታደርገውን ድብደባና ጥቃትም አጠናክራ እንደቀጠለች ነው። የሶሪያ ደቡባዊና ምእራባዊ ግዛቶችም እየተሸረፉ ወደ እስራኤል እየገቡ ነው። የሶሪያ ጦር እስካሁን አንዲት ጥይት እንኳ እስራኤል ላይ የመተኮስ ድፍረትም ትእዛዝም አላገኘም። መሪዋ አህመድ አልሸርአም አሜሪካን መለማመጥ ላይ ተጠምዶ ማእቀቦች እንዲነሱለትና ከምእራባውያን ጋር ወዳጅነትን ማጠናከር ላይ እንጅ ግዛቱን መከላከል ላይ የሚጨክን ልብ የሚቆርጥ ወኔም አላገኘም። አይጠግቤዋ እስራኤል ግን መስፋፋቷን አጠናክራ ቀጥላለች። ቱርክም የሚጮህ አንበሳ እንጅ የሚናከስ አንበሳ አልሆነችም። እስካሁን እስራኤል ጋር አልተጋፈጠችም። የቃላት ባይራክታርና የፉከራ አኪንጂዎቿን ብቻ በመሪዋ ኤርዶጋን በኩል እያዥጎደጎደቺው ነው። ኤርዶጋን ሲዝት በማግስቱ ሀያ ኢለል ቂታል የሚል ነው የሚመስለው። ዌስት ባንክ ሙሉ ለሙሉ ወደ እስራኤል ገብቷል ማለት ይቻላል። ደቡባዊ ሊባኖስን ለመጠቅለል ከሂዝቡላህ ጋር ጦርነት ማድረግ ከጀመረች ይሄው አመት አለፈው። እዚያ ከባድ ዋጋ ብትከፍልም የአየር ሀይል የበላይነቷን ተጠቅማ ሊባኖስን እያፈራረሰች ትገኛለች። ከዚህ በፊት እንዳልኳችሁ የእስራኤል ትልቁ አላማዋ ታላቋ እስራኤልን መገንባት ነው። ያንን ለማድረግ አሁን ላይ ብዙ እርቀትን ተጉዛለች። አሜሪካን የበለጠ በቁጥጥሯ ስር እያደረገቻት በመሆኑ ቀጣይ ግዛቶቼ አሉባቸው ብላ ከምታስባቸው ግብፅና ሳኡዲ አረቢያ ላይ ለምታደርገው ዝግጅት የበለጠ እየገፋች እየተጓዘች ትገኛለች።