uk
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Відкрити в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 19 946 підписників, посідаючи 1 156 місце в категорії Медицина та 1 680 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 19 946 підписників.

За останніми даними від 28 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -539, а за останні 24 години на -5, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.64%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 7.06% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 5 115 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 408 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 9.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 29 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Медицина.

19 946
Підписники
-524 години
-1197 днів
-53930 день
Архів дописів
የስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እንዲሁም እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቱ ምን ይሆን ??? በአለማችን ከ60-80 ሚሊዮን የሚሆኑ ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ ችግር ያጋጥማቸዋል ለዚህ ችግር ከሚጋለጡበት ምክንያት አንዱ ፡- • የእስፐርም መጠን ማነስ • እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ • ትክክለኛ ቅርፅ የሌለው እስፐርም • የማህፀን ቱቦ ጠባሳ መኖር • የማህፀን እጢ መኖር • የእንቁላል ምርት ላይ ችግር ካለ • የሆርሞን ችግር መኖር • ለረጅም ጊዜ መድሀኒት መውሰድ ከላይ ከጠቀስናቸው ውስጥ ለዛሬ የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንገልፅላችሆለን • የሆርሞን ችግር • ኢንፌክሽን ካለ • ብልት አካባቢ ጉዳት ከደረሰ • ያልወረደ የዘር ፍሬ • ከዚህ ቀደም ሰርጀሪ ተሰርተው ከነበረ • ብልት አካባቢ የሚገኝ የደምስር እብጠት • የውስጥ ደዌ ህመሞች • ካንሰር ወይም ካንሰር ያልሆኑ እባጮች መኖር • ጭንቀት ፣ ድብርት • አብዝቶ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ፣ ማጨስ • ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር ውድ የዶክተር አለ ተከታታይ በዛሬው ፁሁፋችን የእስፐርም መጠን ማነስ ምክንያት እና እስፐርም ማህፀን ላይ የመድረስ ፍጥነት መቀነስ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ልንገልፅላችሁ ወደናል

አቮካዶ 1. በሰውነታችን የሚገኝን የኮሌስትሮል መጠን ዝቅ በማድረግ ረገድ አቻ የለውም፣ 2. በውስጡ ያዘለው ቫይታሚን ኤ ለልብ ህመም/ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል፣ እርጅናን ለመ
አቮካዶ 1. በሰውነታችን የሚገኝን የኮሌስትሮል መጠን ዝቅ በማድረግ ረገድ አቻ የለውም፣ 2. በውስጡ ያዘለው ቫይታሚን ኤ ለልብ ህመም/ ስትሮክ የመጋለጥ ዕድላችንንም በእጅጉ ይቀንሳል፣ እርጅናን ለመከላከል እና የቆዳ ውበት ተጠብቆ እንዲቆይ ይረዳሉ፣ 3. በአቮካዶ ውስጥ በብዙ መጠን የሚገኘው አንቲ ኦክሲዳንት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና የሞቱ የቆዳ ሴሎች እራሳቸውን እንዲተኩ ሲያግዝ ካሮቲኖይድስ የተባለው ንጥረ ነገርም በቆዳ ላይ የሚታዩና የቆዳን ውበት የሚቀንሱ ምልክቶች እንዳይከሰቱ ያደርጋል። 4. ክብደት ለመቀነስ ፍቱን ነው፣ 5. ለስኳር ህመምተኞች ተመራጭ ነው፣ በአቮካዶ ውስጥ በጥሩ መጠን የሚገኘው ፖታሺየም በደማችን ውስጥ ያለውን የግሉኮስ መጠን በማመጣጠን በሰውነት ውስጥ የልብ ስራንና የስኳር መጠንን የተረጋጋ እንዲሆን ያስችላል። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

የኩላሊት ጠጠር እንዳለብዎት የሚያሳብቁ ምክያቶች 1. ኃይለኛና የማያቋርጥ ህመም በብሽሽቶ እና በጀርባዎ የታችኛው ክፍል ላይ መሰማት 2. በሽንቶ ውስጥ ደም መኖር 3. ደስ የማይል እና እንግዳ ያለው ሽታ በሽንቶ ላይ መታየት 4. ትውኪያና ማቅለሽለሽ 5. ነጭ የደም ህዋሰ ወይም መግል በሽንትዎ ላይ መታየት 6. ሽንቶ አንዳንዴ ድፍርስ ውሃ መምሰል 7. የሚሸኑት ሽንት መቀነስ 8. በሚሸኑ ጊዜ የማቃጠል ስሜት መኖር 9. ሽንቶ ቶሎ ቶሎ መጣው ማለት 10. በጠጠሩ ምክንያት ኢንፌክሽን ከተፈጠረ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ሊያጋጥሞ ይችላል፡፡ የኩላሊት ጠጠር እንዴት ይከሰታል 1. ለኩላሊት ጠጠር ዋነኛ መከሰት መንስሔ ተደርጎ የሚወሰደው በቂ ውሃ በየዕለቱ ያለመጠጣት ነው ፡፡ በዚህም የተነሳ ዩሪክ አሲድ የተሰኘው የሽንታችን አካል ታጥቦ ወደ ውጭ ስለማይወጣ ወደ ኃይለኛ አሲድነት ይቀየራል፡፡ በዚህ የተነሳ አሲዱ በቀጥታ ወደ ጠጠርነት ራሱን በሂደት ይለውጣል፡፡ 2. ጨው የበዛባቸው ምግቦች መመገብ፡- ይሄ ደግሞ ድርቀትን በመፍጠር በሽንት አማካኝነት ታጥበው የሚወጡ ነገሮች በጊዜ ሂደት ወደ ጠጠርነት እንዲቀየሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ 3. በፕሮቲን የበለጸጉና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የኩላሊት ጠጠር እንዴት እንከላከል 1. በቂ ውሃ በየቀኑ ይጠጡ ቢያንስ ከ6 እስከ 8 ብርጨቆ 2. የአልኮል አወሳሰድ መጠን ይቀንሱ 3. ጨው የሚበዛባቸው ምግቦችን ይቀንሱ፡- የድንች ጥብስ፣ የስጋ ቋንጣ፣ የታሸጉ ምግቦች፣ ኑድሎችን ከመግብ ገበታዎ ያስወግዱ 4. ስኳር፣ካፊን እና ካርቦኔት ያለባቸውን መጠጦች አይውሰዱ 5. ካልሲየም እና ሲትሪክ አሲድ በከፍተኛ ሁኔታ የያዙ ምግቦችን እንደ ሎሜ፣ ብርቱካንና ማንጎ ጭማቂዎችን ያዘውትሩ 6. በቂ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ፡፡ ክብደቶን ያስተካክሉ፡፡ መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ! የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ፈስቡክ ምንም ዳታ ሳይበላብን ለመጠቀም አዲስ አፕ በጣም ፈጣን ሞክሩት እኔ ተመችኛል

የሺሻ ጉዳት #Like #Share ሺሻ ማጨስ የተጀመረው ቱርክ ወይም ህንድ ውስጥ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ አሁን ግን በመላው አለም በተለይም አሜሪካ፤ካናዳ እና እንግሊዝ በመሳሰሉት ያደጉ ሃገሮች ውስጥ ሳይቀር እየተስፋፋ መጥቷል፡፡ ሺሻ የሚጠቀሙ ሰዎች ብዙ ጊዜ "ሺሻ እኮ ምንም ጉዳት የለውም፡፡ ተፈጥሯዊ ነገር ነው፡፡ ይሄ እኮ ከፍራፍሬ ነው የሚሰራው" ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ግን እውነት ሺሻ ምንም ጉዳት የለውም? ሺሻ ምንድን ነው? ሺሻ ማለት የትንባሆ ቅጠልን ከሞላሰስ (የስኳር ተረፈ ምርት) ወይም የፍረፍሬ ጣእም ካለው ሲረፕ ጋር ቀላቅሎ ማጨስ ማለት ነው፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ሺሻን ለማጨስ የምንጠቀመው ከሰል ነው፡፡ የትንባሆው ቅጠል በሞላሰሱ ወይም በፍራፍሬ ሲረፕ እርጥብ ይሆናል፡፡ ብዙ ጊዜ የእንጆሪ፤ የአፕል፤ ቸኮሌት፤ ኮኮናት እና የናና ጣእም ያላቸው የፍርፍሬ ሲሮፖች ለሺሻ ተመራጭ ናቸው፡፡ ያንን በከሰሉ አሙቆ የሚወጣውን ጭስ በውሃ ውስጥ እያለፈ ሲመጣ ጭሱን በቱቦ መማግ ነው ሺሻ ማጨስ የሚባለው፡፡ ሺሻ ውስጥ ምን አለ? የትንባሆውን ጭስ ለማጣፈጥ እና ጉሮሮ ላይ እንዳይከብድ ለማድረግ ቅጠሉ ከፍራፍሬ ሲረፕ ወይም ከሞላሰስ ጋር ይቀላቀላል እንጂ ልክ እንደ ሲጋራ ሺሻም የሚሰራው ከትንባሆ ቅጠል ነው፡፡ ስለዚህ በውስጡ ልክ እንደ ሲጋራ ኒኮቲን (ትንባሆ ውስጥ የሚገኝ አነቃቂ እና ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገር) ፤ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ፤ አርሰኒክ እና ሊድ የተባሉትን መርዛማ እና ጎጂ ንጥረ ነገሮች ይዟል ማለት ነው፡፡ ሲጋራ ከማጨስ ሺሻ ማጨስ አይሻልም? ብዙ ጊዜ ሰዎች ሺሻን የሚያጨሱት ለተወሰነ ሰአት ስለሆነ እና እንደ ሲጋራ በየቤቱ ስለማይገኝ ከሲጋራ ይሻላል ይላሉ፡፡ የሺሻ ጭስ የፍራፍሬ ጣእም ስላለው እና ጭሱ በውሃ ውስጥ ስለሚያልፍ ጎጂ የሆኑት ንጥረ ነገሮች በውሃው ይፀዳል ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ♣ ልክ እንደ ሲጋራ ሁሉ ሺሻም ኒኮቲን ስላለው ሱሰኛ ያረጋል፡፡ እንደውም በሺሻ ውስጥ ያለው ኒኮቲን በሲጋራ ውስጥ ካለው ኒኮቲን በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ♣ አንድ የሺሻ ፕሮግራም ቢያንስ ቢያንስ አንድ ሰአት እና ከዛ በላይ ይፈጃል፡፡በዚህ ጊዜ አንድ ሰው ከ 150 እስከ 200 ጊዜ ያህል ጭሱን ይምጋል፡፡ አንድ ሲጋራ አጭሶ ለመጨረስ ግን 20 ጊዜ ጭሱን መማግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ስለዚህ አንድ የሺሻ ፕሮግራም 8 ወይም ከዛ በላይ ሲጋራ አከታትሎ ማጨስ እንደ ማለት ነው፡፡ (ይሄ ጥናት የተሰራው በአለም የጤና ድርጅት ነው) ♣ ሲጋራም ሆነ ሺሻ የሚሰሩት ከትንባሆ ቅጠል ስለሆነ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣሉ፡፡ ከነዚህ በሽታዎች ውስጥ የሳንባ ካንሰር እና የመተንፈሻ አካል ችግሮች፤ የጉሮሮ ካንሰር፤ አፍ ውስጥ የሚወጣ ካንሰር፤ ከጉሮሮ ወደ ጨጓራ ምግብን የሚወስደው የምግብ ቧንቧ ካንሰር እና የልብ ችግሮች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ለአይን ህመም እና ለቆዳ መሸብሸብ ይዳርጋል፡፡ ♣ ከሲጋራ በተለየ ሁኔታም ሺሻውን ለማጨስ በከሰል ስለምንጠቀም ከከሰሉ የሚወጣውን መርዛማ ንጥረ ነገር ነገር ካርቦን ሞኖኦክሳይድን ጨምሮ ወደ ሳንባችን ይገባል፡፡ ♣ አሁን አሁን የትንባሆ ቅጠል የሌለባቸው ኸርባል በመባል የሚታወቁ ሺሻዎች ወደ ገበያው እየመጡ ነው፡፡ ከምን እንደሚሰሩ አምራቾቹ ግልፅ አድረገው መናገር አይፈልጉም፡፡ቢሆንም እሱም ቢሆን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ካርቦን ሞኖኦክሳይድን ጨምሮ ወደ ሳንባችን ማስገባቱ አይቀርም፡፡ ♣ ሺሻ ሲጨስ በቡድን ተቀምጦ እየተቀባባሉ ስለሆነ የሚጨሰው የተለያዩ በትንፋሽ እና በምራቅ የሚተላለፉ በሽታዎች ከአንዱ አጫሽ ወደ ሌላው አጫሽ በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ለምሳሌ እንደ ቲቢ እና ሄፒታይተስ የመሳሰሉት በሽታዎች ይገኙበታል፡፡ ♣ ሲጋራ ወይም ሺሻ የሚጨስበት ቦታ መገኘት ባናጨስ እንኳን በእጅ አዙር ለጭሱ እና ለጉዳቱ ያጋልጠናል፡፡ ስንተነፍስ ጭሱን መማጋችን አይቀርም፡፡ ይሄንን ፈረንጆቹ ሰከንድ ሃንድ ስሞክ ይሉታል፡፡ ♣ ስለዚህ ለጤንነታችን ሲባል በተቻለ አቅም ሺሻን ማጨስ ማቆም አለብን፡፡ ለጤናዎ የሚጠቅሙ ፅሁፎችን ለማንበብ ገፃችን ላይክ ያድረጉ፡፡ ዶክተር ሀሎ

በእርግዝና ጊዜ ከማህፀን ደም መፍሰስ ችግር እንዴት ይከሰታል ማንኛውም ከ28 ሳምንት እርግዝና በኃላ የሚከሰት ከማህፀን ደምመፍሰስ ሲኖር በፍጥነት ወደጤና ተቋም መምጣት ተገቢ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ከመሀፀን የሚመጣ መድማት በፍጥነት ህክምና ካልተደረገ ለህይወት አደገኛ የሆነ የደም መፍሰስና ለፅንሱ መውረድ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡ከ 2-5% እርግዝና ላይ ይህ ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ * ብዙ ምክንያቶች ይህን የደም መፍሰስ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ከ50% በላይ በውል ምክንያቱ ባይታወቅም ዋና ዋናዎቹ 1. የእንግዴ ልጅ ከመሀፀን ግድግዳ ጋር በትክክል ካልተያያዘ ወይም የተያያዘው ክፍል በጥቂቱ ሲለቅ 2. የእንግዴ ልጅ ከመሀፀን ግድግዳ ከላይ ክፍል መያያዝ ሲኖርበት ከህፃኑ ጭንቅላት ቀድሞ ከታች ሲጣበቅ 3. የእንግዴው ልጅ የራሱ ሆኑ የአፈጣጠር ችግሮች ሲኖሩት 4. የማህፀን ወይም የማህፀን በር ጫፍ ኢንፌክሽንየመውደቅ ወይም 5. ማንኛውም ማህፀንን ሊነካ የሚችል ምት ወይም ግፊት 6. የደም ህዋሳት በሽታ 7. የማህፀን እንዲሁም ተያያዥ ክፍሎች ካንሰር እነዚህን ምክንያቶች ብዙውን ጊዜ የደም መፍሰስ እስኪከሰት ድረስ ሌላ ምልክቶች ቀድመው አያሳዩም፡፡ ስለዚህም ለእናቶች ቀድሞ ለማወቅና ለመጠንቀቅ አዳጋች ናቸው፡፡ነገር ግን በየጊዜው የቅደመ ወሊድ ክትትል በማድረግ ችግሮች የከፋ ሳይሆን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ መከላከያ መንገዶች . በጣም ሰውነትን ጫና የሚፈጥሩ ስራዎችን አለመስራት . በተደጋጋሚ የቅድመወሊድ ክትትል ማድረግ . እርግዝና ከመምጣቱ በፊት ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረግ . ማህፀን እረፍት እንዲያደርግ እርግዝናን ቢያንስ 2አመት ማራራቅ . የታዘዙ መድሀኒት ካለ በተገቢው መውሰድበደንብ እረፍት ማግኘት . የመውደቅ ወይም የመመታት አደጋ ካጋጠመ መድማት እንኳን ባይኖር የጤና ተቋም ሄዶ መታየት * የሚያመጣው ችግር . ከጊዜው በፊት ምጥ ማምጣት . የፅንሱን አስተዳደግ መቀነስ . የሽንት ውሀ ማነ . ስሽንት ውሀ ከጊዜው በፊት መፍሰስ(ምጥ ከመምጣቱ በፊት) . በኦፕሬሽን እንድትወልድ ግዴታ መሆን . ከወሰደች በኃላ ደም መፍሰስ . የማህፀን መሰንጠቅ . የፅንስ መውረድ የእናት ሞት * ህክምና ከላይ እንደተጠቀሰው ማንኛውም አይነት ደም መፍሰስ ሲኖር በአፋጣኝ የጤና ተቋም መምጣት የሁሉም እናት ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት፡፡ በጤና ተቋም በመጀመሪያ የደሙን ቀለም አብሮት የሚመጣ ህመም መኖር አለመኖሩን ብዛቱንና ከዚህጋር ተያያዞ የደም ግፊት የልብ ምት ሰላም መሆኑን ማጣራት አለበት፡፡ ከዚያ በአልትራሳውንድ እንዲሁም ተያያዥ ምርመራዎች ምክንያቱ መታወቅ ይኖርበታል የፅንሱ ሁኔታም በተለያዩ መንገዶች ይጣራል፡፡ ከነዚህ ምርመራዎች በኃላ እደምክንያቶቹ ህክምና ከመደረጉ በፊት በደም ስር ፈሳሽ ወይም ደም ካስፈለገ ሊሰጣት ይችላል፡፡ ከዚያም እንደአስፈላጊነቱ በመድሀኒት ህክምና ብቻ የሚስተካከል ከሆነ መድሀኒት በመስጠት በእረፍት የሚቀነስ ወይም የሚጠፋ ከሆነ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ በፍጥነት ልጅ መውለድ ካለበት ድንገተኛ ቀዶ ጥገና በማድረግ እርዳታ ልታገኝ ትችላለች፡፡ ባጠቃላይ ማንኛውም እርጉዝ የሆነች ሴት ከማህፀን ደም የመፍሰስ ችግር ካጋጠማት አፋጣኝ እርዳታ ማግኘት ተቀዳሚ ተግባሯ አድርጋ ተያያዥ የሆኑትን ችግሮች መከላከል ትችላለች፡ መልካም ጤንነት ሽር ሽር

ለመላው ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! ኢድኩም ሙባረክ !! كل عام وانتم بخير تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال!
ለመላው ሙስሊም ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! ኢድኩም ሙባረክ !! كل عام وانتم بخير تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال!

ጠቃሚ ምክር ሴጋ(Masturbation) እና መዘዙ (ብዙም ስለማናወራው ነገር ግን ስለምናደርገው ጎጂ ልማድ ለምክክር እንዲረዳ በግለጽ ቋንቋ የተጻፈ ነውና ምቾት የሚነሳህ መስሎ ከተሰማህ ያለማንበብ ምርጫው ያንተ ነው) ጀግናው ወንድሜ! ዛሬ ስለ ግለ-ወሲብ ከአሁን በኋላ ሴጋ እያልኩ የምጠራውን ጎጂ ልማድ በአንተ እና በትዳርህም ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ላወራህ እፈልጋለሁ። ይኽ ጎጂ ልማድ ከሚያመጣው መዘዞች ውስጥ መንፈሳዊ ጉዳቱን ሳይኾን አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ጠባይዓዊ.. ) ኪሳራውን ላወያይህ ፈልጌያለሁ። ይኼም ጽሑፍ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጽሑፎቼ ከራሴ ሕይወት የተማርኩትን በንባብም ያዳበርኩትን እውቀት ያማከለ ነው። እነኾ.... ሴጋ (በወንዱም ኾነ በሴቷ) መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ የእድሜ ልክ ክፉና ጎጂ ልማድ ነው። ክፉ አልኩት ይኽ ዐመል አንዴ ከተጠናወተ(ሴቷንም ኾነ ወንዱን) ለመተው እጅግ ከባድ ነውና፤ ጎጂም አልኩት አንተን አለመልቀቁ ሱሰኛም ማድረጉ አንተ ላይ አካላዊ፣ አእምሮኣዊና ስነልቦናዊ ጉዳትን ያመጣልና ነው። ሴጋና ልጆች ሴጋ ከሚያስከትለው ዘለቄታዊ አንዳንዴም(በወቅቱ ካልቆመ) የእድሜ ልክ ችግር ከመኾኑ አንጻር ልጆች ወደ ጉርምስና እድሜያቸው እየተቃረቡ ሲሄዱ ስለወሲብ ጸጋነትና አግባባዊ አጠቃቀሙ መማር አለባቸው። በተለይም አኹን ባለንበት ነባራዊ ዘመን የወንዶች ወንዳወንድነት ባሽቆለቆለበትና አባቶችም ወንዳወንድ ጠባይ በማያሳዩበት በዚህ ወቅት ልጆች በተለይም ሴቶች ልጆች ቶሎ ለመጎርመስና ለተሳሳተ የወሲብ ግንዛቤና ድርጊት ይጋለጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዘመን በወለዳቸው የቴክኖሎጂ ውጤት በኾኑ መሣሪያዎች የምናገኛቸው የወሲብ ትዕይንቶች(Pornography) ችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ። ምንም እንኳ ሴጋ በአብዛኛው የወንዶች ክፉ ልማድ ቢኾንም ከወሲባዊው አብዮት ወዲህ ግን የሚለማመዱት ሴቶቹም ቁጥር ጨምሯል። አንተ ታዲያ ሚስትህንና ልጆችህን(ወንዱንም ኾነ ሴቷን) ስለወሲብና ትክክለኛ(አግባባዊ) አፈጻጸሙ፣ ስለሴጋም ጎጂነት ታስተምር ዘንድ አንተ መጀመሪያ አውቀኸው(ጉዳቱንም ጭምር) ራስህንም ጠብቀህ ልትገኝ ይገባል። በዚህም መሠረት ሚስትህም ኾነች ልጆችህ በዚህ ልማድ እንዳይገኙ ሥርዓትን ልትሠራላቸው፣ ልትመክራቸው ፈጽመውት ቢገኙ ደግሞ ልትቀጣቸው ይገባሃል። የሴጋ ጎጂ ልማድነት(ከወንዶቹ አንጻር) ጉዳት ፩ አካላዊ ጉዳት ውዱ ወንድሜ! ሴጋ በቋሚነት የምትመታ ከኾነ የሰውነትህን ፈሳሽ፣ ወዝህን፣ ጉልበትህን አሟጦ ይጨርሰዋል። ይኽም ማለት ከሴጋህ በኋላ ሰውነትህ ይልፈሰፈሳል፣ አይንህ ይፈዛል(ስብር ይላል)። "እንዴዬ ወሲብስ ከሚስቴ ጋር ስፈጽም ይደክመኝ የለ?" ብትለኝ አዎን ወሲብም ከሚስትህ ጋር ብትፈጽም ይደክምሃል። ነገር ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ሰውነትህን የማይመጥ ጉልበትህንም የማይጨርስ ይልቁንስ መታደስ ያለበት ነው። ይኽ የሚኾነው ግን ከእርሷ ጋር የምትፈጽመው ወሲብ ሴጋህን የሚያስረሳ እርካታውም የጋራ መኾን ያለበት እንጂ ዝምብለህ እንደነገሩ ተንደፋድፈህ መነሳት ከኾነ ውጤቱ ከሴጋው ብዙም አይለይም። ጉዳት ፪ አእምሮአዊ ጉዳት በተለይም በዚህ ዘመን ለሴጋ ወሲባዊ ትዕይንቶች(Pornography) ከፍተኛ መንሴዔዎች ናቸው። በስሜት ሕዋሶቻችን የተቀበልናቸውን መልእክቶች ተንተርሶ አስፈላጊው አጸፋዊ ምላሽ በሚመለከተው የሰውነት ክፍል እንዲሰጥ የሚያዘው አእምሮ ነው። በወሲባዊ ትዕይንቶች የተነካው(መልእክት የተቀበለው) የአእመሮአችን ክፍል የልብ ምታችን እንዲጨምር፣ ደምም በፍጥነት እንዲዘዋወር (በተለይም ወደ ብልታችን) ከዚህም የተነሳ እንዲነቃቃ ያደርጋል። ይኽን ልማድ ያደረገው አእምሮህ ታዲያ ሚስትህን ስታይ፣ ጠረኗ ሲሸትህ፣ ሰውነቷን ስትዳብስ(ስትዳብስህ)፣ ለወሲብም ወደምንጣፍህ ስትወጣ አእምሮህ ሰውነትህን ለማዘዝ ይዘገያል(አያዘውም)። ምክንያቱ ደግሞ እርሱ የሚያውቀውና የለመደው ስሜት መቀስቀሻ ሌሎች ወሲብ ሲፈጽሙ ማየት ነውና። ጉዳት ፫ ስነልቦናዊ ጉዳት ሴጋ ስትመታ "ወሲቡ"(ከተባለ) አንተ በራስህ ለራስህ ብቻ የምትፈጽመው የምትወዳትን ሚስትህን ያላሳተፈ ነውና በራስወዳድነት ማዕበል እየተንገላታህ ለሚስትህ ያለህ ናፍቆትና ስስትም እየቀነሰ ይሄዳል። አለባበሷን ማድነቅ፣ የናፍቆትና የፍቅር ቃላትን መናገር፣ ፈቃዷን መፈጸምና ፍላጎቷንም በአግባቡ ማርካት ይሳንሃል። ምክንያቱ ደግሞ የእነዚህ ምንጭ የኾነውን ወሲባዊ ስሜት (መነቃቃት) በሴጋ አድርቀኸዋልና ነው። ጉዳት ፬ ከሴት ያርቅሃል ሴጋን በቋሚነት ለሚመታ ወንድ ሴቶችን መቅረብ(መጥበስ)፣ ማናገር(መጀንጀን) ይሳነዋል። የመጠየቅ፣ የመነጋገርና የመግባባት ብሎም የመፋቀርን ሽልማትና እርካታ በዋዛ በሴጋ ያገኘዋልና(ምንም እንኳ ሴጋ ለወሲብ ምትክ ባይኾንም)። ጉዳት፭ ወኔህን ይሰልበዋል ፈርጀብዙ የኾነ አባወራዊ ሚናህን የምትወጣበትን ወኔ ይገድለዋል። እያደርም ለቤትህ፣ ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ግድ የሌለህ በራስወዳድነት ባሕር ሰምጠህ እንድትቀርም ያደርግሃል። ጉዳት ፮ ለስንፈተ ወሲብ ይዳርግሃል ውድ ወንድሜ! እኔ ይኼን ስጽፍልህ ትማርበት ዘንድ በእርሱም ፈጣሪ የሰጠህን ጸጋ በአግባቡ ተጠቅመህ በትዳርህ አንድነትህን ታጠነክርበት ዘንድ ነው። እርግጠኛ ኾኜ የምነግርህ ሴጋ ለስንፈተ ወሲብ እንደሚዳርግህ ነው። እንዴት? .... ይቆየን።

የወንዶች የወሲብ ችግር # Doctor_Alle_8809_MenDecreasedL ibidoTips የብልት ያለመቆም ችግር የብልት ያለመቆም ችግር አለ የምንለዉ የወንድ ብልት ለግብረ ስጋ ግንኙነት ሲዘጋጅ አልቆም ሲል ወይም የተወሰነ ቢቆምም ምንም ጥንካሬ የሌለዉ ከሆነ ነዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከቀጠለ በወንድየዉ ላይ ጭንቀትን፣በራስ ያለመተማመንንና የግብረስጋ ግንኙነት ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል፡፡ የወንዶች ብልት ያለመቆም ችግርን ለህክምና ባለሙያዎ ማወያየት የሚከብድ ቢመስልም ለብልት ያለመቆም ችግር መንስኤ የሆኑና ቢታከሙት ችግሩን ሊያቃልል የሚችሉ እንደ የልብና የስኳር ህመም ያሉ የውስጥ ደዌ ችገሮች ስላሉ ምንም ሳያፍሩ የህክምና ባለሙያዎን ማወያየት ይመከራል፡፡ ችግሩን ያመጡትን ነገሮችን በመታከም ለዉጥ ከሌለዉ ደግሞ ሌሎች ስንፈተ ወሲብን ሊያክሙ የሚችሉ መድሃኒቶች ስላሉ ባለሙያዎትን ማማከርን አይርሱ፡፡ የወንድ ብልት ያለመቆም ችግር ምልክቶች • የብልት አልቆም ማለት • የብልት ቆሞ ያለመቆየት/ ቶሎ መልፈስፈስ • የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ የህክምና ባለሙያዎትን ማማከር ያለቦት መቼ ነዉ? • የብልት ያለመቆም ችግር ወይም ሌሎች የወሲብ ችግሮች እርስዎንና አጋርዎን ካስጨነቅዎ • ከብልት ያለመቆም ችግር ጋር ተያያዥ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ የስኳር፣ የልብ ህመም ወይም ሌሎች የጤና ችግሮች ካለዎ • ከስንፈተ ወሲብ ጋር የሚገናኙ የማይመስሉ ሌሎች የህመም ምልክቶች ከስንፈተ ወሲብ ጋር አብሮ ካለዎ ለብልት ያለመቆም ችግር ምክንያቶች ምንድን ናቸዉ? ለወንዶች የወሲብ ስሜት መነቃቃት አእምሮ፣ ሆርሞኖች፣ ነርቮች፣ ጡንቻዎች፣ የደም ስሮችና ስሜት (emotions) የሚሳተፉ ሲሆን ይህ ሂደት እጅግ ውስብስብ ነዉ፡፡ የብልት ያለመቆም ችግር ከእነዚህ በአንዱ ወይም በሌለኛዉ ላይ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ሊመጣ ይችላል፡፡ ጭንቀትና የስነ አዕምሮ ችግሮች ችግሩን ሊያባብሱት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ የብልት ያለመቆም ችግርን ሊያመጡ የሚችሉ አካላዊ ችግሮች • የልብ ህመም • የደም ስሮች መዘጋት ( atherosclerosis) • የደም ግፊት መጨመር (የደም ብዛት) • የኮሌስትሮል መጨመር • የስኳር ህመም • ዉፍረት • የፓርኪንሰንስ ህመም • መልቲፕል ስኬሎሮሲስ • የወንዶች ሆርሞን (ቴስቴስትሮን) መጠን መቀነስ • በወንዶች ብልት ዉስጥ ጠባሳ መፈጠር • ለህክምና የሚታዘዙ መድሃኒቶች • መጠጥ (አልኮሆል)ና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች • የፕሮስቴት ዕጢ ማበጥ ወይም የፕሮስቴት ዕጢ ህክምና • በዳሌ አካባቢ ወይም በህብለሰረሰር ላይ በሚደረግ ቀዶጥገና ወቅት የሚደርስ አደጋ የብልት ያለመቆም ችግር የሚያመጡ ስነ ልቦናዊ ምክንያቶች፡ አዕምሮ ተከታታይነት ያለዉ አካላዊ ሁነቶችን በማነሳሳት ለብልት መቆምና ወሲባዊ ደስታዎችን በማምጣት ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል፡፡ ለወሲባዊ ስሜቶች ችግርና ለብልት ያለመቆም ችግርን የሚያባበሱ የተለያዩ አዕምሮአዊ ነገሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ፡ • ድብርት፣መረበሽ ወይም ሌሎች የስነ አዕምሮ ችግሮች • ጭንቀት • በጭንቀት ምክንያት የግንኙነት ችግሮች፣ የሰዉ ከሰዉ ተግባቦት ችግር ወይም ሌሎች ነገሮች ለብልት ያለመቆም ችግር የሚያጋልጡ ነገሮች ዕድሜዎ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ብልት ለመቆም ረዘም ያለ ሰዓት የሚወስድ ሲሆን ከቆመም በኃላ በጣም ጠንካራ ላይሆን ይችላል፡፡ ዕድሜ እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት የብልት ያለመቆም ችግር የሚከሰተዉ ከእድሜ መጨመር ጋር አብረዉ የሚመጡ የጤና ችግሮችና የሚወስዷቸዉ መድሃኒቶች ስላሉ ነዉ፡፡ ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች • የውስጥ ደዌ ችግሮች፡ ስኳርና የልብ ችግሮች • ሲጋራ ማጨስ • ዉፍረት፡ በተለይ በጣም መወፈር • የተወሰኑ መድሃኒቶች፡ ለድብርት፣ ለአለርጂዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች፣ ለካንሰርና ለደም ግፊት ህክምና የሚሰጡ መድሃኒቶች • አደጋ፡ በተለይ ለብልት መቆም የሚረዳዉ ነርቭ ላይ አደጋ ሲደርስ • ስነልቦናዊ ችግሮች፡ ጭንቀት፣ድብርት • አደንዛዥ ዕፅና አልኮሆል የሚጠቀሙ፡ በተለይ ረዘም ላለ ጊዜ ለተጠቀሙ ለረጅም ጊዜ ብስክሌት የሚያሽከረክሩ፡ ይህ ነርቮችን ስለሚጫንና ወደ ብልት በሚሄደዉ የደም ዝዉዉር ላይ ግዜያዊ ጭነት ስለሚያመጣ ግዜያዊ የብልት ያለመቆም ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለብልት ያለመቆም ችግር ጊዜ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች፡ • አካላዊ ምርመራ፡ በብልትዎ፣ በዘር ፍሬዎና በነረቮች ላይ ምርመራ ማድረግ • የደም ምርመራዎች • የሽንት ምርመራ • የአልትራሳዉንድ ምርመራ • በእንቅልፍ ሰዓት የብልት መቆም ምርመራ፡ • ስነልቦናዊ ምርመራዎች ለብልት ያለመቆም ችግር የሚደረጉ ህክምናዎች መጀመሪያ የሚደረገዉ ለሌላ ህመም እየወሰዱ ያለ መድሃኒት ካለ ለብልትዎ ያለመቆም ችግር ምክንያት መሆን ያለመሆኑን ማረጋገጥ በአፍ የሚዋጡ መድሃኒቶች • ሲልደንፊል (ቪያግራ) • ታደልፊል (ሲያሊስ) • ቫርድንፊል እነዚህ መድሃኒቶች የሚሰሩት ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ሲሆን የብልትዎን ጡንቻዎች በማላላትና ወደ ብልት የሚሄደዉን ደም በመጨመር ወሲባዊ መነቃቃት በሚፈጠርበት ወቅት ብልትዎ እንዲቆም ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን መድሃኒቶች ከመዉሰድዎ በፊት የጤና ባለሙያዎትን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የሚከተሉት ነገሮች ካሉ ላይሰሩ ይችላሉ ወይም ለጤና አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡ • ናይትሬት ያላቸዉን መድሃኒቶች እየወሰዱ ከሆነ (ናይትሮግላይሴሪን) • ለደም ማቅጠኛ የሚሰጡ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ፣ አልፋ ብሎከርስ የሚባሉና ለፕሮስቴት ህክምና እየወሰዱ ከሆነ፣ የደም ግፊት መቀነሻ መድሃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ • የልብ ችግር ወይም ድካም ካለዎት • የደም ግፊት በጣም መቀነስ ካለዎት ወይም በህክምና ያልተቆጣጠረ የደም ብዛት ካለዎት • በስትሮክ ከዚህ በፊት ታመሁ ከሆነ • በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ካለዎት ሌሎች መድሃኒቶች (በኢትዮጵያ ውስጥ ላይገኝ ይችላል) • እራስን በራስ የሚወጉ አልፕሮስታዲል • በብልት የሚገቡ አልፕሮስታዲል • የወንዶች ሆርሞንን(ቴስቴስትሮን) መተካት ከመድሃኒቶች አልሰራ ካሉ ወይም በተለያ ምክንያት መድሃኒቶችን መጠቀም የማቻል ከሆነ ሀኪምዎ የሚከተሉትን ሊያዝሎት ይችላል • ፔኒስ ፓምፕ • ፔኒስ ኢምፕላንትስ • የደም ስር ቀዶጥገናዎች ስነልቦናዊ ምክሮች የብልት ያለመቆም ችግርዎ ከጭንቀት፣መረበሽ ወይም ድብርት ጋር የተገናኘ ከሆነ የስነዓዕምሮ ባለሙያዎችን ወይም የስነልቦና ባለሙያዎችን ማማከር ያስልጋል፡፡ የብልት ያለመቆም ችግር የመጣዉ አካላዊ በሆነ ችግር ቢሆን እንኳ ጭንቀትና የግንኙነት ችግር ማምጣቱ ስለማይቀር እነዚህን ባለሙያዎች ማማከር ይጠቅማል፡፡ የኑሮ ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ • ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቛረጥ • ክብደትን መቀነስ • የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ/ማዘዉተር • አደንዛዥ ዕፅ ወይም አልኮሆል በመዉሰድ እየተቸገሩ ከሆነ ህክምና ማግኘት • የግንኙነት ችግሮች ካለቦት መፍትሄ መፈለግ ተጨማሪ ምክሮች • ችግሩ ለረጅም ጊዜ ያለ/የሚቀጥል ነዉ ብሎ ያለመዉሰድ • የትዳር ወይም የፍቅር አጋረዎን በመፍትሄዉም ይሁን በችግርዎ ዉስጥ አጋር ማድረግ • ጭንቀትን፣መረበሽንም ይሁን ማንኛዉንም የስነአዕምሮ ችግሮች ችላ ብሎ ያለማለፍ በቀጣይ በስንፈተ ወሲብ ዙሪያ ከባለሙያ ጋር የተደረገ ሰፋ ያለ ዝርዝር ማብራሪያ ይዘን እንቀርባለ፡፡ @ @DrSofonias #share

የጥቁር_አዝሙድ_ዘይት ----------------------------------- #ለካንሰርና #እባጮች አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ ግማሽ ሠዓት በፊት ይጠቀሙ። #ለስኳር #በሽታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመጨመር ስኳርን በማቆም የአመጋገብ ለውጥ ያድርጉ። #ለተቅማጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ እርጎ ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። #ለደረቅ #ሳል ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከቡና ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ጀርባዎና ደረትዎን በዘይት ይሹት። #ለጆሮ #ህመም በስሱ የተቆላ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ይውሰድ ከዚያም ጥቂት የኦሊቭ ዘይት ጠብታዎች በመጨመር በደንብ ይቀላቅሉት። ሰባት ጠብታ በሲሪንጅ ውስጥ ይክተቱ ከዚያም ጠዋት እና ማታ ጆሮዎ ውስጥ ይጨምሩ። #ለዓይን #ህመም እና #ለእይታ #ችግር ወደ መኝታ ከመሄድዎ ከግማሽ ሠዓት በፊት የአይን ቆብዎንበጥቁር አዝሙድ ዘይት ይሹት። ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባይ የካሮት ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ይጠጡ። #ለፊት #ፓራሊሲስ አንድ የሻይ ማንኪይ ዘይት ለብ ባለ ውሃ ውስጥ በመጨመር እንፋሎቱን ይታጠኑ። #ለጉንፋን አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት ይውሰድ። በእያንዳንዳቸው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ይጨምሩበት። #ለሃሞት #ጠጠር እና #ለጉበት #ጠጠር አንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝምድ ፍሬ ከማር ጋር በብርጭቆ ውስጥ ይቀላቅሉት ጥቂት ለብ ያለ ውሃ ይጨምሩበት። በመጨረሻም በመጨረሻም አንድ የሻይ ማንኪያ ዘይት ይጨምሩበት ይህን ውህድ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ይጠጡ። #ለአጠቃላይ #ጤንነትና #ደህንነት አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ይጠቀሙ። ወይም ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት በየቀኑ ይጠቀሙ። #ለፀጉር #መሳሳት እና #ያለዕድሜ #ሽበት በመጀመሪያ ፀጉርዎን ይታጠቡ ከዚያም በቂ የሆነ የኦሊቭ ዘይት ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር በመቀላቀል ይቀቡት። ከአንድ ሠዓት ቆይታ በኋላ ያለቅልቁት ወይም ይታጠቡት። #ለራስ #ህመም እና #ማይግሬን ከግንባርዎ ግራ ክፍል ትንሽ ዝቅ ብሎ ወይም ቴምፕል በሚባለው የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመቀባት ይሹት። ጥቂት ጠብታዎች በአፍንጫዎ ቀዳዳ እና ጭንቅላትዎ ላይ ያድርጉ። በቀን ሁለት ጊዜ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬና ማር ይብሉ። #ለማስታወስ #ችሎታ ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሶስት ጊዜ ይመገቡ። #ለአፍ #ኢንፌክሽን #ቫይረስ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ በአፍዎ ውስጥ ከ 10 – 15 ደቂቃ ይያዙት። #ለጡንቻ #ህመም አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከማር ጋር በመቀላቀል በቀን ለሶስት ጊዜ ይውሰድ። የቅልጥም መረቅ በየቀኑ ይጠጡ የቻሉትን ያክል ዘቢብ በየቀኑ ይመገቡ። ኩሽ ቲዩብን ይቀላቀሉ #ለሪህና #ጀርባ #ህመም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ሞቅ በማድረግ የሚያምዎትን ቦታ ይሹት። በየቀኑ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ እና ማር ይመገቡ። #ለሆድ #ህመም በአንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከማር ጋር በመቀላቀል ይጠቀሙ። ጥቂት የፔፐርሜንት ሻይ ይጠጡ ከዚያም የረሃብ ስሜት ከተሰማዎት የተቀቀለ ሩዝ ውሃ ይጠጡ። ለጥርስ ህመም እና #ድድ ኢንፌክሽን በኩባያ የሎሚ ጭማቂ በማድረግ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ይጨምሩበት ከዚያም ያፍሉት። ሼር በማድረግ ላላወቁ ያሳውቁ

*ለኩላሊት በሽታ የመጋለጥ አጋጣሚን መቀነስ የሚቻልበት ፱ መንገዶች።* ኩላሊት የባቄላ መሰል ቅርጽ ሲኖረው የጀርባ አጥንት ባላቸው እንስሳት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ የቁጥጥር ሚና ያለው የሰውነት ክፍል(አካል) ነው።ከመጠን ያለፈ ግልኮስ ሲኖር ማስወገድ፣በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ ሂደቶች ሁሉ የሚፈጠሩትን ተረፈ ምርት ማስወገድን (ከውሃ ሽንት ውስጥ ፺ በመቶ የሆነውን ውሃ በማምጠጥ ለዳግም ጥቅም እንዲውል የሚደረገው በዚሁ አካል ነው።) እንዲሁም ለሽንት ተረፈ ምርት መዘጋጀትና መወገድ፣የአሲድ ቤዝ መጠን በሰውነት ውስጥ ማመጣጠን፣የደም ግፊትን መቆጣጠር(ውሃ እና ጨውን ማመጣጠን) እና ኤሌክትሮላይትን የመቆጣጠር ሥራ ይሰራል። ኩላሊት እንደ ተፈጥሯዊ ማጣርያ ሊቆጠር ይችላል።ደምን በማጥራት በውሃ ውስጥ የሟሙ ተረፈ ምርቶችን ወደ ሽንት ከረጢት ይልካል።ኩላሊት በተጨማሪም የተለያዩ ሆርሞኖችን ያመርታል።ለምሳሌ ካልሲትሪኦል፣ኤራይቶሮፖኤቲ እና ሬኒንኢንሃምን። ኩላሊት የስረኛው የጎድን አጥንት አካባቢ ሲገኝ ከልብ ጥንድ በሆኑት የደም ላኪ ቧንቧዎች ደም ተቀብሎ በማጣራት ጥንድ ለሆኑት ደም መላሽ ይልካል።በዚህ ጊዜ ኩላሊት ያስቀረው አላስፈላጊ ተረፈ ምርት ወደ ሽንት ከረጢት(ፊኛ) ይላካል። የተለያዩ አይነት የኩላሊት በሽታዎች ኤሉ።የሽንት ቧንቧ ቁስለት(ኢንፌክሽን)፣የሽንት ቧንቧ እክል መግጠም ፣የተለያዩ የኩላሊት ካንሰር፣የኩላሊት ምች(renal cysts) እና የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል። የኩላሊት ካንሰርንና የኩላሊት ምች(renal cysts) ሊታከም የሚችለው የተጠቃውን ኩላሊት በማስወገድ ብቻ ነው። የተቀሩትን ደግሞ በኩላሊት ንቅለ ተከላና በዲያላሲስ ሊታከሙ የሚችሉበት አማራጮች ናቸው። በተጨማሪም አስጊ የሆነ የኩላሊት ጠጠር በአልትራ ሳውንድ ህክምና ጠጠሮቹን በመሰባበር ወደ ጥቃቅን ስብርባሪዎች በመቀየር በሽንት በኩል እንዲወጡ ይደረጋል።ምንም እንኳን ጠጠሩ በሽንት ቧንቧ ውስጥ ተጉዞ ሲወገድ የህመም ስሜት ቢፈጥርም። በመሆኑም በሚከተለው መንገድ ኩላሊትን በእነዚህ በሽታዎች የመጠቃት እድሉን መቀነስ ይቻለል። ፩) አትክልትና ፍራፍሬን በመመገብ ፪) ተከታታይነት ያለው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ፫) የደም ስኳር መጠን በመጠበቅና ዝቅ በማድረግ ፬) መደበኛ የሆነ የደም ስኳር መጠን ልኬት በማድረግ ፭)ወደ ሰውነት ውስጥ የሚገባውን የጨው መጠን ዝቅ በማድረግና ውሃ በብዛት በመጠጣት(ቢያንስ በቀን ፪ ሌትር) ፮) ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ በማቆም ፯) ከፋብሪካ መድሃኒቶች(ኪኒን) ይልቅ ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ ምግቦችን በመጠቀም ፰) በየጊዜው የኩላሊት ምርመራ ክትትል በማድረግ