uk
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Відкрити в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 19 946 підписників, посідаючи 1 156 місце в категорії Медицина та 1 680 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 19 946 підписників.

За останніми даними від 28 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -539, а за останні 24 години на -5, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 25.64%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 7.06% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 5 115 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 408 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 9.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 29 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Медицина.

19 946
Підписники
-524 години
-1197 днів
-53930 день
Архів дописів
ቃር /Heartburn ******************** ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው። በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ (አሶፕሃጉስ) ሲገባ ነው። ✔ ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች? * ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ * ሽንኩርት * ሲትረስ ያላቸው ምግቦች * ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች * ቸኮሌት * የአልኮል መጠጦችን መውሰድ * ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ * ከጥጋብ በላይ መመገብ * ከመጠን ያለፈ ውፍረት * ነፍሰጡርነት ናቸው። ✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው? ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው። ✔ ከዚህ በተጨማሪ * በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ * ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ * ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት * የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል። ✔ ቃርን ለማስታገስ መደረግ ያለባቸው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች * የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል * ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ * የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ * ሲጋራን አለማጤስ * በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው። ጤና ይስጥልኝ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

"የልጆች የሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ምንድነው? [ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም?] . ብዙ ጊዜ እናቶች ልጄን ብርድ መታው እና በጣም ያስላል ይላሉ:: እውነት ብርድ የሚባል የልጆች በሽታ አለ? ይሄንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት እስኪ ስለ ሳምባ ምች የተወሰነ ነገር ልበል:: . ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት የሳምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል መቆጣት እና መታመም ነው:: . ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን ሲሆን ይህ አካል ደሞ ኒሞኒያ በሚባለው በሽታ ሲጠቃ ሳምባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት(Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላል በዚህም ምክንያት ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን አያገኝም:: የልጆች ሳምባ ደሞ በደምብ ያልዳበረ እና ጠባብ ስለሆነ በወቅቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል:: . እንደ ዓለም የጤና ድርጅት (WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል:: . 👉 ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) መንስኤው ምንድነው? ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ, በባክቴርያ, በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው:: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል:: ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ከገባ ኒሞኒያ ሊያስከትል ይችላል:: ከ5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም ከጉፋን መሰል ምልክቶች ነው:: . 🛑ልጆችን ለሳም ባምች(ኒሞኒያ) የሚያጋልጡ ነገሮች 1. የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት 2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል:: 3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም(በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት) 4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር 5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች 6. የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው:: . ምልክቶቹ ምንድናቸው? ➡️ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ➡️ ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ ➡️ ትኩሳት ➡️ ማቃሰት ➡️ ትውከት ➡️ የደረት ውጋት ወይም ህመም ➡️ ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው:: . 🛑 ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ እና ማሳከም ይኖርቦታል:: . 🛑 ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው? 📌ክትባት 📌ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ 📌 ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲሮር ማድረግ 📌የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ 📌 እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ 📌ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ 📌ልጆችን ጉፋን ከያዛቸዉ ሰዎች በተቻለ መጠን ማራቅ . - በመጨረሻም ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም? ለሚለው ጥያቄ በአጭሩ በዘመናዊ ሕክምና ዉስጥ ብርድ የሚባል ነገር የለም! አንዳንድ ሰዎች ብርድ የሚለው ቃል ከሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ጋር ሲያምታቱ ይታያል ይሄ ትክክል አይደለም ቀዝቃዛ አየር የሳምባ ምች አያመጣም! በርግጥ ቀዝቃዛ አየር ሊያነሳሳቸው የሚችሉ በሽታዎች ይኖራሉ ለምሳሌ የአፍንጫ ወይም የሳይነስ አለርጂ እና የመሳሰሉት:: ለማንኛዉም ማህበረሰቡ ብርድ የሚለውን ቃል ከምን ከምን ጋር እንደሚያይዘው ጠለቅ ያለ ምርምር ይጠይቃል ብዬ አምናለሁ::

የሰውነት ላብ እና ጠረን እንዴት ማሶገድ እንችላለን ቪድዮውን ይመልከቱ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

#ሰላም #ጤና #ይስጥልኝ #ውድ #ተከታታዮቻችን #ለዛሬ #ለእናተ #ይጠቅማል #ብለን #ያሰብንውን #ጤና #መረጃ #ይዘን #ቀርበናል #እንድታነቡ #በአክብሮት #ተጋብዛችኃል። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መፈክ
#ሰላም #ጤና #ይስጥልኝ #ውድ #ተከታታዮቻችን #ለዛሬ #ለእናተ #ይጠቅማል #ብለን #ያሰብንውን #ጤና #መረጃ #ይዘን #ቀርበናል #እንድታነቡ #በአክብሮት #ተጋብዛችኃል። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መፈክሮች • ውሃ በብዛት ይጠጡ፡፡ • በቂ የሆነ እንቅልፍ ያግኙ፡፡ • ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ፡፡ • የሚያዝናናዎትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ይምረጡ፡፡ • አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ይመገቡ፡፡ • የሚስብ ቀለም ያላቸውን ምግቦችን ይምረጡ፡፡ • የታሸጉ ምግቦችን መመገብዎን ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • ራስዎን ይውደዱ፡፡ • አልፎ አልፎ በባዶ እግርዎ ይራመዱ/ይሩጡ፡፡ • አይሆንም የሚለውን ነገር ከውስጥዎ ያስወግዱ፡፡ • በሽታዎን ሊያስነሱ የሚችሉ ምግቦችን መውሰድ ያቁሙ፡፡ • መጠኑ ጥቂት የሆነ ገበታ ይመገቡ፡፡ • በጥልቀት ይተንፍሱ፡፡ • ከጠገቡ በኋላ በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ትርጉም ያለው ህይወት ይኑሩ፡፡ • ቅባት ወይም ዘይት የበዛባቸው ምግቦች በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ስኳር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • አቋምዎን ያስተካክሉ፡፡ • ሶዳ እና ካፌይን ይቀንሱ ወይም አይጠቀሙ፡፡ • አልኮል አይጠጡ፡፡ • የራስዎን ምግብ ራስዎ ማዘጋጀት ይልመዱ፡፡ • ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ፡፡ • የአፍና ጥርስዎን ጤንነት ይጠብቁ፡፡ @DrSofonias

#ሰላም #ጤና #ይስጥልኝ #ውድ #ተከታታዮቻችን #ለዛሬ #ለእናተ #ይጠቅማል #ብለን #ያሰብንውን #ጤና #መረጃ #ይዘን #ቀርበናል #እንድታነቡ #በአክብሮት #ተጋብዛችኃል። ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መፈክሮች • ውሃ በብዛት ይጠጡ፡፡ • በቂ የሆነ እንቅልፍ ያግኙ፡፡ • ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ፡፡ • የሚያዝናናዎትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ይምረጡ፡፡ • አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ይመገቡ፡፡ • የሚስብ ቀለም ያላቸውን ምግቦችን ይምረጡ፡፡ • የታሸጉ ምግቦችን መመገብዎን ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • ራስዎን ይውደዱ፡፡ • አልፎ አልፎ በባዶ እግርዎ ይራመዱ/ይሩጡ፡፡ • አይሆንም የሚለውን ነገር ከውስጥዎ ያስወግዱ፡፡ • በሽታዎን ሊያስነሱ የሚችሉ ምግቦችን መውሰድ ያቁሙ፡፡ • መጠኑ ጥቂት የሆነ ገበታ ይመገቡ፡፡ • በጥልቀት ይተንፍሱ፡፡ • ከጠገቡ በኋላ በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ትርጉም ያለው ህይወት ይኑሩ፡፡ • ቅባት ወይም ዘይት የበዛባቸው ምግቦች በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ስኳር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • አቋምዎን ያስተካክሉ፡፡ • ሶዳ እና ካፌይን ይቀንሱ ወይም አይጠቀሙ፡፡ • አልኮል አይጠጡ፡፡ • የራስዎን ምግብ ራስዎ ማዘጋጀት ይልመዱ፡፡ • ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ፡፡ • የአፍና ጥርስዎን ጤንነት ይጠብቁ፡፡

#የጨጓራ #በሽታን #በቤት #ውስጥ #ማከም የጨጓራ ህመም ምንድን ነው? የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠት ሲሆን ህመሙ ወደ ጎን ጥንት አካባቢ ጨምሮ ሊስማ ይችላል፡፡በእንግሊዘኛ መጠርያው ጋስትራይቲሰ ማለትም የጨጓራ ቁስለት ባሁን ሰዓት በሀገራችን አንገብጋቢ የጤና ችግር እየሆነ መቷል፡፡ በአጠቃላይ የጨጓራ ችን የላይኛው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች መላጥ፤መጎዳትና መቁሰል ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ለጨጓራ ቁስለት/ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች የጨጓራ ባክቴሪያ በመባል የሚጠራው ኤች. ፓይሎሪ አንዱ የጨጓራ በሽታ መነሻ ነው ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ግድግዳን የሚያጠቃ ሲሆን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል የተዛባ የእመጋግብ ስርአት ለጨጓራ ጸር የሆኑ መድሀኒቶች NSAID,TB መድኃኒቶች….. የጨጓራ ባክቴርያ በጨጓራችን ውስጥ መኖር የሚያቃጥሉና የሚለበልቡ ምግቦች ማዘውተር እርግዝና ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት ዕድሜ (የጨጓራ ግድግዳ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እየሳሳ ይመጣል · የመመገቢያ ሠአትን ጠብቆ አለመመገብ የጨጓራ በሽታ ምልክቶች የማቅለሽለሽ ስሜት የሆድ ህመም የሆድ መነፋት ማስታወክ የምግብ አለመፈጨት የማቃጠል ወይም የማግሳት ስሜት በምግብ ሰዓት አካባቢ ወይም በማታ ሰዓት ስቅታ(ስርቅታ) የምግብ ፍላጐት መቀነስ የደም ወይም የቡና ቀለም ያለው ትውከት ጥቁር ቀለም ያለው ዓይነ ምድር ናቸው። የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ምንድነው? ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ካፌይን ያላቸው መጠጦች (ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ) አለመጠቀም ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎች ( ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ) አለመጠቀም ሲጋራ ሚያጨሱ ከሆነ ማቆም ከፍተኛ የቅባት/ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው ከነዚህ ምግቦች መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህንና መስል ለጤናችን ተስማሚ የሆኑ ነገሮችን ብንጠቀም የጨጓራ ህመምን በቀላሉ ልንከላክል እንችላልነ. ሆኖም ግን ህመሙ የባሰና ልንቋቋመው ካልቻልን በአፋጣኝ ወደ ሃኪም ቤት መሄድ ይኖርብናል፡፡ የጨጓራ ህመምን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን? 1. ዝንጅብል! - አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡ 2. እርጎ! - በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡ 3. ድንች! - ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት። 4. ቆስጣ እና ካሮት! - የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት። 5. ውሃ! - በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት። 6. በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ… 7. ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ። 8. ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት። 9. በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ። 10. ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ። 11. በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ። 12. ሥጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም። 13. አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም። 14. ቡናና ሻይ መቀነስ። 15. ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም። 16. በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ። 17. ቅመማ ቅመም መቀነስ ናቸው።

ብጉንጅን በቤት ውስጥ በቀላሉ ለማከም… ብጉንጅ በቆዳ ላይ በእብጠት መልክ በመውጣት ወደ ቁስልነት የሚቀየር ሲሆን፦ በተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል። ብጉንጅ በሰውነት ላይ ከሚፈጥረ
ብጉንጅን በቤት ውስጥ በቀላሉ ለማከም… ብጉንጅ በቆዳ ላይ በእብጠት መልክ በመውጣት ወደ ቁስልነት የሚቀየር ሲሆን፦ በተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል። ብጉንጅ በሰውነት ላይ ከሚፈጥረው እብጠት እና የመቁሰል ምልክት በዘለለ የከፋ አደጋ ጉዳት እንደማያደርስም ነው የሚነገረው። ሆኖም ግን አልፎ አልፎ የሰውነት ትኩሳት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ አይነት ምልክቶች ሊያሰከተል ይችላል። ብጉንጅ የሰውነታችን አካል ላይ የመቆረጥ አደጋ ሲያጋጥም በሚፈጠር ቁስል ወይም በጭንቅላታችን ላይ ባለ የጸጉር መውጫ ቀዳዳ በኩል ወደ ሰውነታችን በሚገቡ ባክቴሪያዎች አማካኝነት ሊከሰት ይችላል። ይህንን ችግር በቤት ውስጥ በሚዘጋጁና ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎችን እነሆ ብለናል። ኦ.አር.ኤስ ወይም በተለምዶ የእንግሊዝ ጨው በሙቅ ወይም ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ኦ.አር.ኤስ ወይም በተለምዶ የእንግሊዝ ጨው በመባል የሚታወቀዉን በመጨመር በሚገባ ከደባለቅን በኋላ ሰውነታችንን በውሃው መታጠብ ከብጉንጅ በቀላሉ ሊፈውሰን ይችላል ይላሉ ተመራማሪዎች። ዳቦ ዳቦ ብጉንጅን ለማጠፋት ፍቱን ነው የተባለለት ሲሆን፦ ለብ ያለ ውሃ ወይም ወተት ካዘጋጀን በኋላ ዳቦውን እዛ ውስጥ ጨምረን በማዋሃድ ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ በቀን ሁለት ጊዜ በመቀባት ራሳችንን በቀላሉ ማከም እንችላለን። ነጭ ሽንኩርት ለብዙ ህመሞች ፈዋሽ መሆኑ የሚነገርለት ነጭ ሽንኩርት ብጉንጅን ለማከምም ጠቀሜታ እንዳለው ነው የሚነገርለት። ብጉንጅን ለማከም በመጀመሪያ ነጭ ሽንኩርቱን በእሳት ላይ ሞቅ እንዲል በማድረግ ይጠበቅብናል በመቀጠልም ብጉንጁ ባለበት ቡታ ላይ በማድረግ ለ10 ደቂቃ ያክል ማቆየት፤ ይህንን ለተወሰኑ ቀናት ደጋግሞ በመጠቀም ለውጥ ማግኘት የቻላል ተብሏል። በDr የሚቀርቡ ዝግጅቶችን ለማግኝት https://t.me/DrSofonias

#የጥርስ_መቦርቦር ========== #ምንነት፡- የጥርስ መቦርቦር ማለት ጥርስ በተለያዩ ባክቴሪያዎች አማካኝነት በቀላሉ ሲሰበር ወይንም ሲሸራረፍና የተፈጥሮ ቀለሙንና ቅርፁን ሲቀይር ማለት ነው፡፡ ምግብ ከበላን በኋላ ካላፀዳነው በጥርሳችን የሚቀር ቅሪት (debris) ለተለያዩ ባክቴሪያዎች መራባት ምክንያት ይሆናል፡፡ እንደ አለም ጤና ድርጅት ጥናት ከሆነ በአለም ላይ ወደ ሁለት ነጥብ ቢሊዮን ህዝብ (የአለም 36 በመቶ) በጥርስ መቦርቦር የተጠቃ ነው፡፡ #መንስኤዎች፡- አጋላጭ ነገሮች፣ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችን መመገብ ፣የአፍ (የጥርስና የድድ) ንጽህናን አለመጠበቅ፣ጫት መቃም፣ሲጋራ ማጨስ፣የአፍ መድረቅ ወይም ምራቅ በበቂ አለመመረት (dry mouth)፣በሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ፣ስኳር በሽታ መኖር #ምልክቶች፡- ጥርስ ነጭ ወይም ቢጫ በመሰለ ልጥፍ ነገር መሸፈን፣ነጭ የነበረው የጥርስ አካል ወደ ቡናማ ቀለም መቀየር፣መጥፎ የአፍ ሽታ መኖር፣ሞቃት፣ቀዝቃዛና ጣፋጭ ምግቦችን ወይም መጠጦችን ስንበላና ስንጠጣ የህመም ስሜት መኖር፣ምግብ በምንበላ ጊዜ የጥርስ መሰንጠቅ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ጤና ተቋም ሄደን ብንታይ

5ቱን የጉበት ገዳይ በሽታዎች እናስተዋውቃችሁ ሂፐታይተስ የጉበት ብግነት ነው፡፡ የብግነቱ ሁኔታ በጉበት ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ወይም ጉበትን ሊያኮማትር ወይም ደግሞ ካንሰር ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለሂፐታይተስ መፈጠር ሂፐታይተስ ቫይረስ ዋነኛ ምክንያት ሲሆን ሌሎች ኢንፌክሽኖች እና መርዛማ ነገሮች ማለትም አልኮልና የተወሰኑ መድኃኒቶች እንዲሁም የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅም አዳካሚ በሽታዎች ለሂፐታየተስ መፈጠር ተጠቃሽ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት አምስት ዓይነት የሂፐታየተስ ቫይረሶች እያንዳንዳቸው አምስት የሂፐታየተስ በሽታዎችን ያስከትላሉ፡፡ ሂፐታየተስ ኤ፣ቢ፣ሲ፣ዲ እና ኢ በሽታዎች በመላው ዓለም ለብዙዎች ሕመምና የሞት ምክንያት ናቸው፡፡በተለይ ሂፐታየተስ ቢ እና ሲ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በጉበት መኮማተርና ካንሰር ተጠቅተው ወደ ሞት የሚወስዱ አደገኛ በሽታዎች ናቸው፡፡ ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ ( ኤች ኤ ቪ) 1. ሂፐታይተስ ኤ ቫይረስ የሚገኘው በተበከለ ሰው አይነምድር ውስጥ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአይነምድር የተበከለ ምግብ ወይም ውሀ በምንወስድበት ጊዜ ነው፡፡ 2. የተወሰነ የግብረስጋ ግንኙነት ይህን ቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ 3. የንፅህና ጉድለት ባለባቸው የዓለም ክፍሎች በስፋት ይህ ቫይረስ የሰዎችን ሕይወት እየነጠቀ ይገኛል፡፡ 4. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ (ኤች ቢ ቪ) 1. ቫይረሱ የሚተላለፈው በደም፣በስፐርም እና በሌሎች ፈሳሽ ነገሮች ነው፡፡ 2. ሌላው የቫይረሱ መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተጠቃች እናት በምትወልድበት ጊዜ ወይም ህፃናት በልጅነት ጊዜያቸው በቫይረሱ ከተጠቃ የቤተሰብ አባል ሊሆን ይችላል፡፡ 3. በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 4. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 5. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 6. የጤና ባለሙያዎች በሕክምና ወቅት መርፌ ሊሰበርባቸውና ራሳቸውን ሊወጉ ይችላሉ በዚህም ለብክለት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ 7. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት በየአገሩ ይሰጣል፡፡ ሂፐታይተስ ሲ ቫይረስ (ኤች ሲ ቪ) 1. አብዛኛው ጊዜ የሚተላለፈው በተበከለ ደም አማካኝነት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በቫይረሱ የተበከለ ደምና የደም ተዋሀፆ በመስጠት ወይም በማስተላለፍ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ 2. በሕክምና ወቅት በቫይረሱ የተበከ መርፌ በመጠቅም አንዱ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ 3. በመርፌ በሚወሰዱ አድገኛ መድኃኒቶችና እፆች አጠቃቀም ወቅት ሌላው መተላለፊያ መንገድ ሲሆን በተለይ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጥንቃቄ ንቅሳት (ታቱ) የሚሰሩ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡፡ 4. በግብረስጋ ግንኙነት ሊተላለፍ ይችላል ነገር ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ 5. ይህን ቫይረስ ለመከላከል ምንም አይነት ክትባት የለም፡፡ ሂፐታይተስ ዲ ቫይረስ (ኤች ዲ ቪ) 1. በዚህ ቫይረስ የሚጠቁት በሂፐታይተስ ቢ ቫይረስ ብቻ የተጠቁ ሰዎች ናቸው፡፡ 2. በሁለቱ ቫይረሶች የሚጠቁ ሰዎች ለአደገኛ በሽታ የሚጋለጡ ሲሆን ውጤቱም እጅግ መጥፎ ሊባል የሚችል ይሆናል፡፡ 3. የሂፐታይተስ ቢ ክትባት በዚህ ቫይረስ ለሚጠቁ ሰዎች መከላከያ በመሆን ያገለግላል፡፡ ሂፐታይተስ ኢ ቫይረስ (ኤች ኢ ቪ) 1. ብዙን ጊዜ የሚተላለፈው የተበከለ ምግብ ወይም ውሃ በምንጠቀምበት ጊዜ ነው፡፡ 2. በተዳጊ አገሮች በስፋት ለሚታየው የሂፐታይተስ ስርጭት ይህ ቫይረስ ግንባር ቀደም ነው፡፡ 3. ይህን ቫይረስ ለመከላከል አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ ክትባት ቢኖርም በስፋት ማግኘት ያዳግታል፡፡

💔በየትኛው የእድሜ ክልል ውስጥ ወሲብ መጀመር ጥሩ? ✅በጥናት የተረጋገጠ ማብራሪያ 👌እንግሊዝ ውስጥ ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በለጋ ዕድሜያቸው ድንግልናቸውን ያጡ ወጣቶች የኋላ ኋላ ይቆጫሉ። 🧩በጥናቱ ከተሳተፉት በአፍላ ዕድሜ የሚገኙ አንድ ሦስተኛ ሴቶችና አንድ አራተኛ ወንዶች፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ የፈጸሙት በትክክለኛው ዕድሜ እንዳልነበር ይናገራሉ። በእንግሊዝ ሕግ መሠረት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረት ወሲብ መፈጸም የሚቻለው ጥንዶቹ 16 እና ከዚያ በላይ ሲሆኑ ብቻ ነው። በየአሥር ዓመቱ የሚከናወን ጥናት ግን በዚህም ዕድሜ ለወሲብ ዝግጁ መሆን አይቻልም ይላል። ውጤቱ በቅርቡ ይፋ ለተደረገው ጥናት መረጃ የተሰበሰበው ከ3000 ወጣቶች ሲሆን፤ እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ለንደን ባሉ ሳይንቲስቶች የተሰራ ነው። የጥናቱ ውጤቱ ከጥናቱ ተሳታፊዎች 40% የሚሆኑት ሴቶችና 26% የሚሆኑት ወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅሙ በተገቢው ዕድሜ ላይ እንዳልነበር ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ ትንሽ ዘግይተው ቢሆን ኖሮ ደስ ይላቸው እንደነበረም ገልፀዋል። አብዛኛዎቹ ወሲብ ማድረግ የጀመሩት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ሲሆን፤ ቢያንስ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ደግሞ 16 ዓመት ሳይሞላቸው የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርገዋል። ፈቃደኝነት ጥናቱ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የማድረግ አቅምና ዝግጁነትንም ጭምር ተመለከተ ነው። ማለትም አንድ ሰው አመዛዝኖ፣ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ማድረግ ይችላል ወይ? የሚለው ከግምት ገብቷል። የማመዛዘን ብቃት ሲለካ፤ ከአሥር ሴቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑትና ከወንዶቹ ደግሞ አራቱ ሳይልፉ ቀርተዋል። ከአምስት ሴቶች አንዷና ከአስር ወንደች አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረጉት ብዙም ፈቃደኛ ሳይሆኑና በፍቅረኛቸው ተገፋፍተው እንደነበረ ይናገራሉ። የ'ናትሳል' ጥናት መሥራች የሆኑት ፕሮፌሰር ካዬ ዌሊንግስ እንደሚሉት፤ ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ሕጋዊ ተብሎ የተቀመጠው ዕድሜ አንድ ሰው ለግብረ ሥጋ ግንኙነት ዝግጁ ወይም ብቁ ነው ማለት አይደለም ይላሉ። "ሁሉም ወጣት የተለያ ነው። አንዳንድ የ15 ዓመት ወጣቶች ዝግጁ ቢሆኑም አንዳንዶች ደግሞ በ18 ዓመታቸው ብቻ ዝግጁ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችለላል" ሌላዋ አጥኚ ዶ/ር ሜሊሳ ፓልመር፤ "ግኝታችን እንደሚያሳየው አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በፍቅረኛቸው ግፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረጋቸውን ነው" ይላሉ። በጥናቱ መሰረት፤ ከአሥር ወጣቶች ዘጠኙ መከላከያ ቢጠቀሙም፤ "ለወደፊትም ወጣቶች ከበሽታ እንዲጠበቁ ለጤናቸው ትኩረት መሰጠት አለበት" ብለዋል። በተጨማሪም የወጣቶች የመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጤናማ እንዲሆን ትምህርት ቤቶች ተገቢውን የጤና ጥበቃ አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት መስጠት አለባቸው ብለዋል። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ያለብን መቼ ነው? የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሊያደርጉ ከሆነ ለራስ ✅እነዚህን ጥያቄዎች መሰንዘር ያሻል፡ ✅የሚሰማኝ ትክክለኛ ስሜት ነው? ✅አብሬው ከምተኛው ሰው ፍቅር ይዞኛል? ✅ያፈቅረኛል/ታፈቅረኛለች? ✅ከኤችአይቪና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች ራሳችንን ለመከላከል ኮንዶም ስለመጠቀም ተነጋግረናል? ✅ካልተፈለገ እርግዝና ለመጠበቅ የወሊድ መከላከያ አዘጋጅተናል?።። ✅ሃሳቤን መቀየር ብፈልግ በማንኛውም ሰዓት እምቢ የማለት አቅም አለኝ? ፍቅረኛዬስ ይህን ውሳኔ ያከብራል? ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሹ አዎ ከሆነ ወሲብ ለመፈጸም ትክክለኛው ጊዜ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከዚህ በታች ላሉት ጥያቄዎች መልሱ አዎ ከሆነ ትክክለኛው ጊዜ ላይሆን ይችላል፡ ❌ከጓደኞቼ ወይም ከፍቅረኛዬ ግፊት እየተሰማኝ ነው? ❌በኃላ ሊቆጨኝ ይችላል? ❌አሁን ወሲብ ማድረግ የፈለኩት ከጓደኞቼ እኩል ለመሆን ወይም እነሱን ለማስደሰት ነው? ❌ግንኙነት ለማድረግ ፈቃደኛ የሆንኩት ከፍቅረኛ ጋር ላለመለያየት ብዬ ነው? ኢዛቤል ኢንማን ስለ ወሲብ ትምህርት በሚሰጥ መጽሐፍ ይህን ብለዋል፡ "ወሲብ ለመፈጸም ተገቢ ስለሆነው ዕድሜና ጊዜ ለወጣቶች ትምህርት መሰጠት አለበት። ሲያድጉ የሚበጃቸው ውሳኔ ላይ ለመድረስ አይቸገሩም። ትምህርቱ በትምህርት ቤቶች መሰጠት ቢጀመርም ጠቃሚ ነው። የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias

ክፍል 2 የእንስላል ቅጠል ወይም ፍሬን አፍልቶ መጠጣት የኩላሊት ጠጠርን በሽንት መልክ እንደሚያሶግድ ያውቃሉ?? ቶሎ ቶሎስ ሽንት ለመሽናት እንደሚጠቅምስ?? እንስላል (Pimpinella anisum) ለባህል መድኃኒትነት ከሚውሉ የአረም ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ መድኃኒትነቱ በሀገራችን ቢታወቅም ብዙ ሰው አይጠቀምበትም፣ በጓሮው አያበቅለውም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ይቆጫል፡፡ እንስላል በሌላው ዓለም ለምግብነትም ሆነ ለመድኃኒትነት በደንብ ጥቅም ላይ የዋለ የተክል ዓይነት ነው፡፡ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ዲፓርትመንት አንድ ተማሪ የማስተርስ ዲግሪው ማሟያ ይሆን ዘንድ በእንስላል ላይ ጥናት ሰርቶ ነበር፡፡ ከተማሪው “ቴሲስ” ያነበብሁትን ላካፍላችሁ፡፡ የሜዲትራሊያን አካባቢ ምግብ ሥርዓት በዓለም ካሉ ምርጥ የምግብ ሥርዓቶች(አንደኛ ሳይሆን አይቀርም) አንዱ፡፡ በሚዲትራሊያን የምግብ ሥርዓት ውስጥ አንስላልን መጠቀም የተለመደ ነው፤ የምግባቸው ዋና አካል ነው፡፡ በኢጣሊያ ቀንበጡን በማኜክ የአፍ ቁስለትን ለማዳን ይጠቀሙበታል፡፡ በማዕከላዊ ሰርቪያ ፍሬው፣ ዘሩ ለአፍ መጉመጥመጫነት ይወላል፡፡ በብራዚል እንደ ሻይ በማፍላት የእንቅልፍ እጦትን ይከላከሉበታል፡፡ በህንድና በካሽሚር ዘሩን እንደ ሻይ በማፍላት ከስኳር ጋር በመጨመር ለሆድ ድርቀት መከላከያነት ይጠቀሙበታል፡፡ በኢኳዶር አበባውንና ቅጠሉን በመጭመቅ ለካንሰርና ለዓይን ህመም መድኃኒትነት ይጠቀሙበታል፡፡ በሚያሚና ፍሎሪዳ በተባለው የአሜሪካ ግዛት ስሩንና ፍሬውን በመጭመቅ ብዙ ሽንት ለማሸናት ይጠቀሙበታል (ብዙ የሚያሸኑ እጾች እንደ መድኃኒት(diuretics) ይወሰዳሉ፡፡ ሳማ እና ጌሾ በዚህ ጥቅማቸው ይታወቃሉ) ፡፡ በኢጣሊያ፣ በቱርክና በዮርዳኖስ እያንዳንዱን ክፍል በመጭመቅና እንደ አጥሚት በመጠቀም የሆድ ቁርጠትን ለመከላከል ይጠቀሙበታል፡፡ ሮም ውስጥም ለጉንፋን፣ ነቃ ለማለት፤ ለተነፋ ሆድ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎችም ፈውስ የተክሉን የተለያዩ ክፈሎች በፈላ ውሃ በመጭመቅ ይጠቀሙበታል፡፡ በደቡብ አፍሪካ የቅጠሉ ጭማቂ ለቁርጥማት ማስታገሻነት ይውላል፡፡ በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎችና በሶማሌ ስሩን በመጭመቅ ለወባ በሽታ ይጠቀሙበታል፡፡ በፍሬው ጭማቂ በተደረገ ጥናት ፀረ ባክቴሪያነቱን በተለይም “ስትሬፕቶ ኮከስ ሙታንስ” የተባለውን የጥርስ መበስበስ የሚያስከትል ባክቴሪያ የማጥፋት ሀይል እንዳለው ተረጋግጧል፡፡ለዚህ ይሆን ብዙ ሰዎች ጥርሳቸውን በእንስላል ሲፍቁ የሚታዩት፡፡ በሀገራችን አንስላልን ለመድኃኒትነት እንጂ ለምግብነት የሚፈልገው የለም፡፡ እረ ምን ይሻለናል? ቦታ ያለችሁ ሰዎች ትከሉት፣ ተጠቀሙበት፡፡ እንስላል እንዴት ደስ ይላል፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረንን ወይም ሃሊቶስስን የሚያመጣዉ ምንድነዉ? መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡ • የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ • የድድ ህመም መኖር • ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት • እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት • የሳይነስ እንፎክሽን • መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች) • ሲጋራ ማጨስ • የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች) • የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር • የሆድ ድርቀት መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ? • መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት • በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች • ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ) • ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት • ምላስዎትን መቦረሽ • አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት • የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ የሥነ አዕምሮና የሥርዐተ ፆታ ኤክስፐርት በ Dr Sofonias የሚቀርቡ አስተማሪ ዝግጅቶችን በቴሌግራም ያገኙበታል https://t.me/DrSofonias