uk
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Відкрити в Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Канал ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 19 967 підписників, посідаючи 1 154 місце в категорії Медицина та 1 678 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 19 967 підписників.

За останніми даними від 26 червня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на -547, а за останні 24 години на -20, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 24.05%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 7.27% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 4 805 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 453 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 9.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 27 червня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Медицина.

19 967
Підписники
-2024 години
-1217 днів
-54730 день
Архів дописів
የኩላሊት ህመም ምልክቶች የኩላሊት ምልክቶች ሕመም አብዛኛውን ጊዜ ምልክት የለሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የህመም ምልከቶች ከታዩም ደግሞ ከህሙማን ሕሙማን ይለያያሉ፡፡ በተለይ የሕመሙ መጀመሪያ አካባቢ መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አበይት ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ • የፊት እብጠት ብዙ ጊዜ የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት የኩላሊት ህመም መለያ ናቸው፡፡ በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋን በታች ሊከሰት ይችላል፡፡ (ይህ የፔሪኦሮቢታል እብጠት ይባላል) በተለይ በማለዳ ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን ሁሉም እብጠት የ የኩላሊት ሕመምን ያመለክታል ማለት አይደለም፡፡ በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ ይችላል፡፡ • የምግብ ፍላጎት ማጣት ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው:: • ከፍተኛ የደም ግፊት አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል። • የደም ማነስ እና ድክመት የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት ዋንኛ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አነዚህ ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል። ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -መለስተኛ ደረጃ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በልጆች ላይ ደግሞ በሚገባ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የእግር አጥንት ቀጥ አለማለት የህመሙ መኖር ማሳያ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች 1. የሽንት መጠን መቀነስ የኩላሊት ህመሞ በጣም የተለመደ ነው። 2. በመሽናት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት እና የሽንት ቧንቧ ህመም በሽታውን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው። 3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማውጣት ችግር ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሐኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የጨጓራ በሽታ አለብዎት? እንግዲውስ መፍትሄዎቹን እነሆ ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የኢትዮጤና ገጽ ተከታታዮች ለጨጓራ ህመም መፍትሄ የሚሆኑ ሃሳቦችን ይዘን ቀርበናል እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡ የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ወይም ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ የጨጓራ ግድግዳ መድከም ወይም መሳሳት በቀላሉ ግድግዳው ለምግብ መፍጫ አሲዶች እንዲጋለጥ ስለሚደርገው ለቁስለት ይዳረጋል በዚህ አማካይነት የጨጓራ በሽታ ይከሰታል፡፡ የተጐዳ እና ስስ የጨጓራ ግድግዳ ካለዎት በጨጓራ በሽታ የመያዝ ዕድልዎ ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የጨጓራ በሽታ መነሻ ምክንያቶች አሉ፡፡ የጨጓራ ባክቴሪያ በመባል የሚጠራው ኤች. ፓይሎሪ (H.Pylori) አንዱ የጨጓራ በሽታ መነሻ ነው። ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ግድግዳን የሚያጠቃ ሲሆን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል በተጨማሪም በተበከለ ውሃ እና ምግብ ይተላለፋል፡፡ ☑️ ሌሎች ለጨጓራ ሊያጋልጡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል፦ 🔹 ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት 🔹 በመደበኛ ሁኔታ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቴች መጠቀም ለምሳሌ፦ ኢቡፕሮፊን፣ አስፕሪን እና ኮኬይን መጠቀም 🔹 ዕድሜ (የጨጓራ ግድግዳ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እየሳሳ ይመጣል) ሌሎች ለጨጓራ ህመም መነሻ ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው ምክንያቶች መካከል፤ በህመም፣ በአደጋ ወይም በቀዶጥገና ጊዜ በሚፈጠር ጭንቀት፣ በቫይረስ ኢንፌክሽን እና በምግብ ስልቀጣ ወይም መፈጨት ችግሮች ሊከሰት ይችላል፡፡ ☑️ ጨጓራን በቤት ውስጥ እንዴት ልንከላከለው ወይም ልናክመው እንችላለን? 🔺 ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ። 🔺 ከመጠን ያለፈ አልኮል አይጠጡ። 🔺 ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠጡ። ለምሳሌ ቡና እና ሻይ። 🔺 ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቂዎችን አይጠጡ። ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ 🔺 ከፍተኛ የቅባት ወይም ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ፡፡ 🔺 በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ (H. Pylori) የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው። 👉 ከእነዚህ ምግቦች መካከል:- 🔸 ቀይ ሽንኩርት 🔸 ነጭ ሽንኩርት 🔸 አበባ ጐመን 🔸 የምግብ ማጣፈጫ ተክል 🔸 ጦስኝ 🔸 ሽምብራ እና 🔸 አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡

☑️ በርግጥ መንታ የማርገዝ እድልን እንዴት ማስፋት ይቻላል? ዶክተሮች በአንዳንድ አርግዝናዎች ላይ እንዴት መንትዮችን ማርገዝ እንደሚቻል ሙሉለሙሉ አልተረዱትም ይላሉ የዘረፉ ባለሙያዎች፡፡ ብዙ ጊዜ በማህፀን ውስጥ ሁለት የዳበሩ እንቁላሎችን የወንድ የዘር ፍሬ ሲያገኛቸው አልያም አንድ እንቁላል ከወንድ ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ ለሁለት ከተከፈለ መንትያዎች የመፈጠር እድል አላቸው የሚል እንዲሁ አጠቃላይ መላምት ቢኖራቸውም እስካሁን በደረሱበት ምርምር ግን መንታ ልጆች ሊረገዙባቸው የሚችሉባቸውን ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፣ 🔹 እድሜ እንደ የሴቶች ጤና ቢሮ መረጃ ከሆነ እድሜዋ 30 አልያም ከሰላሳ በላይ የሆነች ሴት መንታ የመፀነስ እድሏ የሰፋ ነው፡፡ ለዚህ ዋነኛው ምክንያት በዚህ እድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶች በመራቢያ ወቅታቸው ጊዜ በርከት ያሉ እንቁላሎችን ያመርታሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ሁለት እንቁላሎችን የመስበር አቅም ካለው መንትዮች ይፈጠራሉ፡፡ 🔹 በቤተሰብ ውስጥ መንታ የመውለድ ታሪክ ከአባታቸው ይልቅ በእናታቸው በኩል መንታ የመውለድ ታሪክ ያላቸው ሴቶች መንትዮችን የመውለድ እድላቸው በጥቂቱም ቢሆን እንደዚህ አይነት ታሪክ በቤተሰባቸው ውስጥ ከሌላቸው ሴቶች የተሻለ መንታዎችን የማርገዝ እድል አላቸው፡፡ በተለይ የማይመሳሰል መንትያ ያላቸው ሴቶች ከ1 እስከ 60 በሚሆኑ የእርግዝና ጊዜአቸው መካከል መንትዮችን የመፀነስ እድል አላቸው፡፡ ነገር ግን የማይመሳሰል መንትያ ያላቸው ወንዶች መንታ ልጆችን ማስፀነስ የሚችሉበት እድላቸው ከ1 እስከ 125 በሚደርሱ እርግዝናዎች ውስጥ ነው፡፡ በነራችን ላይ አንዳንዶች መንታ ልጆችን መውለድ ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ክስተት ነው ሲሉ ቢደመጡም ይህን ጉዳይ የሚደግፉ ማስረጃዎች እምባዝም አይገኙም፡፡ 🔹 የሕክምና ድጋፍ እንደባለሙያዎቹ ገለፃ ከሆነ የመራባት ሕክምናን በመውሰድ መንታ ልጆችን ማርገዝ የሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ከሚውሉ መድሃኒቶች መካከል አንዳዶቹ ስራቸው የሴቶችን እንቁላል ማነቃቃት ሲሆን ይህም ሴቶቹ በርካታ እንቅላሎችን በአንድ ጊዜ ማምረት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል፡፡ ይሄን ጊዜ የወንዱ ዘር ሁለት እንቁላሎችን የመስበር አቅም ካገኘ መንታ ልጆች ይፀነሳሉ፡፡ በብልቃጥ ውስጥ የሚደረገውም እንቁላልን የማዳበር ስራ መንታዎች እንዲፈጠሩ የማድረግ አቅም አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ባለሙያዎቹ የሴቶችን እንቁላል በመውሰድ በላብራቶሪ ውስጥ ከወንድ ዘር ጋር በማዳቀል ሽል ይፈጥሩና መልሰው ወደሴቷ ማህፀን ያስገቡታል፡፡ በዚህም መንታዎችን ማግኘት እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ በዚህ መንገድ መንታዎች የማግኘት እድልን ለማስፋት ባለሙያዎቹ ሁለት ሽሎችን ወደ ማህፀን ያስገባሉ፡፡ ነገር ግን የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት /CDC/ ይህን መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጠቀሙ ወጣት ሴቶች ወደ ማህፀናቸው አንድ ሽል ብቻ እንዲያስገቡ አበክሮ መምከሩም ሳይዘነጋ፡፡ 🔹 ቁመትና ክብደት ቁመታቸው ረዘም ያሉና ክብደታቸውም ከፍ ያሉ ሴቶች ቢያንስ የማይመሳሰሉ መንትዮችን የማርገዝ እድላቸው ሰፋ ያለ ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡ በርግጥ ለዚህ ምክንያት ግልፅ የሆነ ማስረጃ የሌለ ቢሆንም እንደመላምት ግን እነዚህ ሴቶች በአመጋገብ ስርዓታቸው የተሻሉ ሊሆኑ ስለሚችሉና ሰውነታቸውም ገዘፍ ያለ በመሆኑ ሁለት ፅንሶችን ለመፍጠር የሚያስችል ግብዓት ሰውነታቸው ሳያዘጋጅ አይቀርም ይላሉ፡፡ ምንጭ: ሜዲካል ኒውስ ቱደይ መልካም ጤንነት!!

መንታ ልጆች እንዴት ማርገዝ ይቻላል? ለወትሮው ቢሆን መንታ መውለድ ለብዙዎች አስገራሚና አስደሳች ክስተት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በተለይ የልጆቻቸው ቁጥር ከሁለት እንዲበልጥ ለማይፈልጉና በእርግ
መንታ ልጆች እንዴት ማርገዝ ይቻላል? ለወትሮው ቢሆን መንታ መውለድ ለብዙዎች አስገራሚና አስደሳች ክስተት መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በተለይ የልጆቻቸው ቁጥር ከሁለት እንዲበልጥ ለማይፈልጉና በእርግዝና ወቅት ተያይዘው የሚመጡ ጫናዎችን ዳግም ማየት ለማይልጉ ወላጆች መንታ መውለድ ከደስታው ባሻገር እረፍትና እፎይታን ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካዊ ናት፡፡ ፕሪቶሪያ ውስጥ ነው የምትኖረው፡፡ ጎሳሜ ታማራ ትባላለች፡፡ ከዚህ በፊት 2 ልጆች የነበሯት የ37 ዓመቷ ይህቺ እንስት አሁን ደግሞ 7 ወንዶችንና 3 ሴቶችን በአንድ ጊዜ ወልዳለች፡፡ 5ቱን በተፈጥሮአዊ መንገድ ስትውልድ 5ቱን ደግሞ በቀዶጥገና ነው የወለደችው ይላል የቢቢስ ዘገባ፡፡ አሁን አሁን በአለማችን ላይ ብዙ ልጆችን የሚወልዱ እናቶች እዚህም እዛም ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ እ.አ.አ በ2009 አንዲት አሜሪካዊት እናት 8 ልጆችን በአንድ ጊዜ በመውለድ የአለማችን የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መስፈር ችላ የነበረ ሲሆን ባሳለፍነው ወር ደግሞ ከወደ ማሊ አንዲት የ25 ዓመት እናት 9 ልጆችን በመውለድ ሪከርዱን በእጇ አስገብታ ነበር፡፡ የቢቢሲዋ ዘጋቢ ሮዳ ኦዲያምቦ እንደምትለው ከሆነ በርከት ያሉ ልጆችን በአንድ ጊዜ መውለድ እምብዛም የተለመደ አይደለም፡፡ እንዲህ ያሉ ልጆችን ለመውለድ የተለያዩ የህክምና ድጋፎችን መጠቀም ያሻል ብትልም 10 ልጆችን በአንዴ የወለዱት ጥንዶች ግን እርግዝናቸው ተፈጥሮአዊ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡ የሕመሙ
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡ የሕመሙ መጠን ከሰው ሰው የሚለያይ ሲሆን አንዳንዴም የዕለት ኑሮን እስከማቃወስ ይደርሳል፡፡ ☑️ በወር አበባ ጊዜ የሕመም ስሜት እንዲሰማሽ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች፦ 🔹 ዕድሜሽ ከ30 ዓመት በላይ ከሆነ 🔹 የወር አበባሽ ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ 🔹 ልጅ ያልወለዱሽ ከሆነ 🔹 በወር አበባሽ ጊዜ ከፍተኛ ሕመም የሚሰማውት የቤተሰብ አባል ካለች። 🔹 ሲጋራ የምታጨሽ ከሆነ ናቸው።

ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምክሮች • ውሃ በብዛት ይጠጡ፡፡ • በቂ የሆነ እንቅልፍ ያግኙ፡፡ • ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ፡፡ • የሚያዝናናዎትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ይምረጡ፡፡ • አትክልትና ፍራፍሬ በብዛት ይመገቡ፡፡ • የሚስብ ቀለም ያላቸውን ምግቦችን ይምረጡ፡፡ • የታሸጉ ምግቦችን መመገብዎን ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • ራስዎን ይውደዱ፡፡ • አልፎ አልፎ በባዶ እግርዎ ይራመዱ/ይሩጡ፡፡ • አይሆንም የሚለውን ነገር ከውስጥዎ ያስወግዱ፡፡ • በሽታዎን ሊያስነሱ የሚችሉ ምግቦችን መውሰድ ያቁሙ፡፡ • መጠኑ ጥቂት የሆነ ገበታ ይመገቡ፡፡ • በጥልቀት ይተንፍሱ፡፡ • ከጠገቡ በኋላ በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ትርጉም ያለው ህይወት ይኑሩ፡፡ • ቅባት ወይም ዘይት የበዛባቸው ምግቦች በፍጹም አይመገቡ፡፡ • ስኳር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ይቀንሱ ወይም ያቁሙ፡፡ • አቋምዎን ያስተካክሉ፡፡ • ሶዳ እና ካፌይን ይቀንሱ ወይም አይጠቀሙ፡፡ • አልኮል አይጠጡ፡፡ • የራስዎን ምግብ ራስዎ ማዘጋጀት ይልመዱ፡፡ • ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ፡፡ • የአፍና ጥርስዎን ጤንነት ይጠብቁ፡፡ መልካም ጤንነት!!

በአንደኛው አይነት የስኳር ህመም (type 1 diabetes) የመያዝ ስጋትን የሚጨምሩ ምክንያቶች አንደ ሁለተኛው አይነት በቀላሉ ማስቀመጥ ባይቻልም ፤ በፀረ መል ( genetics) እና አካባቢያዊ ( environmentally) የሆኑትን እንደ ምክንያት ማስቀመጥ እንደሚቻል ይታመናል። በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም ( gestational diabetes) ከአጠቃላይ እርግዝናዎች በአምስት ከመቶ (5%) በመሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ የሚከሰት ነውና ነገር ግን በአብዛኛው የእርግዝና ወቅት በሚጠናቀቅበት ግዜ ይጠፋል ። ሆኖም በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም የገጠማቸው ሴቶች በሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም የመያዝ ስጋታቸው ከፍተኛ ይሆናል። ምንም እንኳን በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም የመከሰቻው ምክንያት በወል ባይታወቅም ፤ በቤተሰባቸው ውስጥ የስኳር ህመም ያላቸው ፥ በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ያላቸው ፥ ወይም የዘር ግንዳቸው ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ በሆኑ ሴቶች ላይ በብዛት ሲከሰት ይስተዋላል ። በሀያ አራተኛው (24) ሣምንት የእርግዝና ወቅት የሚከሰተው የሰውነት ንጥረ ነገር ለውጥ ( hormonal change) የኢንሱሊን እምቢተኝነትን ስለሚያመጣ የስኳር ህመም ሊያመራ ይችላል። ስለሆነም በእርግዝና ወቅት የስኳር ህመም የሚከሰትባቸው ሴቶች የተለየ ጥንቃቄ እና ከሀኪም ጋር ቅርብ ክትትል በማድረግ እርግዝናቸው በሰላም እነዲጠናቀቅ መስራት ይኖርባቸዋል። በስኳር ህመም ምክንያት የሚያጋጥሙ መወሳሰቦች ( complications) የሱኳር ህመም ሕክምና የስኳር ሕመም ህክምና ዋንኛው አላማ በታማሚው ደም ውስጥ ያለውን የሱካር (glucose)መጠን በተቻለ መጠን ከተለመደ (Normal) የስኳር መጠን ጋር ተቀራርቦ እዲቆይ ማድረግ ነው:: ይህን ማድረግ ደግሞ ከዚህ በፊት የተዘረዘሩትን በሱኳር ህመም ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉትን የጤና መውሳሰቦችን ለማስወገድ ይረዳል :: ለዚህም ነው የደም ውስጥ የሱኳር መጠንን በተከታታይ መለካትና መከታተል የምያስፈልገው :: የስኳር ሕመም ታማሚዎች የስኳር(glucose) መጠናቸው ሲለኩ በደማቸው ውስጥ ምን ያህል ስኳር እንደተከማቸ እያረጋገጡ ነው :: በሰውነታችን ውስጥ ኢንሱሊን የማይመረት ከሆነ ወይም በአግባቡ ስራውን ካልሰራ ስኳር (glucose) በደማችን ላይ ይከማቻል፣ ጥቅም ላይ ሳይውል በሽንት አማካኝነት ይወገዳል :: ምንም እንኳን በደማችን ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን ቢኖርም ስኳር (glucose) ወደ ሴሎች ስለማይደርስ ሰውነታችን ዋንኛ የሀይል ምንጩን ያጣል ማለት ነው :: የሱካር መጠን መለካት ሁልጊዜ ላይመች ይችላል ነገር ግን ሰውነታችንን ለምንመገበው ምግብ ምን አይነት ምላሽ እየሰጠን እንደሆነ ለማረጋገጥ ውጤታማ መንገድ ነው :: ሁለተኛው የሱኳር ሕመም አይነት ለማከም ሲታሰብ ሕክምናው የሱካር መጠንን መለካትን የአመጋገብ ዜዴና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያካተተ መሆን ይኖርበታል :: በአፍ የሚወሰዱ እንክብሎች ወይም ኢንሱሊን ህክምናም ሊያስፈልግ ይችላል ::አንደኛውን አይነት የሱኳር ሕመም ለማከም በቅን ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ እንሱሊን መውጋትን የተመጣጠነ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያካትታል :: በተጨማሪም ተደጋጋሚ የሱኳር መጠንን መለካትንና በጥንቃቄ የታቀደ አመጋገብን ማድረግ ይገባል :: የስኳር ህመምን በአግባቡ መቆጣጠር የሱኳር ህመምን በአግባቡ ስለመቆጣጠር ስናስብ ለአንድ ሰው ውጤታማ የሆነ መንገድ ለሌላው ሰው ሊሰራ ስለማይችል አካሄዳችንን በግለሰብ ደረጃ መሆን እዳለበት መረዳት ይኖርብናል:: የስኳር ህመምን ተቆጣጥረው በጥሩ ጤና ለመኖር የግዴታ እንዴት አርገው የስኳር ህመምን በአግባቡ መቆጣጠር እንዳለቦት ዕውቀት ሊያዳብሩ ይገባል:: የስኳር ህመምን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቆጣጠር ተያይዘው ከሚመጡ በሽታዎች እራስን ለመጠበቅ ጤናማ የሆነ አመጋገብን ማዘውተር፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና አዘውትሮ የስኳር መጠኖን መከታተልና በመደበኛ ወደ ጤና ተቋም ዘንድ በመሄድ ክትትል ማድረ ይጠበቅቦታል:: በዚህ አንፃር ጥሩ ውጤት ለማግኘት የተለያዩ የጤና ባለሞያዎችን ጋር በቅርበት መስራት ያስፈልጋል:: ይህም የምያስፈልግበት ምክንያት የግል የሆነ የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር የሚያስችል እቅድ ለመቅረፅ እንደ የአኗኗር ዘይቤና አመጋገብን ተዛማጅ የጤና አካሎችንና የህክምና ዘዴዎችን ባካተተ መልኩ መሆን ስላለበት ነው::

የስኳር ህመም ማለት ምንድን ነው? የስኳር ህመም ዘወትር ከምንመገበው ምግብ የምናገኘውን ስኳር ሰውነታችን በአግባቡ ወደ ሀይል እንዳይቀይር የሚያደርግ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ነው። ጤነኛ ሠዎች ስኳር ወደ ሴሎች ዘልቀው እንዲገቡና እነደ ሀይል ምንጭነት እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችለው አስፈላጊ የሆነ ኢንሱሊን የተባለው ንጥረ ነገር በጣፊያ ውስጥ ይመረታል። ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች አንድም ጣፊያቸው ኢንሱሊንን በበቂ ሁኔታ አያመርትም ወይም ደግሞ ሰውነታቸው የተመረተውን ኢንሱሊን በአገባቡ መጠቀም አይችልም:: ይህም ማለት ሰውነታቸው የቀን ተቀን ተግባሩን ለመከወን የሚያስፈልገውን ሀይል አያገኝም ማለት ነዉ ። ስለዚህ የስኳር ህመምን፣ አንድ ሰዉ የሚያስፈልገዉን ሀይል ከሚመገበዉ ምግብ መገኘት አለመቻል ብለን ልንገልፀዉ እንችላለን። የሰኳር ህመም ምልክቶች እና ስሜቶች... በአለማችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች 2ተኛዉ አይነት የስኳር ህመም ( type 2 diabetes) ቢኖርባቸዉም፣ ህመሙ እንዳለባቸዉ ሳያዉቁ ይኖራሉ። ይህም ማለት ህመማቸዉ ሳይታወቅላቸዉና ምንም አይነት የህክምና እርዳታ ሳያነገኙ ይኖራሉ ማለት ነዉ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ብዙ ሰዎች የስኳር ህመምን ምልክቶችና ስሜቶችን ሳያሳዩ ወይም ምልክቶቹ በጣም አነስተኛ ስለሚሆኑ፣ ትኩረት ሳይሰጧቸዉ ስለሚቀሩ ነዉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ፣ የህመሙ ስሜት ቢሰማቸዉም ያን ያህል አስጊ ስለማይመስላቸዉ ወደ ህክምና ሳይሄዱ ይቀራሉ። ስለሆነም ታማሚዎቹ በስኳር ህመም ምክንያት በሚከሰቱ ተያያዥ በሸታዎች፤ ለምሳሌ የአይን እይታ ብዥታ አጋጥሞአቸዉ ወደ ህክምና እስኪሆዱ ድረስ ለስኳር ህመማቸዉ ህክምና ሳያደርጉ ለረዥም አመታት ይቆያሉ። የስኳር ህመምን በቶሎ ማወቅ በህመሙ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ውስብስብ አካላዊ ጉዳቶችን ለመከላከል ይረዳል። እንደ (National Inistitue of Diabetes and Digestive & Kidney Diseases) ጥናት፤ አርባ አሞስት አመት ከዛ በላይ የሆናቸዉ አዋቂዎች፤ የስኳር ህመም ስሜት ባይሰማቸዉ እንኳን፣ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከአርባ አምስት አመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ፣ የህመሙ ስሜቶች ከተከሰቱባቸው ወይም የስኳር ህመም የመከሰቱ ስጋት ከፍተኛ ከሆነ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከቅርብ አመታት ወዲህ ቅድመ የስኳር ህመም (prediabetes) የሚለውን የህክምና ቃል በተደጋጋሚ እንሰማለን። ይህ ቃል አንድየሰዉ በ2ተኛዉ አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetese) የመያዝ ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነ ለመግለፅ የሚጠቅም ቃል ነዉ። ደግነቱ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ፤ የኑሮ ዘይቤአቸዉን፤ ማለትም አመጋገብን ጤናማ በማድረግ፣ ቀለል ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማዘዉተርና ፣ ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ክብደትን በመቀነስ፣ የስኳር ህመም መከሰቻ ግዜን መዘግየት ይቻላል። ስለሆነም፥ እርሶም ሆኑ የቤተሰብ አባልዎ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አንዱ ወይም ከዛ በላይ የህመሙ ስሜቶች የሚሰማዎ ከሆነ ባስቸኳይ ወደ ሀኪም ዘንድ በመሄድ ምርመራ ሊያደርጉ ይገባል በሚል በስለ ጤናዎ ምን ያውቃሉ ጠቅላላ እውቀትGeneral knowledge ethiohakim በሚለው ገጽ ላይ የቀረደው መረጃ ያመለክታል፡፡ 1) ከፍተኛ የሆነ የርሀብ ስሜት፣ 2) ቶሎቶሎ ሽንት መሽናት፣ 3) የማይቋረጥ የሀ ጥማት፣ 4) ተደጋጋሚ የሆነ የሰውነት መዛል ሰሜት፣ 5) የእይታ መዛባት ( ብዥታ)፣ 6) ያልተጠበቀ ፈጣን የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ 7) የእጅና የእግር ጣቾች መደንዘዝ፣ 8) በሰዉነት ላይ የሚከሰቱ ቁስሎች በቶሎ አለ መዳን፣ 9) በተደጋጋሚ በተለያዩ በሽታ አምጪ ተዋህስያን መጠቃት፣ የስኳር ህመም አይነቶች..... የስኳር ህመም በዋናነት በሁለት ይከፈላል፦ ሁለተኛዉ አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetes) እና አንደኛው አይነት የስኳር ህመም (type 1 diabetes) በመባል ሲከፈል፤ በተጨማሪም በሶስተኛነት በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (gestational diabetes) አይነትም ይገኛል ። ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetes) ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetes) ከአጠቃላይ የስኳር ህመምተኞች ዘጠና አምስት በመቶ (95%) በሚሆኑት ላይ የሚከሰት ነዉ። በቀድሞ መጠሪያዎቹ ኢንሱሊን የማያስፈልገዉ (Non-Insulin Dependent Diabetes Mellitus (NIDDM)) ወይም በአዋቂዎች የሚከሰት የስኳር ህመም ( adult-inset diabetes) በመባል የሚታወቀው የስኳር ህመም አይነት በብዛት በመካከለኛ የእድሜ ክልል በሚገኙ ጎልማሶች ላይ የሚከሰት ነዉ። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፤ በወጣቶችና በታዳጊዎች ላይም የመከሰት አዝማሚያ እያሳየ ይገኛል ። ይህ የስኳር ህመም በሰዎች ላይ ተከሰተ የሚባለዉ ፤ አንድም የታማሚዉ ጣፊያ ኢንሱሊንን በበቂ መጠን ሳያመርት ሲቀር አለበለዚያም የተመረተዉን ኢንሱሊን በአግባቡ መጠቀም ሳይችል (የኢንሱሊን እምቢተኝነት) ሲከሰት ነዉ። ለሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም በይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑት አነማን ናቸዉ? • ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች፣ • ዕድሜያቸው አርባ አምስት እና ከዛ በላይ የሆናቸው ሰዎች፣ • ቤተሰባቸው ውሰጥ የስኳር ህመምተኛ ያላቸው ሰዎች፣ • የዘር ግንዳቸው ከ (Africa, Hispanic, Native America and Asia) የሆነ ሰዎች፣ • በቂ ወይም ምንም አይነት የሰውነት እነቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች፣ • በሰውነታቸው ውሰጥ የሚገኝ የኮሌስትሮል አይነቶች የ(HDL) መጠን ዝቅ የ(HDL) መጠን ከፍ ካለ • ከ2.5 ኪ.ግ. በላይ የሚመዝን ልጅ የወለዱ ሴቶች ናቸው ። አንደኛው አይነት የስኳር ህመም (type 1 diabetes) ከአጠቃላይ የስኳር ታማሚዎች አምስት በመቶ (5%) በሚሆኑት ላይ የሚከሰት የስኳር ህመም አይነት ነው ። ይህ በቀደመው አጠራሩ ፤ የልጅነት የስኳር ህመም (Juvenile Diabetes) ወይም ኢንሱሊን የሚያስፈልገው (Insulin Dependent Diabetes Mellitus (IDDM)) በመባል የሚታወቀው የስኳር ህመም አይነት የኢንሱሊን እጥረት ባለባቸው ህፃናት እና ታዳጊ ወጣቶች የሚከሰት ነው ። በዚህ አይነት የስኳር ህመም የሚጠቁ ሰዎች ፤ የገዛ ሰውነታቸው የበሽታ የመከላከያ ስርአት በጣፊያቸው ውስጥ የሚገኙ ቤታ (beta) ሴሎችን ያጠፋቸዋል። ስለዚህ ከዚህ አይነት የስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች ፤ በጣም ጥቂት ወይም ምንም ኢንሱሊን አያመርቱም ማለት ነዉ ። ስለሆነም ሰውነታቸው የሚያስፈልገውን ኢንሱሊን ለማግኘት በየቀኑ ኢንሱሊን መወጋት ይጠበቅባቸዋል ።

የደም ማነስ/ Anemia የደም ማነስ በደምዎ ውስጥ በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎች ወይም ሄምግሎቢን ሲያንስ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ሄሞግሎቢን ዋናው የደም ሴሎቻችን ክፍል ሲሆን ከኦክስጅን ጋር ይጣመራል በጣም ጥቂት ወይም ጤናማ ያልሆኑ ቀይ የደም ሴሎችን ካሉን ወይም ጤናማ ያልሆነ ጥቂት ሄሞግሎቢን ካለን በሰውነታችን ውስጥ ያሉት ሴሎች በቂ ኦክስጅን አይደርሳቸውም፡፡ የደም ማነስ ምልክቶች ከሆኑት አንድ የሆነው የድካም ስሜት የሚከሰተው የሰውነት አካሎቻችን በትክክል ለመስራት የሚፈልጉትን ያክል ኦክስጅን ስለማያገኙ ነው፡፡ ሴቶች ህፃናት እና ከባድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ★ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነገሮች እነሆ፦ ✔አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች በዘር የሚተላለፉና በወሊድ ጊዜ ህፃናትን የሚያጠቁ ናቸው፡፡ ✔ለአቅመ ሂዋን የደረሱ ሴቶች በብረት እጥረት ለሚከሰተው የደም ማነስ በተለየ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው ምክንያቱም በወር አበባ ጊዜ የደም መፍሰስ እና በእርግዝና ወቅት የደም ፍላጎት ስለሚጨምር ነው፡፡ ✔በእድሜ የገፉ ሰዎች በደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ምክንያቱም በምግብ እጥረት እና የተለያዩ የህክምና ችግሮች ስለሚኖሩባቸው ነው፡፡ የተለያዩ የደም ማነስ አይነቶች አሉ ሁሉም የተላያዩ መነሻ እና የተለያየ ህክምና አላቸው፡፡ በብረት እጥረት የሚከሰተው የደም ማነስ በጣም የተለመደ በሽታ ነው አመጋገባችንን በመቀየር እና የብረት ንጥረ ነገር በመዉሰድ በቀላሉ መታከም እንችላለን፡፡ አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች ለምሳሌ በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው ጤናማ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ እድሜ ልክ የሚዘልቁ ናቸው፡፡ ★ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች! ከ400 የሚበልጡ የደም ማነስ አይነቶች አሉ እነሱም በሶስት መደቦች ይከፈላሉ፦ 1. በደም መፈሰስ የሚከሰት! 2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር! 3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት የደም ማነስ አይነቶች ናቸው፡፡ 1. በደም መፍሰስ የሚከሰት የደም ማነስ! ደም በሚፈሰን ጊዜ ብዙ ቀይ የደም ሴሎችን እናጣለን ይህም የሚከሰተው በትንሹ ለረጂም ሰዓት ደም ስለሚፈሰን ሲሆን ይህን ነገር ብዙ አናስተዉለውም፡፡ እንደዚህ አይነቱ ከባድ የደም መፍሰስ በሚከተሉት መንገዶች ይከሰታል ✔ ከጨጓራና አንጀት ጋር የተያያዘ በሽታዎች (ክንታሮት፣ቁስለት፣የጨጓራ ህመም እና ካንሰር) ✔ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች(አስፕሪን ወይም አይቡፕሮፊን) ✔ የወር አበባ እና በወሊድ ጊዜ(በተለይ በወር አበባ ጊዜ የደም ፍሰት ከመጠን በላይ ከሆነ እና በተደጋጋሚ እርግዝና ከተከሰተ) 2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር! ይህ አይነት የደም ማነስ በሽታ በሚከሰትበት ጊዜ ሰዉነታችን በጣም ጥቂት የደም ሴሎች ማምረት ወይም የደም ሴሎቻችን በትክክል ተግባራቸውን መወጣት ሲያቅታቸው ሲሆን በሁለቱም አጋጣሚዎች የደም ማነስ ይከሰታል፡፡ ቀይ የደም ሴሎች ችግር ይኖርባቸዋል ወይም በቁጥር ይቀንሳሉ የዚህ ምክንያት ጤናማ ያልሆኑ የደም ሴሎች ሲኖሩ ወይም ተግባራቸውን በብቃት ለመወጣት የሚያገለግሉ ሜኔራሎችና ቫይታሚኖች እጥረት ሲኖር ነው፡፡ ለዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ✔ ሲክል ሴል የደም ማነስ(አኒሚያ) ✔ በብረት እጥረት የሚመጣ የደም ማነስ ✔ በቫይታሚን እጥረት ✔ በመቅኒ እና አባት/መነሻ ሴል ችግር ✔ ሌላ የጤና ችግሮች ናቸው። በሲክል ሴል የሚከሰት የደም ማነስ በዘር የሚተላለፍ ሲሆን ቀይ የደም ሴሎች የጨረቃ ቅርጽ እንዲኖራቸው ያደርጋል ስለዚህ በቂ ኦክስጂን ወደተለያዩ አካሎች ማድረስ ያቅተዋል፡፡ የጨረቃ ቅርጽ ያላቸው የደም ሴሎች በጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ውስጥ ይቀረቀራሉ ይህም ህመም ያስከትላል፡፡ በብረት እጥረት ምክንያት የሚከሰተው የደም ማነስ ብረት በተባለው ሚኒራል እጥረት ሲኖር ነው፡፡ በአጥንታችን ውስጥ ያለው መቅኒ ኦክስጂን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍል የሚደርደውን ሄሞግሎቢን ለመስራት ብረት ያስፈልገዋል፡፡ በቂ የሆነ የብረት ሜኔራል ከሌለ በቂ የሆነ ሄሞግሎቢን አይመረትም የዚህ ውጤት በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ✔ የብረት እጥረት ያለባቸው ምግቦችን የመመገብ ዘይቤ ✔ እርግዝና እና ማጥባት የእናትን የብረት ክምችት መጠን ይቀንሳል ✔ የወር አበባ ✔ በተደጋጋሚ የደም ልገሳ ማድረግ ✔ ከባድ ስፖርታዊ ልምምዶች ✔ የምግብ መፍጨት ችግሮች ✔ አንዳንድ መድሃኒቶች በቫይታሚን እጥረት የደም ማነስ የሚከሰተው በቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሌት እጥረት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ቫይታሚኖች ቀይ የደም ሴሎችን ለመስራት ያገለግላሉ፡፡ ★ ለዚህ ችግር መነሻ ምክንያቶች! ✔ ሜጋሎብላስቲክ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት ✔ ፐረንሸስ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 በጨጓራ የመመጠጥ ችግር ነው ✔ የምግብ እጥረት፡ ትንሽ ስጋ ወይም ሙሉ ለሙሉ ስጋ አለመመገብ ✔ እርግዝና፣ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ የአልኮል ሱሶች፣ የአንጀት በሽታዎች አፕላስቲክ አኒሚያ፡ አባት(መነሻ)ቀይ የደም ሴሎች በቁጥር ሲቀንሱ ነው። ✔ ታላሲሚያ የሚከሰተው ቀይ የደም ሴሎች በትክክል መብሰል እና ማደግ ሲያቅታቸው ነው ✔ ሊድ ለተባለው መርዛማ ማዕድን መጋለጥ የአጥንት መቅኒ እንዲጎዳ ያደርገዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የደም ማነስ መነሻው ለቀይ የደም ሴሎች ምርት የሚጠቅሙ ሆርሞኖች እጥረት ሲሆን በዚህ አይነት ምክንያት የሚከሰቱት የሚከተሉት ናቸው:: ✔ ከባድ የኩላሊት በሽታ ✔ የታይሮይድ እጥረት ✔ የተለያዩ በሽታዎች(ስኳር፣ ካንሰር፣ ሪህ፣ ኢንፌክሽን) ✔ የእድሜ መግፋት። 3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት ደም ማነስ ! ቀይ የደም ሴሎች በሚሰባበሩበት ጊዜ እና የደም ዝዉዉር ውጥረት መቋቋም ሲያቅታቸው ያለ እድሜያቸው ይፈነዳሉ ከዚያም ሄሞላይቲክ አኒሚያ ይከሰታል፡፡ ይህ ችግር ስንወለድ ወይም ካደግን በኃላ ሊከሰት ይችላል አንዳንድ ጊዜ መነሻ ምክንያቱ አይታወቅም፡፡ መልካም ጤንነት!!!

ውድ አንባብያን የምች አምጪ ተህዋሲያን እጅግ ተላላፊ በመሆናቸው የምች በሽታ በሚከሰትብን ጊዜ የፊታችንን እና የእጃችንን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ ያስፈልገናል። ቁስለቶቹ ባጋጠሙን ጊዜ የምንጠቀምባቸውን የከንፈር ቀለሞች እና ቅባቶች ሌሎች እንዳይጠቀሙ በአግባቡ ማስወገድ ወይም ለይቶ ማስቀመጥ ብልሃት ነው።

የምች በሽታ የምች በሽታ ምንድን ነው? ምች (cold sore) በተለምዶ ከሚከሰቱ የቆዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛው ሲሆን በተለይም የላይኛው ወይም የታችኛው የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቆዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ ውሃ የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች ይታወቃል። ☑️ ከምች በሽታ በሰተጀርባ ምን አለ? በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን ነው። የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች በቫይሮሎጂ የትምህርት ዘርፍ በስፋት ከተጠኑ የቫይረስ ቤተሰቦች መካከል አንዱ ነው። በውስጡም ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያዎች ሲኖሩ 8ቱ በሰዉ ልጅ ላይ በሽታ ያስከትላሉ። ከነዚህም መካከል የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 ይገኙበታል። የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች ቆዳን ጨምሮ በኣይን፣በመራብያ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ኢንፌክሽኖች ያስከስታሉ። ግዙፉ የምርምር መረጃ ቋት ፕብ ሜድ በገጹ እንዳሰፈረዉ በአለም ላይ ከ90% በላይ በአዋቂ እድሜ ላይ ያሉ ጝለሰቦች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የኸርፒስ ቫይረስ ተለክፈዉ ይገኛሉ። የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) እንዲሁም ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV2) ከጨቅላ ህጽፃናት እስከ የእድሜ ባለፅጋ የእድሜ ክልል ኢንፌክሽን መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) በምች አምጪ ባህሪዉ ይታወቃል። ኤች.ኤስ.ቪ -1 (HSV-1) ከሰዉ ወደሰዉ በቆዳ-ቆዳ እና በቆዳ-የሚውከስ ሽፋን (የአፍ ዉስጥ ለስላሳ ሸፍን መሰል) ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2) ደግሞ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንዲሁም ከመራቢያ አካላት-ፊት በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል። የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ዝርያዎች በነጭ የደም ሴሎቻችን ተጠቅተዉ ከሰዉታችን ሙሉ በሙሉ በመወገድ ፈንታ በሰዉነታችን የነርቭ አካላት ዉስጥ በመሸሸግ የሰዉነታችን ዉስጣዊ ሁኔታዎች ምቹ እስኪሆኑ በመጠባበቅ ከተሽሽጉበት በመዉጣት በድጋሜ የምቸ በሽታን ያስከትላሉ። ☑️ የምች በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ የምች በሽታ ተህዋስያን ለመጀመርያ ጊዜ በሰዉነታችን ኢንፌክሽን ስያስከስቱ በአብዛኛዉ ምንም ምልክት አይኖራቸዉም ነገር ግን በሚከተሉት ጊዜያት ሲከሰቱ የሚከተሉትን የመሳሰሉ ምልክቶች ሊያሳዩ ዪችላሉ። የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ፣የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ከዚህም ከ 24 ሰአታት በኋላ ከስራቸው ቀልተዉ ዉሃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ይፈጠራል። በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከተፈጠሩበኋላ በቀላሉ በመፈንዳት ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ይሸፈናሉ። ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጟዳኘ የራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ውስጥ የሚገኙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ እጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል። ቁስለቶቹም በተለምዶከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ። ☑️ የምች በሽታን በተደጋጋሚ የሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? 🔸 ለሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም የመዉረድ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች(የኤች.አይ.ቪ፣የካንሰር ህመሞች) 🔸 በየወር አበባ ጊዜየሚከሰቱ ሆርሞናዊ ለውጦች 🔸 በተለምዶ በቫይረስ በሚመጡ እንደ ጉንፋን ያሉ ኢንፌክሽንዎች መጠቃት 🔸 ለጸሃይ ጨረር እና ነፋስ መጋለጥ 🔸 ጭንቀት እና የአእምሮ ዉጥረት ☑️ በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቤታችን ምን ማድረግ እንችላለን? 🗣 የህመም ማስታገሻ በምች በሽታ ሚመጡን ቁስለቶች በተያያዘ የሚሰማዎትን ህመም ለመቀነስ ያለ ሃኪም ትዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን (Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን (Paracetamol) በፋርማሲ ባለሙያው ትዕዛዝ መሰረት መጠቀም። 🗣 ቅዝቃዜ ከምች በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን በቁስለቶቹ ዙርያ የሚከሰት የቆዳ መቅላት እና መቆጣትን ለመቀነስ በቀዝቃዛ ውሃ በተነከረ ጨርቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በከን ውስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ለ5-10 ደቂቃ በቦታው ላይ መያዝ እንደሚረዳ የቆዳ ሃኪሞች ይናገራሉ። 🗣 እራስን ከጭንቀት ነጻ ማድረግ የአእምሮ ውጥረትን መቅነስ የሰውነትን በሽታ መከላከል አቅም እንደሚጨምር በጥናቶች ተረጋግጧል። ስለዚህም የሚያዝናኑን ነገሮችን በመፈለግ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከዚህም በዘለለ የባለሙያ ምክር በማግኘት ልንከላከለዉ ይገባል። ☑️ ለምች በሽታ የባህል ህክምናን መጠቀም ተገቢ ነዉ? የባህል ህክምና የአንድ አካባቢ ተወላጆች ለዘመናት ያካበቷቸዉ እንስሳን እና እጸዋት ነክ እዉቀቶችን አንዲሁም ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን መሰረት ያደረገ የህክምና ዘርፍ ነዉ። ጆርናል ኦፍ እስያ-ፓሲፊክ ባዮዲቨርሲቲ(Journal of Asia-Pacific Biodiversity) ባወጣው ጥናት መሰረት የአለማችን 64% የሚሆነዉ ማህበረሰብ ለሚገጥሙት የጤና እክሎች የባህል ህክምናን እንደ መጀመርያ አማራጭ ይጠቀማል። በአገራችን ኢትዮጲያ ደግሞ ከ80% በላይ የሚሆነው ማህበረሰብ የባህል ህክምና ተጠቃሚ እንደሆነ የተለያዩ አገር በቀል ጥናቶች ያመለክታሉ። የምእራባዉያን ባህል ህክምና በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ ብርቱካን፣ ኪዊ እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን እንድንጠቀም ይመክራል። የአገራችን የባህል ህክምና ደግሞ ዳማከሴ(Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ሃገር በቀል ተክል ቅጠሎች ጭማቂ በመጠጣት ወይም ቅጠሎቹን አንድ ላይ በመጨፍለቅ ቁስለቶቹ ላይ በማድረግ እንድንጠቀም ይመክራል። በዳማከሴ(Ocimum Lamiifolium) ጠቅላላ አጠቃቀም እንዲሁም ስለጸረ ምች አምጪ ትህዋስያን ባህሪያቱ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ስለ አጠቃላይ ጸረ-ህዋስ እና ጸረ-የሰዉነትመቆጣት (Anti-inflammatory) ባህሪያቱ የሚያወሱ አንዳንድ የ ሃገር በቀል ጥናቶች ብቅ ብቅ ብለዋል። ☑️ ለምች በሽታ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነዉ? በምች በሽታ የሚመጡ ቁስለቶች በአብዛኛዉ ጊዜ በራሳቸዉ የሚድኑ በመሆናቸዉ የሃኪም ምክር መሻት ላያስፈልግ ይችላል። ነገር ግን ከታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች በሚከሰቱበት ጊዜ የሃኪም ምክር ማግኘት የግድ ይላል። 🔻 የኤች.አይ.ቪ ወይም የካንሰር ተጠቂ ከሆንን 🔻 የምች በሽታ ቁስለቶች አይናችን አካባቢ ከተከሰቱ 🔻 ከ2 ሳምንታት በላይ ሳይድኑ የሚቆዩ ቁስለቶች 🔻 የአቶፒክ ደርማታይቲስ (Atopic dermatitis) ታማሚ ከሆንን 🔻 በተደጋጋሚ ቁስለቶች የሚ ያጋጥሙ ከሆነ ሃኪም ማማከር ግድ ይላል። ☑️ ሃኪምዎ ምን ሊረዳዎት/ልትረዳዎት ይችላል/ትችላለች? ሃኪምዎ ቁስለቶቹን አጢኖ ከተመለከተ/ች በኋላ አሳይክሎቪር (Acyclovir) እና ቫልሳይክሎቪር (Valcyclovir) የመሳሰሉ ጸረ ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎችን እንዲሁም የተለያዩ የህመም ማስታገሸ መድሃኒትዎችን ልያዝሎ ይችላል። ጸረ- ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎቹ በቆዳ ላይ የሚቀቡ ወይም በ ኣፍ የሚዋጡ ሊሆኑ ይችላሉ።

የዲስክ መንሸራተት - ችላ የተባለው ጉዳይ (በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና) #EthioTena የዲስክ መንሸራተት ማለት በሁለት የጀርባ አጥንቶች መካከል የሚገኘውና የአጥንቶቹን ንክኪ የሚቀንሰዉ ዲስክ ወደፊት ወይም ወደኃላ አሊያም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ በኩል ቦታዉን ለቆ በሚንሸራተትበት ወቅት የሚመጣ ነው። ✔ የህመሙ ምልክቶች ስለመከሰቱ ምንም እዉቅና ሳይኖርዎ ወይም ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳይኖር የዲስክ መንሸራተት ሊኖር/ሊከሰት ይችላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች ሳያሳዩ በምርመራ ወቅት በራጅ ላይ የዲስክ መንሸራተት መኖሩ ሊታወቅ ይችላል፡፡ ※ የዲስክ መንሸራተት በሚኖርበት ወቅት የሚኖሩ የህመም ምልክቶች፦ • የእጅ/የእግር ላይ ህመም፡- የዲስክ መንሸራተቱ ያጋጠመዉ በታችኛዉ የጀርባ አጥንቶች አካባቢ ከሆነ ከፍተኛ ህመም በመቀመጫዎ፣ በጭንዎና በባትዎ አካበቢ እንዲሁም መርገጫዎ/የእግር መዳፉ ላይ ሊሰማዎ ይችላል፡፡ የዲስክ መንሸራተት ያጋጠመዎ አንገትዎ ላይ ከሆነ ህመሙ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰማዎ በትከሻና በእጅዎ ላይ ነዉ፡፡ ሕመሙ በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበት ወቅት ወይም ወደ ተወሰነ አቅጣጫ የጀርባ አጥንቶችዎን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት ሊባባስ ይችላል፡፡ • የመደንዘዝ ወይም የመጠቅጠቅ ስሜት • የእጅ/ እግር መስነፍ፡- በዲስክ መንሸራተት ምክንያት የተጎዳ ነርቭ ካለያ የተጎዳዉ ነርቭ እንዲሰራ የሚያደርገዉ ጡንቻ ሊደክም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ መራመድ መቸገር፣እቃ ማንሳት ያለመቻል ወይም መያዝ ያለመቻል ሊከሰት ይችላል፡፡ ✔ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው? የጀርባዎ ህመምዎ ወደ እጅዎና እግርዎ የሚሰራጭ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያስፈልጋል። ✔ ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች/ምክንያቶች፦ • የሰዉነት ክብደት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ የጨመረ ከሆነ በጀርባ አጥንትዎና ዲስኩ ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡ • የስራዎ ሁኔታ፡- የስራቸዉ ፀባይ ጉልበት የሚጠይቅ ስራ የሚሰሩ ሰዎችከ ሌሎች ይልቅ ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡ በተደጋጋሚ ከባድ ነገር የሚያነሱ፣ የሚጎትቱ፣ የሚገፉ፣ ወደ ጎን መታጠፍና መጠማዘዝ የሚያበዙ ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡ • በዘር የሚመጣ፡- አንዳንድ ሰዎች ለመሰል ችግር ተጋላጭነታቸዉ መጨመር በዘር ሊወረስ ይችላል፡፡ ✔ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና • የህመም ማስታገሻ፡- ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ እንደ አይቡፕሮፌን/ አድቪል/ መዉሰድ። • ሙቀት/ቀዝቃዛ ነገር መጠቀም፡- በመጀመሪያ ቀዝቃዛ ነገር ቦታዉ ላይ መያዝ ህመሙንና መቆጥቆጡን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኃላ ሙቅ ነገር መያዝ ምቾትና የህመም ፈዉስ እንዲሰማዎ ስለሚያደርግ በቦታዉ ላይ መያዝ። • ከመጠን ያለፈ እረፍት ያለማድረግ/ማስወገድ፡- ከመጠን ያለፈ እረፍት የመገጣጠሚያዎች መጠንከር/መተሳሰር እና ጡንቻዎች መስነፍ እንዲመጣ ስለሚያደርግ የፈዉሱን ጊዜ አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይልቁንም በሚመችዎ አቅጣጫ ለ30 ደቂቃዎች እረፍት ማድረግና ከዚያን ለአጭር ጊዜ ወክ ማድረግ አሊያም የተወሰኑ ስራዎችን ማከናወን፡፡ ከህመምዎ እያገገሙ ባሉበት ወቅት ህመሙን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች/እንቅስቃሴዎች መቆጠብ። ✔ የዲስክ መንሸራተትን እንዴት መከላከል ይቻላል? • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡- የጀርባ ጡንቻዎችን ለማጠንከር ስለሚረዳ የጀርባ አጥንቶችን ለመደገፍና ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ • ትክክለኛ የሰዉነት አቋም/ Maintain good posture / እንዲኖርዎ ማድረግ፡- ጥሩ የሰዉነት አቋም ካለዎ በጀርባ አጥንትዎና ዲስኩ ላይ የሚመጣዉን ጫና ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጡ ከሆነ ቀጥ ብለዉ ለመቀመጥ መሞከር፡፡ ከባድ እቃ በሚያነሱበት ወቅት ስራዉን/ ክብደትዎን ከጀርባዎ ይልቅ በእግሮችዎ ላይ ማድረግ፡፡ • ክብደትዎን በትክከል መጠበቅ፡- ከመጠን ያለፈ ክብደት በጀርባ አጥንትዎና ዲስክዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ክብደትዎን መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ መልካም ጤንነት!!

" የቲማቲም_ፈውሶች!!" ………የአሜሪካ ፍርድ ቤት እ,ኤ,አ በ1893 ዓመተ_ምህረት "ቲማቲም ዘሯ ከምን ይመደብ!?" የሚለውን ውሳኔ "ከአትክልት" ብሎ ቢደመድምም ከጊዜ በኋላ ግን በተደረገ ማሻሻያ መሰረት ቲማቲም "ፍራፍሬ" ነሽ ተብላ እስካሁን እዚያ ቤተሰብ ውስጥ ትኖራለች። ……በሀገራችን ከታችኛው ማህበረሰብ አንስቶ እስከላይኛው ድረስ ቲማቲምን በተለያየ አዘገጃጀት ይመገበዋል። ከጉሊት ገዝቶ በቁርጥ መልኩ ከሚመገበው የኔ ቢጤ ጀምሮ……ትንሽ ሻል ያለው ደግሞ የዶሮ_ወጥ ቃና እስኪፈጥር አቁላልቶ በወጥ መልኩ ይበላዋል። በትላልቅ ሱፐር ማርኬት በቆርቆሮ ታሽጎ የሚሸጠው የቲማቲም_ድልህ ደግሞ ከእነ_ፓስታ; መኮሮኒ አይነት ምግቦች ጋር ውህደት በመፍጠር በጥፍጥና አክሲዮኑ ወደ ሆድ ኤክስፖርት ይደረጋል። ……ከአመታት በፊት በሀገራችን አደገኛ የሆነ የቲማቲም በሽታ ገብቶ በርካታ እርሻዎች ላይ የነበሩ ቲማቲሞች ከወደሙ በኋላ እጥረት በመፈጠሩ ዋጋው ተወዶ የነበረ ሲሆን አሁን በምን ያህል ዋጋ ኪሎው እንደሚሸጥ ባላውቅም…… መርካቶ ዶሮ ተራ መንገድና ፒያሳ አትክልት ተራ ዛሬም ሴቶች መሬት ላይ አንጥፈው ሲሸጡ ይታያል። .........የበርካታ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን የዕለት ጉርስ የሆነው ቲማቲም በአንዳንድ ሀገራት መጫወቻ ሆኖ ሳታዩት እንዳልቀራችሁ እገምታለው። በተለይ በአውሮፓዊቷ ስፔን በየአመቱ በትላልቅ ተሳቢ የጭነት መኪናዎች ተጭኖ የመጣውን የቲማቲም ክምር መሬት ላይ ከዘረገፉላቸው በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስፔናዊያን እና የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች እስኪበቃቸው በውርወራ ይፋለሙበታል። ……በእርግጥ እነዚህ ቲማቲሞች የበሰበሱና የተጨፈለቁ ሲሆን ብዛታቸው ሲታይ ግን በምግብ ዕጦት ለሚሰቃዩ የድኀ ሀገራት ዜጎች ምራቅ ማስዋጡ አይቀርም። በእርግጥ ዓለም በእንዲህ አይነቱ የኑሮ ልዩነት የተሞላች ጉራማይሌ መድረክ ናት። እኛ የምንጠጣው የቧንቧ ውሃ ምናልባት በሌላው ዓለም አትክልት ለማጠጣት እንኳን ብቁ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ስፔኖች ለድብድብ ሲጠቀሙበት እኛ ደግሞ ቢሰጠው በቃኝ ለማይለው ለደደቡ_ሆድ እንወረውርለታል። ………ከቲማቲም ጋር ተያይዞ የሚነሱ እንደ_አተት; አሜባ; የመሳሰሉ ሆድን የሚያውኩ አጣዳፊ በሽታዎች እንዳሉ ሁሉ ቲማቲም በሌላ በኩል ከምግብነቱ በተጨማሪ ለበርካታ በሽታዎች ሁነኛ ፈውስ የሆነ አስደማሚ የአትክልት ዝርያ ነው። በሀገራችን አይለመድ እንጂ ቲማቲም በጭማቂ መልክ የሚጠጡ የውጪ ዓለም ሰዎች ነብስ ነው ይሉታል። በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ያሉ ሕዝቦች ምሽት ላይ ከቮድካው አብዝተው ከጨለጡ ጠዋት ለአንጎቨር ማስለቀቂያ ሮጠው የሚሄዱት የቲማቲም_ጭማቂ ወደሚሸጥባቸው ቤቶች ነው። ……ቲማቲምን ከምግብና ከመጠጡ ሰፈር አውጥተን ወደጤና ጣቢያ ስንወስደው በርካታ የጤና ጠቀሜታዎቹን እናገኛለን። በሜዲትራኒያን ሀገሮች ዘንድ ቲማቲም……ፍራፍሬም_አትክልትም እንደሆነ የሚታመን ሲሆን በሌሎችም የዓለም ክፍሎች በርካታ ማዕዶች ላይ እንደዋና ምግብ ባይሆንም እንደቡፌ ማድመቂያ ዲኮርም ይቀርባል። ሌላው በፋስትፉድ ደረጃ ተዘጋጅቶ የአዳም ዘር በብዛት የሚቋደሰው ፒዛ ዋንኛው የምግቡ አምበል ቲማቲም ነው ማለት ይቻላል። …………ቲማቲም "lycopene" የተባለውን ንጥረ_ነገር በከፍተኛ ሁኔታ ይዟል። ይሄው አንቲኦክሲዳንት ካንሰርን የሚያስከትሉትን……"ፍሪ ራዲካልስ" ተብለው የሚታወቁትን ነገሮች ድምጥማጣቸውን ያጠፋቸዋል። ይህን ጠቀሜታውን በእሳት በስሎ ከተዘጋጀ ቲማቲም ሆነ ከketchup ጭምር ማግኘት ይቻላል። ከቲማቲም ብዙ የጤና በለስ ይሸመታል……የዓይን ጤንነትን ይጠብቃል; ጥሩ የሆድ መረጋጋት እንዲኖረን ያደርጋል; የደም ግፊት ይቀንሳል; ለስኳር በሽታም የጠቀሜታ ድርሻ ያለው ሲሆን በቆዳ ላይና በሽንት ፊኛ ለሚፈጠር ኢንፌክሽንም የፈውስ ምላሽ አለው። ………ቫይታሚኖችን እና ሚኒራሎችን በከፍተኛ መጠን በመያዙም የተለያዩ የደም_ሥር በሽታዎችን በመከላከሉ ረገድ የተዋጣለት ነው። ቲማቲም የጡት እና የአፍ ካንሰሮችንም እንደሚከላከል……"በሃርቫርድ ስኩል ኦፍ ፐፕሊክ ሔልዝ" አማካኝነት ለንባብ የበቁ ጥናቶች ገልፀዋል። ………በሀገራችን ከከተሜነት የኑሮ_ዘይቤ ጋር እየተስፋፉ ከመጡ በሽታዎች ውስጥ በኮሌስትሮል አማካኝነት የሚመጣ የልብ ህመም የተጠቂዎች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል። ቲማቲም ላይኮፔን የተሰኙ ተከላካይ ንጥረ_ነገሮችን በመልቀቅ የልብ ደም_ስር በሽታዎችን የሚከላከል ሲሆን በተለይ ቲማቲምን በቋሚነት መመገብ በደም ውስጥ ldl ተብሎ የሚጠራውን የኮሌስትሮል አይነት እንዲቀንስ ያደርጋል። እነዚህ ጎጂ ኮሌስትሮሎች በደም_ስር የስብ ክምችት እንዲፈጠር በማድረግ የልብ ደም_ስር ህመም እንዲከሰት በማድረግ ይታወቃሉ። ……አንዲት ቲማቲም ለአንድ ቀን ከሚያስፈልገን የቫይታሚን ሲ መጠን ውስጥ 40 ከመቶ ያህሉን ትሰጠናለች። በተጨማሪ በቲማቲም ውስጥ ቫይታሚን ኤ እና ፖታሲየም እንዲሁም አይረን በከፍተኛ መጠን ይገኛሉ።ፖታሲየም የነርቮችን ጤንነት በመጠበቅ ረገድ የማይናቅ አስታውፆ ያለው ሲሆን አይረን ደግሞ የደም ጤንነት እንዳይዛባ ያደርጋል። የደም መርጋትን እና መድማትን የሚቆጣጠረው ቫይታሚንም በከፍተኛ መጠን ቲማቲም ውስጥ ከምናገኛቸው ንጥረ_ነገሮች አንዱ ነው። ………በሲጋራ ሱስ ለተለከፉ አጫሾችም ቲማቲም በውስጡ ሚስጥር ያዘለ ሲሆን በቲማቲም ውስጥ ያሉት coumaric acid እና chlorogenic acid በሲጋራ አጫሾች ዘንድ የሲጋራ ፍላጎትን የሚቀሰቅሱትን nitrosamines በመዋጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣሉ። ቲማቲም ለአይናችንም የማየት ብቃቱን ለማሻሻል የሚያግዘው ሲሆን በምሽት አለማየትን night blindness እና የዓይን መድከምን macular degeneration ያስወግዳል። ………በጆርናል ኦፍ ዘ አሜሪካን ሜዲካል አሶሲየሽን በተደረገ አንድ ጥናት በየዕለቱ ቲማቲምን መመገብ በ type 2 diabetes ላይ የoxidative stressን ይቀንሳል ብሏል። ቲማቲም የጥርስ; የአጥንት; የጸጉር እና የቆዳ ጤንነት የተጠበቀ እንዲሆን አስታውፆ ያደርጋል። በቆዳ ላይ በፀሓይ አማካኝነት የደረሰ መለብለብን የቲማቲም ጭማቂ በመቀባት ማዳን ይቻላል። በየዕለቱ ቲማቲምን መመገብ ቆዳን ከፀሓይ ጨረር ለመከላከል ይረዳል። የእርጅናን መፋጠን የሚከላከሉ ምርቶችን ለማዘጋጀት ከሚውሉ ግብዓቶች ውስጥ ቲማቲም በአንደኝነት ተቀምጧል። ……ቲማቲም ሌሎችም የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን የሽንት ትቦ ኢንፌክሽንን ከመከላከሉም በላይ የሽንት ፊኛ ካንሰርን የሚከላከል ሲሆን በቋሚነት ከተመገብነው የሃሞትና የኩላሊት ጠጠሮችን አሟሙቶ ለማጥፋት ያስችላል። ፀጉራችን ጠንካራና አንፀባራቂ በማድረጉም ይታወቃል። ሼር ያርጉ @DrSofonias

Repost from N/a
#የተለየ #ክትትል #የሚፈልጉ #የእርግዝና #አይነቶች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️ 🔵#ብዙ የእርግዝና ክትትሎች የተለመዱ የክትትል ሂደቶች ዉጪ
#የተለየ #ክትትል #የሚፈልጉ #የእርግዝና #አይነቶች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️ 🔵#ብዙ የእርግዝና ክትትሎች የተለመዱ የክትትል ሂደቶች ዉጪ የተለየ ምርመራ ባያስፈልጋቸውም አንዳንድ ለየት ያለ ወይም በብዛት ቀጠሮ እንዲሁም ምርመራ የሚያስፈልጋቸው የእርግዝና ዓይነቶች አሉ፡፡ ይህም ለጽንሱ እንዲሁም ለእናት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ይረዳል።ከእነሱም መሃከል፡- 🔵#የደም ማነስ 🔹ብዙ እናቶች ከእርግዝና በፊት የደም ማነስ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ይህ የደም ማነስ በቅድሚያ መስተካከል ይኖርበታል የእናቲቱን እና የህፃኑን እድገት ለማጎልበት እንዲሁም በምጥ ጊዜ በሚመጣ መድማት ጉዳትን ለመከላከል በብረት የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በዶክተር የሚታዘዙ የብረት እንክብሎችን መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ 🔹እነዚህ የምግብ አይነቶች ቀይ ስጋ߹ቆስጣ߹ አሳ ߹ ዶሮ እና ኮክ የመሳሰሉ ምግቦችን ያጠቃልላል፡፡ 🔵#ስኳር በሽታ 🔹 ከማርገዝ በፊትም ሆነ በእርግዝና ወቅት የሚመጣ የስኳር በሽታ ተቆጣጥሮ መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም የሚሆነው በየጊዜው የስኳር መጠንና ተያያዥ ምርመራ በማድረግ߹ የመድሀኒት አጠቃቀምን በማስተካከልና መድሀኒቱ ስኳሩን መቆጣጠሩን በማረጋገጥ ነው፡፡ ኢንሱሊን የሚወስዱ ነፍሰ ጡር ሴቶች የሚወስዱት መጠን በዶ/ር መስተካከል አለበት ምክንያቱም እርግዝና የሰውነት እንዲሁም የውስጣዊ የሰውነት አሰራርን ሊቀይር ስለሚችል ነው፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ አመጋገብን እና የሰውነት ክብደትን መከታተልም ተመራጭ ነው፡፡ 🔵#የማህፀን በር መሳሳት 🔹በጤናማ የእርግዝና ወቅት የማህፀን በር ምጥ እስኪመጣ ድረስ ተዘግቶ ይቆያል፡፡አንዳንድ እናቶች ግን ጊዜው ሳይደርስ በተለያዩ የጤና መታወኮች ምክንያት ተደጋጋሚ ውርጃ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል

አይን ማሳከክ ሁላችንንም በህይወታችን የሚያጋጥመን ህመም ነው። እልህ አስጭራሽ እና አታካች ደረጃም ሊደርስ ይችላል። ከማሳከክ አልፎም አይንን የማቃጠል፣ ውሃ የመቋጠር፣ የመቅላት እና የፍሳሽ ችግሮች አብረውት ይታያሉ። ብርሃን ለማየት መቸገርም ሊመጣ ይችላል። አብዛኛው ግዜ የማሳከክ መንስኤው አልርጂ እና ኢንፌክሽን ናቸው። ደረቅ አይን፣ ኮንታክት ሌንስ፣ የአይን ንጽህና መጓደልም መነሻ ይሆናሉ። አይናቸውን በእጃቸው በሚነኩ ሰዎች ላይ ችግሩ ይበልጥ ይታያል። የማሳከክ ስሜቱ በተበከለ አካባቢ እና አየር በሚለዋወጥበት ወቅት ሲባባስ ይታያል። አይን የማሳከክ ስሜትን በፍጥነት መፍትሄ ካልተበጀለት ወደ ኮምፕሊኬሽን ሊያመራ ይችላል። በአይን ላይ ዘላቂ ጉዳት የማድረስ ስጋት አለው። ህመሙን ለማስታገስ ቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችለው 10 ነገሮች እነሆ።(ህመሙ ለውጥ ካላሰየ ግን በፍጥነት የአይን ሃኪም ሂደው እንዲታዩ እንመክራለን።) ቀዝቃዛ በረዶ ቀዝቃዛ በረዶ በጨርቅ ጠቅልለው የሚያሳክክዎት አይን ክዳን ላይ ማድረግ ስሜቱን ይቀንሰዋል። ጨርቁ ለስላሳ እና ንጹህ መሆን አለበት። ይህ መፍትሄ በአለርጂ ምክንያት ለመጣ ማሳከክ ይረዳል። ለአይን መድረቅና የመጠዝጠዝ ስሜት ሲኖር የሚረዳ መፍትሄ ነው። ጨርቁን አይንዎት ላይ ከ5-10 ደቂቃ እንዲያደርጉ ይመከራል። ከ2-3 ጊዜ መደጋገም በቂ ነው። በረዶ ካልተገኘ ጨርቁን ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ነክረው የጭመቁና አይንዎ ላይ ያድርጉ። ካሞሜል ካሞሜል ሻይ ለአለርጂ የሚረዳ ንጥረ ነገር አለው። በካሞሜል አይን መታጠብ የህመሙን ስሜት ለመቀነስ ይረዳል። ካሞሜል ሂስታሚን የሚባለውን ኬሚካል ከሰውነታችን የሚወጣበትን ፍጥነት ይቀንሳል። በማድረግም የአለርጂክ ቁጣ እንዳይኖረን ይረዳል. ካሞሜልን ለአይን በሁለት መንገድ ማድረግ ይቻላል። – ካሞሜል ቅጠሉን የፈላ ውሃ ውስጥ ለ5 ደቂቃ ይንከሩ። ከዛ ቅጠሉን ያውጡና ሻዩ እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁ። በቀዘቀዘው ሻይ አይንዎን ይጠቡት። በቀን 2 ወይም 3 ግዜ ማድረግ ይመከራል። – የካሞሜል ቅጠሉን ፍሪጅ ውስጥ ከተው ያቅዝቅዙት። የቀዘቀዘውን ቅጠል የተጨፈነው አይን ላይ ለ10 ደቂቃ ያድርጉ። በቀን 3 ወይም 4 ግዜ ማድረግ ይመከራል። ዝኩኒ ዝኩኒ መጠዝጠዝን የሚረዳ እና አንቲኦክሲዳንት ንጥረ ነገር አለው። ለአይን ማቃጠል እና መጠዝጠዝ የሚረዳ አትክልት ነው። ዝኩኒውን በደንብ ካጠቡ በኋላ በቀጭኑ ይክተፉት። የከተፉትን ዝኩኒ ፍሪጅ ውስጥ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ያድርጉ። አውጥተው ቁርጥራጩን በጨፈኑት አይን ላይ ለ10 ደቂቃ ያድርጉ። በቀን ከ4 እስከ 5 ግዜ ማድረግ ይመከራል። ቀዝቃዛ ወተት ቀዝቃዛ ወተት አይንዎት ላይ ለሚሰማዎት የማቃጠል ስሜት ይረዳል። ንጹህ ጥጥ በቀዝቃዛ ወተት ውስጥ ይንከሩና በተዘጋ አይንዎት ላይ ቀስ ብለው ይሹት። በቀን ሁለት ግዜ እንዲያደርጉት ይመከራል። ጧት እንዴ ማታ እንዴ። ማሸት ካልፈለጉ ጥጡን አይንዎት ላይ ከ15-20 ደቂቃ ማስቀመት ይችላሉ። አረንጓዴ ሻይ 1 ብርጭቆ የፈላ ውሃ ውስጥ ሁለት አረንጓዴ ሻይ ቅጠል ከተው 5 ደቂቃ ያቆዩ። ቅጠሉን አውጥተው እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁ። አይንዎትን ይጠቡበት። በቀን ሁለት ግዜ እንዲያደርጉ ይመከራል። እንደ አማራጭ የቀዘቀዘውን ሻይ ቅጠል አይንዎት ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ማድረግ ይችላሉ። ጨው አይንዎን በጨው ማጠብ በአለርጂ ወይም በአቧራ የሚከሰትን ማሳከክ ይቀንሳል። የጨው ውህድ አይንዎ ላይ ያለ ቆሻሻ ያጸዳል ባክቴሪያዎችንም ይገላል። መጀመርያ 1 ንኬል ውሃ ያፍሉ። እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁና 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይጨምሩበት። በደንብ ያማስሉና አይንዎን ይጠቡበት። ካልሆነ ጥጥ ነክረው አይንዎን መዳበስ ይችላሉ። በቀን ሁለት ሶስት ግዜ ማድረግ ይመከራል። እሬት(Aloe Vera) እሬት ሌላ የቅባት ይዘት ያለው አትክልት ነው። እሬት ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ለአይን ማቃጠል ስሜት ህክምና ይውላል። የእሬት ቅጠሉን በደንብ ይጠቡና በቢላዋ ልጠው ውስጥ ያለውን ቅባት ያውጡ። ቅባቱን አይንዎ ክዳን ላይ በመቀባት ለ15-20 ደቂቃ ያውሉ። እንዳስፈላጉነቱ በቀን ሁለት ግዜ ማድረግ ይችላሉ። እንዳማራጭ ፍሳሹን በጥጥ አንስተው አይንዎን ለ15 ደቂቃ መዳሰስ ይችላሉ። የጉሎ ዘይት (Castor Oil) የጉሎ ዘይት የልስላሴ ንጥረ ነገር ያለው ዘይት ነው። ደረቅ እና የሚያሳክክ አይን ለማከም ይረዳል። በተጨማሪም በውስጡ ጸረ-ቃጠሎ እና ጸረ-ባክቴሪያ ንጥረ ነገሮች አሉት። የአይን ኢንፌክሽን ለማከም ይረዳል።

የፀጉር በሽታዎች Disease of the hair ፀጉር ሲባል ሥርና ግንድ ያለው ሆኖ ከቆዳ ውስጥ የሚያድግ ነው፡፡ ከለስላሳ ህዋሳት ተገንብቶ ከየመሀሉ ያለው ምግብ እንዲዘዋወር የሚያስችል መጠን አለው፡፡It is of fibrous character የፀጉር ሕዋሳት በቁመታቸው ልክ ኘሮሜንት የተባለ ቀለም ተሰራጭቶ ስለሚገኝ ይጠቁራል፡፡በአንፃሩ ነጭ ፀጉር ኘሮሜንት ሳይሆን በቁመቱ ልክ አየር ሞልቶት ስለሚገኝ ነው፡፡የፀጉር ስር ፋይብረስ ፓፒዩል በተባለው ላይ ቆሞ ይገኛል፡፡ ምግቡንም ከዚሁ ያገኛል፡፡ ስሩ ያለው ወደታች ሩቅ ሲሆን ታዳጊው ክፍል ከታች ወደ ላይ እየተገፋ ወደ ውጭ ዕድገቱን ይቀጥላል፡፡ለ በአንድ ዓመት ዉስጥ ስድስት ኢንች ያህል ብቻ ያድጋል፡፡ ሆኖም ያንዳንዱ ሰዎች ፀጉር እድጎ ሲያበቃ በሌላ ታዳጊ ፀጉር ይተካል፡፡በገዛ ራሱ ተነቅሎ ይወድቃል፡፡ በሰውነት ውስጥ በራስ ቅል በታች follicle የተባለ ትንሽ ጡንቻ ይገኛል፡፡ በዚህ አማካኝነት ፀጉር ከዕጢ ውስጥ ቅባቱን ያገኛል፡፡ ሥራውን በትክክል የሚሠራ እንደተቀሩት የሰውነት አካላት ሁሉ ምግብ የሚቀርበው በደም ሲሆኝ ፀጉር ምግብ ሲያጣ ማድረስ የሚቻለው ፀጉርን በኃይለኛ በማሸት ነው እንጂ፣እንደሚባለው የተለያዩ ክሬሞችና ሎሽኖችን በመቀባት አይደለም፡፡ አንድ ሰው በልጅነቱ ሳይሰለች ራሱን ያሹለት እንደሆን በእይወቱ ዘመን ሁሉ የፀጉር ደን ሊኖረው ይችላል፡፡ የፀጉር መነቀል ፀጉር መነቀል ሲጀምር ምክንያቱን በቶሎ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ በሽታው ሲታወቅ ታክሞ ማዳን ያስፈልጋል፡፡ In this case the hair falling acts as a barometer. ይህ እንደተከሰተ ወዲያውኑ rigorous massage ኃይለኛ እሽታ ይጀምር፡፡ ባርኔጣ ወይም ኬኘ የሚለብስ ከሆነ መጥበቅ አይኖርበትም፡፡ከዚህ በላይ በቀዝቃዛ ውሀ መለቅለቅና ማበጠር፣ በቀዝቃዛ ውሃ ሁልጊዜ ወሽ ማድረግ ጠቃ ሚ ነው፡፡ ለአንድ ደቂቃ ያህል ፀጉርን አንዳለ በውሀ ውስጥ መዝፈቅ፣ በጣት ማበጠርና በማሸት ማድረቅ ይሆናል፡፡ ጄል የምትጠቀሙ ከሆነ alcohol free የሚለውን ጄል ይጠቀሙ በተጨማሪም ጄል ከተቀቡ በኋላ ሳይታጠቡት በተደጋጋሚ በዛው ላይ ቀንም ይቀቡ ከሆነ ፀጉርን ይጐዳል፡፡ ለምለም የድንብላል ቅጠሎችን ወቅጦ በውሀ በመበጥበጥ ፀጉርን ቀብቶ (ለተከታታይ ቀናት) ከሁለት ሰዓታት በኃላ መታጠቡ የፀጉር መሳሳት ችግርን ይቀርፋል፡፡ በራሀማነት Baldness Patchy blandness: alopecia areata የበራሀማነት መንስኤ እንደሚባለው በባክቴሪያ ወይም በሌላ ሕይወት ባለው ቁስ አካል አይደለም፡፡ በሲምፓቴክ ነርቭስ ሲስተምም አይለደም ፡፡ ዋነኛው ምክንያት ወደ ቆዳ ምግብ በሚደርሱት ቬይኖች ደም መላሾች በሚደርሰው እክል ነው፡፡ ለማንኛውም ፀጉር የተወሰነ ዕድሜ ስላለው ረረኪ ከሌለ ግለሰቡ ለበራነት ይጋለጣል በፀጉር ውስጥ የተፈጥሮ ዘይቶች መድረቅ ሲጀምሩ ፀጉርም ምግብ ያጣና እየተሰባበረ ይወድቃል፡፡ ፀጉርን በውሀ አርጥቦ በኃይል ማሸት በሕይወት እንዲቆይ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም በየቀኑ በቀዝቃዛ ውሃ ፀጉርን መታጠብ እና በእጅ ማፍታታት ፀጉራችን እድሜ እንዲኖረው ይረዳል፡፡ ፍሮፎር ፡- ዳንድረፍ (DANDRUFF) ራስ ቅልን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን የሚከሰተውም አንዱ የተለየ ዕጢ sebacrous glands የተባለ የጮማ ፍስሳት ወደ ውጭ ሲበተን ነው፡፡ ይህ ፍስሳት ከአቧራና ከሌላ ቆሻሻ ጋር ሲገናኝ ፎሮፎር ይሆናል፡፡ ለፀጉር ምግብ እንዳይደርስ ስለሚከላከል ለበራነት የዳረጋል፡፡ ተላላፊም ስለሆነ ሰዎች የፀጉር ዕቃዎችን ባይዋዋሱ መልካም ነው፡፡ ፎሮፎር ያለበት ሰው ፀጉሩን በአጭሩ ቢቆረጥና ፀጉሩን በንፅህና ቢይዘው መልካም ነው፡፡ ፀጉርን በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ በሎሚ ጭማቂ ለብ ካለ ውሃ ጋር አደባልቆ ፀጉርን መታጠብ ፣ በአጓት መታጠብ ፀጉርን በፖፓያ ለቅልቆ 1ዐ ደቂቃ በኃላ መታጠቡ ፎሮፎርን ለማጥፋት ይጠቅማል፡፡ ሁለት የቫይ ማንኪያ የሽንብራ ዱቄትን በሎሚ በቀጭኑ አላቁጦ የራስ ቅልን በማሸት ወዲያውኑ በውሃ በተደጋጋሚ በመለቃለቅ ፎሮፎርን የፀጉር መርገፍንና የማሳከክ ስሜትን ለማጥፋት ይጠቅማል፡፡