cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ንቁ ትውልድ-Niku Twld

እኛ ንቁ ትውልዶች ነን!

Більше
Рекламні дописи
3 992
Підписники
-424 години
-177 днів
-9030 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
አሜን አሜን አሜን🥰🙏
1771Loading...
02
አጭር እውነተኛ ታሪክ 💚🧡❤️💚🧡❤️ አንድ ገበሬ የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉሮሮ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው። ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ። ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ! ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች።  የመጀመርያው ቀንሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ። ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው። በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ። ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች- "በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች። ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ። ፍየል ደስ አላት። "ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮሇች። ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩሇት ነው ብለው ሲያዩ ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው።ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው። እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ። ----------------------------------------------------------------------- አንዱ የሌላው መሰላል ነው። ለአንዱ ሂወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ሂወት የደሀው ችግር ግድ ነው። ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው። አለም የምትመራበት ህግ ነው።    ✍ አጫጫር ጽሁፎች
2462Loading...
03
#ስኬትና ስህተት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ያለስህተት #ስኬት የለም፡፡ ከሰው በላይ ስኬታማ የሆነ ሰው ካያችሁ ከሰው በላይ ስህተት የሰራ ሰው እንደሆነ እወቁ፡፡ 🌴 ለስኬታማ ሰዎች ስህተት ጓደኛቸው ነው፡፡ይውዱታል፡፡ምክንያቱም  አስተማርያቸው ነው፡፡ ወደ ስኬት ከፍታ የሚወጡት በስህተት ላይ ተረማምደው ነው፡፡ ሲሳሳቱ ማህበረሰቡ በሚወረወርባቸው ትችትም አይናደዱም፡፡ ትችቱ እውነት ካለው ይማራሉ፡፡እንቶ ፈንቶ ከሆነም ይተውታል፡፡ ትኩረታቸው #ወደፊት መሄድ ላይ ነው፡፡ ሰዎች የተሰራነው በሙከራ እና በስተት እንድንማር ነው፡፡ 👉#መራመድ ስንማር ብዙ ጊዜ ወድቀናል፡፡ 👉#ማውራት ስንማር ብዙ ጊዜ ተኮላትፈናል፡፡ 👉#መጻፍ ስንማር ብዙ ጊዜ ወረቀቱን አበላሽተናል፡፡ 👉እንጀራ መጋገር ስንማር ቂጣ መሰል እንጀራ ጋግረናል፡፡👉ወጥ መስራት ስንማር ጨው አብዝተናል፡፡ 👉ሳይክል መንዳት ስንማር ብዙ ጊዜ ተላልጠናል፡፡ 👉መኪና መንዳት ስንማር ብዙ ጊዜ ተጋጭተናል፡፡ አሁን በጣም የቻልናቸውን ነገሮች የቻልናቸው  ከስህተት ወደ ስህተት እየሄድን በመማር ነው፡፡ የመጀመርያ ሁለት ሶስት ቢዝነስሽ ከሰረ ቢዝነሱ ከሰረ ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላ ለምትሠርያቸው ቢዝነሶች ትምህርት ይሆንሻል፡፡ተማሪበት፡፡ የመጀመርያ ፍቅረኛሽ ጋር ጥሩ ታሪክ ከሌለሽ አታለቃቅሺ፡፡ይህ የአለም ፍጻሜ አይደለም፡፡ በእርግጥ የህይወትሽ ምርጡ አጋጣሚ ነው፡፡ ለምን? ከዚህ የፍቅር ግንኙነት ተምረሽ ለወደፊት ትዳርሽ ገራሚ ሴት ትሆኛለሽ፡፡ ሰዎች ፊት ስታወሪ ላብ ካሰመጠሽ ለምን ብለሽ አትናደጂ፡፡ሰው ፊት ቆመሽ በራስ መተማመን እያጠመቀሽ ለማውራት ራስሽን አዘጋጂው፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ ምንም ነገር adapt የማድረግ አቅም አለው፡፡ ሰዎች ጨረቃ ላይ ሄደዋል፡፡ ከውቂያኖስ ወለል ውስጥም ደርሰው አይተዋል፡፡ ሙቀትንም ሆነ ብርድን  ሰው የመቋቋም አቅም አለው፡፡የሰው አእምሮ ምንም ነገር መማር ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰው የሚማረው #ስህተት በመስራት እና በማጥፋት ነው፡፡ መጥፎው ነገር ስህተት ስንሰራ ሰው ይተቸናል፡፡ይህ ደግሞ ስሜተ ደካማ ለሆንን ሰዎች ልብ ይሰብራል፡፡በሰው ትችት ልባችን እንዳይሰበር በመፍራት ስህተት መስራት እናቆማለን፡፡መማር እናቆማለን፡፡እንደ ድንጋይም ቆመን እንቀራለን፡፡ከስኬትም ግን እንርቃለን፡፡ስህተት ጥሩ እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ግን ስኬት ላይ ናቸው፡፡ የአለማችን ጠንካራው ሰው david goggins "እሳሳታለሁ---እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ-----እሳሳታለሁ---እሳሳታለሁ---እንድ ቀን #አሸንፋል፡፡ይሳካልኛል፡፡" ብሎ ነበር፡፡ ቸርችልም፡ "ስኬት ከውድቀት ወደ ውድቀት ጉጉት ሳያጡ መጓዝ ነው፡፡" ብሎ ነበር፡፡ የfacebook መስራችና CEO ማርክም "ስህተቶቼን እወዳቸዋለው!" ብሎ ነበር፡፡ ክርትያን ሮናልዶ፡ "የማሸንፈው መሸነፍን ስለማልፈራ ነው!" ይላል፡፡ መብራትን በመፍጠር አለምን ከጨለማ ያወጣው ቶማስ ኤድሰን የተሳካለት ከአስር ሺህ ሙከራ በኋላ ነበር፡፡ ኤድሰን "ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ መብራት የማይፈጠርበትን መንገድ አገኘው እንጂ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጊዜ አልተሳሳትኩም፡፡" ብሏል፡፡ የቅርጫት ኳስ ንጉሱ ማይክል ጆርዳን "የተሳካልኝ ብዙ ጊዜ ስለወደኩኝ ነው፡፡" በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ #ተሳስቶ መማር #ወድቆ መነሳት የስኬታማ ሰዎች ህይወት ነው፡፡የማህበረሰቡን ትችት  አትፍሩ፡፡መቶ ጊዜ ስትወድቁ የሳቀባችሁ  አንድ ቀን ሲሳካላችሁ የኔ ጀግና እያለ ያወድሳችኋል፡፡ #ግፉበት👉👉👉👉▶➡➡➡➡➡🏆 #ልፉበት 👉👉👉👉▶➡➡➡➡➡🏆 Firaw kiya ስኬታማ ቀን ይሁንላችሁ🙏🙏
3013Loading...
04
#ደስተኛህይወት_እንዲኖረን.........! 1👉 #ምስጋና አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገን” በሉ ሲባሉ “ምን ምስጋና የሚገባው ነገር አለና” የሚሉ አሉ፡፡ ግን ብዙ “ተመስገን የሚያስብሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ቆም ብለን ብናስብ በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ 2👉ቀና ማሰብ ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ የእውነት እንደዚያ ካደረግን ለውጡን እናየዋለን፡፡ 3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም “ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ፤ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡ 4. ደግነት ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ወደዚያ ጎራ ብሎ አንድ መልካም ነገር አድርጎ መመለስ ደስታን አጭዶ መመለስ ነው፡፡ 5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት “ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡ 6. ይቅርታ “ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡ 7. የምንወደውን ነገር ማድረግ 8. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡ 9. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ከሲኦል ቢያድነንም ባያድነንም ወደ ቤተ-እምነት መቅረባችን ደስታን ይገዛልናል እንጂ ደስታችንን አይነጥቀንም፡፡ ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግጧል፡፡ 10. ሰውነታችንን መንከባከብ አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ብቻ ሳይሆን የተዋበ ሰውነት እንዲኖረን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ ስፖርት መስራትና በተለያየ መንገድ ጥረት ማረግ አለብን፡፡ 🙏🙏😍😍🙏🙏 firaw kiya
3243Loading...
05
🚺✅ #የስጦታ_ዋጋ ✅🚺 ባል ሚስቱን የስጦታ መሸጫ መደብር ይዟት ይሄዳል። "የኔ ማር እስኪ ለእናቴ ስጦታ የምሰጣት ቆንጆ ስጦታ ምረጪልኝ አላት። እርሷም በውስጧ ስለቀናች በጣም ርካሽ ስጦታ መረጠች። ስጦታውን አስጠቀለለና ባል ወደ እናቱ ጋር እንደሚሄድ ነግሯት ተለያዩ። ማታ ላይ የመረጠችውን ስጦታ ይዞ መጣና ሰጣት። "ስጦታው ለአንቺ ነው። ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈለኩ ግን ምርጫሽን ስላላወኩ ራስሽ እንድትመርጪ አደረኩኝ።"አላት። ሚስት በስራዋ አዘነች። ሌላውን እንደ ራሷ ብትወድ ኖሮ  ስጦታዋ ያማረ ይሆን እንደነበር ተረዳች። መልካምነት ለራስ ነዉ የሚባለው ለዚህ ነው።
4191Loading...
06
🌀✅"#ስኬት_በርግጥም_ልፋትን_ይጠይቃል"✅🌀 ✳ ጉንዳን ካሰበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች፤ትነሳለች ✳ ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች ✳ ወፍ መኖርያ ጎጆዋን ለመሥራት ማልዳ ወጥታ አምሽታ ትገባለች ✳ "ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል" ✳ ተኩላ ያለመውን ለማደን ቦታና አቅጣጫ ቀያይሮ ያደባል ✳ ድመት የተመኘችውን ለማግኘት በትእግስት ትጠባበቃለች ❇ አንበሳ ያቀደውን ለመያዝ በአንክሮ ይከታተላል ❇ "ስኬትና ውጤት ያለ እንቅስቃሴ አይገኝም" ❇ ነብር ካልተወረወረ አይዝም ❇ ሰይፍ ካልተሰነዘረ አይገድልም 🌀✅"#ተንቀሳቀስ_አትተኛ"✅🌀 ✴ለረጅም ጊዜ የተኛ ውሃ ይሸታል ✴በቦታው ለዘመናት የቆየ ድንጋይ አንድ ቀን ይፈለጣል ✴ሽቶ ጫን ጫን ሲሉት ነው ጥሩ እሚሸተው ✴ሠንደል ሲያቃጥሉት ነው አካባቢን የሚያውደው ✴የሰው ልጅም በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም ያለ ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደርስም ✴"ዓለምን እልህ የተጋባ ነው የሚያሸንፋት" ✴ህይወት ሩጫ ናት የስኬት ገበያ ሁሉ ውድድር አለው ✴መጀመሪያ የጨሰ ነው ኋላ ብርሃን የሚወጣው። ✍አጫጫር መጣጥፎች ስኬታማ ቀን🙏🙏
5285Loading...
07
መልካም ቀን🥰🙏
5391Loading...
08
ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው ፡፡ : #በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። #የሰማንያ ዓመት #ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት #በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። : #ምክርን ብትሰማ #በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። #ብልህ ከሆንህ #በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን #በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። : የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። #ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። : ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። #የምትሄድበት እናዳይጠፋህ #የመጣህበትን አትዘንጋ ። : #የአባቶችህን መልካም ሥራ #አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን #ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ #እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ። : ክፋት አይሙቅህ ፣ #መልካም ነገርም #ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ #ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ #የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። : ገንዘብ የሚመልሰው #የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና #ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ። : ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው #አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን #ሴት ሁሉ #የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ። : #እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ። : ሥልጣን ሲሰጥህ #መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። : በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። #ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ። : የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ። : ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! : መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ #በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ። : ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ። : ደጋፊዎች #ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ። : ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ። : ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ። : የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !! : ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። : ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ። : እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። : የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ። : ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። ሰናይ ዕለተ አርብ🙏🙏
6498Loading...
09
#ወዳጄ ♨በወንድምህ ውድቀት አትደሰት ነገ ሌላ ቀን ነው ♨ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና ♨የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ እርሱ ካንተ ጋር ነውና ♨ድሆችን እርዳ ሰደቃ/ምፅዋት ወንጀልን ታብሳለችና ♨ተስፋህ በፈጣሪ ከሆነ መቼም ቢሆን አትወድቅም ♨በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ካጣኸው በኃላ ይቆጭሀልና ♨ባጣኸውም ነገር አትበሳጭ የተሻለውን ፈጣሪ ይሰጥሀልና ♨የበደለህን ይቅር በል አምላክ ይቅር ባዮችን ይወዳልና ♨ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ጌታህን አመስግን እርሱ አመስጋኞችን ይወዳልና ♨ባለህ ነገር አመስግን ፈጣሪ ይጨምርልሀልና ♨ሰዎችን አትመቀኝ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለችና ♨ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነውና ♨አምላክህን አፍቅረው እሱ የእውነተኛ ፍቅር ባለቤት ነውና 🔸ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ ነውና 🔹ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም ውሳኔው የፈጣሪ ነውና 🔸በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አምላክ ከታጋሾች ጋር ነውና 🔹ለሁሉም ነገር አትቸኩል ችኮላ የሸይጧን ነውና ▫አትበሳጭ ብስጭት የሸይጧንን በር ትከፍታለችና 🔸የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ ያስታውስሀልና።     Firaw//78!"
5405Loading...
10
ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ🥰🙏
5011Loading...
11
📍«በሰው ዘንድ አለቀ ተቆረጠ የተባለን ነገር ሁሉ በእምነት ከጠበቅን #ፈጣሪ  የተቆረጠን ነገርን ይቀጥላል!» : 📍እምነት ማለት ማመን መታመን ማለት ነው። ፈጣሪ መኖሩን ዓለምን ያስገኘ አንድ አምላክ መኖሩን ሳናይ ሳንዳስስ ሳንጨብጥ ያለጥርጥር ይደረግልኛል ይሆንልኛል ማለት #ማመን ነው። ፡ 👉ይህን ማመናችንን የምናረጋግጠው ደግሞ በመታመን ብቻ ነው። መታመን ማለት እምነትን በሥራ መግለጥ ማለት ነው። መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ መመጽወት መታመንን ይገልጣሉ። ፡ ↪አንድ ሰው ፈጣሪ ያዘዘውን ካልሠራ ታመነ አይባልም። ፈጣሪ ያስተማረህን እንድትሆን ያዘዘህን ሆነህ መገኘት ካልቻልህ ታማኝ አይደለህም ማለት ነው። ፡ ↪እምነት መታመን ከሌለበት ከንቱ ነው። ዝም ብሎ ጠዋት ማታ ጌታዬ ጌታዬ ማለት ብቻውን አያድንም። ፡ ↪አንድ ዘበኛ ቤት እንዲጠብቅ ተቀጥሮ ሳለ የቀጣሪውን ንብረት ከሰረቀ ታማኝ እንደማይባልና ከሥራ እንደሚባረር ሁሉ እምነታችንም መታመን ከሌለበት ከእምነት ለመውጣት እንገደዳለን። ፡ ↪እምነት የምትታመንበት ነው እንጅ በአፍህ ብቻ አምናለሁ እያልህ የምትቀልድበትና የምታሾፍበት አይደለም። ፡ ↪ለማመንህ መገለጫው መታመንህ ነው። አምንሃለሁ ለምትለው ፈጣሪ ልትገዛ ትእዛዙን ልትጠብቅ ያስፈልጋል። ፡ ➊.አትብላ ሲልህ አለመብላት፣ ፡ ➋.ትስረቅ ሲልህ አለመስረቅ፣ ፡ ➌.አትዋሽ ሲልህ አለመዋሸት፤ ፡ ➍.አመስግነኝ ሲልህ ማመስገን፤ ፡ ➎.ጹም ሲልህ መጾም፣ ፡ ➏.ጸልይ ሲልህ መጸለይ ወዘተ አለብህ የመገዛትህ ወይም የመታመንህ መገለጫ ነውና። : ↪ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምጽዋት የሌለበት እምነት ከንቱ ነው። ለምታምነው አምላክ የመገዛትህን መገለጫ ማቅረብ አለብህ። ፡ ↪ይህ የመታመንህ መገለጫ ደግሞ በዘፈቀደ የሚደረግ ሳይሆን ሥርዓት ሊኖረው ግድ ይላል። ፡ ሰናይ ቀን🙏🙏
6575Loading...
12
📕ያለፍክበት የህይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራስህ ምርጫ ነው፡፡ 📕በህይወትህ የደስታ ምንጭ መሆን ባትችል እንኳን ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትሁን፡፡ 📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡ 📕በምድር ላይ ምንም ፍፁም ነገር የለምና አንተም ፍፁም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍፁም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ሁሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡ 📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡ 📕በህይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡ መልካም ቀን!🙏
6465Loading...
13
ትዕግስት ይኑረን🙏🙏
6451Loading...
14
Media files
10Loading...
15
📙አንብቤ ከወደድኩት ላካፍላቹ👇 ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማንዴላ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ። እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማንዴላ "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም !!! ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናት! ውብ ቀን ተመኘንላችሁ🙏
7856Loading...
16
እንደ አሸናፊ አስብ! ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?! በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው! ሰናይ ቀን😍😍 ✍️ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
6971Loading...
17
እድሎችን አጠብቅ ፍጠራቸው!😍 መልካም 🙏
1 7392Loading...
18
ደፋር ሁን…!! ደፋር መሆን እንኳን ባትችል ደፋር መሆንን አስመስል ፣ልዩነቱን ማንም ሊያውቀው አይችልም‼️😝 መልካም ቀን🙏
7671Loading...
19
#ከድንጋይ_ፈላጩ_ተማር በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው። አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ለመንገስ ትዕግስት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው። ከውጤታማዎቹ የኤን ቢ ኤ ቡድኖች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ሳን አንቶኒዮ ስፐርስ ከማህበራዊ ቀራፂው ከጃኮብ ሪስ ወስዶ በተጨዋቾቹ ሎከር ላይ የሰቀለው አንድ ጥቅስ አለ፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤ ሁሉ ነገር ምንም ለውጥ የማያመጣ በሚመስለኝ ጊዜ ሄጄ የማየው አንድ ድንጋይ ፈላጭ አለ፡፡ ይህ ፈላጭ ድንጋዩን በድንጋይ መፍለጫው መቶ ጊዜ ይመታዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ድካም ውስጥ ግን ምንም የመሰንጠቅ ምልክት ድንጋዩ ላይ አይታይም፡፡ በመቶ አንደኛው ምት ግን ድንጋዩ ለሁለት ይሰነጠቃል፡፡ እኔ ግን ድንጋዩን የሰነጠቀችው 101ኛዋ ምት ብቻዋን ሳትሆን መቶ አንዱም ምቶች በአጠቃላይ ተደማምረው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡” ከልማድ ኃይል መጽሐፍ የተወሰደ
8480Loading...
20
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል🙏🙏 @nikutwld
6410Loading...
21
አይገርምም ጋዜጠኛዋ ቢሊኒየሩን ቃለመጠይቅ እያደረገችለት ነው… የስኬትህ ሚስጥር ምንድነው? ቢሊየነሩ ባዶ ቼክ ለጋዜጠኛዋ አቀበላትና የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊበት አላት! ጋዜጣኛዋ በእንቤታ ቼኩን እየመለሰች «አይ እኔ እንደሱ አይነት ነገር ፈልጌ አይደለም የስኬት ሚስጥሮን መጠየቅ ፈለጊ ነው» አለች። ቢሊየነሩ ድጋሚ ቼኩን መልሶ ሰጣትና «የፈለግሽውን ያህል ገንዘብ ፃፊ» አላት። ጋዜጠኛዋ እንቢ አሻፈረኝ አለች። ቢሊየነሩ ቼኩን እያሳያት «የስኬቴ ሚስጥር አሁን አንቺ ያጋጠመሽን አይነት እድል አሳልፌ አለመስጠቴ ነው…የስኬቴ ሚስጥር ያገኘሁትን እድል ሁሉ መጠቀሜ አሁን አንቺ እንድልሽን ተጠቅመሽ ቢሆን ኖሮ የአለማችን ሃብታሟ ጋዜጣኛ ትሆኚ ነበር… እኔ ሁለቴ እድል እንደሰጠሁሽ አለም ሁለተኛ ዙር እድል አትሰጥሽም አንዴ ያጋጠመሽን እድል መጠቀም የስኬት ሚስጥር ነው ምን ያህሎቻችን በየቀኑ የተሰጡንን እድል እየተጠቀምን ይሆን??? ብዕር🖊 ሰናይ ጊዜ🙏
8333Loading...
22
⭐️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! መልካም በዓል🙏🙏
7173Loading...
23
🎯ፍላጎትና ጥረት ትልቅ ልዩነት አላቸው። ፍላጎት ማለት አንድ ነገር ሲመቻችልህ ማድረግ ነው፤ ጥረት ግን ቢመችህም ባይመችህም ምንም ምክንያት ሳትደረድር ለምትፈልገው ነገር ዋጋ መክፈል ነው። ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን? እንግዲያውስ ዳይ ወደ ጥረታችን! ሰናይ ቀን ተመኘንላችሁ🙏 ✍ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
7723Loading...
24
"ትግስት ይኑርህ አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ቦታ ለመድረስ በመጥፎ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ ይጠበቅብሃል፡፡" መልካም ቀን🙏 ✍ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
7850Loading...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አሜን አሜን አሜን🥰🙏
Показати все...
🙏 9👍 4 1
አጭር እውነተኛ ታሪክ 💚🧡❤️💚🧡❤️ አንድ ገበሬ የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ወደ እንስሳት ሀኪም ጋር ይዞት ይሄዳል። ሀኪሙም ፈረሱ ጉሮሮ ድረስ በመሄድ በሚገባ መረመረው። ለገበሬውም - "ተላላፊ በሽታ ስላለበት ለሶስት ቀን መድሀኒት እንስጠውና ካልተሻለው ወደሌሎቹ ፈረሶች እንዳይዛመት እንገለዋለን" ብሎት ሄደ። ይሄንን ሲያወሩ ፍየል ተደብቃ ሰምታቸው ኖሯል ለፈረሱ እያለቀሰች ያወሩትን ነገረችውና "እንደምንም ብለህ ተነስ! ያለበዛ ይገሉሀል" እያለች ተንሰቀሰቀች።  የመጀመርያው ቀንሀኪሙ መጥቶ መድሀኒቱን ሰጥቶት ወጣ። ወድያው ፍየል ለምለም ሳርና አተላ ይዛለት መጣች ና "እንደምንም ተነስ!" ብላ ተማፀነችው። በሁለተኛውም ቀን ሀኪሙ ሲመጣ ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም መድሀኒቱን ወግቶት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠብቆት ካልተሻለው እንደሚገለው ለገበሬው ነግሮት ሄደ። ይሄን ግዜ ፍየል ለምለም ሳር ፈልጋ ለፈረሱ በማምጣት አፅናናችው። የመጨረሻ ቀን ሀኪሙ ሲመጣ አሁንም ፈረሱ ምንም ለውጥ አላመጣም ይሄን ጊዜ ከገበሬው ጋር ቢገሉት እንደሚሻል በር ላይ ቆመው ሲያወሩ ፍየል ቀስ ብላ ተደብቃ ፈረሱ ጋር ገብታ እየተንሰቀሰቀች- "በናትህ አኔንም ጓደኛ አታሳጣኝ ካልተነሳህ ይገሉሀል" ብላ አለቀሰች። ፈረሱ በፍየሏ ግፊት ቀስ ብሎ ተነሳ። ፍየል ደስ አላት። "ጎበዝ አስኪ እሩጥ" እያለች አበረታችው። ፈረሱ በወኔ በፊት ከሚሮጥበት ፍጥነት በላይ ሮጠ። ይሄን ጊዜ ፍየል በደስታ ጮሇች። ገበሬውና ሀኪሙ የምን ጩሇት ነው ብለው ሲያዩ ያዩትን ማመነን አቃታቸው።ፈረሱ በሓይል አየሮጠ ነው።ገበሬው በደስታ ብዛት ሀኪሙን አንቆ ሳመው። እረኛውን ጠርቶት "ዛሬ እኔ ቤት ትልቅ ድግስ አለ! ስለዚህ ቶሎ በሉ ፍየሏን እረዱልኝ! ምሳ እዚህ ነው" አለ። ----------------------------------------------------------------------- አንዱ የሌላው መሰላል ነው። ለአንዱ ሂወት ለሌላው ሞት ነው። ለሀብታም ሂወት የደሀው ችግር ግድ ነው። ለአንዱ ማለፍ የሌላው ውድቀት ወሳኝ ነው። አለም የምትመራበት ህግ ነው።    ✍ አጫጫር ጽሁፎች
Показати все...
🥰 3👌 2 1
#ስኬትና ስህተት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ያለስህተት #ስኬት የለም፡፡ ከሰው በላይ ስኬታማ የሆነ ሰው ካያችሁ ከሰው በላይ ስህተት የሰራ ሰው እንደሆነ እወቁ፡፡ 🌴 ለስኬታማ ሰዎች ስህተት ጓደኛቸው ነው፡፡ይውዱታል፡፡ምክንያቱም  አስተማርያቸው ነው፡፡ ወደ ስኬት ከፍታ የሚወጡት በስህተት ላይ ተረማምደው ነው፡፡ ሲሳሳቱ ማህበረሰቡ በሚወረወርባቸው ትችትም አይናደዱም፡፡ ትችቱ እውነት ካለው ይማራሉ፡፡እንቶ ፈንቶ ከሆነም ይተውታል፡፡ ትኩረታቸው #ወደፊት መሄድ ላይ ነው፡፡ ሰዎች የተሰራነው በሙከራ እና በስተት እንድንማር ነው፡፡ 👉#መራመድ ስንማር ብዙ ጊዜ ወድቀናል፡፡ 👉#ማውራት ስንማር ብዙ ጊዜ ተኮላትፈናል፡፡ 👉#መጻፍ ስንማር ብዙ ጊዜ ወረቀቱን አበላሽተናል፡፡ 👉እንጀራ መጋገር ስንማር ቂጣ መሰል እንጀራ ጋግረናል፡፡👉ወጥ መስራት ስንማር ጨው አብዝተናል፡፡ 👉ሳይክል መንዳት ስንማር ብዙ ጊዜ ተላልጠናል፡፡ 👉መኪና መንዳት ስንማር ብዙ ጊዜ ተጋጭተናል፡፡ አሁን በጣም የቻልናቸውን ነገሮች የቻልናቸው  ከስህተት ወደ ስህተት እየሄድን በመማር ነው፡፡ የመጀመርያ ሁለት ሶስት ቢዝነስሽ ከሰረ ቢዝነሱ ከሰረ ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላ ለምትሠርያቸው ቢዝነሶች ትምህርት ይሆንሻል፡፡ተማሪበት፡፡ የመጀመርያ ፍቅረኛሽ ጋር ጥሩ ታሪክ ከሌለሽ አታለቃቅሺ፡፡ይህ የአለም ፍጻሜ አይደለም፡፡ በእርግጥ የህይወትሽ ምርጡ አጋጣሚ ነው፡፡ ለምን? ከዚህ የፍቅር ግንኙነት ተምረሽ ለወደፊት ትዳርሽ ገራሚ ሴት ትሆኛለሽ፡፡ ሰዎች ፊት ስታወሪ ላብ ካሰመጠሽ ለምን ብለሽ አትናደጂ፡፡ሰው ፊት ቆመሽ በራስ መተማመን እያጠመቀሽ ለማውራት ራስሽን አዘጋጂው፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ ምንም ነገር adapt የማድረግ አቅም አለው፡፡ ሰዎች ጨረቃ ላይ ሄደዋል፡፡ ከውቂያኖስ ወለል ውስጥም ደርሰው አይተዋል፡፡ ሙቀትንም ሆነ ብርድን  ሰው የመቋቋም አቅም አለው፡፡የሰው አእምሮ ምንም ነገር መማር ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰው የሚማረው #ስህተት በመስራት እና በማጥፋት ነው፡፡ መጥፎው ነገር ስህተት ስንሰራ ሰው ይተቸናል፡፡ይህ ደግሞ ስሜተ ደካማ ለሆንን ሰዎች ልብ ይሰብራል፡፡በሰው ትችት ልባችን እንዳይሰበር በመፍራት ስህተት መስራት እናቆማለን፡፡መማር እናቆማለን፡፡እንደ ድንጋይም ቆመን እንቀራለን፡፡ከስኬትም ግን እንርቃለን፡፡ስህተት ጥሩ እንደሆነ የሚያውቁ ሰዎች ግን ስኬት ላይ ናቸው፡፡ የአለማችን ጠንካራው ሰው david goggins "እሳሳታለሁ---እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ----እሳሳታለሁ-----እሳሳታለሁ---እሳሳታለሁ---እንድ ቀን #አሸንፋል፡፡ይሳካልኛል፡፡" ብሎ ነበር፡፡ ቸርችልም፡ "ስኬት ከውድቀት ወደ ውድቀት ጉጉት ሳያጡ መጓዝ ነው፡፡" ብሎ ነበር፡፡ የfacebook መስራችና CEO ማርክም "ስህተቶቼን እወዳቸዋለው!" ብሎ ነበር፡፡ ክርትያን ሮናልዶ፡ "የማሸንፈው መሸነፍን ስለማልፈራ ነው!" ይላል፡፡ መብራትን በመፍጠር አለምን ከጨለማ ያወጣው ቶማስ ኤድሰን የተሳካለት ከአስር ሺህ ሙከራ በኋላ ነበር፡፡ ኤድሰን "ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ መብራት የማይፈጠርበትን መንገድ አገኘው እንጂ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጊዜ አልተሳሳትኩም፡፡" ብሏል፡፡ የቅርጫት ኳስ ንጉሱ ማይክል ጆርዳን "የተሳካልኝ ብዙ ጊዜ ስለወደኩኝ ነው፡፡" በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ #ተሳስቶ መማር #ወድቆ መነሳት የስኬታማ ሰዎች ህይወት ነው፡፡የማህበረሰቡን ትችት  አትፍሩ፡፡መቶ ጊዜ ስትወድቁ የሳቀባችሁ  አንድ ቀን ሲሳካላችሁ የኔ ጀግና እያለ ያወድሳችኋል፡፡ #ግፉበት👉👉👉👉▶➡➡➡➡➡🏆 #ልፉበት 👉👉👉👉▶➡➡➡➡➡🏆 Firaw kiya ስኬታማ ቀን ይሁንላችሁ🙏🙏
Показати все...
👍 10
#ደስተኛህይወት_እንዲኖረን.........! 1👉 #ምስጋና አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገን” በሉ ሲባሉ “ምን ምስጋና የሚገባው ነገር አለና” የሚሉ አሉ፡፡ ግን ብዙ “ተመስገን የሚያስብሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ቆም ብለን ብናስብ በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ 2👉ቀና ማሰብ ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ የእውነት እንደዚያ ካደረግን ለውጡን እናየዋለን፡፡ 3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም “ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ፤ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡ 4. ደግነት ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ወደዚያ ጎራ ብሎ አንድ መልካም ነገር አድርጎ መመለስ ደስታን አጭዶ መመለስ ነው፡፡ 5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት “ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡ 6. ይቅርታ “ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡ 7. የምንወደውን ነገር ማድረግ 8. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡ 9. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ከሲኦል ቢያድነንም ባያድነንም ወደ ቤተ-እምነት መቅረባችን ደስታን ይገዛልናል እንጂ ደስታችንን አይነጥቀንም፡፡ ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግጧል፡፡ 10. ሰውነታችንን መንከባከብ አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ብቻ ሳይሆን የተዋበ ሰውነት እንዲኖረን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ ስፖርት መስራትና በተለያየ መንገድ ጥረት ማረግ አለብን፡፡ 🙏🙏😍😍🙏🙏 firaw kiya
Показати все...
6👍 3
🚺✅ #የስጦታ_ዋጋ ✅🚺 ባል ሚስቱን የስጦታ መሸጫ መደብር ይዟት ይሄዳል። "የኔ ማር እስኪ ለእናቴ ስጦታ የምሰጣት ቆንጆ ስጦታ ምረጪልኝ አላት። እርሷም በውስጧ ስለቀናች በጣም ርካሽ ስጦታ መረጠች። ስጦታውን አስጠቀለለና ባል ወደ እናቱ ጋር እንደሚሄድ ነግሯት ተለያዩ። ማታ ላይ የመረጠችውን ስጦታ ይዞ መጣና ሰጣት። "ስጦታው ለአንቺ ነው። ሰርፕራይዝ ላደርግሽ ፈለኩ ግን ምርጫሽን ስላላወኩ ራስሽ እንድትመርጪ አደረኩኝ።"አላት። ሚስት በስራዋ አዘነች። ሌላውን እንደ ራሷ ብትወድ ኖሮ  ስጦታዋ ያማረ ይሆን እንደነበር ተረዳች። መልካምነት ለራስ ነዉ የሚባለው ለዚህ ነው።
Показати все...
👍 17👌 1
🌀✅"#ስኬት_በርግጥም_ልፋትን_ይጠይቃል"✅🌀 ✳ ጉንዳን ካሰበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች፤ትነሳለች ✳ ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች ✳ ወፍ መኖርያ ጎጆዋን ለመሥራት ማልዳ ወጥታ አምሽታ ትገባለች ✳ "ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል" ✳ ተኩላ ያለመውን ለማደን ቦታና አቅጣጫ ቀያይሮ ያደባል ✳ ድመት የተመኘችውን ለማግኘት በትእግስት ትጠባበቃለች ❇ አንበሳ ያቀደውን ለመያዝ በአንክሮ ይከታተላል ❇ "ስኬትና ውጤት ያለ እንቅስቃሴ አይገኝም" ❇ ነብር ካልተወረወረ አይዝም ❇ ሰይፍ ካልተሰነዘረ አይገድልም 🌀✅"#ተንቀሳቀስ_አትተኛ"✅🌀 ✴ለረጅም ጊዜ የተኛ ውሃ ይሸታል ✴በቦታው ለዘመናት የቆየ ድንጋይ አንድ ቀን ይፈለጣል ✴ሽቶ ጫን ጫን ሲሉት ነው ጥሩ እሚሸተው ✴ሠንደል ሲያቃጥሉት ነው አካባቢን የሚያውደው ✴የሰው ልጅም በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም ያለ ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደርስም ✴"ዓለምን እልህ የተጋባ ነው የሚያሸንፋት" ✴ህይወት ሩጫ ናት የስኬት ገበያ ሁሉ ውድድር አለው ✴መጀመሪያ የጨሰ ነው ኋላ ብርሃን የሚወጣው። ✍አጫጫር መጣጥፎች ስኬታማ ቀን🙏🙏
Показати все...
👍 12 5🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መልካም ቀን🥰🙏
Показати все...
17
ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው ፡፡ : #በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። #የሰማንያ ዓመት #ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት #በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ። : #ምክርን ብትሰማ #በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። #ብልህ ከሆንህ #በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን #በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ። : የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። #ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ። : ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። #የምትሄድበት እናዳይጠፋህ #የመጣህበትን አትዘንጋ ። : #የአባቶችህን መልካም ሥራ #አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን #ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ #እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ። : ክፋት አይሙቅህ ፣ #መልካም ነገርም #ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ #ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ #የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ። : ገንዘብ የሚመልሰው #የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና #ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ። : ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው #አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን #ሴት ሁሉ #የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ። : #እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ። : ሥልጣን ሲሰጥህ #መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ። : በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። #ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ። : የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ። : ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ! : መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ #በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ። : ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ። : ደጋፊዎች #ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ። : ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ። : ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ። : የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !! : ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ። : ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ። : እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ። : የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ። : ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ። ሰናይ ዕለተ አርብ🙏🙏
Показати все...
👍 12🙏 4👌 4 2

9👍 4🙏 4
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ🥰🙏
Показати все...
👏 12 3