Ethiopian Broadcasting corporation ®
Відкрити в Telegram
Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media. https://telega.io/c/EBC_TV ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!! https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0
Показати більше8 933
Підписники
Немає даних24 години
-97 днів
-2430 днів
Архів дописів
👉1 የእንቅስቃሴ አይነት ሊመጡ ካሉ 8 በሽታዎች እንደሚጠብቅ ያቃሉ።
• የዲመንሽያ (የአእምሮ የመረሳት ሕመም) ተጋላጭነት በ 63% ይቀንሳል፣
• የዓይነት 2 ስኳር በሽታ ተጋላጭነት በ 60% ይቀንሳል፣
• የጉበት ስብ (Fatty liver) በሽታ ተጋላጭነት በ 48% ይቀንሳል፣
• ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ተጋላጭነት በ 44% ይቀንሳል፣
• ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ተጋላጭነት በ 41% ይቀንሳል፣
• በበሽታ መከላከል ሥርዓት ሳቢያ የሚከሰቱ የብግነት (Immune-mediated inflammatory) ሕመሞች ተጋላጭነት በ 39% ይቀንሳል
• የከባድ የልብና የደም ቧንቧ ሕመሞች ተጋላጭነት በ 31% ይቀንሳል፣
• የኤትሪያል ፊብሪሌሽን (የልብ ምት መዛባት) ተጋላጭነት በ 29% ይቀንሳል እና
• በማንኛውም ምክንያት የሚከሰት የሞት ተጋላጭነት በ 46% ይቀንሳል።
በሮዉ ፊትነስ ጤናዎን እና ሰዉነቶን ይጠብቁ ።
በጀሞ 2 በከፈትነዉ አዲሱ ጂማችን ምዝገባ ስለጀመረ ፈጥነዉ ቤተሰብ ይሁኑ
ለበለጠ መረጃ
☎️0929153030 ይደዉሉ
RAW fitness center
ኢሬቻ እና ሀገራዊ ምክክር፡ የዕርቅ እና የሰላም የአዲስ ምዕራፍ ጉዞ
ኢሬቻ! ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር የተሸጋገረ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ፈጣሪን የሚያመሰግንበት፣ ሰላምን የሚያውጅበት፣ ይቅርታን የሚያወርድበት እና አንድነቱን የሚያበስርበት ታላቅ በዓል ነው::
ኢሬቻ የሰው ልጅ ከተፈጥሮና ከፈጣሪው ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ከወንድሙም ጋር የሚያደርገው ታላቅ የሰላም ውል ነው
+5
Toyota Yaris 2006
Transmission automatic
Year 2006
Condition excellent
Price 1,750,000 negotiable
2% commission
Contact: 0911765299
Toyota Yaris 2006
Transmission automatic
Year 2006
Condition excellent
Price 1,750,000 negotiable
2% commission
Contact: 0911765299
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
🎁 MACZO GIVEAWAY ALERT 🎁
Enter code:
🔥 CODE158879 🔥
and claim 200 FREE SPINS instantly! 🎰
👥 Limited to the first 200 users only
⚡ Once they’re gone, they’re gone — no second round!
Redeem now and start spinning immediately!
👉 @maczo_official_global
👉 maczo.co
+1
ስፔን የ23ኛው ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።
በጭማሪው ክፍለ ጊዜ 106ኛው ደቂቃ ላይ ፌራን ቶሬስ ያስቆጠራት ግብ ስፔንን አሸናፊ አድርጋለች።
በዚህም ስፔን ከ16 ዓመታት በኋላ ውድድሩን አሸንፋ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
+2
የሥልጣን መያዣው መንገድ በምርጫ ብቻ መሆን እንዳለበት ሕዝቡ በተግባር አሳይቷል፡- የኢዜማ መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት
**********************
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ከኢቲቪ ወቅታዊ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የድህረ ምርጫ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና የፓርቲያቸውን የቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መሪው በምርጫው ወቅት የታየውን ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ያደነቁ ሲሆን፣ ሕዝቡ በተለያዩ ተግዳሮቶች ሳይበግረው ረጅም ሰዓት ተሰልፎ መምረጡ ከሰላማዊ አማራጭ ውጪ በጠመንጃ ሥልጣን የመያዝ አባዜ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ሙሉ በሙሉ መወገድ እንዳለበት ያሳየበት ግልጽ መልዕክት ነው ብለዋል፡፡
ኢዜማ ወደ ምርጫው የገባው የኢትዮጵያን ተጨባጭ የፖለቲካ ምኅዳር በጥልቀት ገምግሞ መሆኑን የገለጹት አቶ እዮብ፣ ፓርቲው አስቀድሞ ካስቀመጠው ግብ አንጻር የአሁኑ ተሳትፎው ከሞላ ጎደል ስኬታማ እንደነበርና ምርጫ ሲደርስ ብቻ የሚደናገጥ ሳይሆን ራሱን ወዲያውኑ ለቀጣዩ ምርጫ ማዘጋጀት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
ኢዜማ በክልልና በፌደራል ምክር ቤቶች በድምሩ 86 ወንበሮች …https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Ze5JfrcbzrDpg52grMGAj2s7ChAt7tu7BokwRRAQueDYmQ8H5uyuEv6Xm1nqvwbBl
+9
የሴትነት ውለታ ሌላኛው ገጽታ፤ በዱር እንስሳት ጥበቃ ግንባር ላይ ያሉ የኢትዮጵያ እና የዓለም ጀግና ሴት ሬንጀሮች
*************
ከቤት የሚጀምረው ጥልቅ እንክብካቤና የእናትነት ታላቅ ኃላፊነት ወደ ዱር ዘልቆ በመግባት፣ ተፈጥሮንና የዱር እንስሳትን በፅናት በመጠበቅ ረገድ በዓለም ዙሪያ የማይተካ ሚና እያበረከቱ ያሉ ጀግና ሴቶች መገኛ ሆኗል።
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አማካኝነት ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚከበረው "ዓለም አቀፍ ሴት የዱር እንስሳት ጠባቂዎች/ሬንጀሮች ሳምንት" (World Female Ranger Week) እነዚህን ደፋር እንስቶች በደመቀ ሁኔታ ለማክበርና ለማበረታታት የሚውል ታላቅ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ነው።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ የተሰማሩ ሴቶች ቁጥር ከ11 በመቶ በታች ቢሆንም፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በማኅበረሰብ ተሳትፎ እና በሕገ-ወጥ አደን መከላከል ላይ የሚያሳርፉት ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ የዘንድሮው የሳምንቱ መሪ ቃል "ተጽዕኖ" በሚል መመረጡ ተገቢነቱን ያሳያል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ሴቶች በዚህ አስቸጋሪ ተግባር ላይ ከፍተኛ የጀግንነት አሻራ እያበረከቱ የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ የምትሰራውን ፈቲያ ኡስማን…https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0D63fMjgYqpbBbi9rCmndqVaEeJ2oycLQ85tQkshfWivg8MB17i3ruterWmgvAT8xl
ከ55 ኮርሶች 46ቱን 'A+' ያስመዘገበው ባለ ብሩህ አዕምሮው መሐንዲስ
********************
አላምረው ዋጋው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የ2018 ትምህርት ዘመን እጩ ተመራቂ ነው፡፡
አላምረው በዩኒቨርሲቲ ቆይታው 4 ነጥብ (CGPA) በማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲው ልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ይህ ባለ ብሩህ አእምሮ ወጣት ዕጩ ተመራቂ መሐንዲስ ለዚህ ከፍተኛ ክብር ሊበቃ የቻለው በትምህርት ቆይታው ከወሰዳቸው 55 አጠቃላይ ኮርሶች መካከል በ46ቱን 'A+' እንዲሁም በቀሪዎቹ 9 ኮርሶች 'A' በማምጣት ባስመዘገበው ውጤት ነው።
አላምረው ዋጋው ባሳየው በዚህ አስደናቂ የትምህርት አፈጻጸም፣ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ7ኛው ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በልዩ ሁኔታ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ከአዊ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia #EBC #ebcdotstream #Education
+1
ፈረንሳይ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
****************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን አጠቃላይ ምርጫ ይፋዊ ውጤት ማሳወቁን ተከትሎ የፈረንሳይ መንግሥት ለምርጫው ስኬታማነት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የፈረንሳይ መንግሥት በመልዕክቱ አዲስ የተመረጡ የፓርላማ አባላትን፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን እንዲሁም በሂደቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪክ ማኅበራትን ለስኬቱ አድንቋል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ ምርጫውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ላከናወነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፉን ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia #EBC #NEBE #France #EthiopianParliament
+4
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክሩ መሳካት ሁሉም ወገኖች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ
****************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከቀረቡለት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳዮች መካከል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው 8 ዓበይት አጀንዳዎችን መለየቱን አስታውቋል።
እነዚህ አጀንዳዎች በመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚጀምረው ታላቅ ጉባኤ ላይ 130 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብን የሚወክሉ ተሳታፊዎች በሰፊው የሚመክሩባቸው ዋና ዋና ጭብጦች መሆናቸውን ገልጿል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የተመረጡት 8 አጀንዳዎች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተካሄዱ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02manwTgihXyRC5CDjhxV7mMkzhkQ2TEAt6RFt5Li5stYjG48nDUAHqQ5yrz52GVjRl
+3
አጀንዳዎቹ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ እና ፍላጎት የተቀዱ ናቸው፡- ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ
*****************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር) ኮሚሽኑ ላለፉት አራት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ እና በውጭ ሀገር ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን በማማከርና በማወያየት ያሰባሰባቸውን ዋና ዋና አጀንዳዎች ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ሀገራዊ መግባባትና የጋራ ዕድልን በጋራ መበየን በሚያስፈልጋት ታሪካዊ መስቀለኛ መንገድ ላይ የምትገኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ኮሚሽኑ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሕዝብን ተሳትፎ ያረጋገጠና ከታች ወደ ላይ የሚመጣ ስልትን በመከተል አካታችና ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ ስምንት ሀገራዊ አጀንዳዎችን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በዚህ መሠረት የተዘጋጁት ስምንቱ አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0Ajrt8YFPVB14LFsrc8bamSTTU8LbcuoJM6hxM6dpe4am3vEk4BwYo3skavLSAwWYl
