607
Підписники
Немає даних24 години
-57 днів
-1730 днів
Архів дописів
በ 12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ "ምን እንደምማር ግራ ገብቶኛል" ይላል
"የሚከብደኝ ትምህርት አለ ብዬ አላስብም ግን ምን እንደምማር ነው ግራ የገባኝ። አንድ ነገር ለመሆን አልፈለኩም። የሆነ ዘርፍ ላይ እንዳተኩር ያነሳሳኝ ነገር ደግሞ የለም መሰለኝ። ብቻ ገና ውሳኔ ላይ አልደረስኩም"
"ድሮም ይህን እሆናለሁ ብዬ እያሰብኩ አልተማርኩም። ምን እንደምሆን፣ ምን እንደምማር አስቤበትም አላውቅም። ለዚያ ይሆናል አሁን ግራ የገባኝ"
ምናልባት መማሩ በራሱ እያስደሰተው ስለቆየ ትምህርቱ የት እንደሚወስደው ለማሰብያ ጊዜ ነስቶት ይሆን🤔
📌"ቤተሰቦችህ ይሄን ተማር አላሉህም?"
"እነሱ ቀስ ብለህ አስብበትና ትወስናለህ ነው ያሉኝ።"
📌እናቱ ዶ/ር ሔለን በዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ።
"እሱ የሚለን የመጀመርያ ዲግሪዬን በጠቅላላ ሳይንስ ሠርቼ ምን እንድምፈልግ ሳውቅ ብመርጥ ይሻላል ነው። እኛም ቸግሮናል። እሱም ግራ ገብቶታል።"
📌የአሜሪካው ዩኒቨርስቲ ተስፋ ሰጥቶታል። ተጠባባቂ ሳያደርገው አልቀረም። ያ ካልተሳካ ግን አገር ቤት ተመልሶ ለመማር ቁርጠኛ ነው። እሱን የቸገረው ዩኒቨርስቲው መቼ ሆነና። ብሩክን የቸገረው ምን ዘርፍ ማጥናት እንዳለበት መወሰን ላይ ነው።
Via- atc
🔗Share share🔗
JOIN : @Qesem_Academy
JOIN : @Qesem_Academy
