uk
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Відкрити в Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Показати більше
1 677
Підписники
-124 години
-17 днів
-1730 днів
Архів дописів
photo content

ውስጥ አገር የተቀደደ አገር ሲጥፉት ቢጋፋ ድንብርብሩ ድንበር እያደር ባይሰፋ ባቆመችህ ቦታ እግርህን ደግፋ ደረትህን ገልብጠህ ወደልብህ ዙረህ ጥሩአንባህን ንፋ ህዋስ ሳለህ ስውር ኗሪ ደቂቅ ፍጡር ም
ውስጥ አገር የተቀደደ አገር ሲጥፉት ቢጋፋ ድንብርብሩ ድንበር እያደር ባይሰፋ ባቆመችህ ቦታ እግርህን ደግፋ ደረትህን ገልብጠህ ወደልብህ ዙረህ ጥሩአንባህን ንፋ ህዋስ ሳለህ ስውር ኗሪ ደቂቅ ፍጡር ምንነትህ እንኳን ለዓለም ላንተም ምስጢር ዛፍ አይደለህ አትነቀል ወይ መልሰህ አትተከል ከስንቱ ጋር በስንቱ አጀብ ‘ምትታጀብ ከስንቱ ጋር ለስንቱ አጀብ ‘ምታጅብ ስንት ለሊት ስንት መዓልት ስንትስ ዘመን ካለ ትዕይንትህ ‘ምትተውን ‘አገሬ መሬት ነው ወንዝና ተራራ አገሬ ባህል ነው ምግብና ጭፈራ አገሬ ሰዉ ነው ኦሮሞና አማራ’ ከማንም ሳትወግን ማንንም ሳትጠራ ማንንም ሳትፈራ ይቻልህ እንደሆን ከቆምክባት ቦታ አገርህን ስራ ከምትመታው ልብህ አንድ የደም ጠብታ ከመዋደድ ፀጋም ቆንጥረህ በእርጋታ ሰላም አፀድ መሃል ውስጥህ አኑራታ በክብር በሞገስ ሰንደቅህን ተክለህ ከአይምሮ ባርነት ሰዉን ነፃ አውጥተህ ከዓለም ሰመመን ሁሉን ቃል አንቅተህ ባልጠፋ ሸማኔ ባልቸገረ ፈታይ ድሪቶን አትስፋ ኑር እንጂ አብርተህ የተቀደደ አገር ሲጥፉት ቢጋፋ ድንብርብሩ ድንበር እያደር ባይሰፋ ባቆመችህ ቦታ እግርህን ደግፋ ደረትህን ገልብጠህ ወደልብህ ዙረህ መለከትህን ንፋ ‘ማንነህ?’ ሲልህ ያኔ ሰው ሞኙ ወገኔ ስም አማኝ ዘመዴ እኔ ማለት አንተው እራስህ ነኝ ብለህ ንገረው በዘዴ ሰይፈ ተማም 2009

ለባይተዋር ክንፎች (ከቴዎድሮስ ካሳ) አያልቅም ቅዠቱ ደርዝ አለዉ ሌሊቱ ለአንድ ባለቅኔ መኖር ሁለት ነዉ ሁለት ክዋኔ አንድ የፀሀይ ነበልባል የፀሀይ ወጋገን ከተቀመጠበት ደርሳ እንደምትልሰዉ እንደምትዳስሰዉ ረዥም ቀሚሷን እንደሚዳስሳት በነበልባል ቃሉ ቅኔ እያለበሳት ። ፥ ሁለት ጠልፋ ከምስታስቀር የናፍቆት ኩሬ ላይ በመዳፏ ጨልፎ ሁልጊዜ መጠጣት ህመሙን ቢያብሰዉ ወደ ጥልቁ ባህር ጠልቆ እንደገባ ሰዉ የፀሀይን ነጠብጣብ አይችልም መጠጣት ይንጠራራል እንጅ አንድ'ዜ ሊዉጣት ።

ቴዎድሮስ ካሳ ፥ በጥልቀት ወደ ግጥሙ ባህር ያደላል ። በእርሱ ስራዎች ዉስጥ መንፈሳዊ ልዕልናዎች ጎልተዉ ይወጣሉ ። ዉበት ፣ እምነት ፣ እዉነት ፣ ፍቅር እና የፈጣሪ ሁለንታ አፅንኦት ተሰጥቷቸዉ ይ
ቴዎድሮስ ካሳ ፥ በጥልቀት ወደ ግጥሙ ባህር ያደላል ። በእርሱ ስራዎች ዉስጥ መንፈሳዊ ልዕልናዎች ጎልተዉ ይወጣሉ ። ዉበት ፣ እምነት ፣ እዉነት ፣ ፍቅር እና የፈጣሪ ሁለንታ አፅንኦት ተሰጥቷቸዉ ይዳሰሳሉ ። ግጥሞቹ የማንንም ቤት ባይዳስሱ ይወዳል ፥ ይልቁኑ በራሳቸዉ ቁመት የደረሱበትን አሻግረዉ እንዲያዩ ይለቃቸዋል ። ተወልዶ ያደገዉ ደሴ ነዉ ። ግጥም ዉስጥ ጠልቆ የገባዉ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እያለ ነዉ ። ዩኒቨርሲቲዉ ሳይኾን እድሜየ ነዉ እሳት ዉስጥ የገባዉ ባይ ነዉ ። አዲስአበባ ከመጣ በኃላም በብዙ መዉጣት ባይፈልግም በ ግጥማዊት ቅዳሜ ( poetic Saturday ) @poeticsaturday አንዳንድ ስራዎቹን አቅርቧል ። አሁን ላይ አዲስ የግጥም ቤት ለመስራት እየሰራ ይገኛል ። ስራዎቹን በፌስቡክ ገፁ ( ቴዎድሮስ ካሳ ) ላይ መከታተል ይቻላል ።

Agar (By Liyou Libsekal) I remember a yellow scarf fashioned every which way and beautiful bones that peaked at the cheeks. Mounted proud “young mother” in eyes mourning a daughter left behind Families don’t speak of shame and hindsight lives in layers. She was pieces of you strolling tall, slender and curved but you were with me as she cocooned and rolled and stretched. Always in a flowered dress, always drenched in fate you sit, a lakeside lullaby a picture of youth then, and forever and forever I gnaw on whether you knew near the end but with age as authority, we lived in darkness why expect more in death? My anger lives in layers un-abandoned, if only for my sake. https://www.ethiobeauty.com/article/ethiopian-poet-liyou-libsekal-wins-the-2014-african-poetry-prize

Meet the Amazing Ethiopian Poet, Liyou Libsekal. Liyou's poetry explores themes of home, identity and displacement. Liyou's c
Meet the Amazing Ethiopian Poet, Liyou Libsekal. Liyou's poetry explores themes of home, identity and displacement. Liyou's chapbook, Bearing Heavy Things, is included in the African Poetry Book Fund's New Generation African Poets series. Her work has been included in Missing Slate Magazine, Badilisha Poetry and Cordite Poetry Review. Libsekal is winner of the 2014 Brunel University African Poetry Prize. (https://en.wikipedia.org/wiki/Liyou_Libsekal) Known for her incredibly powerful poetry and social activism, Liyou Libsekal has made a profound impact on people through her inclusive writing. Libsekal is a contemporary African poet who spent her early years traveling around East Africa with her family, before moving to the states to attend George Washington University. This period in her life is when she discovered her love for writing, and channeled much of her observations and frustrations about the sharp contrasts between Africans and Americans into her poetry. https://beyondthesinglestory.wordpress.co

If you are interested, please let us know who you are, what project you are working on and how long you would like to use the
If you are interested, please let us know who you are, what project you are working on and how long you would like to use the space. You can DM us on Facebook/Instagram (@zellancreatives) with your links or email us on info@zellan.art We will let you know the availability upon scheduling. Please be aware that we expect everyone to respect WHO recommendations on preventing the spread of COVID-19. ዘላን የፈጠራ እና የባህል ማዕከል የልምምድ ቦታ ለሚፈልጉ ሙዚቀኞች፣ ለሰዓሊዎች ክፍል/ ግቢ እንዲሁም ለአዳዲ ስራዎች አምሮአቸውን ለሚያዘጋጁ የፈጠራ ባለሙያዎች ቦታውን በነፃ እንዲጠቀሙበት ይጋብዛል። ፍላጎት ካሎት ማንነትዎን፣ የሚሰሩበትን የስራ ዕቅድ እና ቦታውን ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም እንደሚፈልጉ ማህበራዊ ገፆቻችንን እና info@zellan.art በመጠቀም መልዕልት ይላኩልን። ክፍት የሆኑ ቀኖችን እናሳውቆታለን። የዓለም የጤና ድርጅት ያወጣውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረጎን አይዘንጉ::

መስከረም አይሆን ፀደይ ከሌለው አደይ፣ ሰኔም ካለዝናብ ሰኔ ነው አትበይ ፣ እኔም አንቺን ላፍታ ያጣው እንደሆን፣ ቀኑም ቀን አይሆንም እኔም እኔ አልሆን። Anchihoye One of Ethiopias
መስከረም አይሆን ፀደይ ከሌለው አደይ፣ ሰኔም ካለዝናብ ሰኔ ነው አትበይ ፣ እኔም አንቺን ላፍታ ያጣው እንደሆን፣ ቀኑም ቀን አይሆንም እኔም እኔ አልሆን። Anchihoye One of Ethiopias only Music Scale Mixed with Reggae Track number 2 from the Book Selamta New Sound! #rasjanyethiopia #Anchihoye #reggae #awtar #loveformusic

Rebel Edition ከTsenatMagazine_Rebel2020 Stay safe out there, better yet stay home 🖤 @KeTsenatMagazine

". . . ፎጋሪና ፎካሪስ መሃልስ አንድ ፊደል ነው ልዩነት የሚያመመጣው ሁለቱም ግን ለወግ ነው ትልቅነት የጎደለው ውሃ ውስጥ መስመጥ ባይቻልም ያንሳፍፋልም እንጂ አገር አያቋርጥም እውነት አልዋጥ ያ
". . . ፎጋሪና ፎካሪስ መሃልስ አንድ ፊደል ነው ልዩነት የሚያመመጣው ሁለቱም ግን ለወግ ነው ትልቅነት የጎደለው ውሃ ውስጥ መስመጥ ባይቻልም ያንሳፍፋልም እንጂ አገር አያቋርጥም እውነት አልዋጥ ያለው ትውልድስ ምን ላይ ያተኩራል. . . . . . የዛሬ ሰው ሲጠማውስ ቁምነገሩም በልኩ ፊትለፊት 'ሚናገር 'ሚያወጣውስ ከልቡ ልብ መርጫለሁ እኔም ይቅርብኝም ስኬት ከመቶ አጨብጫቢም አንድ ወዳጅን በልክ. . . " ፓምፋሎን

"Let's take a trip but not of the physical Sense of direction on a kid who's artistical Through a gallery of thoughts, of cou
"Let's take a trip but not of the physical Sense of direction on a kid who's artistical Through a gallery of thoughts, of course it's dope Pay it tough like the name on my rope Watch it be weary instead of steppin' wit the boys A musical massacre of inadequate noise By the new authority 'cause of majority Of peers who hear will award superiority To those who know you knew now it's inevitable I laid the track and it's simple unforgettable..." The D.O.C. - "Portrait of a Masterpiece" (Verse 1)

Black church services, murderers, Arabs serving burgers As cats with gold permanents, move they bags as herbalists The dirt i
Black church services, murderers, Arabs serving burgers As cats with gold permanents, move they bags as herbalists The dirt isn’t just fertile, it’s people working and earning this The curb getters go where the cash flow and the current is It’s so hot that niggas burn to live The furnace is, where the money moving, the determined live We talk shit, play lotto, and buy German beers It’s so black packed with action that’s affirmative The corners Common

ጌትዬ በማርያም - 1 "ጌትዬ በማርያም!" አለችኝ የደረቀ ስንጥቅ እጇን - ወዳይኔ ጫፍ ሰንዝራ የተዝረከረከ ያ ቆንጅዬ ልጇን በእጆቿ ጠፍራ ''ጌትዬ'' አለችኝ አንዱን ምስኪን ባርያ መንገድ የጠፋበት መሄጃውን 'ማያቅ ሰው አገኘሁ ብላ የሚያበራ ድቅድቅ መች አወቀች እሷ የስልኬን ውስጥ ድብቅ እየተከተለች ትለምነኛለች ይቺ የኔው ቢጤ መንገድ ያከነፈኝ ሁል ጊዜ መጤ መንፈግ ያስኮፈሰኝ - ጌታ የጠማው ለት የሆንኩኝ ኮምጣጤ እኔ ደባብቄው አፍኜው እያለሁ ሁሉንም በውስጤ በእናትየው ስም ለምና - በልጅየው ስም ጠራችኝ ''ጌትዬ በማርያም በማርያም'' አለችኝ ማርያምና ልጇ ማናለ ቢራሩ ለሷ እንድደርስላት ለኔ ቢለመኑ ? 'ማርያም ትስጥልኝ' ልበላት ወይስ ልጇን ልጥራ አላህ ይስጥሽ ልበል ወይስ ኪሴን ላጥራ ጌታ ተብላለች ልቤ እንዴት አትፈራ ይች የምርያም ወዳጅ እኔን ጌታ ብላ ጌትዬዋ ሆንኩኝ ባስረገዛት ወንዱ የበላይዋ ሆንኩኝ ጠቦባት መንገዱ እኔስ ጨልሞብኝ ጠፍቶብኛል ገዱ አለብኝ ቀጠሮ በ'ለት ሃያ አንዱ የምድሩን ህግ የናቀ የሳምዩን ላያከብር እንደ ክቡር ዳኛው ልንገራት እንደምን መጥሪያ ተቀብዬ እንደምሄድ ችሎት እንዳለብኝ እስር መንገዴን ሰርዤ ከኮንትራት ታክሲ በሚኒባስ ልግባ እንድሰጣት ሳንቲ ወይስ ሚኒባሱ ይቅርና ከቶ በባሱ ታጭቄ ልስጣት አንድ መቶ በእግር ብጓዘው አልደርስም ከችሎት ወይ ጌትዬ መባል ጌታው የረሳን ለት!

የዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ " ሰበዝ " የተሰኘው ዐዲሱ መጽሐፍ በሳምንት ውስጥ ስድሳ ሺህ ቅጂ ታትሞ ነው ለንባብ ገበያ የቀረበው :: ጃዕፈር መጻሕፍት :: ለቴሌግራም - @jafbok ለዌብሳይታችን -
የዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ " ሰበዝ " የተሰኘው ዐዲሱ መጽሐፍ በሳምንት ውስጥ ስድሳ ሺህ ቅጂ ታትሞ ነው ለንባብ ገበያ የቀረበው :: ጃዕፈር መጻሕፍት :: ለቴሌግራም - @jafbok ለዌብሳይታችን - www.jaferbooks.com መገኛችን :- ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያው አጠገብ ተወልደ ሕንጻ ስር ::

We are happy to announce that you can now find all our previous articles and magazine issues on our website www.getzmag.com
We are happy to announce that you can now find all our previous articles and magazine issues on our website www.getzmag.com

አበቦቹ ተናንሽ አበቦች የፍካት ጨረሮች የብራ አለም ሰዎች የንጹህ አገር ዜጎች ለሃሴት አፎቱ ለፍቅርም ቤቱ ውበት ምልክቱ . . . ትናንሽ አበቦች. . . እንደጽገሬዳ የልብ ነጋሪ እንደ አደይ አበባ ብሩህ ቀን አብሳሪ ውስጠትን ሰርሳሪ በውበት አሳሪ. . . እነዚን አበቦች ለጌጥነት ያጨ እነዚን አበቦች ለጌትነት ያጨ ምንጩን አደረቀ ነገውንም ቀጨ (ለልጆቻችን. . .) #seifetemam @seifetemam

Join the conversation this evening! Power of Art: Performance and Collaborative Expressions Event Format: Online (Zoom) Event
+1
Join the conversation this evening! Power of Art: Performance and Collaborative Expressions Event Format: Online (Zoom) Event Date: 11 June 2020 at 6:00pm Hosted by Goethe-Institut Addis Abeba Event Link: https://bit.ly/2Ap8RaM Part of Tibeb Online Make sure to download and enjoy the June 2020 edition of LinkUp Addis digital magazine: https://bit.ly/2Mg68CO #linkupaddis #eventsinAddis #EthiopianCulture

'ርቀት 'ራቀኝ - በሰይፈ ተማም.aac1.24 MB

ገጣሚ ሲሞሸር ፍቅርን ፍቅር ይዞት. . . የሰማያት ምንጣፍ ከንጻትም ላቀ ሁሉ ብሩህ ሆነ ጌትየው ታወቀ ለሰው ተገለጸ ቃል ሰውን ታጠቀ ስጋም ወግ ደረሰው በአምላክ ተጠለቀ ሰውን አጠለቀ ሰውን አመጠቀ ፍቅርን ፍቅር ይዞት እዩት ሲነፋረቅ ግረፉኝ ስቀሉኝ እያለ ሲማቅቅ ከቅዱስ ማደሪያው ሳይለይ ለአፍታ ማጥንቱ ሲያደምቀው ሲገለጥ በማታ እንደ ብርሃን ፈለግ መታየት ሲጀምር እንዳዘቀዘቀች እንደ ማታ ጀምበር ከድርደራው መሃል እንዳልተነካ አውታር ከማለዳው በፊት እንደሰሙት አዛን ኅያሉ ተገልጾ ለታናሾች ታየ ተሰማ በጆሮ ውብ ዜማው ተለየ በሙዚቃ - ሰረገላ - አረገ - መጠቀ ከመንፈሱ መዳፍ ውበት ተጨመቀ ከውበት ጭማቂም ጥበብ ተጠመቀ ውሃው ወይን ሆነ አየሩ ታወደ መውደድም እራሱ መውደድን ወደደ ከድርደራው መሃል እንዳልተነካ አውታር እንዳዘቀዘቀች እንደ ማታ ጀምበር ከአይን ሲገባ መታየት ሲጀምር ግጥም ተጫጫሰ ገጣሚ ሲሞሸር ሰይፈ ተማም 2012