uk
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Відкрити в Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Показати більше
1 719
Підписники
-224 години
-77 днів
-1830 день
Архів дописів

Repost from LinkUp Addis
The 11th edition of Gitem Sitem Open Mic Circle is happening at Shifta on 02 February 2022. The event will feature several ta
The 11th edition of Gitem Sitem Open Mic Circle is happening at Shifta on 02 February 2022. The event will feature several talented poets and artists. Doors will open at 6:00pm and show starts at 6:30pm. Entrance fee is ETB 50. Have you tried our brand new app: https://bit.ly/3Fqrpno @linkupaddis

👨‍👩‍👧‍👧 ሰላም ውድ ቤተሰቦች እንደቃላችን መሰረት እንደ ጅምር ቅምሻ "ሀቅ" የተሰኝ የሙዚቃ አልበም ይዘንላችሁ ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። በቅርቡ ይጠብቁን 2014/2022 #newal
👨‍👩‍👧‍👧 ሰላም ውድ ቤተሰቦች እንደቃላችን መሰረት እንደ ጅምር ቅምሻ "ሀቅ" የተሰኝ የሙዚቃ አልበም ይዘንላችሁ ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። በቅርቡ ይጠብቁን 2014/2022 #newalbumalert #newethiopianhiphopalbum #fyp #AtniHAQ #OmmieHaq #HAQmusic #comingsoon #alert @Haqcrew

ስጠኝ ትራጀዲ [ፀሎት ለትራጀዲው ጌታ] -------------------------------- አምላክ ሆይ ፀሎት ነው ስማ ከልጅህ ዘንድ ብርቱ ልመና ስጠኝ ትራጀዲ ስጠኝ ማጣት መቸገር መች ትቶኝ ሄዶስ
ስጠኝ ትራጀዲ [ፀሎት ለትራጀዲው ጌታ] -------------------------------- አምላክ ሆይ ፀሎት ነው ስማ ከልጅህ ዘንድ ብርቱ ልመና ስጠኝ ትራጀዲ ስጠኝ ማጣት መቸገር መች ትቶኝ ሄዶስ ቀድሞ ነገር እንዲሁ ነው ነገሩን የፍራቻ የሥጋቴን ስጠኝ ትራጀዲ ለጥበብ ግብአት ይሁነኝ ''ደክሞኛል መኖር ላለመሞት በህይወት ከርሞ ለመቆየት ፈቅ እማይል ከ ፈቀቅታ ሠርክ ሮሮ ሁሌ ዋይታ" እያልኩ:- ፈፅሞ አላማርርህም ይሁነኝ ትራጀዲ ለጥበብ ስንቅ ኑሮ'ንዲህ ነው ለገጣሚ የሚናፈቅ በምቾት ውስጥ የታል ጥበብ የታል ግጥም? ሁሉ ነገር አንድ ቀለም ለትየባ ምን ሊጠቅም? ምን ረብ አለ እማግኘት ውስጥ? ከሀብት ወዲያ ወደየት ለውጥ? ሁሉ ቆመ ጥበብ የታል ከሉክ ደረት ምን ይውላል የደላው ግን ግጥም ያውቃል? ለሙት መታሠቢያ ሚፃፍግጥም ጥበብ ሊባል ይቻለዋል? ኤድያ ቲሽ ማግኘት ቢላሽ ግን እንጃልኝ ፤ ግን እንጃልን ሀሳብ ያልቃል የደላኝ ቀን አምላኬ ሆይ አደራህን ጣለው ከህይወቴ አሽቀንጥረህ ወዲያ በልልኝ ምቾት ብሎ ነገር ችግሬ አርምሞን ያምጣ አስቦ በማስፈር ልመር ልግጠም የት-አባቱ ይህ ነው የኔ ጊዜ ፅፌ ሳረቅ የለፋሁት አድማጭ ሳገኝ የደም-ወዜ ችግር ማጣት ምን ቢጠላ ለገጣሚ መልኩ ሌላ አቆይልኝ ድህነቴን ልግጠምበት ደስ ይለኛል ድሎት ክፉ ከመክሊቴ ያርቀኛል ምቾት ክፉ ይነጥቀኛል አቦ [ልግጠም] ይሻለኛል︎! ። © ዘር:ታዬ

ነፋስማ ገፍቶሽ ነበር - ከአውሎ ጋር ተመሳጥሮ እየታጠፍሽ እረታሽው - ሰገደልሽ ተሽከርክሮ አወይ አንቺ! ሞትን በዳንስ የምትረቺ። ©️ ሠይፈ ወርቅ

This is my first release, wanted to do it right here. Hope you enjoy! 💙
This is my first release, wanted to do it right here. Hope you enjoy! 💙

Watch "ግጥም-ሲጥም @10" on YouTube https://youtu.be/o21Lli_Q8lQ

with thoughts of his and hers, they all think, they all dread, who to glory and who will lose their head. Their Eyes slow in blinking, single sweat from their faces and their Shields connecting, With the song of my steel, helms are worn and hoorah is roared. HOORAH!! HOORAH!! Men once still now hastily moving . Take all and show no mercy, for king and country, cleave and burry. Here, here, for king and country show no fear, make way my entry, go and make all mine. To the gods do look up and from your heels do spring, long live this life, long live the king. ©️OKEANOS Art by Brenda Erickson #Art_to_Earth #ጥበብ_ለምድር @gitemsitem @tibeb_be_adebabay_2021

SEIGE Down on one knee I grab the earth below The Land of the free Me, the invader, Shining in armor Steel mesh and Helm unde
SEIGE Down on one knee I grab the earth below The Land of the free Me, the invader, Shining in armor Steel mesh and Helm under my arm Sword on my hip For i came to do harm. My eyes in the sun light I hear the noise behind Of men ready for a fight. a touch on my shoulder I Turned my eyes To a field in smolder. Loud sound to my left My captain of wars Right wing man I kept. "It is time my king" Time to plunder and kill death and fire to bring. "Aye" I replied With A look of bravery From my soul I lied. I reach for my helm Red feathers and steel From the devil's realm. I turn to my men... Lined up and waiting "Do it" I said To my captain nodding. A roar he let out Sounds quickly followed From the lions snout. The men now heed I mount my friend My steed of stampede. I draw my father's razor Sharp as pythons fangs Old, man flesh grazer. Go home the coward Leave my place of war anywhere but forward for my war drums are now blowing. the loud thunderous roar of my nations blood flowing.

photo content

ገጣሚዎቻችን ቅዳሜ እና እሁድ በለባዊ ተገኝተው ይነሻሸጣሉ የታዳሚውንም የግጥም ችሎታ ይፈትናሉ
ገጣሚዎቻችን ቅዳሜ እና እሁድ በለባዊ ተገኝተው ይነሻሸጣሉ የታዳሚውንም የግጥም ችሎታ ይፈትናሉ

The Arts Mailing List newsletter – 17th Jan 2022 is out now!!!!! https://bit.ly/3qupGIC The place for Ethiopian creatives to
The Arts Mailing List newsletter – 17th Jan 2022 is out now!!!!! https://bit.ly/3qupGIC The place for Ethiopian creatives to find opportunities and apply This week we are featuring the fascinating work of Biniyam Kassahun https://www.instagram.com/biniyam_almaz/ @artsmailinglist

---ምንታዌ--- (ሁለታዊነት) በአእምሮ:ሳይንስ:በስነ ልቦና: በአውደ :ናሙና: ምስጢሩ:ሲጠና: ባንዱ:የሚያስጨነቅ:ባንዱ:የሚያዝናና: ባንዱ:እያስፈቀረ:ባንዱ:የሚያጣላ: የሰው:ልጅ:ባህሪ:ሁለት:ነው:
---ምንታዌ--- (ሁለታዊነት) በአእምሮ:ሳይንስ:በስነ ልቦና: በአውደ :ናሙና: ምስጢሩ:ሲጠና: ባንዱ:የሚያስጨነቅ:ባንዱ:የሚያዝናና: ባንዱ:እያስፈቀረ:ባንዱ:የሚያጣላ: የሰው:ልጅ:ባህሪ:ሁለት:ነው:እንጂ: አይደለም:ነጠላ !! ©️ዳዊት ጥኡማይ 20/2/2014 E.c (Carl Jung)

ይሰለቻል ከአፍንጫዬ ጠርዝ ላይ የደረቀ ንፍጥ መቅረፌ ለሰው ይቀፍፋል እንዴ ጉድፌን ከሰው መግደፌ? ልቤን ሲመታ ማድመጤ ብሶብኝ በመደንገጤ ከምት ላላመልጥ ድባቴ ከሞት አምልጬ መሞቴ ኧረ ሰለቸኝ እቴ ዓይኔም ከቂጥ ጋር ሲፎካከር ዓይን አር ይዞ ሲዞር ሰውን ያስከፋል ይሆን? ታከተኝ ለሰው መጠንቀቅ ሰለቸኝ እራሴን መንጠቅ ባይተነፈስስ ቢቀር ተብሎ አይተው ዓየር ነጻ ፈቃድ ከተሰጠኝ ምነው ዋጋ የሚያስከፍል የፈቀድኩትም ሲፈቅደኝ የቀፈፍኩትም ሳይቀርፈኝ . . . የሚበላኝን ጫጫታ ላይዳብስ ለማያክልኝ የገባሁበት ኤጭታ መኖሬ ነጸብራቅ እንጂ እያጣ የመኖር ኖታ ቅኝት የሳተ ድም ድም ድንብር የሳተ ዝም ዝም ይሄንን ይሆን ያለችው ሸዋ ስ'ተርት 'ግም ለግም'? ሁሉ ተሳካ እንኳ ቢባል ይሰለቻል ትግል ሲግል ከማሸነፍ ለማይዘልል ከዛስ? ቀጣዩ ትንፋሽ እስኪሳብ ህይወት ቅጽበቷ ሲሳብ ለግብ የገባ ግብግብ ሞት ለማይጠግብ ሳንባ ሳብ ዓየር ና ከእኔ ግባ ምታ ልብ በምትህ አንባ አምባ ሂድ ከኑሮ ደባ ከዛስ? ሰው አሸን ሆኖ በዙሪያህ ውስጡን ሊሸሸው ሲያሻው ደስታውን ካንተ ሲያስስ ከአፍንጫህ ጠርዝ ላይ ንፍጥህን ይነቅፋል እንደ ዓይንህ ጉድፍ . . . ይሰለቻል! አቻ መቆያ ፍለጋ በእድፍ መግፈፊያ መዳፌ መሃላዎች አስደግፌ ሳድል ማረጋገጫ ስንቱን እየረገጥኩኝ ስንቱን ማምለጤን እንጃ እሺ ቢረጋገጥስ እርግጥ ቢል ነገር ሁሉ አይሰለች ይሆን መተንፈስ ስንት ንጋቶች ናቸው አዲስ ቀናት የሚባሉ? ይሰለቻል መጠየቅ ያስጠይቃል ደሞ መልሱ ልብ ለምን ይመታል መውደድ በሆነ ጓዙ . . . ኧረ ምንድነው እሱ? እሺ ሁሉም ተመለሰ . . . ግን ከዛስ? መታመምን የለመደ ምን ይውጣል ሳግ ከሄደ? ለሰው የሚበጅ መንገድ አንድ ፍሬ ቃል ላይፈልቀኝ ምን ይጠቀማል ማንስ የግሉ አድርጎ ቢፈቅደኝ ምን ልሰራለት ይህ ዓየር ዝምብሎ 'ሚተነፈሰኝ ለእናቴስ ምን ላ'ረግላት ከህመም የተነጠለ ያለኝ ይመስል በረከት አሳምሜያት ምድር ድረስ ዓየር ስቤ እስከማለቅስ ልቧን በጥያቄ አውልቄ መውደጃ ማቄን አጥልቄ አድጌም የሷው ሰቀቀን በአፌ አትሜ ደግነቷን ያልተባረኩ ስሜ ልቧን መታመምን የለመደ ምን ይውጣል ሳግ ከሄደ? . . .አቦ ስሰለች! ©️ ሰይፈ ተማም

Watch "Aman - Teywa Official Video from Studio 30 Vol 1 Album" on YouTube https://youtu.be/DuUBXEHEmFw

ከፍላጎቴ በላይ ምን ጠላት አለኝ ? ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ ? . (ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ። ) . ስስ ነኝ ፤ በእቅፍሽ ባይሆንልኝ_ ምናለ በፀሎትሽ ብታስቢኝ ደረቅ ነሽ፤ ከአብሮነታችን_ ብቸኝነቱ ነው የሚያድንሽ ? . በአለም ካሉ ጠጣሮች እንደ ሰው ልብ አላየሁ አስቸገርኩ አይደል ወድጄሽ ? አስቸገርኩ አይደል ጠርቼሽ ? ................ድባቴሽን ቀምቼሸ ? ................ሰቆቃሽን ቀምቼሽ? ...............ብቸኝነትሽን ቀምቼሽ ? አስቸገርኩኝ አይደል ? . (ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ !) . . . እኔማ _ ሴጣኔም ለምዶኝ ህመሜም ለምዶኝ ሰማይ ሜዳው ለምዶኝ እንዴት 'መሰሌ' ሰው ጋር ተገፋፋው፣ ብዬ አንጂ የእውነት ሰለቸኝ ወደ የትም የማይሄድ ዝምድና መጎተት .. . . ምናልባት ምናልባት የመንገዱ መብዛት ይሆናል እንዳንገናኝ ያረገን የአማራጭሽ መብዛቱ ይሆናል አማራጭ ያሳጣሽ . (ይኸው ራሴን መሰድኩብሽ።) . .. ድሮም ከፍላጎቴ በላይ ምን ጠላት አለኝ ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ . (ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ )

photo content