uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку 👈

Abdu Book Center

Abdu Book Center

Відкрити в Telegram

በመጻሕፍት መደብራችን ፡ የታሪክ መጻሕፍት የትምህርት አጋዥ እና መማሪያ መጻሕፍት የተለያዩ ልበ-ወለድ እና መንፈሳዊ መጻሕፍት ቆየት ያሉና አዳዲስ መጻሕፍት ሌሎችም.. አድራሻችን=አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ አባቢያ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ለበለጠ መረጃ በ0929574133 ደዉልሉን @Abduseller

Показати більше
2 003
Підписники
+424 години
+87 днів
+2330 днів
Архів дописів
📚#አይ_ምፅዋ 📖 #ኤርትራን_ከኢትዮጵያ_የነጠለ_ጦርነት ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙኀን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለውም። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ሕዝቧ ት
📚#አይ_ምፅዋ 📖 #ኤርትራን_ከኢትዮጵያ_የነጠለ_ጦርነት ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙኀን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለውም። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነው። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙውን ጊዜ ወረራ ፈጽመውብን በተደጋጋሚ ያሳፈርናቸውና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባውያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተው ይፈነጥዛሉ። ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነውንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየውን የባህር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባህር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህም ደግሞ የሞት ሞት ነው። ​ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቂያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናው ሕዝቧ ሕዝባዊ የባህር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘለዓለም አይኖርም። ጊዜውን ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላቱን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የፀና ነው።» 👏ብ/ጄኔራል ተሾመ ተሰማ ​ከውስጥ ገጽ የተወሰደ

ከመጽሐፉ የተወሰደ ✍️​ኢብራሂም አወል ሀገራዊ የኤ.አይ ባለቤትነት (Sovereign AI) እና የቋንቋ ጥበቃ ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም። ቋንቋዎቻችን እና ባህሎቻችን በዲጂታል ዘመን ህያው
ከመጽሐፉ የተወሰደ ✍️​ኢብራሂም አወል ሀገራዊ የኤ.አይ ባለቤትነት (Sovereign AI) እና የቋንቋ ጥበቃ ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም። ቋንቋዎቻችን እና ባህሎቻችን በዲጂታል ዘመን ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ፣ ቴክኖሎጂውን የራሳችን ማድረግ ግዴታ ነው። የውጭ ቴክኖሎጂዎችን ዝም ብሎ ተጠቃሚ ከመሆን በመውጣት፣ የራሳችንን የመረጃ ካዝና በራሳችን ባለሙያዎች ገንብተን ትውልዳዊ እና ሀገራዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ማሳየት ይገባናል። ይህ ሂደት ውስብስብ እና ረጅም ቢሆንም፣ ዲጂታል ነፃነታችንን ለማረጋገጥ እና ባህላዊ ማንነታችንን ከዲጂታል መጥፋት ለመታደግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ነው። ​"የAIን ውስብስብ ጽንሰ ሐሳቦች በቀላል አማርኛ በማቅረብ ትልቅ ክፍተት የሞላ መጽሐፍ ነው። ኢብራሂም ቴክኖሎጂውን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያደረገውን ጥረት እያደነቅሁ፣ በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያለ አንባቢ ሊኖረው የሚገባውን መሠረታዊ እና አስፈላጊ የAI ዕውቀት የሚያስጨብጥ ምርጥ ሥራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።" ​ሶስና ጋሻው (ረዳት ፕሮፌሰር) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የአዳም ረታ መዝሙረ ሄላም መጽሐፍ በመደብራችን ያገኙታል።
የአዳም ረታ መዝሙረ ሄላም መጽሐፍ በመደብራችን ያገኙታል።

#ደንበኛሎጂ ​#ከልምድ_ወደ_ልኅቀት ​ደንበኞች የማንኛውም ሥራ መሠረት ናቸው። ግን ልብ የሚነካ አገልግሎት መስጠት ብቻ በቂ አይደለም – ሥርዓት፣ ባለሙያ፣ ክህሎት፣ አሰራር እና ጥልቅ ግንዛቤን ይጠ
#ደንበኛሎጂ ​#ከልምድ_ወደ_ልኅቀት ​ደንበኞች የማንኛውም ሥራ መሠረት ናቸው። ግን ልብ የሚነካ አገልግሎት መስጠት ብቻ በቂ አይደለም – ሥርዓት፣ ባለሙያ፣ ክህሎት፣ አሰራር እና ጥልቅ ግንዛቤን ይጠይቃል። ይህ መጽሐፍ በዘርፉ ከረጅም ዓመታት ተሞክሮ የተገኘ የዕውቀት ዉድ ሀብት ነው። ​በውስጡ የሚያገኙት፦ ©​የደንበኛ ስሜትን የሚረዱበት ተግባራዊ መንገዶች፤ ®​ውጤታማ የአገልግሎት ሂደቶች እና ቅደም ተከተሎች፤ ©​ከእውነተኛ የሥራ ሁኔታዎች የተወሰዱ ተሞክሮዎች፤ ®​ደንበኛን ለማስደሰት የሚጠቅሙ ዘመናዊ ልምዶች፤ ©​ሙያዊ ጠባይ እና ከልምድ ወደ ልቀት የሚመሩ ስልቶች፤ ​#ደንበኛሎጂ ቲዎሪ ብቻ አይደለም – በየቀኑ በሥራ ቦታ ሊተገበር የሚችል ተግባራዊ መመሪያ ነው። ለጀማሪ፣ ለተማሪ፣ ለአስተዳዳሪ እና ለባለሙያ በኩል ጠቃሚ ነው። ደንበኛዎን እንደ ቁልፍ ከፍ አድርገው ማገልገል ከፈለጉ ይህ መሠረታዊ መጽሐፍ ለእርስዎ ነው።

ከታሪክ ተምሮ በተሰጠው መክሊት ልክ በራሱ ታሪክ የማይሰራ ሰው እርሱ ሰው ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ፍጥረት ከምድር ደርሶ ወደ መቃብር ምድር እንዲመለስ ታስቦ ለቁጥር ማሟያነት የተፈጠረና በ
ከታሪክ ተምሮ በተሰጠው መክሊት ልክ በራሱ ታሪክ የማይሰራ ሰው እርሱ ሰው ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ፍጥረት ከምድር ደርሶ ወደ መቃብር ምድር እንዲመለስ ታስቦ ለቁጥር ማሟያነት የተፈጠረና በሁለት እግሩ የሚሄድ ሰው መሳይ እንስሳ ከመሆን አያልፍም። የሰው ልጅ የትናንትን በመስማት፣ በማንበብና በማገናዘብ፣ የዛሬን በማየትና በመኖር ህይወቱን መስመር እንዲይዝ ከማድረግ ወጪ፣ ነገን በትክክል አሻግሮ የማየት አልያም የመተንበይ ችሎታ እንደሌለው ግልጽ ነው። ​የሰው ልጅ በማያውቀው አጋጣሚ የሚፈጠሩበትን የህይወት ምስቅልቅል አንድም ታግሎ በማሸነፍ ለችግር እጅ የማይሰጥና አይበገሬ ስለመሆኑ በተግባር በማሳየት በትውልዶች መካከል ፋና ወጊ ሆኖ ዘላለም የሚታወስበትና ለሰው ልጅ የሚጠቅም ታሪክ ሰርቶ ያልፋል፣ ሁለተኛም የደረሰበትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግር መቋቋም አቅቶት ህይወት እንደጎመዘዘችው ለትውልድ ሊሻገር የሚችል አንዲት የረባ ተግባር ሳይፈጽም ይህን ዓለም ፈርቶ በመሰናበት ስም አልባ ሆኖ ይቀራል፣ ሦስተኛም የሚደርስበትን ማንኛውንም መከራና ግፍ በጸጋ ተቀብሎ ለወጪ ወራጁ አንገቱ እያቀረቀረና እያጎበደደ ለዘመናት በጭንቀትና በስቃይ ተሞሽሮ ሞቶ እየኖረ በዚህ ዓለም ለመኖር የተፈቀደለትን የህይወት ዘመን ማብቂያ ጊዜ እየናፈቀ ሕልፈቱን በጥር ይ his ይጠባበቃል። ....... 📚ጉራጌነት ትናኖትና፣ዛሬ እና ነገ «የጉራጌ ዘበር ዘፕርም ወገግ በር» በ386 ገፆች የተቀነበበ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ✍️ከዶ/ር ድርሻ ደማም ወንጩሳ

ይህ መጽሐፍ የአእምሮ ትኩረት መንገዶችን ያስተውቀናል፡፡ ከምንፈልገው ስኬት እንዳንደርስ እንቅፋት የሆኑብንን የውስጠ ህሊና ገደቦች የምናስወግድበትን ብልሃትም ይጠቁመናል፡፡ ​በዚህ መጽሐፍ ዶ\ር መር
ይህ መጽሐፍ የአእምሮ ትኩረት መንገዶችን ያስተውቀናል፡፡ ከምንፈልገው ስኬት እንዳንደርስ እንቅፋት የሆኑብንን የውስጠ ህሊና ገደቦች የምናስወግድበትን ብልሃትም ይጠቁመናል፡፡ ​በዚህ መጽሐፍ ዶ\ር መርፊ የእውነተኛ ታሪክ እማኞችን በመጠቀም አስደናቂ አእምሮአዊ አቅማችንን በማውጣት የራስ መተማመናችንን መገንባት፤ ግንኙነታችንን ማሻሻል፤ ሙያዊ ስኬት ማግኘት፤ ፍርሃትን ማስወገድ፤ እንዲሁም ጤንነትና ደስታችንን ማሻሻል እንደምንችል ያረጋግጥልናል፡፡ ​ዶ\ር መርፊ አስደናቂውን የውስጠ ህሊና ኃይል የምትከፍቱበትን መሣሪያ በዚህ ሥራው ይሰጣችኋል፡፡ ይህንን አስደናቂ ኃይል እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ ከተማራችሁ በኋላ ማንኛውንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ የውስጠ ህሊናቸውን ቁልፍ ካገኙ ሚሊዮኖች ጐራ ለመቀላቀል ይህንን መጽሐፍ ማጥናትና ሥልቶቹን ተግባራዊ ማድረግ የግድ ነው፡፡ ​መላው ነገር የሚጀምረው ከውስጥ ነው፡፡ የግለሰቡ አመለካከት ሲለወጥ መላው የሕይወት መንገድ ይቀየራል፡፡ ይህ መጽሐፍ በራሱ ሙሉ እምነት ላለው የሚሆን የለውጥ መንገድ ነው፡፡ መንፈስ አነቃቂ ጽሑፍ ሲሆን በሕይወታችሁ ለውጥ የምትሹ ከሆነ ዛሬውኑ አንድ ቅጂ(ኮፒ) በመያዝ ለመኖር የምትፈልጉትን ለውጥ ተመልከቱ፡፡

...ግራኝ አህመድ...የተዋጊነትና ያዋጊነት መንፈስ የሞላዉ፣...ከሚስቱ ከድል ወንበራና ከሹማምንቱ ጋር ከልብ ቆርጦ የተነሳ፣ባገሩ ዉስጥ ከነአቡበክር ሱልጣን ጋር ካደረገዉ ጦርነት ዉጭ ከክርስቲያኖቹ
...ግራኝ አህመድ...የተዋጊነትና ያዋጊነት መንፈስ የሞላዉ፣...ከሚስቱ ከድል ወንበራና ከሹማምንቱ ጋር ከልብ ቆርጦ የተነሳ፣ባገሩ ዉስጥ ከነአቡበክር ሱልጣን ጋር ካደረገዉ ጦርነት ዉጭ ከክርስቲያኖቹ ከነፋኑኤል፣ከነ ራስ ደግሃል ጋር ያለእረፍት እየተዋጋ ሰዉነቱን ያላቀማጠለ፣ክብርን፣ሥልጣንን፣ግዛትን ገና ያልጠገበ፣ምኞቱን ገና ወደ ፍጻሜ ያላደረሰ አፍላ የጦር መሪ፣ራሱ ጦርጦራ ተዋጊ ስለሆነ...ሁልጊዜ የድል አዝማሚያዉና ዝንባሌዉ አፍላና ፈቃደኛ፣ደፋርና ዉካት ወደሆነዉ ወገን ነዉ» (ተ/ፃዲቅ መኩሪያ የግራኝ አህመድ ወረራ ገፅ 95)

48ቱ የኃይልነት ሕጎች 📚 ​ይህ በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ሽያጭን ያስመዘገበ፤ በብዙ ሃገራት ባሉ እስር ቤቶች ውስጥ እንዳይነበብ የታገደ አወዛጋቢ መጽሐፍ፤ በውስጡ ታሪካዊ የኃይልነት ሚስጥሮችን
48ቱ የኃይልነት ሕጎች 📚 ​ይህ በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ሽያጭን ያስመዘገበ፤ በብዙ ሃገራት ባሉ እስር ቤቶች ውስጥ እንዳይነበብ የታገደ አወዛጋቢ መጽሐፍ፤ በውስጡ ታሪካዊ የኃይልነት ሚስጥሮችን እና ምሳሌዎችን በብዛት ይዟል፡፡ እንደ ማኪያቬሊ፣ ሰን ዙ እና ክላውስዊትስ ካሉ ተደማጭነት ካላቸው አሳቢዎች ፍልስፍና በመነሳት በሕይወትህ ውስጥ እንዴት ኃይልን ማግኘት እንደምትችል ያሳይሃል፡፡ የሦስት ሺህ ዓመታት የስልጣን እና የኃይል ጥበብን በመጭመቅ፤ በአርባ ስምንት ሕጎች ቀርበውልሃል፡፡ እነዚህ ሕጎች እንደ ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ናፖሊዮን ቦናፓርት ያሉ ባለስልጣናት የተጠቀሙባቸው ሲሆኑ፤ እነዚህን ምሳሌዎች በማጥናት፤ አንባቢዎች ስለ ኃይል ዳይናሚክስ ግንዛቤዎችን ማግኘት እና ኃይልን በብቃት እንዴት ማሰስ እና መጠቀም እንደሚችሉ ያውቃሉ፡፡ እነዚህን ሕጎች በመጠቀምም በሕይወታቸውም ውስጥ ወደሚፈልጉት የመጨረሻ ስኬት መድረስ ይችላሉ፡፡ ማስጠንቀቂያ – አንዳንድ ተቺዎች ይህ መጽሐፍ ተንኮለኝነትን እና አጭበርባሪነትን በተወሰነ ደረጃ ያበረታታል ብለው ይከራከራሉ፡፡ አንባቢዎችም ይዘቱን በትኩረት እንዲመለከቱት እና ተፈጻሚነቱን በራሳቸው የሥነ ምግባር ማዕቀፍ ውስጥ እ ን ዲ ያ ደ ር ጉ ት ያስፈልጋልና 48ቱ ሕጎች በ ጥ ን ቃ ቄ ይተግብሩ!!

በቀደም ለት ጉንጬ መሐል በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፤ ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ። ​ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ ስቄ ስቄ እንዳባራሁ፤ ' ጥርስህ ሲያምር ' ስላለችኝ ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ። ​ተካ
በቀደም ለት ጉንጬ መሐል በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፤ ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ። ​ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ ስቄ ስቄ እንዳባራሁ፤ ' ጥርስህ ሲያምር ' ስላለችኝ ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ። ​ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ ' እፍ ' አልሽብኝ ድብቅ ውበት፤ እስቲ እባክሽ አሁን ደግሞ ' ሰው ሁን ' ብለሽ ሹሚኝ ' ና ሰው መሆኔን ልመንበት። ​ሰው ተብዬ ልጠራበት 📚ወደ ነገ ሒያጅ ነኝ 📚 የግጥም ሥብሥብ

ለደስታህ ትልቁ ጠላት በጭንቅላትህ ውስጥ የሚኖረው ሃሳብህ ነው!!! ​ከመጠን በላይ ማሰብ ልማድ ብቻ አይደለም፤ እንዲደክምህ፣ እንዲጨንቅህ እና እንድትሰነካከል የሚያደርግ ወጥመድም ነው። የዛሬ ሦስት
ለደስታህ ትልቁ ጠላት በጭንቅላትህ ውስጥ የሚኖረው ሃሳብህ ነው!!! ​ከመጠን በላይ ማሰብ ልማድ ብቻ አይደለም፤ እንዲደክምህ፣ እንዲጨንቅህ እና እንድትሰነካከል የሚያደርግ ወጥመድም ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት የተከሰተን ወደፊት ደጋግመህ እያሰብክ ወይም ስለ ነገ ስብሰባ እየተጨነቅክ ከሆንክ አእምሮህ በአንተ ላይ እየሰራ ነው። ​Stop Overthinking በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ታዋቂው ደራሲ ኒክ ትሬንተን የአእምሮህን መሪነት ለመረከብ ሳይንሳዊ ዘዴን ያቀርባል። ይህ የተለመደው "በጎ አስብ" የሚል ፍልስፍና ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የአንጎልህን ኬሚስትሪ እና የአእምሮ ልማዶችህን ለመቀየር የሚረዳ ዘዴና መመሪያ ነው። «ጭንቀትን ማሸነፍ» 📚

Classic Masterpiece Available Now! 📚 ​Looking for your next deep and captivating read? Dive into "The Adolescent" by the leg
Classic Masterpiece Available Now! 📚 ​Looking for your next deep and captivating read? Dive into "The Adolescent" by the legendary Fyodor Dostoevsky (translated by the acclaimed Richard Pevear and Larissa Volokhonsky). ​✨ Why read it? A powerful exploration of youth, ambition, family drama, and moral dilemmas in 19th-century Russia. An essential addition to every book lover’s shelf! ​Condition: Excellent / Brand New ​ ​Delivery / Worldwide ) ​📩 Limited copies available! Send a direct message (DM) or call [0929574133] to grab yours today! ​#BookLover #classicliterature #dostoevsky #TheAdolescent #EthiopiaReads #addisbooks #bookstoreethiopia

ሰባተኛው ማኅተም ምንድነው? ኤልያስ ገብረ አዕምሮ ማነው? ውድቀትና መነሳት ሲገለጥ ​ ህልም እንዴት ይፈታል? ​ የመነጠቅ ጊዜ ደርሷልን? ዳግም ውልደት? * * ዳግም ፍጥረት እውነት ነውን? የሚሻገ
ሰባተኛው ማኅተም ምንድነው? ኤልያስ ገብረ አዕምሮ ማነው? ውድቀትና መነሳት ሲገለጥ ​ ህልም እንዴት ይፈታል? ​ የመነጠቅ ጊዜ ደርሷልን? ዳግም ውልደት? * * ዳግም ፍጥረት እውነት ነውን? የሚሻገረዉና የሚወድቀዉ ማነዉ? ​ ከምንድነውሰ የምንድነው? የሙት ባህር ጥቅልል? መንግስተ ሰማይ የት ናት? ​ ሶፊያ ማናት? ​ ​ሁሉዜአዊ ጥበብ ትርጓሜ? ​ ​የአዳም አሰራር? ​የአብነ አድማስ ጥበብ? ​እባቧና ፍሬዋ? ​አምላክ አለ ወይስ የለም? ​አምላክ አካል አለው ወይስ የለውም? ​አምላክ አንድ ነው ወይስ ሦስት ወይስ ብዙ? ​ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት? ​ ​የጥበብ ሰባት ምሶሶዎች ምንድናቸው? ​ቸክራዎች ምንድናቸው? ​የወንዳዊና ሴታዊ ኃይላት ውቅር? ​ትዊን ፍሌምና ካርማ ነፍሳት ባህሪ? ​የገንዘብ ፍሰት ምስጢር? ​ ​የነፍስ የዕድገት ጉዞ? ​ ​እውነት ምንድነው? * ​የክርስቲያኖቹ ወይስ የሙስሊሞቹ ኢየሱስ? ​ትክክለኛው ሃይማኖት የቱ ነው? ​የሚያድነው እምነት ወይስ ሥራ? ​666 ማነው? ደጃልና AI? ​ከጋንንትና ጂኒ ፈተናዎች? ​የሰለሞን ጥበብ? ​አልኬሚስቱ? 📚አርምሞ2

ኦላ ! ሴቶች ​"ከኢያሪኮ አወዛጋቢውን መምህር ቀቁን ያስተዋወቀን በቆሸሹ ሳቆች ይቺ ዱንያ ምንድንነች ያስባለን ፣ በቺ (235) ጓደኛዋን ኢቺን ያበሰረን! እነሆ በ«ኦላ ሴቶች» ጉጉዳ በርተሚዎስን
ኦላ ! ሴቶች ​"ከኢያሪኮ አወዛጋቢውን መምህር ቀቁን ያስተዋወቀን በቆሸሹ ሳቆች ይቺ ዱንያ ምንድንነች ያስባለን ፣ በቺ (235) ጓደኛዋን ኢቺን ያበሰረን! እነሆ በ«ኦላ ሴቶች» ጉጉዳ በርተሚዎስን አርሂቡ ይለናል።" (አሳታሚው) ​* ​"በህገወጥ ቃላት ባይታጨቅም፣በተንኳሽ ትረካዎች ባይሟሽም ፣አንዳንድ በዝቅታ እና በከፍታ በሚነሱ የሀሳብ ስንዝሮች የተነሳ ከ17 ዓመት በላይ ያሉ እንዲዋጁት በትህትና እጋብዛለሁ!" (ደራሲው) አዘርግ 📚📖

"አሰብ ቀይ ባህር ወደባችን በዚያን ጊዜ" ግሩም መጽሐፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።አሰብ ከዉልደት እስከ ዘመናዊና ስትራቴጂካዊ የወደብ ከተማ ለመሆን እንዴት በቃች? ለሚለዉ ጥያቄ በርካታ መጻሕፍትንና መዛግብ
"አሰብ ቀይ ባህር ወደባችን በዚያን ጊዜ" ግሩም መጽሐፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።አሰብ ከዉልደት እስከ ዘመናዊና ስትራቴጂካዊ የወደብ ከተማ ለመሆን እንዴት በቃች? ለሚለዉ ጥያቄ በርካታ መጻሕፍትንና መዛግብትን አገላብጦ፣የከተማዉን ነዋሪ ዜጎች ጠይቆ፣እንዲሁም ከግለ-ታሪኩም ጋር አያይዞ ብዙ ቁም ነገሮችን አቅርቦልናል። ይህ ብቻም አይደለም፣በአሰብና አካባቢዋ ነዋሪ ስለሆነም የአፋር ሕዝብ ስነ ልቦና፣ታሪክና ባህል ሰፊ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ያካተተ መጽሐፍ ነዉ።አባቴ ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ለአሰብ ወደብ ዝመና፣ለከተማዉ ዕድገትና ዉበት የባህር ትራንስፖርት ባለስልጣን ስታፎችንና መላዉን የወደብ ሰራተኛ በማስተባበር የሰሯቸዉን በርካታ የልማት ስራዎች፣እንዲሁም አስተዋጽኦ የታሪካችን አካል ነዉና አዉቄበታለሁ።በአቀራረቡም ረክቻለሁ። ለወደፊቱም ሰፊ ታሪካዊም ሆነ ወቅታዊ በሆኑ የማሪታይም ጉዳዮችና የማሪታይም ስትራቴጂ ተመራማሪዎችና አጥኝዎች ትልቅ ግብአት ከሚሆኑ መሰረታዊ ሰነዶች አንዱ እንደሚሆን አምናለሁ። ነዓምን ዘለቀ የቀድሞ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ የኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ልጅ። የመጽሐፉ ዉስን ቅጅ በእጃችን ይገኛል። የተለያዩ የአለም ሃገራት ሆናችሁ መጽሐፍትን እዘዙ።በፍጥነት በታማኝነት በያላችሁበት እንልክላችኋለን። አድራሻችን፦ አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

«የሰማያት በሮች» እና «የነፍስ እንጉርጉሮ» እንደአንድም እንደኹለትም 📚 እኛ እና እኛ ጀምበርም ጠለቀች፣ ደጉ ዘመን ሄደ፣ የተካበዉ ሁሉ፣ ደርሶ እየተናደ፣ ለፍቅር የሚያንሰን ዕድሜያችን ገሽቦ፣
+1
«የሰማያት በሮች» እና «የነፍስ እንጉርጉሮ» እንደአንድም እንደኹለትም 📚 እኛ እና እኛ ጀምበርም ጠለቀች፣ ደጉ ዘመን ሄደ፣ የተካበዉ ሁሉ፣ ደርሶ እየተናደ፣ ለፍቅር የሚያንሰን ዕድሜያችን ገሽቦ፣ ለፀብ ያስተረፍነዉ ከየት መጣ ተስቦ። ✍️ሙሐመድ ፈረጅ

ይህ መፅሀፍ ስለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ቤተሰቦቻቸው የታሪካዊ ስነልሳን ጥናት መውሰድ እስከሚችለው የጊዜ ገደብ ድረስ በመጓዝ መሰረታዊ መረጃ ያቀርባል:: ቋንቋና ተናጋሪው የሚለያዩ አይደሉምና፤ ከቋንቋዎ
ይህ መፅሀፍ ስለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ቤተሰቦቻቸው የታሪካዊ ስነልሳን ጥናት መውሰድ እስከሚችለው የጊዜ ገደብ ድረስ በመጓዝ መሰረታዊ መረጃ ያቀርባል:: ቋንቋና ተናጋሪው የሚለያዩ አይደሉምና፤ ከቋንቋዎቹ አንፃር በመነሳት የኢትዮጵያን ህዝብ ማንነትና ቅድመታሪክ ይዳስሳል:: የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከተወሰኑ ብቸኛ ቋንቋዎች በስተቀር አፍሮኤሽያቲክና ናይሎሰሀራን ከሚባሉ ታላቅ ቤተሰቦች ይመደባሉ:: ከጥቂት የናይሎሰሀራን ቋንቋዎች በስተቀር ሌሎች ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ የነበሩ ናቸው:: መፅሀፉ የአፍሮኤሽያቲክ ቋንቋዎች ከእስያ በተለያየ ወቅት ወደኢትዮጵያ ገቡ የሚለውን መላምት በስፋት መርምሮ ይህ ስላለመሆኑ አሁን ያለው መረጃ ማረጋገጫ እንደሌለው ያሳያል:: ከዚህም በላይ በህብረተሰብ መሀከል ስላለ ውህደትና ልዩነት በስፋት ይዘረዝራል:: ቋንቋና ነገድ በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነትና ቅድመ ታሪክ 📚📚📚 ✍️ግርማ አዉግቸዉ ደመቀ

"ሀገር ያጣ ሞት" ራሱ እንደሚለው "ከቅኝት ትዝታ፣ ከስሜትም ኀዘን" የሚገንንበት፤ ኀዘኑ አንባቢን የሚወርስ፤ እንደዐፈር ግድግዳ የሚንድ የሚያፈራርስ፤ መራር ሂዩመሩ ለሣቅ የተገለጠን ጥርስ በመሸማቀ
"ሀገር ያጣ ሞት" ራሱ እንደሚለው "ከቅኝት ትዝታ፣ ከስሜትም ኀዘን" የሚገንንበት፤ ኀዘኑ አንባቢን የሚወርስ፤ እንደዐፈር ግድግዳ የሚንድ የሚያፈራርስ፤ መራር ሂዩመሩ ለሣቅ የተገለጠን ጥርስ በመሸማቀቅ አግጥጦ የሚያስቀር፤ ለፈገግታ የተዛና ጉንጭ ቆዳን በኀፍረት የሚሸበሽብ፤ የገዛ ስጋ ወደሙን ከአንባቢ የሚያዋሕድ ኃይለ ድርሰት ነው። ​በጽሕፈት ባልተቀነፉ ትእምርተ ጥቅሶቹ ውስጥ የስብሃት አጋፋሪያዊ ፈሪሃ ሞት፤ የፎስትም የነፍስ ቁማር (Faustian bargain)፤ የአዳም የሕይወትን ኪስ አራግፎ ቅራቅንቦዉን የማጋለጥ ተጋድሎ፤ የእንዳለጌታ የመከራ "ምጣድ"፤ የበዕውቀቱ ዕረፍት የሚያሥሡ ታካች ነፍሶች፤ በጊዜ ስም "የአጥቢያ ዳኛ" ኾኖ የመጣ እግዜር፤ ከጸሐፌ ትእዛዝነት ወደ ጽሕፈ ዘመንነት የተሻገረ ሊቁ ዘነብ፤ ከቅዱሳት መጻሕፍት ከባህል ትርክትም በተውሶ የመጡ (ደራጎን ገዳይ፤ ሠላሳ ዘላይ ተጋዳሊ የሌላቸዉ) "ገድሎች"፤ ሕይወትን የሚፈክሩ ሐዲስ ሚቶሎጂዎች እና እኛ ኹላችን ከነዘመናችን ተከትበናል፡፡ በወሬ ስም የተጠራ ሀገር "አባት የለሽ ትዉልድ" ኾነን፤ በወሬ ምንነት ተስለናል፡፡ ​ሔኖክን "በነሀስ ሰሌዳ ደጋግመኽ ንቀሰን" በሚያሰኝ፤ ከተገነባባቸው የወለፈንዲ ሕልውናዎች ፍርስራሾች የተነሣ በሚያፍን፤ ነገር ግን ሊሸሹት በማይሹት ሥልት፤ ከግሩም ድርሰት በተዳሩ ቃላት፤ በነጠሩ ዐዳዲስ ገለጻዎች የተደረሰበት፤ እንደ ራሳችንን በዐሥራ ዐሥር አዉታር (multi-dimension) የምናይበት ስሙ ር ሥራ ነው። ​–ቴዎድሮስ ካሣሁን ​|ደራሲና ሐያሲ|

አርቅይሁን በላይነህ የሸዋን ታሪክ በኢትዮጵያውያን ልማዳዊ ታሪክ ትረካና ትንታኔ ስልት፤ ነገር ግን ለዘመናዊው የአካዳሚክ የታሪክ ጥናት ስልት በቀረበ መልኩ፣ ጥልቅ ትንታኔ አቅርቧል፡፡ የሸዋ ነገሥታ
አርቅይሁን በላይነህ የሸዋን ታሪክ በኢትዮጵያውያን ልማዳዊ ታሪክ ትረካና ትንታኔ ስልት፤ ነገር ግን ለዘመናዊው የአካዳሚክ የታሪክ ጥናት ስልት በቀረበ መልኩ፣ ጥልቅ ትንታኔ አቅርቧል፡፡ የሸዋ ነገሥታትንና መኳንንትን የትውልድ ሐረግና ትንቢት እንዲሁም የፖለቲካ፣ ወታደራዊና አስተዳደራዊ በሳል የአመራር ጥበብን በጥልቀት ተመልክቶታል፡፡ በተጨማሪም በመሳፍንቱ መካከል የነበረውን የሥልጣን ትግል፣ አመጽና መፈንቅለ መንግሥት እስከ ቅጣትና ምሕረቱ እንዲሁም ሹም ሽሩ በድራማዊ አገላለጽ ተርኳል፡፡ ይህ መጽሐፍ በታሪክ ተመራማሪዎች ብዙም ትኩረት ያልተሰጠውን፣ ነገር ግን ምናልባትም ወሳኝ የሆነውን የኢትዮጵያን ታሪክ በአማርኛ ቋንቋ ስለሚዳስስ፣ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አንባቢ ተመራጭ እንዲሁም ወደፊት ለሚደረጉ የታሪክ ምርምሮች በመነሻነት የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ ​ዶ/ር ተፈሪ መኰንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የታሪክ ተመራማሪ 2006 ዓመተ ልደት

“ምሁራዊ፣ ግልፅ ትችት የቀረበበት እና ቆሰቋሽ የሆነው ይህ መፅሐፍ፤ በውብ መንገድ ተፅፎ ተነባቢነትን ከሃሳብ ሰጪነት ጋር አጣምሯል። በሕይወት ዘመን የተለየ ምርምር ታግዞ፣ የዚህን የአፍሪካ ክፍል
“ምሁራዊ፣ ግልፅ ትችት የቀረበበት እና ቆሰቋሽ የሆነው ይህ መፅሐፍ፤ በውብ መንገድ ተፅፎ ተነባቢነትን ከሃሳብ ሰጪነት ጋር አጣምሯል። በሕይወት ዘመን የተለየ ምርምር ታግዞ፣ የዚህን የአፍሪካ ክፍል ተለዋዋጭነት ፊትለፊት የገጠመ አስፈላጊ እና ቅርት ያለ አስተምህሮን አሰናስሏል። እናም ለዚህ አካባቢ ዜጎች፣ ተሟጋቾች፣ ተመራማሪዎች እና ተማሪዎች አስተሳሰብ አነቃቂ ተግባቦት ነው።” ​ሳሪ ካቫናግ፣ ኤዲንበርግ ዩኒቨርሲቲ ​“ክርስቶፈር ክላፋም ምንም ጥርጥር በሌለው መንገድ በዓለም ላይ ዋነኛው የአፍሪካ ቀንድ ሊቅ ነው፤ እናም ይህ፣ በአካባቢው ላይ ለሚሰራ ሁሉ በግድ መነበብ ያለበት መፅሐፍ ነው። በተለመደው ወግ አዋቂነቱ እና ለቀንዱ ሕዝብ ባለው ጥልቅ ርህራሄ፣ በእጅጉ የተለየ ውስብስብ እና ብዙውን ጊዜም አሳዛኝ ፖለቲካዊ ጅምላውዥክ ስላበበበት አካባቢ የአዳሜ ዘመንን መረዳቶች አጋርቶናል።” ​ኬን ሜንክሃውስ፣ በዴቪድሰን ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር «የአፍሪካ ቀንድ።» 📚📚📖📖 ደራሲ፦ክርስቶፈር ክላፋም ትርጉም፦ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ

ነገ ወደ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ማስላክ የምትፈልጓቸዉ መጽሐፍት ካሉ አነጋግሩን። Abdu Book Delivery 0929574133 መጽሐፍትን እስከ ደጃፍዎ ክፍላተ ሃገር ከሃገር ዉጭ ላላችሁም ዴሊ
ነገ ወደ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ማስላክ የምትፈልጓቸዉ መጽሐፍት ካሉ አነጋግሩን። Abdu Book Delivery 0929574133 መጽሐፍትን እስከ ደጃፍዎ ክፍላተ ሃገር ከሃገር ዉጭ ላላችሁም ዴሊቨር እናደርግላችኋለን። በሚገርም ግራፊክስ፣መጽሐፍትን በሚገልጽ ከፅሁፉ ጋር በሚሄድ ስራልኝ።