በቃል ጥበብ
Відкрити в Telegram
2 836
Підписники
Немає даних24 години
-127 днів
-3730 днів
Архів дописів
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ሁሌ ማለዳ ስነቃ ቀኑ በራሱ ግራ አጋብቶኝ ነው። አሁን ላይ ለንጋት የነበረኝ ጉጉት ሀሞቱ ፈሷል። ትከሻዬ በወጣትነት የመለወጥና ከስኬት የመራቅ ወላፈናም ጥያቄና ድካም አዝሎታል። ቢሆንም ፍትሀዊ ያልሆነችው ህይወት ለነፍሴም ለሰውነቴም መዳከም ከስቃይ ጋር መቀጣጠሯን አታቆምም። በዛ ላይ ጊዜም ያግዛታል። እግሮቼ ወደፊት ለመራመድ ካመነቱ ቆዩ። ከማመንታትም አልፈው ለግመዋል። ልቤ ከዚህ ማለቂያ ከሌለው ሩጫ፣ ከከንቱ መዳከርና ግራ ይሁን ቀኝ ጽንፍ ከሌለው አዙሪት ጋር መዋጋት ሰልችቷታል።
፧
ፈተናዎች ልክ እንደ ከባድ ማዕበል በየአቅጣጫው ከበውኛል። በዛላይ ፅልመታም ናቸው።.... ዳተኛም ናቸው። መልከ ብዙ፣.... ፀባየ ብዙ፣ ....ግበ' ብዙ ጉራማይሌም ናቸው። መታመም መዳን ዳግም መታመም፤ ዛሬም ነገም ቀለሙ ተመሳሳይ የሆነ የጭንቀት ውልብታ፣ የበረታ ህመም እና የብቸኝነት ጥላ አብረውኝ አሉ። ተስፋ መቁረጥ ደረቱን ነፍቶ መላ ማንነቴን ሲወርረው፣ ባይተዋሯ ትርታዬ «እስከመቼ?» እያለች ትጠይቃለች፣ ....ትሞግታለች። መልስ የሌለው ዝምታ ግን ነፍሴን ይበላታል፥ ለዛውም እንደተራበ የጅብ መንጋ።
፧
ለምንና በማን ጥፋት እንደሆነ ባላውቅም ወጣትነቴ ገና ከጅምሩ በቁስል ታስሯል፤ ጠባሳውም አይጠፋም፤ ከንፈሬ ፈገግታን ከረሳ ሰነባብቷል፣ ህልሞቼም ጨሰው አመድ ሆነዋል። ለኔ ሳይሆን ለሌላው ብርሀን ስል ያነደድኳቸው መስዋዕትነቶች ከዚህ በኋላ ለመታገልም ሆነ ዳግም ለመነሳት ጉዞዬን አድካሚ አድርገውብኛል። የነተበ ትከሻዬ የተሸከመው የዚህን ዓለም ከንቱነት ብቻ እንደሆነ እያስታወሰኝ፣ ብሶቴ ፈልቶ እንደገነፈለ ተባል አልቀዘቅዝ ብሏል ፤ ከዕለት ወደ ዕለትም እየከረረ ጨለማው ውስጥ ብቻዬን ቀርቻለሁ።
፧
ለምን ካላችሁኝ..... በሁሉም ማዕዘናት የሚወደቁብኝ ድብደባዎች የማምለጫ ቀዳዳ አሳጡኝ። አዕምሮአዊ ውጥረቱ እና የአካል ስብራቱ ከወትሮው ጫ'ን ሲሉኝ፣ ትንፋሼ ራሱ እንደ ባዕድ ነገር ይከብደኛል። ማንም ሊሰማኝ የማይችለው ከዚህ የማያባራ ስቃይ ከምታላቅቀኝ፣ አጭር መፍትሄ የሌለባት ረዥም ጎዳና ላይ ቆሜያለሁ። የምርጫዎች ሁሉ መጨረሻ ባዶነት እንደሆነ ስላየው፣ ለትግል የሚሆን አንዳችም አቅም ከውስጤ ተራቁቷል። ቀሪው ዘመኔ በዚህ የሰለቸና ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ብቻ ተዘፍቆ እንዲቀጥል የተፈረደብኝ ይመስለኛል።
፧
ብቻ..... ብቻኣ......ይህ ሁሉ ነገር አንድ እውነትን እውነት አድርጎልኛል «መኖር ከመሞት ይከብዳል!»
፧
ጥያቄ ለእናንተ ዛሬ የሚሰማን ሸክምነት የወደፊት ፍርዳችን ቢሆንስ? በተጨነቀ መክሰል ውስጥ የአልማዝ ጠብታውና ውበቱ ሁሌም አለ?
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧፧
ስቃ በራሱ ዋጋ አይደለም ‼️
፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
©ezra kassahun
22/2/19
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ሁሌ ማለዳ ስነቃ ቀኑ በራሱ ግራ አጋብቶኝ ነው። አሁን ላይ ለንጋት የነበረኝ ጉጉት ሀሞቱ ፈሷል። ትከሻዬ በወጣትነት የመለወጥና ከስኬት የመራቅ ወላፈናም ጥያቄና ድካም አዝሎታል። ቢሆንም ፍትሀዊ ያልሆነችው ህይወት ለነፍሴም ለሰውነቴም መዳከም ከስቃይ ጋር መቀጣጠሯን አታቆምም። በዛ ላይ ጊዜም ያግዛታል። እግሮቼ ወደፊት ለመራመድ ካመነቱ ቆዩ። ከማመንታትም አልፈው ለግመዋል። ልቤ ከዚህ ማለቂያ ከሌለው ሩጫ፣ ከከንቱ መዳከርና ግራ ይሁን ቀኝ ጽንፍ ከሌለው አዙሪት ጋር መዋጋት ሰልችቷታል።
፧
ፈተናዎች ልክ እንደ ከባድ ማዕበል በየአቅጣጫው ከበውኛል። በዛላይ ፅልመታም ናቸው።.... ዳተኛም ናቸው። መልከ ብዙ፣.... ፀባየ ብዙ፣ ....ግበ' ብዙ ጉራማይሌም ናቸው። መታመም መዳን ዳግም መታመም፤ ዛሬም ነገም ቀለሙ ተመሳሳይ የሆነ የጭንቀት ውልብታ፣ የበረታ ህመም እና የብቸኝነት ጥላ አብረውኝ አሉ። ተስፋ መቁረጥ ደረቱን ነፍቶ መላ ማንነቴን ሲወርረው፣ ባይተዋሯ ትርታዬ «እስከመቼ?» እያለች ትጠይቃለች፣ ....ትሞግታለች። መልስ የሌለው ዝምታ ግን ነፍሴን ይበላታል፥ ለዛውም እንደተራበ የጅብ መንጋ።
፧
ለምንና በማን ጥፋት እንደሆነ ባላውቅም ወጣትነቴ ገና ከጅምሩ በቁስል ታስሯል፤ ጠባሳውም አይጠፋም፤ ከንፈሬ ፈገግታን ከረሳ ሰነባብቷል፣ ህልሞቼም ጨሰው አመድ ሆነዋል። ለኔ ሳይሆን ለሌላው ብርሀን ስል ያነደድኳቸው መስዋዕትነቶች ከዚህ በኋላ ለመታገልም ሆነ ዳግም ለመነሳት ጉዞዬን አድካሚ አድርገውብኛል። የነተበ ትከሻዬ የተሸከመው የዚህን ዓለም ከንቱነት ብቻ እንደሆነ እያስታወሰኝ፣ ብሶቴ ፈልቶ እንደገነፈለ ተባል አልቀዘቅዝ ብሏል ፤ ከዕለት ወደ ዕለትም እየከረረ ጨለማው ውስጥ ብቻዬን ቀርቻለሁ።
፧
ለምን ካላችሁኝ..... በሁሉም ማዕዘናት የሚወደቁብኝ ድብደባዎች የማምለጫ ቀዳዳ አሳጡኝ። አዕምሮአዊ ውጥረቱ እና የአካል ስብራቱ ከወትሮው ጫ'ን ሲሉኝ፣ ትንፋሼ ራሱ እንደ ባዕድ ነገር ይከብደኛል። ማንም ሊሰማኝ የማይችለው ከዚህ የማያባራ ስቃይ ከምታላቅቀኝ፣ አጭር መፍትሄ የሌለባት ረዥም ጎዳና ላይ ቆሜያለሁ። የምርጫዎች ሁሉ መጨረሻ ባዶነት እንደሆነ ስላየው፣ ለትግል የሚሆን አንዳችም አቅም ከውስጤ ተራቁቷል። ቀሪው ዘመኔ በዚህ የሰለቸና ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ብቻ ተዘፍቆ እንዲቀጥል የተፈረደብኝ ይመስለኛል።
፧
ብቻ..... ብቻኣ......ይህ ሁሉ ነገር አንድ እውነትን እውነት አድርጎልኛል «መኖር ከመሞት ይከብዳል!»
፧
ጥያቄ ለእናንተ ዛሬ የሚሰማን ሸክምነት የወደፊት ፍርዳችን ቢሆንስ? በተጨነቀ መክሰል ውስጥ የአልማዝ ጠብታውና ውበቱ ሁሌም አለ?
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧፧
ስቃይ በራሱ ዋጋ አይደለም ‼️
፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
©ezra kassahun
22/2/19
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ርዕስተ እኔ
~~~
ናት እ ና' ውብ
፥
ለሰማይ ደጅ ንጣፍ
እውነተኛ ብርሀን።
ለቅድስና ርኡይ
ታላቅ ህልው' ምስጢር።
፧
ናት እ ና' ድንቅ
፥
ከአፈር የገዘፈው
በአፈር የከበረው
በዓለም ከተሰራው
የርእስት ርትዕና።
፧
ናት እ ና' ህዋ'
፥
ቀደምት ጣኦት
አንድ እስትንፋስ
የማንነት ሚናስ።
፧
ይቺ' የቀን ጮራ
በደሜ ውስጥ የምታጓራ
ብፈልግ ባልፈልግ
ከእርሱ አስበልጩ
ማወድስ ማመልካት
ብትንትን ውትንትል አንድያ ነፍሴ ናት።
፧
በል ተቀየም እግዜሩ 😊
©ezra kassahun
9/2/19
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ቃላት ቅመም
ሚደብቅ የነፍስ ህመም
ጣፋጭ ዜማ ለህሊና
......ለእስትንፋስ.......
እውነት ሚያጭቅ።
፧
ግጥም አለም፦
ዝለት ጉድለት የህሊና እምባ
ለጨለማው መሸሸጊያ
ከብርሀን በዝምታ መታረቂያ
...................ብቸኛ አምባ።
፧
ለስላሳ እውነት
ህመም መንፈስ የሚቃኘው
ክህደት ሀጥያት መከራ የደረሰው።
፧
ግጥም እናት፦
ፍቅር ሲወርድ ከጥልቁ
ዳፍንትና ፅልመት ከብርሀን ሲርቁ
መንገድ መሪ ድኅነት ምስጢር
ሲደረመስ የጥርጣሬው ድንበር
ለፍርስራሽ ቀልቤ ነፃነት
ቃላት ፊደል ንፁህ እምነት።
፧
ግጥም አባት፦
ጠንከር ያለ ሆሄ የሚዳኘው
ለስለስ ያለ ሀቅ የከበበው
በጠለቀ ህሊና የሚተከል
ምርጥ ዜማ ቆንጆ ቅኔ
እንደዚህ ነሽ አንቺ ለእኔ።
©ezra kassahun
6/2/19
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
የቡናው ፡ ጠይም ፡ መልክ
የሽታው ፡ መዓዛ፥
ሙዚቃና ፡ ዜማው
መፅሃፍ ፡ ከብእር ጋ'፤
ስጡኝ ፥ ነፍሴ ትረፍ
ልቤ ፡ ከአለም ፡ ብዙም ፡ አትሻ'።
አቅርቡ ፡ ቡና ቁርስ
ፈንድሻውም ፡ ይፍካ
ሉባንጃውም ፡ ይጢስ
አቦል ፡ ከበረካው በቶና ፡ ይተካ።
፧
ለእኔ ፡ በቂዬ ነው
በእፍኝ ፡ ከሰል ፡ ሙቀት፤
የብርድ ፡ ዝምታ
የሸክላው ፡ እሳት ፡ ሐሩር፤
የቡናው ፡ ከበጃ'
በማሰብ ፡ ነፃነት፤
ሰው ፡ የመሆን ፡ እርካታ።
ስጡኝ..........፦
የጢስ ፡ ዳንኪራውን፥
የዜማ ፡ አድባሩን
ያለ እርሱ ፡ እኔስ ፤
መክረሜንስ ፡ እንጃ።
አምጡ ፡ ክራር ፡ ልምታ
ድምፁ ፡ ያቃስር
አእምሮ ፡ ይሰርስር
ይዳብስ ፤ ያስስ
የልብን ፡ ማህደር።
ቡና ፡ ፉት ፡ ልበል
ከዛሬ ፡ ልነጠል
በሀሳብ ፡ ሽቅብ ፡ ልጓዝ፤
........ ልሻገር .........
ከምናቤ ፡ ድንበር።
ልናፍቃ ፡ ልተክዝ
ነፍሴ ፡ እንድትቦርቅ
ካለፈው ፡ ትዝታ ፤
ከምርጡ ፡ ልታረቅ።
እኔ ፡ ከእራሴ ፡ ጋር
በልክ ፡ እንዳወጋ፤
ዝምታን ፡ እንዲያከብር
የነገር ፡ አለንጋ፤
ነውና ፡ ጋሻዬ ፡ ለህልሜ ፡ ጠበቃ
ሌላ ፡ አልፈልግም ፤
፧
ስጡኝ፥
ቡና ፣ መፅሀፍ ፣ ብእርና' ሙዚቃ።
5/2/19
©ezra kassahun
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ስፈራ በተስፋ
እስትንፋሴን እምቅ
አየር ምን አባቱ...፤
፧
ዘመን ከተዋጀ
ሳዝን አጨብጭቤ
የዘራሁት ደርሶ
ያጨድኩትም ጎድሎ'
አየሁ ተደብቄ።
፧
አየሁኝ.............
አግኝቼ አጥቼ
በኩርማን እንጀራ
ቀኔን አንጣጥቼ
ሕመሞች ማያልፉኝ
ቆየው...........፥
ደስታዬም ነጥፎብኝ።
፧
አለው
አንድ እኔ የሰው ልጅ
የተውኩት ችላ ያልኩት ቀንቶ
ውሃ ያላጠጣሁት አብቦና ፈክቶ
በመፈለግ ትክት ልቤ ግራ ገብቶት።
፧
በነተበች ነፍስ ውስጥ
በዚህ የጊዜ ንፋስ
በዚህ የሕይወት ቅዠት
እንኳን ለመቆም አይደለም
ለማረፍ እኔ የለኝም እረፍት።
፧
ደሞ ለዳተኛ
መቆም አይቻልም
ወደፊት ከመዳህ
መንገድ ከመከተል
ሌላ አማራጭ የለም።
፧
እናም መጨረሻው
ጥላዬ ሳይጠፋ
በብዕሬ ላስቀምጠው
እሾሁ አቁስሎ ፍሬው የፈካበት
..................የጊዜን እጥፋት
የነበርኩበትን የዳናዬን መስር
የተሰበረውን የከረመውን ሀቅ።
©ezra kassahun
27/1/19
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
እናቴ አደራ አስብላኝ
አላፊ ጠልፎ እንዳይረሳኝ
ለሚቀር......................
ቃል ስቼ እንዳልቀር፥
ለሚሞት.....................
ነፍሴን ሰጥቼ እንዳልከስር፤
ፀጥ!
ለአላፊው አፌን ሳልከፍተው
ዝግ' ዝም ብዬ እንድተው።
፧
እናቴ አደራ ብላኝ
ተባይ' ቃል እሳት የሚጭር
ትንፋሽ ሚያሳጥር....፥
ነዳፊ ጩኸታም ቢያዝብኝ
ከንፈሬ ደርቆ ምላሴ ታስሮ
ስንቱን ዝም አልኩት
አይቼ አለፍኩት
ታዝቤ ተውኩት
.................መኣት እሮሮ።
፧
ዙሪያዬ የነገር እቁብ
ዘመኑ የበቀል ወፍጮ
ሀሳቤን ላይቀበሉት
ላይቆጥሩት ከቁብ፥
ጣል ቢሉኝ ቃል ከኣንደበቴ
አደራ ይዞኝ የእናቴ፤
አቋምና አቅሜን ደብቄ
ስንቱን አሳለፍኩት ታምቄ፣
የዋህ..............
ራሴን አለማወቄ!
፧
የሚያልፈው ካፊያ ሳይመታኝ
ለማለፍ ዙሪያዬን ስቃኝ
በአየሁት ቃሌ እየቃጣ
ስውጠው ፈርቼ ጣጣ፤
ሳምቀው ኖሬ ሳፍነው.
ምስኪን!
ይሁሉ ድካም እኔው ለማልፈው!
©ezra kassahun
22/1/19
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ቀዥቃዣ ልቧ ከእኔ ረጋ ያለ ግራ መጋባት ጋር ስትገናኝ፤ ማንም የማይረዳውን ድንበር አልባ መኖሬን ታገኘዋለች። መውደዷ የማይከብድ ጉልበት አለው።
፧
ለዛም' ይመስኛል ዓለም ሥርዓትና አጥር ስትፈልግ፥ እኛ የሌሊቱን ንፋስ በቅዱስ ወሲብ የምንባርከው። መሸሸጊያችንም አልጋችን ግን ስሜት ብቻ አይደለም። ከንጋትም ጋር የምንወዳጀው በራሳችን ህግ ነበር።
፧
ተፈጥሮ ጠዋት ነው ብላ ቁጥርና ስም ልትሰጠን ከምስራቅ ብቅ ስትል እኛ ገና ትንፋሽ ከመዋዋስ አንወጣም ነበር። የነጋው ከቅዱሱ ተግባር ላልሆኑት ነው፤ ለእኛ የሌሊቱ ድፍረታችን ይቀጥላል።
፧
ፍሬው ከገለባ በንፋስ እንደሚለይ ፥ ያልተጨከነበት ፍቅር፤ ያልተረጋጋች ነፍስ ፥ የነበረበትን አጥር ሁሉ አፍርሶ ሜዳ ላይ የሚያስቀር ውብ ድፍረት አለው።
፤
ትዝታ በነበር ብቻ መወሰኑ ያናድዳል!
፧
@melos3
©ezra kassahun
21/1/19
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
የጥል መጋረጃ የብርሃኑን በር ጋርዶ
ሰው በራሱ ምስጢርና እውነት ተናዶ
በእሳትና ውኃ መካከል ሲጋደል
በእምነት ጭልፋ ከሐሰት ድስት ይቀዳል
እያወቀም ይሁን ወይም በቸልታ
የራሱን ምስጢር ከራሱ ይጥላል።
ይሄ መቅበዝበዙ
የነፍሱን እንቆቅልሽ ሊፈታው ሲቃረብ
ወዴት ይሄዳል ሲጣደፍ መነሻው ተረስቶት
ማን ማንንስ ፍለጋ ይከንፋል ተራርቦት?
ሰው በብርሃንና በጥላ መካከል የሚወዛወዝ፣ የራሱን ምስጢር ለመፍታት ሲታገል የራሱ እንቆቅልሽ የሚሆን ጥልቅ ፍጡር ነው። በእሳቱ የሚቃጠለውንና የሚያቃጥለውን ያህል በውኃው የሚበርድ፣ በሐሳብ ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የexistenceን ትርጉም ይፈልጋል።
የነፍሱን ጥያቄዎች ለመመለስ በራሱ የልብ ምት ውስጥ ይጓዛል። ነገር ግን የመልሱን በር ለመክፈት ሲቃረብ የራሱን ጥላ ፈርቶ ወደ ኋላ ይመለሳል። በመንፈሱ ውስጥ የሚነደውን እሳት በቃል አልባ ሕመም እያዳፈነ፤ ከምድር አፈርና ከሰማይ መንፈስ የተሰራውን እውነተኛ ማንነቱን ፍለጋ ይደክማል፥ ይኳትናል። በመጨረሻም ፈጣሪን ወይም ሰውን ለማወቅ ሲሻ፥ በመስታወቱ ውስጥ የተደቀነውን የራሱን ምስጢራዊ ገጽታ እያየ በተመስጦ ይቆማል።
©ezra kassahun
20/1/19
@melos3
2 836
አንድ-አንዴ እወድሻለሁ....‼️
፧፧፧፧፧
ከውቂያኖሱ ዳር ከማዕበሉ ጠርዝ
ከነጣው አሸዋ ባልኖር ከአጠገብሽ
በቃላት ፍተጋ በሆሄሃት ዳዴ አሁን የምነግርሽ
አንድ-አንዴ ስወድሻ'ለሁ።
፧፧፧
በእርግጥ ፤ አንዴ ነሽ እኔም አንድሽ
በመፍጠር እውነት በቀናት ጉም ዝግነት
ለነፍሴ ውሃ ልክ በልኬ የተሰራሽ።
፧፧፧
አንቺ ንፅህና ፥ የቀናነት ሙዳይ
የክብር ዙፋኑ ከውሸት ተገንጣይ
የአንዴ ውበት ፥ የአንድ ጊዜ ስጦታ
የትህትና እናት የመኖር ከፍታ።
፧፧፧
ጥዑም ለሚሰማሽ ማትሰለች ዜማ
ልብን ምትዳብሽ............፤
እንደ ታቦት ሸኚ ዝማሬና እልልታ።
የደስታ እርካቡ ለሀሴት እርጋታ
ለህይወት ጋጋታ ምትታመኝ አለኝታ።
፧፧፧
አንድ በሆነው ልቤ፣ በበራው ስንቅሽ
ባለፈው ትዝታ በዛሬው እውነትሽ፤
እወድሻለሁኝ በአንዴም በአንድሽ።
፧፧፧
አንድ በአሃዝ ቁጥር፣ አንዴ በጊዜ ስፍር፣
ቀመር የማይተካው፣ የነፍሴ መዘውር፤
ጊዜውን የቀደምሽ ችሎም' ማይመልስሽ፣
የፅናት ጉልላት ፤ ትውስታሽ የቅጽበታት ክምር።
፧፧፧
አንድ ነሽ በአካል፣ የለሽም አምሳያ፣
አንዴ ነሽ በምድር፣ የኑሮዬ መንታ
የተስፋ መስታውት፥ የህይወት መታያ።
፧፧፧
ስለዚህ እወድሻለሁ...
ከመኖር ሚተርፈው ትዝታ ቢሆንም
ዘመን በማይደግመው፣ በአንዱ ማንነትሽ፣
አንዴ በተሰጠኝ፣ በዚያ በአንድ ፍቅርሽ።
©ezra kassahun
24/9/18
@melos3
@melos3
2 836
A small irony of human history: nearly everyone admires leaders after success arrives, but very few notice the countless days when those same people were simply doing the difficult, unglamorous work of turning a dream into reality. That's where leadership actually lives. ✨
The difference between a dreamer and a leader is action.
A dreamer imagines a better future. A leader works to create it. A dreamer sees opportunities. A leader pursues them. A dreamer waits for change. A leader becomes the change.
Dreams are the starting point. Leadership is the journey that turns dreams into reality.
Dream boldly. Lead courageously. Act consistently.
🚀 #CorelDen #Leadership #Growth #Success #PersonalDevelopment
2 836
☕ Corel Den Coffee Meetup — We’re Back
After a short break, we’re excited to welcome you back this Sunday for another meaningful conversation and networking experience.
🎙 Discussion Topic:
“Why Is Poverty Romanticized in Our Society?”
In many communities, struggle is often praised more than success.
People are sometimes respected for suffering quietly, yet judged for becoming financially successful.
Why does this happen?
Is wealth misunderstood in our culture?
Are we taught survival more than financial growth?
Join us for an open and thoughtful discussion around money, mindset, culture, and Ethiopian social beliefs.
📍 Location: Shalom Cafe — Aposto 3M Building, 3rd Floor
🗓 Sunday
🕘 9:00 Afternoon (Local Time)
☕ Meaningful conversations
🤝 Valuable connections
🧠 Different perspectives
We look forward to seeing you there.
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
ፀሀይ ለሁሉም ቀን አዲስ ቀን ይዛ አትመጣም። አንዳንዱ ቀን ራሱን ይደግማል ።ደግሞ አንዳንዱ ዕለት የምስራች ይዞ ሲመጣ ፣ ሌላው ቀን መርዶ ሊተረክክ ወጋገን ይሰዳል።
በሌላኛው ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ የቤታችን ቆርቆሮ ክዳን በላይችን ላይ አልነበረም። ዓይኖቼ ያረፉት ወደ ሰማያዊ ሰማይ ነበር።በደመ ነፍስ እየተጣዳፍኩ ከወደቅኩበት ተነሰቼ ወደ አባ አመራሁ።ልባቸው እንደ ከበሮ መደለቅ ጀምራ ቁና ቁና እየተነፈሱ ሲያጣጥሩ ከአልጋቸው አጠገብ ደረስኩ። ቤታችን ቅሪት እንኳ አልነበረውም። አውላላ ሜዳ ላይ ነበርን።
ጦርነቱ በህልውናዬ ላይ የፈጠረው ኪሳራ ነበር። ሕይወቴንና ማንነቴን በአንድ አፍታ ቀይሮታል። የማንነቴ ካስማ የተጣለበት ስፍራ እንዳልነበር ኾኗል። በዙሪያዬ ነፍሴን የማስጠልልበት ዓለም አልነበረኝም።
ደካሞች እግዚአብሔርን ምርኩዛቸው ሲያደርጉ ኃያላን ግን በሥልጣናቸው ይመካሉ። ታሪክ የሚያስረዳው ፈጣሪ ይህችን ምድር ይፍጠራት እንጂ በአዛዥ ናዛዥነት የሚያስተዳድሯት ሊቀ መናብርት ሰዎች ናቸው። በየዕለቱ ንጹሓን በግፍ ይገደላሉ። በጨለማ የማሰቃያ ማጎሪያዎች የምስኪኖች ቅስም እንደ አጥንት ሲከተከት እግዚአብሔር የፍጥረታቱን የማያልቅ ሰቆቃቸው እየታዘበ ስለምን ዝም አለ?
ስንት ሰው ሲሞት ነው የእግዚአብሔር ኃይል የሚገለጠው? በመንግሥተ ሰማያት መካሻ ስላዘጋጀ በሰው ልጆች ምድራዊ ሕይወት ጣልቃ አይገባም? ወይስ እንደ ቅጠል የሚረግፉትን ንጹሐን ይታደጋቸው ዘንድ በእርሱ ላይ ያላቸው እምነት ጎዶሎ ነው? ፈጣሪን ልክ ለማድረግ በሚኬድ ርቀት እግዚአብሔር እንዲታደጋቸው ያስጥላቸው ዘንድ ቢማጸኑትም እጁን ከአርያም ሳይሰድላቸው ቀርቶ መከራ ሞትን የተቀበሉ ሰዎች የሰማዕትነት ማዕረግ አልተሰጣቸውምን? ይህስ የሕይወት ወለፈንዲዊነት አይደለምን?
ይህ መከራና ሰቆቃ ዕውቅና የለሽ ነው። እንደ አደባባይ ምሥጢር በግልጽ የሚያወራው የለም። መሃል ከተማ ጥሩ ቀን እያለፈ ይመስላል። የዳር ሀገር ጩኸት የመሀሉ ሀገር ግድ አይሰጠውም እዚ የተለኮሰው እሳት እዛ አይደርስ ይመስል!!
መሽቶ ሲነጋ ከፀሓይ መውጣት ጋር ለኑሯቸው የሚዳክሩ ሰዎች ማልደው ከእንቅልፋቸው ይነቃሉ። በዚህች ቀን ማን መንቃትን በብርቱ እየተመኘ እስከ መጨረሻው አሸልቦ ይኾን? ማንስ በጥልቅ ከዚህች መከረኛ ሕይወት መገላገል እንደ ፈለገ ሳይሳካለት ቀረ ይኾን?
ይብቃ‼️‼️‼️
@melos3
©zephilosophy
2 836
Paying Tribute to the Hands That Create the Future 🛠️🌍
We take a moment on this to honor the thinkers, builders, problem-solvers, and doers who quietly drive progress. 👏
Every system that functions flawlessly, every structure that stands tall, and every vision that comes to pass is the result of a professional who prioritized consistency over comfort and discipline over recognition. ⚙️🏗️
At Corel Den, we value the mindset that goes into work as much as the work itself: dedication, perseverance, and the benchmark for greatness. 🎯
This is more than just a holiday. It’s a reminder. ⏳
A reminder that advancement is constructed rather than desired.🧱Success is earned, not bestowed.🏆And that all professionals, across all industries, contribute to creating a better tomorrow. 🚀
This is your day if you show up, deliver, and take the initiative‼️
#GrowthMindset #LeadershipMatters #InternationalWorkersDay
#CorelDen #FutureOfWork #Entrepreneurship #BrandLeadership
2 836
‼️I noticed such a thing, a poor person has no understanding of what resources are.
The poor man thinks:
“Yes, I have nothing. I have no money"
In fact, any person, even the poor, especially the young and poor, has:
• The most important resource called “Energy”
• The second main resource called “Time”
• The third resource is “Knowledge”
• The fourth resource is money and the rest. Money comes last!
That is, you have a bunch of resources that you can convert into each other.
All resources are converted into each other!💥
🗣 Margulan Seisembayev
https://t.me/corelden
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
«My crime was feeling everything too deeply _»
Fyodor Dostoevsky
፧
Depth is not a gift.
It is a liability in a shallow world. To feel deeply is to refuse numbness. To see meaning where others see routine. To carry weight others are too distracted to notice. That is the crime.
The Real Punishment
«…my punishment was surviving it.»
Not death. Not collapse. But continuation. Because surviving means remembering. It means carrying every disappointment, every truth, every realization without escape. Most people are protected by ignorance.
We are not.
The Hidden Cost of Awareness
Depth isolates. We start to see through people their words, their masks, their inconsistencies. Conversations become predictable. Connections become rare. And slowly, the world feels smaller not because it is, but because we outgrow it.
The Critical Truth
Feeling deeply is not the problem.
Staying there is. If depth does not transform into:
clarity
control
creation
Then it becomes self-destruction.
©ezra kassahun
@melos3
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
መውለድ ሞራላዊ ነውን?አንድ ሰው ወደዚህ ዓለም ከመጣ ቢያንስ ጥቂት ስቃዮችን መቅመሱ የማይቀር ሀቅ ነው ይህ ደግሞ የህይወት ጨለማው ገጽታ ነው። ከአደጋ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አደጋን አስቀድሞ ማስቀረት የተሻለና አስተዋይነት የተሞላበት የሞራል ምርጫ ነው። ስለዚህ አዲስ ህይወትን አለመፍጠር ማለት ሊመጣ የሚችለውን እርግጠኛ ስቃይና መከራ አስቀድሞ መግታት ማለት ነው።
ተፈጥሮ የሰጠችን ጉቦ እና አንቲናታሊዝምአንቲናታሊዝም አንድን ሰው ወደዚህ ዓለም አለማምጣት የተሻለ የሞራል ምርጫ ነው ይላል። ታዲያ የሰው ልጅ ይህንን አመክንዮ ስቶ ለምን መውለዱን ቀጠለ? ለዚህ ጥያቄ ጓደኛዬ አንድ የሚገርም ምልከታ ሰጥቶኛል፦ ወሲብ እንደ መጨባበጥ ያለ ምንም እርካታ የሌለው ተራ ድርጊት ቢሆን ኖሮ ስንት ሰው ይወለድ ነበር?" ተፈጥሮ የሰው ልጅ መወለድ ያለውን ስቃይ እና ሃላፊነት አስቦ እንዳይተወው ወሲብን በከፍተኛ ደስታ ሸፍናዋለች። ተፈጥሮ የራሷን ዓላማ (ዝርያን ማስቀጠል) ለመፈጸም እኛን በደስታ ስሜት ታታልለናለች። እኛ ለራሳችን ደስታ የምናደርገው ይመስለናል ግን እያገለገልን ያለነው የእኛን ደስታ ግድ የማይላትን ተፈጥሮን ነው። ሰው የሚወለደው በወላጆቹ ደቂቃዊ እርካታ ምክንያት ነው። ነገር ግን ለዚያች ደቂቃዊ እርካታ ሲባል የሚፈጠረው አዲስ ሰው የህይወትን ሙሉ ስቃይ ይጋፈጣል። ሀይማኖይቶች ልክ ሚሆኑበት እድል ካለ የገሃነም ስጋት እና ለዘላለም አደጋ ይጋለጣል። ይሄ ሁሉ የሚሆነው ግን እሱ ሳይስማማ ነው። በሌላ አነጋገር የወላጆች ደስታ የልጁ እጣ ፈንታ ላይ ቁማር ይጫወታል ወሲብ እንደ መጨባበጥ ተራ ቢሆን ኖሮ የሰው ልጅ በምክንያታዊነት ያስብ ነበር።ይህ ልጅ ሲወለድ የሚደርስበት ስቃይ ዋጋ አለው? ብሎ ይጠይቅ ነበር። ተፈጥሮ ግን ይህ ጥያቄ እንዳይነሳ አእምሯችንን በወሲብ ደስታ በሆርሞን ትጋርደዋለች። አንቲናታሊዝም ግን ይህንን የሆርሞን ግርዶሽ ገልጠን በምክንያት እንድንወስን ይጋብዘናል የሰው ልጅ መብዛት የጥበቡ ውጤት ሳይሆን የተፈጥሮ የወሲብ ደስታ ጉቦ ውጤት ነው። ያ ጉቦ ባይኖር ኖሮ ማንም ሰው በራሱ ፈቃድ ወደዚህ አስቸጋሪ ዓለም ሌላ ሰው አይጋብዝም ነበር። እናንተስ ምን ታስባላችሁ? መውለድ የነጻ ምርጫ ውጤት ነው ወይስ የተፈጥሮ ወጥመድ? @melos3 @melos3 #life true meaning
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
Fasika is not just a celebration it’s a reflection. ✨
Coz ፆም፣ ጸሎት እና ሥርዓትን ብቻ አይደለም የሚያሳየን it’s how we treat others that defines us. 🤝
«መንፈሳዊነት genuinely በምናደርገው ነው የሚለካው ፥ እንጂ በምንናገረውና በሥርዓታችን ብቻ አይደለም።»
ፆም እና ጸሎት ከፍ ያሉ መንፈሳዊ ልምዶች ቢሆኑም፣ እውነተኛው ፍሬያቸው ለሰዎች የምናሳየው ምሕረት፣ ክብር እና ፍቅር ነው። ❤️
ይህ ተግባር ደሞ ከሰው ጋር የምንኖርበትን የነፍሳችን ጥራት የሚታይበት የህሊና መስታወት ነው ብዬ አምናለሁ።
ፋሲካ ደሞ የመከራ መጨረሻ እና የእድሳት መጀመሪያ ነው። 🌅 ይህም ከውጭ ልማዶች ወደ ውስጣዊ ለውጥ መሻገር ነው።
የክርስቶስ መነሳት መታሰብ መልዕክቱም ይህ ነው፦
፧
ይቅር ማለት ከክብር ጋር 🤍
ሰውን ከፍ ማድረግ ከትህትና ጋር 🙏
በፍቅር እና በ'ርካታ መኖር ከእርጋታ ጋር 🌿
ምክንያቱም true resurrection is not just spiritual it is behavioral.
That is why our actions toward people are the true mirror of our soul. 🪞
በዚህ ፋሲካ፣ let’s go beyond tradition - kindness, respect, and forgiveness should be our real practice. 🌍
እንግዲህ ይህ ፋሲካ ፆምና ጸሎት እንዲሁም የምግብ እልህ መወጫ አይሁን፤ በህይወታችን ለመንፈሳዊ እይታችን መንቃት ይሁን።
Happy Fasika 🍾 let our life reflect our faith. ✨
#Easter #Reflection #FaithInAction #SpiritualGrowth #Leadership #Values #Kindness #Respect #Forgiveness
2 836
Repost from እዝራ ካሳሁን / Ezra Kassahun
Manipulation
ብዙ ጊዜ በፍልስፍና እና የስነልቦና ውይይቶች ውስጥ በተለይም በሃይማኖት እና ፖለቲካ ርዕሶች ላይ Manipulation የሚል ቃል እንጠቀማለን። ይህ ግን ቃል ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆነ ሃሳብም ጭምር ነው።
Manipulation ምንድን ነው? ማኒፒዩሌሽን የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ማታለል ወይም ማጭበርበር ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን ሃሳቡም:
የሰዎች ሃሳብ፣ ስሜት ወይም ድርጊት ላይ ከዕውቅናቸው ውጪ ወይም ሳያስተውሉት ተጽዕኖ ማድረስ ወይም መቆጣጠር የሚል ነው።
Manipulation ግልጽ የሆነ ስለት ያለው ዓይነት ብቻ ሳይሆን ፈገግታ የሚለብሰም ነው። ፍቅርን፣ ፍርሀትን እና ቋንቋን እንደ መሳሪያ የሚጠቀም አይነት ነው።
Manipulation ስለ ጥንካሬ አይደለም። ትክክለኛውን ስሜታዊ ጊዜ የመጠበቅ ችሎታ ነው። ስትደክሙ፣ አብሮነትን ስትራቡ ወይም ትርጉም ስፈልጉ ያውቃል። በሩን አይንኳኳም—በወረስናቸው ታሪኮች እና እኛ ለመፈተሽ በጣም በምንፈራቸው እምነቶች ውስጥ ይንሸራተታል።
ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በመተማመን ነው። አንድ ሰው የእናንተን እሴቶች ያንጸባርቃል፣ ቋንቋችሁን ይናገራል፣ ፍርሃታችሁን “ቅዱስ”፣ ህመማችሁን “የእቅዱ አካል” ብሎ ይጠራቸዋል። ድንገት ስትነቁ እሱን እየተከተላችሁ አይደለም—እሱ እንድትሆኑ የገነባላችሁን የእራሳችሁን ስሪት እየተከተላችሁ ነው።
Manipulation በሃይማኖታዊ አመራር ውስጥ እንደ መለኮታዊ ማስፈራሪያ ሆኖ ይመጣል።
“ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ አትጠይቁ” ተብላችኋል።
ግን የእግዚአብሔር ድምፅ ጭምብል ለብሶ ወግ ቢሆንስ የሚያስተጋባው?
የገሃነም ፍርሃት፣ የመዳን ተስፋ—እነዚህ ሁልጊዜ መንፈሳዊ እውነቶች አይደሉም። ስሜታዊ መልህቆች ናቸው። እምነትን እየመረጣችሁ አይደለም። ከእሳት እየሸሻችሁ ነው።
በፖለቲካውም ውስጥ ተመሳሳይ ቲያትር ነው።
መሪዎች “እኛ የህዝብ ነን እነሱ ጠላት ናቸው” ይላሉ።
እና ልክ እንደዚህ ውስብስብነት አፈር ይበላዋል።
Manipulation ሐሰተኛ ግልጽነትን ይፈጥራል። እንድታስቡ አይፈልጉም—ቶሎ ምላሽ እንድትሰጡ ይፈልጋሉ፣ እንድታስተጋቡ።
ቁጣ ምንዛሬ ይሆናል። ታዛዥነት መልካም ባህርይ ይሆናል። ጥርጣሬ ክህደት ይሆናል።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ እውነተኛ ችግሮች— ድህነት፣ ኢፍትሃዊነት፣ ድንቁርና—ዝምታን ለብሰው ባሉበት ነው።
አንዳንዶች "ሁሉም Manipulation ክፉ አይደለም
አንዳንድ ጊዜ እናት ለልጇ ስለ ከባድ እውነት ለስላሳ ታሪክ ትናገራለች።
አንዳንድ ጊዜ አስተማሪ የተኛ አእምሮን ለመቀስቀስ ምቾት መንሳት ያመጣል።
ያ ጭካኔ አይደለም—ስልታዊ እንክብካቤ ነው።" ሲሉ ይሞግታሉ።
ስለዚህ ጥያቄው የሚሆነው: የማንቂያ Manipulation ስህተት ነው?
ወይስ አሳሪ ሰንሰለት ሲሆን ብቻ ነው ስህተት የሚሆነው?
እና ከዚያ Self-manipulation አለ—በጣም ቅርብ የሆነ አይነት—ራስን ማጭበርበር።
መታዘዝ ጥበብ እንደሆነ እራሳችንን እናሳምነዋለን።
የተወረሱ እሴቶችን እንደ ግላዊ እውነቶች እንቆጥራለን።
ጥርጣሬን ባላየ ፈገግ እንላለን።
ሥነ ምግባር ብለን እንጠራዋለን፤ ግን ምናልባት የተለባበሰ ፍርሃት ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ Manipulationን እንዴት እንዋጋለን?
በንዴት አይደለም። በኩራት አይደለም። በግልጽነት ብቻ።
እንጠይቃለን፡ ይህ እምነት ከየት ነው የመጣው?
የማንን ድምጽ ነው የምታዘዘው?
እያሰብኩ ነው—ወይስ ሀሳብን እየተወንኩ?
ማጭበርበር አንዴ ከተሰየመ ኃይሉን ያጣል።
እና ፍርሃት አንዴ ከተጠየቀ፣ መንገዳችንን ሊመራ አይችልም።
ቀዳማዊ ፍልስፍና
(ዮናታን በጋሻው)
@melos3
@melos3
