cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Більше
Рекламні дописи
34 490
Підписники
+1624 години
+1047 днів
+67130 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
ላብ አደር በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥32 ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا "አደር" ማለት የዕለት ለዕለት የአኗኗርን ዘይቤን ለማመልከት የሚመጣ ፈሊጣዊ አነጋር እንጂ "አዳር" ከሚለው ቃል የሚሳለጥ አይደለም፥ ለምሳሌ፦ "ሠርቶ አደር" "ወጥቶ አደር" "አርሶ አደር" "አርብቶ አደር" "ወዝ አደር" "ላብ አደር" ሲባል ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ስለ ላብ አደር የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ" ብለው ነግረውናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 8 ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَعْطُوا الأَجِيرَ أَجْرَهُ قَبْلَ أَنْ يَجِفَّ عَرَقُهُ ‏"‏ ‏.‏ አንድ አሠሪ የሠራተኛውን ላብ የማይከፍል ከሆነ አሏህ በትንሣኤ ቀን ከሚጻረራቸው ሦስት ሰዎች አንዱ ይሆናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 7 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሥስት ሰዎች ተጻራሪ ነኝ፥ እኔ የማንም ተጻራሪ ከሆንኩ በትንሣኤ ቀን አሸንፈዋለሁ። በስሜ ቃል የገባ ከዚያም የሚያታልል ሰው፣ ነጻ ሰው ሸጦ ዋጋውን የሚበላ ሰው እና ሠራተኛ የሚቀጥር እና ተጠቅሞበት ከዚያም ደመወዙን የማይሰጥ ሰው ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ أَنَا خَصْمُهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَمَنْ كُنْتُ خَصْمَهُ خَصَمْتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ رَجُلٌ أَعْطَى بِي ثُمَّ غَدَرَ وَرَجُلٌ بَاعَ حُرًّا فَأَكَلَ ثَمَنَهُ وَرَجُلٌ اسْتَأْجَرَ أَجِيرًا فَاسْتَوْفَى مِنْهُ وَلَمْ يُوفِهِ أَجْرَهُ ‏"‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯችንን በመካከላችን አከፋሏል፥ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ሀብትን ሰጥቶአል፦ 43፥32 እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናት፡፡ أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَ ۚ نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا ۗ وَرَحْمَتُ رَبِّكَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ የአሏህ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናትና ላብ አደርን በዙልም በመዞለም ጀነት ተነፍጎ አሏህ ከሚጻረረን አሏህን ፈርተን የላብ አደሩን ሐቅ መስጠት ትሩፋት አለው። ዲኒል ኢሥላም የሚያስከብረው ላብ አደርን እንጂ የላብ አደር ቀንን አይደለምና ላብ አደርን እናክብር! አምላካችን አሏህ የሰዎችን ሐቅ ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
3 62025Loading...
02
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦ ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦ ማቴዎስ 26፥26-27 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28: ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል። ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት!  የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው።                                                                     አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።    ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
4 43430Loading...
03
የሰው ሥጋ በባይብል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ እስራኤላውያን በሚያጠፉት ጥፋት አምላክ ቅጣቱ የወንዶች ልጆቻቸውን እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ማድረግ ነበር፦ ዘሌዋውያን 26፥29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፥ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። "ትበላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው ባስጨነቋቸው እና መከራ ባሳይዋቸው ጊዜ የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ነግሯቸዋል፦ ዘዳግም 28፥53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶች እና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ። ለእስራኤላውያን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ የሚያበላው እራሱ አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦ ኤርምያስ 19፥9 የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ "አበላቸዋለሁ"። "አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋል ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ ምን ዓይነት ቅጣት ይሆን? አስበይው አምላክ በይው እስራኤላውያንን ናቸው። በዚህ ምክንያት አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፦ ሕዝቅኤል 5፥10 ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን "ይበላሉ" ልጆችም አባቶቻቸውን "ይበላሉ"። ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦ ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል። ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም። የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦ ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች። በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦ 2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት። ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን?
3 39024Loading...
04
يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
10Loading...
05
የሰው ሥጋ በባይብል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ እስራኤላውያን በሚያጠፉት ጥፋት አምላክ ቅጣቱ የወንዶች ልጆቻቸውን እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ማድረግ ነበር፦ ዘሌዋውያን 26፥29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፥ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። "ትበላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው ባስጨነቋቸው እና መከራ ባሳይዋቸው ጊዜ የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ነግሯቸዋል፦ ዘዳግም 28፥53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶች እና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ። ለእስራኤላውያን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ የሚያበላው እራሱ አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦ ኤርምያስ 19፥9 የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ "አበላቸዋለሁ"። "አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋል ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ ምን ዓይነት ቅጣት ይሆን? አስበይው አምላክ በይው እስራኤላውያንን ናቸው። በዚህ ምክንያት አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፦ ሕዝቅኤል 5፥10 ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን "ይበላሉ" ልጆችም አባቶቻቸውን "ይበላሉ"። ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦ ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል። ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም። የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦ ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች። በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦ 2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት። ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን? ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦ ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦ ማቴዎስ 26፥26-27 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28: ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል። ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት! የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው። አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ
3 64230Loading...
06
Media files
8 89835Loading...
07
"የስላሴ እሳቤ" እና "የተደበቀው እውነት" መጽሀፍ ከአ/አበባ በተጨማሪ አዳማ እና ደሴ ይገኛሉ። አዳማ መጽሀፉን የምትፈልጉ call +251966640370 ደሴ :-አረብገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ          ሸርፍተራ ፋጡማ መክተባ እንዲሁም አህመድ መክተባ ይገኛል አ/አበባ call 0920781016
5863Loading...
08
ግርዶ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ ጭሮ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ጸብ አጫሪ መሆንን ምርጫቸው ያረጉ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "ጸብ በደላላ ካልሆነልን" ብለው ለገላይ በማያመች "ያዙኝ ልቀቁኝ ደግፉኝ ጣሉኝ" በማለት መፎለሉን፣ ማቅራራቱን፣ መሸለሉን፣ መፎከሩን ተያይዘውታል። "አሏህ እንደ እንስት ሒጃብ ይለብሳል" በማለት የሌለ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ያፅፃሉ። ምሁራን "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" እንደሚሉ ስለ ሒጃብ ከሥር መሠረቱ ኢንሻላህ እንመልከት! "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ሸፈነ" "ጋረደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ"cover" "መጋረጃ"curtain" "ግርዶ"screen" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ መርየም ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 19፥17 ከእነርሱም "መጋረጃን" አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا እዚህ አንቀጽ ላይ "መጋረጃ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب እንደሆነ ልብ አድርግ! በተጨማሪ የጀነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከል ያለው አዕራፍ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ስለዚህ "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም አለው። ለተጨማሪ ግንዛቤ እነዚህ አናቅጽ ተመልከት፦ 17፥45 38፥32 41፥5 ሌላው ሴት ልጅ የምትሰተርበት ጉፍታ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦ 33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህ እና ለምእምናን ሚስቶች ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 312 ዑመር"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ "እኔ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ሰናይ እና እኩይ ሰዎች ወደ እርሶ ይገባሉ፥ ለምእመናን እናቶች በሒጃብ እንድታሰትራቸው አስጤናለው" አልኩኝ፥ ከዚያም አሏህ የሒጃብ አንቀጽ አወረደ"። قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، يَدْخُلُ عَلَيْكَ الْبَرُّ وَالْفَاجِرُ، فَلَوْ أَمَرْتَ أُمَّهَاتِ الْمُؤْمِنِينَ بِالْحِجَابِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ آيَةَ الْحِجَابِ‏.‏ እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ አንድን ሰው ነቢይ አርድጎ ለማስነሳት በግልጠት ከሚያናግርበት መንገድ አንዱ ከግርዶ ወዲያ ነው፦ 42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب ሲሆን አሏህን ሳያዩ በድምፅ ብቻ መስማት ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በለይለቱል ኢሥራእ ወል ሚራጅ ጊዜ አምስት ወቅት ሶላትን ሲቀበሉ ያዩት ይህ ሒጃብ ብርሃን ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 350 አቢ ዘር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛን”ﷺ” ጌታህን አይተከዋልን? ብዬ ጠየኳቸው። እርሳቸው፦ "ያየሁት ብርሃን ነው፥ እንዴት እርሱን ማየት እችላለው? አሉ። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم هَلْ رَأَيْتَ رَبَّكَ قَالَ ‏ “‏ نُورٌ أَنَّى أَرَاهُ ‏”‏ ‏.‏ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 201 አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አሏህ አይተኛም፥ እርሱ መተኛት አይገባውም። እርሱ ሚዛኖችን ዝቅ ያረጋል ያነሳልም፥ የእርሱ ግርዶ ብርሃን ነው። أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنَامُ وَلاَ يَنْبَغِي لَهُ أَنْ يَنَامَ يَخْفِضُ الْقِسْطَ وَيَرْفَعُهُ حِجَابُهُ النُّورُ "መንጦላዕት" የሚለው የግዕዙ ቃል "አንጦልዐ" ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥረወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጋረጃ" ማለት ነው። የፈጣሪ መጋረጃ ብርሃን ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል በብርሃን መጋረጃ ይኖራል፦ መዝሙር 31፥20 በፊትህ "መጋረጃ" ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ። תסתירם בסתר פניך מרכסי איש መዝሙር 4፥6 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። ያህዌህ ሆይ! የፊትህ "ብርሃን" በላያችን ታወቀ። רַבִּ֥ים אֹמְרִים֮ מִֽי־יַרְאֵ֪נוּ֫ טֹ֥וב נְֽסָה־עָ֭לֵינוּ אֹ֨ור פָּנֶ֬יךָ יְהוָֽה׃ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። አንድ ሰው እንኳ ያለየው እና ሊያየው የማይቻለው በብርሃን መጋረጃ ስለሚኖር ነው። ከመስማት እና ከመስማማት ይልቅ የመደናቆር እና የመጻረር አባዜ ስለተጠናወታቸው እንጂ በትውፊት እና በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ "ሰባቱ መንጦላይት" የሚባሉት "ሰባቱ የእሳት መጋረጃ" ሲሆኑ አምላክ በእነዚህ ሰባት የእሳት መጋረጃ የተሰወረ ነው፦ ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ ቁጥር 14 "ሥላሴ "በእሳት መጋረጃ" ውስጥ የተሰወረ ነው"። መዓዛ ቅዳሴ ምዕራፍ 1 ቁጥር 51 "በሱራፌል መካከል "የእሳት መጋረጃ" በፊቱ ጋረደ፥ አሳቡን የሚያውቅ የለም። አኳኃኑን የሚረዳ የለም፥ ስውር በሆነ መሰወሪያው እራሱን ሰወረ"። እንግዲህ ቅንፍጥፍ በማለት ከማዛግ ይልቅ ቅልጥፍጥፍ ብላችሁ በአርምሞ እና በጥሞና ብትመረምሩ እና ብትመራመሩ የአሏህ ምሪት ለማግኘት መደንርደሪያ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
7 33429Loading...
09
1. ጥያቄ ካላችሁ፣ 2. መረጃ ከፈለጋችሁ፣ 3. መሥለም ከፈለጋችሁ በዚህ አድራሻ አግኙኝ፦ https://m.me/Wahidapologist
7 10077Loading...
10
"የተደበቀዉ እዉነት" የሚል መጽሐፍ Abdu Book Delivery እኛም ጋር ያገኙታል። አድራሻችን፦ አዲስ አበባ ፒያሳ ለበለጠ መረጃ በ 0929574133 ይደዉሉልን! በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን! ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን። በቴሌግራም👇👇👇 https://t.me/Abdubook በtiktok፦👇??👇👇👇 https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9
8 62328Loading...
11
እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦ 36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው። ( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع ) أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه . መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው።  "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
7 22716Loading...
12
ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
5 05811Loading...
13
36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው። ( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع ) أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه . መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው። "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
10Loading...
14
ሸፊዕ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦ 53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ “ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦ 19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦ 10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ 6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦ 6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع "ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ አሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦ 32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” በመጀመሪያው ሐረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉ ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦ 30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
6 61017Loading...
15
Media files
8 71239Loading...
16
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
17 293132Loading...
17
Media files
12 00941Loading...
18
owdHDfiZEE0QIDiRJgmgFBjfQgR4AFsuYBwFCs.mp4
10 93764Loading...
19
ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል"Bishop Mar Mari Emmanuel" በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የሶሪያውያን ቤተ ክርስቲያን"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት "ክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን"Christ The Good Shepherd Church" ውስጥ ያገለግሉ ነበር። የሶሪያውያን ቤተክርስቲያን የንስጥሮስ ትምህርት ተከታይ ሲሆኑ የንስጥሮስ ትምህርት "ኢየሱስ በአንድ ስም ሁለት ማንነት"person" አለው፥ በፍጹም አምላካዊ ማንነት የአብ ልጅ በፍጹም ሰዋዊ ማንነት የማርያም ልጅ" የሚል ትምህርት ነው፥ ይህ ትምህርት በ 431 የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል የእዛ እሳቤ አራማጅ ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ኦርቶዶክሶች እኚህን አባት እንደ ኦርቶዶክስ አባት አርገው የሚመለከቱት ትምህርታቸው ከራሳቸው ትምህርት ጋር አነጻጽረው በቅጡ መረዳት የማይችሉት ናቸው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የንስጥሮስ ትምህርት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ በጽብሐዊ ኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት የተወገዘ ምንፍቅ ና ነው። ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በእንግሊዝኛ መርሐ ግብር የተለያ እሳቦትን በመተናኮል እና በመጎንተል በዓለም ላይ ይታወቃሉ። እስራኤልን፣ ምዕራባውያንን፣ አሜሪካንን፣ ግብረ ሰዶማ ውያንን ሳይቀር ይተቻሉ፥ አልፎ አልፎ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን ሲላቸውም ዲኑል ኢሥላምን ሲወርፉ ይሰማል። ትላንት አንድ ሰው በሚያስተምሩበት ቤተክርስቲያን አደጋ አድርሶባቸው ህክምና ላይ እዳሉ እየተሰማ ነው። አደጋ ያደረሰባቸው ማንነት እስካሁን እንዳልተጣራ እየታወቀ ክርፋታቸው በተገኘው አጋጣሚ የሚያዝረከርኩ ክርስቲያኖች ለሙሥሊም ያላቸው ጥላቻ ምን ያክል የከፋ እና የከረፋ መሆኑን የምታውቁት ሰውዬውን "ሙሥሊም ነው" በማለት ዲናችንን መዝለፍ እና ማብጠልጠል ተያይዘውታል። ሰውዬው ሙሥሊም ቢሆንስ? ሰውዬውን "ትክክል አይደለም" ብሎ እራሱን ማውገዝ እንጂ ዲናችንን ለምን አሳቻ ሰዓት ላይ ጠብቃችሁ ትጎነትላላችሁ? ስንት እና ስንት ሙሥሊሞች በክርስቲያኖች ተገለው እንደ ኖርማል እየታየ አንድ ክርስቲያን ስለተገደለ ክርስትናን የእውነት ሚዛን አርጎ መውሰድ ቂልነት ነው። በእርግጥም ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለዲኑል ኢሥላም ያላቸው ጥላቻ አይጣል ነው፥ በአገኙት አጋጣሚ ዲናችንን በማበሻቀጥ እና በማብጠልጠል የዘመኑን ዋንጫ ወስደዋል። ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ተከታዮቻቸው "ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ" የሚለውን ሕግ ይዘው "የእጁን እንስጠው" ብለው ግብግብ ሲይዙ ነበር። "ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት" የሚለው የሚሠራው ስብከት ላይ ብቻ ነው፦ ማቴዎስ 5፥38 ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት። አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምንከተል ድረስ እንዳይወዱን አሏህ በቁርኣኑ ነግሮናል፦ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ አሏህ ለእነርሱ ልብ ይስጣቸው! ለእኛም ትእግስቱን ይስጠን! አሚን። አንብበው ሼር በማድረግ አስነብቡ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
10 92344Loading...
20
Media files
7 3517Loading...
21
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 12ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy" 2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" 3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology" 4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology" 5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book" 2.በመጽሐፍት"scriptures" 3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation" 4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization" 5. በባይብል ግጭት"Contradiction" 6. በኦሪት"Torah" 7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው። አባሪ ኮርሶች፦ 1. ዐቂዳህ"creed" 2. ሥነ ምግባር"ethics" 3. ሥነ አመክንዮ"logic" 4. ሥነ ልቦና"psychology" 5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
10 34288Loading...
22
አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦ ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا ‏"‏ ‏ ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦ "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106 አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏ "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦ 7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏ አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦ ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708 አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏ "መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117 ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ ‏ "‏ الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ "‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
8 84538Loading...
23
ን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏
10Loading...
24
የሰው ሥጋ ይበላልን? በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ አምላካችን አሏህ በመልእክተኞች በኩል "ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ" ብሎ ነግሮናል፥ እነዚህ መልካም ምግቦት የሰጠን ሲሳይ ናቸው፦ 23፥51 እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ 2፥172 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደኾናችሁ አሏህን አመስግኑ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ وَاشْكُرُوا لِلَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ሰዎች ሆይ! አሏህ መልካም ነው፥ እርሱ መልካም እንጂ አይቀበልም። አሏህ ምእመናንን መልእክተኞችን ባዘዘው መሠረት አዘዛቸው። እርሱም፦ "እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ" አለ፥ እርሱም፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ اللَّهَ طَيِّبٌ وَلاَ يَقْبَلُ إِلاَّ طَيِّبًا وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ فَقَالَ ‏:‏ ‏(‏يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ ‏)‏ وَقَالَ أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ‏)‏ ‏"‏ ‏.‏ በተቃራኒው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ሐራም ነው፦ 2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና በእርሱም ማረድ ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ቢሆንም በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው ሕይወት ለማትረፍ ተፈቅዷል፦ 2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም። አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ነገር ግን በማንኛውም ወቅት እና ሁኔታ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም መብላት ሐላል ነው፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆኑ ዓሣ እና አንበጣ የማይታረዱ ሥጋ ናቸው። ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ናቸው፦ 16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا 5፥96 የባሕር ታዳኝ እና ምግቡ ለእናንተ እና ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ الْبَحْرِ وَطَعَامُهُ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ ۖ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ الْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا ۗ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 64 ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም ለእኛ ተፈቅዶልናል፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆን ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ أُحِلَّتْ لَنَا مَيْتَتَانِ وَدَمَانِ فَأَمَّا الْمَيْتَتَانِ فَالْحُوتُ وَالْجَرَادُ وَأَمَّا الدَّمَانِ فَالْكَبِدُ وَالطِّحَالُ ‏"‏ ‏.‏ ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 1 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ባሕር እንዲህ አሉ፦ "እርሱ ውኃው ንጹሕ ነው፥ ሙታኑ እንስሳት ለመብላት ሐላል ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏- رضى الله عنه ‏- قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-فِي اَلْبَحْرِ: { هُوَ اَلطُّهُورُ مَاؤُهُ, اَلْحِلُّ مَيْتَتُهُ } ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸው
8 26636Loading...
25
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ! እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ! ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው። አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበለን! አሚን። ዒድ ሙባረክ!
9 87932Loading...
26
"ኢየሱስ በቀጣይ እሑድ ይመጣል" ልደታ ቤተክርስቲያን መምህርት አስካለ በልጅነታችን ኢየሱስ፦ ፨በዕለተ እሑድ ፨በቀኑ 29 ቀን ፨በወሩ መጋቢት ወር ፨በዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ከገጠመ ይመጣል ብላ አስተምራናለች። ባሕረ አሳብን ቀምረው የአገራችን ሊቃውንት "በዘመነ ዮሐንስ እሑድ በመጋቢት 29 ቀን ይመጣል" ባሉት መሠረት እየጠበቅን ነው። ይህን ካልሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐሰተኛ ነቢያት ተለይታ አትለይም። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
12 30777Loading...
ላብ አደር በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥32 ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا "አደር" ማለት የዕለት ለዕለት የአኗኗርን ዘይቤን ለማመልከት የሚመጣ ፈሊጣዊ አነጋር እንጂ "አዳር" ከሚለው ቃል የሚሳለጥ አይደለም፥ ለምሳሌ፦ "ሠርቶ አደር" "ወጥቶ አደር" "አርሶ አደር" "አርብቶ አደር" "ወዝ አደር" "ላብ አደር" ሲባል ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ስለ ላብ አደር የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ" ብለው ነግረውናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 8 ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَعْطُوا الأَجِيرَ أَجْرَهُ قَبْلَ أَنْ يَجِفَّ عَرَقُهُ ‏"‏ ‏.‏ አንድ አሠሪ የሠራተኛውን ላብ የማይከፍል ከሆነ አሏህ በትንሣኤ ቀን ከሚጻረራቸው ሦስት ሰዎች አንዱ ይሆናል፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 7 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሥስት ሰዎች ተጻራሪ ነኝ፥ እኔ የማንም ተጻራሪ ከሆንኩ በትንሣኤ ቀን አሸንፈዋለሁ። በስሜ ቃል የገባ ከዚያም የሚያታልል ሰው፣ ነጻ ሰው ሸጦ ዋጋውን የሚበላ ሰው እና ሠራተኛ የሚቀጥር እና ተጠቅሞበት ከዚያም ደመወዙን የማይሰጥ ሰው ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ أَنَا خَصْمُهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَمَنْ كُنْتُ خَصْمَهُ خَصَمْتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ رَجُلٌ أَعْطَى بِي ثُمَّ غَدَرَ وَرَجُلٌ بَاعَ حُرًّا فَأَكَلَ ثَمَنَهُ وَرَجُلٌ اسْتَأْجَرَ أَجِيرًا فَاسْتَوْفَى مِنْهُ وَلَمْ يُوفِهِ أَجْرَهُ ‏"‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯችንን በመካከላችን አከፋሏል፥ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ሀብትን ሰጥቶአል፦ 43፥32 እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናት፡፡ أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَ ۚ نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا ۗ وَرَحْمَتُ رَبِّكَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ የአሏህ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናትና ላብ አደርን በዙልም በመዞለም ጀነት ተነፍጎ አሏህ ከሚጻረረን አሏህን ፈርተን የላብ አደሩን ሐቅ መስጠት ትሩፋት አለው። ዲኒል ኢሥላም የሚያስከብረው ላብ አደርን እንጂ የላብ አደር ቀንን አይደለምና ላብ አደርን እናክብር! አምላካችን አሏህ የሰዎችን ሐቅ ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦ ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦ ማቴዎስ 26፥26-27 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28: ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል። ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት!  የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው።                                                                     አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።    ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
የሰው ሥጋ በባይብል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ እስራኤላውያን በሚያጠፉት ጥፋት አምላክ ቅጣቱ የወንዶች ልጆቻቸውን እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ማድረግ ነበር፦ ዘሌዋውያን 26፥29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፥ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። "ትበላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው ባስጨነቋቸው እና መከራ ባሳይዋቸው ጊዜ የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ነግሯቸዋል፦ ዘዳግም 28፥53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶች እና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ። ለእስራኤላውያን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ የሚያበላው እራሱ አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦ ኤርምያስ 19፥9 የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ "አበላቸዋለሁ"። "አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋል ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ ምን ዓይነት ቅጣት ይሆን? አስበይው አምላክ በይው እስራኤላውያንን ናቸው። በዚህ ምክንያት አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፦ ሕዝቅኤል 5፥10 ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን "ይበላሉ" ልጆችም አባቶቻቸውን "ይበላሉ"። ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦ ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል። ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም። የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦ ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች። በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦ 2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት። ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን?
Показати все...
يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

የሰው ሥጋ በባይብል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ እስራኤላውያን በሚያጠፉት ጥፋት አምላክ ቅጣቱ የወንዶች ልጆቻቸውን እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ማድረግ ነበር፦ ዘሌዋውያን 26፥29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፥ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ። "ትበላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው ባስጨነቋቸው እና መከራ ባሳይዋቸው ጊዜ የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ነግሯቸዋል፦ ዘዳግም 28፥53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶች እና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ። ለእስራኤላውያን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ የሚያበላው እራሱ አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦ ኤርምያስ 19፥9 የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ "አበላቸዋለሁ"። "አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋል ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ ምን ዓይነት ቅጣት ይሆን? አስበይው አምላክ በይው እስራኤላውያንን ናቸው። በዚህ ምክንያት አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፦ ሕዝቅኤል 5፥10 ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን "ይበላሉ" ልጆችም አባቶቻቸውን "ይበላሉ"። ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦ ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል። ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም። የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦ ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች። በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦ 2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት። ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን? ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦ ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና። የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦ ማቴዎስ 26፥26-27 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ 28: ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል። ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት! የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው። አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram