cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Besmeti 😍😍😍

in dis channel u can get arif arif music 🎶🎶 arif arif keledoch😂 Join as my sweet channel Jøïñ äs 👉 @officalemutiii gruop lelalachu 👉 @emutiii844 Inbox me @mehzeba and @Rehimetii

Більше
Рекламні дописи
606
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » የሚሉት ገንዘብ ስለቸገራቸው ብቻ አይደለም። የሚጠቃቀሙበትን ነገር ወጪ መሸፈን ስላቃታቸው ብቻ አይደለም። በእርግጥ ዱንያ ልጋጋም ነች አስቀይማቸው ሊሆን ይችላል። ነገርን ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ገንዘብን ፍለጋ ብቻ አይደለም። ሰዎች ሰውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማስተካከል « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። አብሽሩ፣ አይዟችሁ የሚላቸውን ፈልገው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። ፈተናዎቻቸው በዝተው መቋቋም ተስኗቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። እራስን ስለማጥፋት እያሰቡ ከዚህ ሀሳብ እንዲላቀቁ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። አኼራቸው አስጨንቋቸው፣ ወንጀላቸው አሳስቧቸው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያስገድዳቸው ነገር ዙርያቸውን ከቧቸው ተስፋ እንዳይቆርጡ ሲሉ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሊሉ ይችላሉ። ሰዎች « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምክንያቶች ይኖራቸዋል። ዱዓ’ን ለገንዘብ ብቻ አትስጡ። የገንዘብ ችግር አንድ እራሱን የቻለ ችግር እንጂ ሁሉንም የሚያጠቃልል አይደለም። ገንዘብ የማይፈታው ስንትና ስንት መዓት የልብ ጉዳይ አለ መሰላችሁ። ማንኛውም ሰው « ዱዓ አድርጉልኝ! » ሲላችሁ Materialistic want/ቁሳዊ ፍላጎት ብቻ እየሻ ነው ብላችሁ አትደምድሙ። ሁሉንም የ« ዱዓ አድርጉልኝ! » አደራዎች ገንዘብ ተኮር ብቻ አድርጎ ማሰብ በራሱ ውስጣዊ የቁስ ባርነትን ማመላከቻ ነው። ይሄኔ ስንቱ በልቡ ጉዳዩን ይዞ « ዱዓ አድርጉልኝ! » ስላለን ቁስ ለመመፅወት ተጣድፈን አሳዝነነው ይሆን? ግዴላችሁም አስፍተን ነገሮችን ለመረዳት እንሞክር። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል። Semir ami📝 Hanui👱‍♀
Показати все...
👍 2
አውቃለሁ #በ 21 አመታቸው ተመርቀዉ እስከ 27 አመታቸው ድረስ ሥራ ያላገኙ ሰዎች አዉቃለሁ ::በ 25 አመታቸው ተመርቀዉ ወዲያው ሥራ ያገኙ ሰዎች አውቃለሁ ::ዩኒቨርሲቲ ሳይሄዱ በ 18 አመታቸው ሚወዱትን ሥራ ያገኙ ሰዎች አውቃለሁ::ጥሩ ገቢ ያለው ሥራ እየሰሩ ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች አውቃለሁ ::ትምህርት አቁዋርጠዉ ሚወዱትን መስራት የ ጀመሩ ሰዎች አውቃለሁ ::በ 16 አመታቸው ለ ወደፊት ሚሰሩትን እርግጠኛ የነበሩ? በ 26 አመታቸው ግን ሃሳብ የቀየሩ ሰዎች አውቃለው ::ልጅ ኖሩዋቸው ትዳር የሌላቸው ሰዎች አውቃለሁ ::ትዳር ያላቸው ግን ልጅ ለማግኘት ከ 8-10 ዓመት የጠበቁ ሰዎች አውቃለሁ ::የ ፍቅር ሁኔታ ዉስጥ ሆነው ሌላ ሚወዱ ሰዎች አውቃለሁ ::ሚዋደዱ ግን አንድ ላይ ያልሆኑ ሰዎች አውቃለሁ :: *ለማለት የፈለኩት ምንድነው ህይወታችን ላይ የሚሆነው ነገር ሁሉ ሚሆነው በ ራሱ ጊዜ ነው!!!! ( Unknown ) Mesturat ✍️✍️ @khumesrah
Показати все...
👍 1❤ 1
Repost from Sophia Ahmed [ Judi ]
ከመኖር ብዙ አለ!❤️‍🩹 ©ሱመያ ሱልጣን ... የሆነ ቀን ህልሜን ሁላ መና ሆኖ ሳገኘው ከፍተኛ የሚባል ድብርት ውስጥ ገባሁ። ቀን ማታ ማልቀስ፣ የብቸኝነት ጊዜዬን መውደድ፣ ሰው ማውራት መጥላት እና ሌላም ነገር... ብቻ ብዙ ብዙዎን ሆንኩት። አልበቃኝም! " ለምን ሞቼው አልገላገልም። በሞቴ ልረፍ!" ብዬ ራሴን ላጠፋ ወሰንኩ። ወንጀልነቱን ባይጠፋኝም በ ጌታዬ አልራህማንነት ተማመንኩ እና የቂኔ ነጻ ያውጣኝ ብዬ ራሴን አሳመንኩ። " የፈለጉት ጊዜ ሞትም ይለግማል" የሚል ጽሁፍ ፌስቡክ ስቶሪ ላይ አስቀምጬ በ ደቂቃዎች ውስጥ ስልኬን ላጠፋ ስል አንድ ወዳጄ (አላህ ዱንያ አኺራውን ያሳምርልህ ውዱ ሰው) ወዲያው በ 1ደቂቃ  ልዩነት ውስጥ አወራኝ። "ደከመኝ" አልኩት። የመንግስት ባለ ስልጣን እንደመሆኑ በ ስብሰባዎች የተጣበበ ጊዜውን ሰውቶ፣ እየሰራ ያለውን ሾል ትቶ ወዲያው ደወለልኝ። አላነሳሁም። ደጋገመው። አላነሳሁም። ምክንያቱም ባነሳው ይለኛል ብዬ የማስበው " ሃራም ነው፣ አላህን ፍሪ! ፣ ያልፋል፣ ቤተሰቦችሽ አያሳዝኑሽም?..." ምናምን ይለኛል ብዬ ነው። ... እኚህ ነገሮች ከዛ ስሜት እንደማያስወጡ አውቃለሁና አለማንሳቱን መረጥኩ። አልተወኝም። ደጋገመው። አነሳሁት በ 5ደቂቃ ውስጥ እራሴን ሥስቅ አገኘሁት። የማስመሰል ሳይሆን ከልቤ። ምን እንዳለኝ አላስታውስም። ግን የሱ ዋና አላማ እኔን ማዘናጋት እና በሳቅ ማስረሳት ፤ ትኩረቱ መምከር ሳይሆን ፊቴ ላይ ፈገግታ ማኖር ነበር። አሁን ፈታ አልኩለት። አወራኝ። ወላሂ ዱንያ ላይ ከፍዬ የማልጨርሰው ከባድ ውለታው አለብኝ። አወራሩ እሱን ጻዲቅ አድርጎ እኔን ተወቃሽ የሚያደርግ አልነበረም። አወራሩ "አዎ እንዴት እስካሁን እራሱ አላደረግሽውም። ጥንካሬሽ ይገርማል!" ምናምን አይነት ነበር። ...እንደኔ ህመሜን እንደ ህመም መቀበሉ በራሱ የህክምናዬ አንዱ አካል ነበር። ፌስቡክ ላይ ያደርኩትን ስቶሪ አስጠፋኝ። ያደረኩት ትኩረት ፍለጋ ሳይሆን ለመተንፈስ ነበር ግን አጠፋሁት። ለሊቱ እስኪጋመስ ድረስ አወራኝ። ሲነጋም አብሮኝ በሃሳብ አለ። አይመክረኝም። ሾለ ተደበርኩበት ጉዳይ አንዱንም አልነገርኩትም። የማወቅ ጉጉትም አልነበረውም። ሾለ ድብርቱ ስሜት ብቻ እነግረዋለሁ። ዝም ብሎ ሃሳቤን ይሰማል። ....ቀኑን ሙሉ በስራ ተወጥሮ እንደሚውል አውቃለሁ ቀን ላይ የተለያዩ ላዳምጣቸው የሚገቡ ኢስላማዊ እና ሌሎችም ትምህርቶች እየላከልኝ እንዳዳምጣቸውና ማታ እንደምንወያይባቸው ይነግረኛል። በጣም አገዘኝ። በተደጋጋሚ ስለማለቅስ አይኖቼ ያባብጡ ነበር። ሥስቅ የሚያውቁኝ በቅርብ ያሉ ሰዎች የ አይኖቼ እብጠት የ እንቅልፍ እንጂ የሌላ ነው ብለው አልጠረጠሩም። ከ አንዲት ህንዳዊት መምህሬ እና የስራ አጋሬ ግን አልተዋጠላትም። ምንም ምንም ሳትለኝ ጥብቅ አድርጋ አቅፋኝ የለበሰችውን ውድ አባያ እንባዬ እንዲያበሰብሰው ፈቀደችለት። አልቅሼ አልቅሼ ደከመኝ እና ሳቆም የሚያረጋጋ መድሃኒት ሰጠችኝ እና እዛው በሷ ቤት ተኛሁ። ስነቃ... በተኛሁበት ክፍል ሳይሆን በስነስርዓት ቁጭ ብለን አወራን። የሳይካትሪስት እገዛ እንደሚያስፈልገኝ ስላመነች ያንን አመቻቸችልኝ። የ ወዳጄ እና የሳይካይሪስቶቹ እገዛ መረጋጋት  እና ደህና መሆን ጀመርኩ። የሚያረጋጋኝን መድሃኒት በ ቀን 2 ጊዜ ከመውሰድ ወደ 1 ከዛም እስከ 0 ወረደ። ...ይህ ሁሉ ሲሆን የሚያውቁት እህቴ፣ ያስሙን የማልጠቅሰው ወዳጄ፣ አንዲት ጓደኛዬ እና ያቺ ህንዳዊት ብቻ ነበሩ። ሁሉም ደከመልኝ። ለደቂቃ ሳይታዘቡኝ፣ ለአፍታ ሳያነውሩኝ ተረባረቡልኝ። አላህ ሁሌም ከጎናችሁ ይሁን!! የማልረሳው ነገር ቢኖር ተሻለች ስባል መልሼ የምወድቀው ነገር ነው። "በጭራሽ እንዳታስቡ ደህና ነኝ አልሃምዱሊላህ እድሜ ለናንተ' ምናምን እልና ድጋሚ እወድቃለሁ። ያን የሚያቁት 2ቱ ብቻ ናቸው። ... አንድ ቀን  ማታ 3 ሰአት ወይ 4ሰዓት አካባቢ " ማሜ አልቻልኩም ደከመኝ" ብዬ ተንሰቀሰቅኩበት ብዙ ጊዜ የሚረብሸኝ የማታ ብቻዬን የምሆንበት ሰዓት ነበር። " ሱሚዬ እኔን ይድከመኝ እኔን ወንድምሽን ድክም ይበለኝ። አሁን እኮ እየጎበዝሽልኝ ነው እናቴ።" ወላሂ ቃል በቃል እንዲህ ነው ያለኝ "እናቴ" ሲለኝ እናቴን አስታወሰኝ ጭንቅ ሲላት እንደምትለኝ ነው" ምናባቴ ላድርግሽ እናቴ" ትለኝ ነበር። አሳዘነኝ። እንደምንም አረሳሳኝ እና ደህና ሆንኩ ከዛ በጊዜ ሂደት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ደህና ሆንኩ። አልሃምዱሊላህ ላቆየኝ ጌታ። ሂወት ቀጠለ ከትላንት የተሻለ ብዙ አዲስ ነገር ሂወቴ ላይ ተፈጠረ አልሃምዱሊላህ። ድጋሚም በሆነ የሂወት መዋዠቅ ውስጥ ራሴን አገኘሁት እና ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ታመምኩ። ራሴን ላጠፋ አጠገቤ ያገኘሁትን መድሃኒቶች ሰብስቤ 6ፍሬ ወሰድኩለት። እያየሁ ልጨምር መሆኑ ነው😂 አላህ ግን በኔ ላይ የፈለገው ኸይር አለና ሞቴን አልሰጠኝም። ልጨምር ተነሳሁ። ወደቅኩ... አለፈ። አሁን 2ኛ ዙር እንደመሆኑ ራሴን በራሴ ለማዳን ቆረጥኩ። እህቴ አብራኝ ሆነች። ስወድቅ ስነሳ። ስታመም ስድን በአላህ እዝነት እና እሱን በማስታወስ ሃይል ደህና ሆንኩ። ...ያረቢ ወላሂ ቁርኣን እና ሰላት እንዴት እንደሚያክሙ። ከዚህ በፊት ቀርቼው እንደማላውቅ ብርቅ ሆነብኝ። ሞቼ ቢሆን የማላየቸውን ብዙ ነገሮች አየሁ። ልሞትለት የነበረው ጉዳይ የእውነት ሞቴ የሚገባው አልነበረም። እንዲያውም አላህ ለ ትልቅ ነገር ልቤን ሊያደነድን የላከልኝ ትልቅ ትምህርት ነበር። አልሃምዱሊላህ ተምሪያለው። ህይወታችሁ ላይ ሞትን የሚያስመርጥ ምንም ችግር የለም። በትእግስታችሁ ልክ ሊመነዳችሁ ጌታችሁ የላከው ፈተና ነውና ታገሱ!! አላህም በርግጥ ከታጋሾች ጋር ነውና! ©ሱመያ ሱልጣን @Sophia_Ahmed1 || @Sophia_Ahmed1 ለአስተያየትዎ 👇👇👇 @sophiaa_ahmed_bot

“ልክ እንደ ልዕልት ተንከባከባት በንግስት እጅ እንዳደግክ ትረዳለች”🤍 እናትህን አስከብር ወንድ ሁን😎
Показати все...
አልሀምዱሊላህ ከሂወታችን ስለወጡ ሰዎች በሙሉ😊 ¶Miracle
Показати все...
👍 2
ካልጠፋ ያጠፋሻል 😒 : መቼም በዚህ ዘመን smart phone ያልያዘ ሰው ማግኘት እየከበደ ነው… ታዲያ በነዚህ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በታጨቁት ዘመናዊ ስልኮች ውስጥ ያለው ብቸኛ አገልግሎት ፎቶ ማንሻ ካሜራ ብቻ ይመስል ሁሉም ሰው በውቡ ካሜራ ቀንና ማታ እራሱን ሲቀርፅ እራሱን ሲያይ ታያቸዋለሽ… በዚህ በፎቶ ጉዳይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽና በታማኝነት ለራስሽ መልሱን መልሺ… በስልክሽ ካሜራ በአንድ ጊዜ ስንት ፎቶ ተነተሽ ስንቱ ፎቶ አስጠልቶሽ ታጠፊዋለሽ? መልሱ አንቺ ጋ ይቆይ… እኔ በራሴ ልምድ አስር ፎቶ ብትነሺ ሶስቱን ብትወስጂው ነው ሰባቱ አስጠልቶሽ ይጠፋል Delete … አስቢው የራስሽን አካል የራስሽን ፊት እሱንም በውብ ቴክኖሎጂ አሳምሮ አስወቦ አንስቶሽ ያስጠላሻል አያምርም ብለሽ Delete ታደርጊዋለሽ🙂 አንዳዱን ደሞ Edit ታደርጊዋለሽ ፎቶሽ ውስጥ የገባውን የማትፈልጊው ቆርጠሽ ታወጫለሽ ቆንጆዋን ፓርት ብቻ መርጠሽ ታስቀምጫለሽ… ይሄ ሁሉ ልፋት ቆንጆ ፎቶዎች እንዲኖረን ነው ሌላ ምንም የተለየ ጉዳይ የለውም… በቃ በወረደ ቋንቋ ሲገለፅ የራስሽን የተዋበ ፎቶ ለራስሽም ሆነ ለሌሎች እያሳየሽ ልትፅናኚ ነው ካሜራው ደሞ ቦታውን አስተካክለሽ አንሳ ካልሺው ያነሳል ይሄ ጥሩ አይደለም ይሄ ጥሩ ነው እያለ አስተያየት አይሰጥም ያየውን ያነሳል በቃ ያ ስራው ነው። አንድ ነገር ግልፅ ነው አንቺ ከኖርሽ በህይዎት ካለሽ ከተነፈስሽ ከተራመድሽ ብዙ ነገር ያጋጥምሻል… ህይዎት ደሞ ብዙ ጉዳዮችን በካሜራዋ ትቀርፃለች እና ይቺ የህይዎት ካሜራ ስራዋ ያየችውን ማንሳት ነው ። ለህይዎትሽ ይጠቅማል ያምራል አስተያየት አትሰጥም ማንሳት መቅረፅ በአእምሮሽ gallery ማስቀመጥ ስራዋ ነው። ታዲያ አንቺ የራስሽን ህይዎት መርምሪው እስኪ በማትፈልገው ነገር ተሞልቶዋል? ያልመረጥሽው ያልወደድሽው ነገር ከቦሻል? አዎ ከሆነ መልስሽ… በቃ አንቺ ህይዎት በውብ በካሜራዋ አንስታ የሰጠችሽን ሁሉ ተቀብለሽ በኑሮ galleryሽ ውስጥ አስቀምጠሻል ማለት ነው… መርጠሽ አላውጣሽም አላጠፋሽም Delete አላደረግሽም የአእምሮሽ storage በትርኪ ሚርኪ ጉዳይ ሞልቶ storage full የሚለውን notification እየላከልሽ ነው ማለት ነው። ይሄ ቀላል አካሄድ ነው ህይዎትሽን እንደካሜራ ቁጠሪያት የአንቺ እግር የደረሰበትን ሁሉ ልቅም አድርጋ አንስታ ወደ አእምሮሽ ታስቀምጣለች ህይዎት ለአንቺ አትመርጥልሽም አንቺ ነሽ ህይዎትሽን መምረጥ ያለብሽ… የህይዎት ካሜራ ከመቅረፅ ውጪ ስራ የለውም ይሄ ጥሩ ይሄ መጥፎ ነው እያለ አይመርጥልሽም። ህይዎትሽ ቆንጆ gallery እንዲሆን ከፈለግሽ ምርጥ ምርጡን መርጠሽ አስቀምጭ።😊 ብዙ ሰው ህይዎቱን ባልመረጠው ባልወደደው ቦታ ያገኛዋል… ለምን? ብሎ አይጠይቅም እድሌ ነው ብሎ ማማረር የባሰ አዘቅጥ ውስጥ መግባቱን ይቀጥላል… ለምን እዚህ ተገኘው? ይሄ ቦታዬ ነው? ከማን ጋር ነው ያለሁት? ኑሮዬ እኔን ይመስላል? እኔስ ኑሮዬን እመስላለው? ብለሽ መጠየቅ አለብሽ አለበለዚያ የህይወት ካሜራ ቀርፃ የሰጠችሽን ብቻ ተቀብለሽ እየኖርሽ ነው። እንደዚያ ከኖርሽ ደሞ ህይወት ምሬት ለቅሶ ነው የምትሆንብሽ። ቀላሉ መንገድ Delete ማድረግ ነው በቃ የማይሆን የማያዋጣ የመሰለሽን ያላማረሽን Delete አድርጊ ቆንጆ ህይዎት ይኖርሻል። አንዳዱ ደሞ ሳትፈልጊው ና ሳትይው ወደ ህይወትሽ ይገባል 😔እሱን ቆርጠሽ Edit አድርገሽ ማውጣት አለብሽ አለበለዚያ galleryሽ ውስጥ ውጥንቅጥ ይበዛዋል virus ያጠቃዋል… ከሁሉም ከሁሉም መፍራት ያለብሽ የህይዎት storageሽን በማያምር በማትፈልጊው ነገር ሞልተሽ የሚያምር የምትፈልጊው ነገር ወደ ህይዎትሽ ሲመጣ ቦታ ይሞላብሻል ማስቀመጫ ታጫለሽ ያኔ አዪዪዪ እፈልገው ነበር ግን ትያለሽ… ለአንቺም ለሰሚውም ግልፅ አይደለም ወይ ደሞ ለመግለፅ ይከብዳል ከአፍሽ (ከግን) ውጪ ማውጣት ሳይከብድሽ በፊት Delete አድርጊ አለበለዚያ ህይዎት እራሷ Delete ታደርግሻለች… Semir ami📝👳‍♂
Показати все...
Repost from N/a
አብዛኛው ጊዜ ራሱን ለማጥፋት ያሰበ ሰው ራስን ስለማጥፋት ሲያወራ አናየውም..... they just hang around with people.. and the next day  they are gone... ይሄ ምንን ያሳያል ትክክለኛ ጠያቂ እና ጓደኛ ማጣትን ነው...! ያገኛችሁት የሳቀ ፣ ያሳቃቹህ ሁሉ ውስጡ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አታውቁም.... እናንተ ፊት መሳቃቸው ፡ መቀለዳቸው it doesn’t mean that they are okay ..... ሁላችንም የራሳችን የምንለው ትግል ውስጥ ነን.... በአሁን ሰዓት ደስተኛ ሰው ያለ አይመስለኝም.. ጓደኛ ተብዬዎች የምትወዱትን ሰው ከፊቱ ሳይሆን ከአይኑ ጠልቃቹህ ለመረዳት ሞክሩ!!! የምትወዱትን ጓደኛችሁን እንዴት ነህ ሳይሆን ደስተኛ ነህ ወይ  ብላቹህ ጠይቁ!!   ጓደኝነታቹህ አብሮ መብላት.... አብሮ መሳቅ.... አብሮ መዋል... ከዛ ፎቶ ከመፖሰት የዘለለ ይሁን!! ተጠያየቁ!! አውሩ!!  ለመብላት ለመጠጣት ብቻ እየተገናኛቹህ ልክ something bad happen ሲያደርግ መደንገጥ.... "  ደህና ነኝ ብሎ ነበር እኮ..."  አይነት ወሬ.... መች ጠይቀነው?? መች ጠይቃችሁን?? መች ተጠያየቅንና ነው ደህና ልሁን..አልሁን..  ደህና ሁኑ አትሁኑ በምን አውቃለሁ?? በምንም!! የሚወዳችሁን ሰው..ጓደኛችሁን ቤተሰባችሁን አታስከፉ... ልባቸውንም አትስበሩ!! ራስን የማጥፋት መንስኤ ተስፋን ማጣት ነው!!.. የሰው ልጅ ደሞ ተስፋውን የሚያድሰው በጓደኞቹ ፣ በቤተሰቦቹ ነው!! ስለዚህ በተቻላቹህ መጠን ለሚወዷቹህ ቤተሰቦቻቹህ ፣ ጓደኞቻቹህ ፣ የፍቅር አጋራችሁ ደስታ ለመሆን ሞክሩ!  ተስፋቸውን ያድሱባችኋል!! በኛም በራሳችንም ሰዎች ላይ ተስፋን መዝራት እንልመድ!! እንጠያየቅ.... ከልብ የሆነን መጠያየቅ!! አላህ ተስፋችንን አያሳጣን 🤲💚 በተረፈ አላህ ሁላችሁንም ያፅናቹህ! ያፅናን!! @officalemutiii @officalemutiii
Показати все...
👍 3
Repost from N/a
አብዛኛው ጊዜ ራሱን ለማጥፋት ያሰበ ሰው ራስን ስለማጥፋት ሲያወራ አናየውም..... they just hang around with people.. and the next day  they are gone... ይሄ ምንን ያሳያል ትክክለኛ ጠያቂ እና ጓደኛ ማጣትን ነው...! ያገኛችሁት የሳቀ ፣ ያሳቃቹህ ሁሉ ውስጡ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አታውቁም.... እናንተ ፊት መሳቃቸው ፡ መቀለዳቸው it doesn’t mean that they are okay ..... ሁላችንም የራሳችን የምንለው ትግል ውስጥ ነን.... በአሁን ሰዓት ደስተኛ ሰው ያለ አይመስለኝም.. ጓደኛ ተብዬዎች የምትወዱትን ሰው ከፊቱ ሳይሆን ከአይኑ ጠልቃቹህ ለመረዳት ሞክሩ!!! የምትወዱትን ጓደኛችሁን እንዴት ነህ ሳይሆን ደስተኛ ነህ ወይ  ብላቹህ ጠይቁ!!   ጓደኝነታቹህ አብሮ መብላት.... አብሮ መሳቅ.... አብሮ መዋል... ከዛ ፎቶ ከመፖሰት የዘለለ ይሁን!! ተጠያየቁ!! አውሩ!!  ለመብላት ለመጠጣት ብቻ እየተገናኛቹህ ልክ something bad happen ሲያደርግ መደንገጥ.... "  ደህና ነኝ ብሎ ነበር እኮ..."  አይነት ወሬ.... መች ጠይቀነው?? መች ጠይቃችሁን?? መች ተጠያየቅንና ነው ደህና ልሁን..አልሁን..  ደህና ሁኑ አትሁኑ በምን አውቃለሁ?? በምንም!! የሚወዳችሁን ሰው..ጓደኛችሁን ቤተሰባችሁን አታስከፉ... ልባቸውንም አትስበሩ!! ራስን የማጥፋት መንስኤ ተስፋን ማጣት ነው!!.. የሰው ልጅ ደሞ ተስፋውን የሚያድሰው በጓደኞቹ ፣ በቤተሰቦቹ ነው!! ስለዚህ በተቻላቹህ መጠን ለሚወዷቹህ ቤተሰቦቻቹህ ፣ ጓደኞቻቹህ ፣ የፍቅር አጋራችሁ ደስታ ለመሆን ሞክሩ!  ተስፋቸውን ያድሱባችኋል!! በኛም በራሳችንም ሰዎች ላይ ተስፋን መዝራት እንልመድ!! እንጠያየቅ.... ከልብ የሆነን መጠያየቅ!! አላህ ተስፋችንን አያሳጣን 🤲💚 በተረፈ አላህ ሁላችሁንም ያፅናቹህ! ያፅናን!! @semu_tube @semu_tube
Показати все...
ፈፅሞ በማይቻልና በሚቻል ጉዳዮች መሃል፤የአሏህ ውሳኔ ብቻ ነው ያለው። ቀጠሮው ሲደርስ፤ኩን ቃሉ በቂ ነው!
Показати все...
❤ 5
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.