cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Sophia Ahmed [ Judi ]

Більше
Рекламні дописи
7 762
Підписники
-324 години
-557 днів
-21130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እንዲህ እያልኩ..... መውደድ አይደል የአንድ ሰው ሁለት ትንፋሽ ? ፍቅር አይደል ከከንቱነት አለም ቀስቃሽ ?       ማበብ እንዳበባ       መፍካት በልብ ቃል በወርሀ መስከረም       ብዙ ብዙ ብሎ. . . መክሰም ካለማረም! መሆን እጣ መራቅ ህምም ያስታቀፈኝ እንዳይቻል ለካ ናፍቆት ለካስ ሀሳብ ይብስ ሆኗል እንደመቻል         ብጠፋ አልኩኝ         እያሰበ ከሚንጠኝ ከልብህ ላይ         ባልኖር አልኩኝ         ከሚስበኝ ካልወሰድከው ትዝታህ ላይ ብርቅ ካለም አንተን ጭምር ካቀፈችው ምኔ ጋር ነው ምን መፅሀፍ ላይ " አንቺ የእርሱ ግራ ጎኑ " በሚል ቃሉ ያረፈችው?       የቱ ጋር ነው       አጥንት ካንቺ ተጋርታል የሚለው ቃል?       እኔ ሳልኖር       እንዲህ በሚል       " አንቺም አጋሩ ነሽ "  አንቀፅ መሀል! ...... ተወኝ ተወው ማስመሰሉን መፅሃፈ ቅዱሱን ሳትኖር በኔ ዙሪያ መርመስመሱን! ተወው . . . . ! @Sophia_Ahmed1 @Sophia_Ahmed1
Показати все...
30👍 6👏 3
Repost from N/a
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
Discount For Today 📍 የኢድ ልብስ ከ 1600 ብር ጀምሮ ይሸምቱ 😍😍 ለማዘዝ 👉 @hasma_fashion1            or 📞+251988118041 📍አድራሻ: ሾላ ሱመያ መስጂድ አከባቢ ወጋገን ባንክ ያለበት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ @hasma_fashion || @hasma_fashion
Показати все...
👍 8
ስለ አላህ አስባለሁ ...... እንዲሁ እንደሚያኖረኝ … እኔ ላይ ቂም አልባ እንደሆነው። በጥፋቴ መቅጣቱን ሳይሆን ይቅርታውን እንደሚያስቀድምልኝ! ነውሬን የመደበቁ ልክ ወስን አልባነቱን! " አንተ አይብን ደባቂ ነህ! " ደብቅልኝ! ስለ አላህ አስባለሁ ስለ እዝነቱ...... ስለሚያሳየኝ የልኮች ሁሉ ከፍታ … ስለሚጠቁመኝ መልካም ነገሮች። ስለ አላህ ስለ እዝነቱ ፤ ከጭካኔው በእጥፍ ስለራቀው። የመኖሬም፤ ነገ ጀነትን የመሻቴም ቁልፍ ስለሆነው ስለ እዝነቱ አስባለሁ። " ከእዝነትህ አታጉድልብኝ! " ስለ አላህ ስለ ውዴታው አስባለሁ..... ስለሰጠኝ ሰፊ ኒዕማ ከኔ ስላለመጠበቁ። ስለ እንክብካቤው … በሶላቱ እንደሚያነፃኝ፣ በፆሙ እንደሚያድሰኝ ፣ በሶደቃው እንደሚያቆመኝ ፣ በዱዐዬ እንደሚጠግነኝ። ስለ ሁሉም ስለኔ ስላለው ስለውዴታው አስባለሁ። " ከውዴታህ አታርቀኝ! አልሃምዱሊላህ! @Sophia_Ahmed1 @Sophia_Ahmed1
Показати все...
50👍 4🥰 4
........ [ ልብህ እንደነበር የሚሰማኝ ለምን ዘግይቼ ተረዳሁኝ? ] __ በብዙ የራስ ጩኸቶች ውስጥ የራሴን ጥሪዎች መልሼ እሰማቸው ጀምሪያለሁ። ይህን ጊዜ << በቃ ንግግሬ ሁሉ ያርፍበት አካል አጣ? >> የሚል የሀዘን ሸለቆ ውስጥ ስምዘገዘግ እራሴን አስተውዬዋለሁ። ያርፍበት ጆር ያጣ ቃል ከተናጋሪው ይመለሳል ይሉት ነገር ባዶነት ከባዶነትም ከፍቶ የታየኝ አሁን ነበር። ስላፈቀረው ልቤ አስባለሁ… እንዲሁ እንደሚናገረው ግን የሚያርፍበት አካል እንደሌለው!. . . . . ስለምናፍቀው ናፍቆት አወራለሁ … የናፈቀኝ የናፈኩት ያለ እስኪመስለኝ! የምናፍቀው እንደሌለኝ ውስጤ እየነገረኝ። . . . . ስለ ተስፋ ፤ ስለ ነገ አስባለሁ… የተሻለ ይሆን ብዬ ተስፋ ለብቻ ምንምነቱ እስካይገባኝ ድረስ … በብዙ የሀሳብ ጎዳናዎች ላይ ነፍሴን ለብቻዋ ባልዋለችበት እንድትውል አንጎራድዳት ይዣለሁ። የሆነ ቀን ስለ ቃልና ስለተለወጡ ነገሮች ስናወራ እንዲህ አልኩት.... ተው አልልህ ቃል እንደሆን ይፈርስ ይዟል እንደቀላል፣ ማደስስ ይከብዳል? ከተለወጠ ተረቱ የሁነት ገፁ ግራ ከሆነም፣ ለምን መሄድህ መምጣት አልሆነም . . . ? ምንም አልመለሰልኝም! ይናገረው ያጣ ይመስል ፣ ለዘመናት ያላወራ ይመስል ፣ ምንም አድርጎ የማያውቅ ይመስል ተለጎመ። ሀሳቡ እውነት አልነበረማ! . . . ቃል ይፈርሳል እውነት ነው። የቃል መፍረስ ግን ፅድቅን ሀጢያት አያደርገውም። የሚለያየው ፍርድ ነው። እውነት ደሞ በፍርድ አትመዘንም። ያለዛ ብዙ እውነቶችን የማደስ አቅም ይኖረን ነበር! .......... እንዲሁ ነው ስሆን የነበረው። እናገራቸው የነበሩ ንግግሮቼ ሁሉ ከፍ ይሉ የነበረው ካንተ ጆሮ ሲደርሱ እንደነበረ ነው የገባኝ። ብናኝ ሆኑብኝ ፣ የማወራውን እናዳለ ሰው የሚሰማው እስኪመስለኝ ድረስ ለስለስ ባለው የድምፄ ከፍታ እበሳጭ ጀምሪያለሁ። ምን ያስጮኸኛል እያልኩ!... . . . ስለምን ጆሮህን እንደማንኛውም ሰው አልሰጠኸኝም? ለምን ነው በልብህ ታደምጠኝ የነበረው? የልቤን አወራ ስለነበር ይሆን? . . . . [ ወይስ የልብ ታማኝነት ለዕውነት ይከብዳል ልትለኝ ነው? ] እንዳሻህ. . . . . ! @Sophia_Ahmed1 @Sophia_Ahmed1
Показати все...
1
የልብ ወግ #3፡ " ያለፈ ታሪክ.... " "ስልችት ብሎኛል!" "ምኑ?" "የሚመረጥ የለውም... መኖር አሰልችቶኛል?" "ጓዝ አበዛሽ እንዴ?" "የምን ጓዝ?" "ተጥሎ መረሳት የነበረበትን ያለፈ ታሪክ ዛሬም ያለ እና የሚኖር እስኪመስልሽ ተሸክመሻል?" "እንዴ? ... ወዴት ይጣላል? የኔ እኮ ነው። የኖርኩት። ማንነቴ የተገነባበት ነው። ወደ የት ነው የምጥለው? አያስፈልገኝም ልጣለው ብልስ ግማሽ አያስቀረኝም?" "ወጣት ነሽ አይደል? ህፃን እያለሽ የነበሩሽን የምትወጃቸውን እና በምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የምትምነሰነሽባቸው ልብሶችሽን ፤ ያለ ምርጫሽ የተገዙልሽ የነበሩ የለበስሻቸውን ሁሉ አሁንም ትለብሻቸዋለሽ?" "አይሆኑኝም እኮ ልኬ አይደሉም እንዴት እለብሳቸዋለሁ? በየጊዜው እየተካካሁ አስወግጃቸዋለሁ" "ያለፈ ታሪክም እኮ እንደዛ ነው ለዛሬው አንቺነትሽ ያዋጣው ነገር ይኖራል እንጂ ለዛሬው አንቺነትሽ ግን ላይበቃሽ ይችላል። ልክ እንደልብሶችሽ በጊዜ ሂደት ወደሚሆንሽ እየተቀየረ በአዲስ መተካት ይኖርበታል!" "የማይጠቅመኝን ያለፈ ነገር ማስወገድ ከመሰላቸት የሚያድነኝ ከሆነ በደስታ አደርገዋለሁ! ቀላል ይመስልሻል ግን?" "ለአመታት በወጉ ያልተያዘን ቤት በደቂቃዎች ውስጥ ማሳመር ቀላል ነው?" "እንዴት ቀላል ይሆናል?" " ይሄም ቀላል አይደለም። ለመሞከር መነሳት ግን በግማሽ መንገዱን ይጠርገዋል!" "በጉጉት መኖር ምን እንደሚመስል ማወቅ እና መኖር እፈልጋለሁ።" "እንዲሆንልሽ ምኞቴ ነው።" @Sophia_Ahmed1 @Sophia_Ahmed1
Показати все...
33👍 14👌 2
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ📍 የስራ መደብ : Henna ena mesh መስራት እንዲሁም ማስተማር የምትችሉ Only Full time! ፃታ፡ ሴት ብዛት ፡ 1 ደሞዝ ፡ በስምምነት Addis Ababa ይደውሉልን 👉 0988116922
Показати все...
👍 1
Фото недоступне
✨ቱርከኛ ቋንቋ የመማር ፍላጎት ላላችሁ ለየት ያለ ለሴት ተማሪዎች ብቻ በ ሴት መምህርት የተዘጋጀ የ 1 ወር መሠረታዊ (basic) ክላስ አዘጋጅተናል✨ ክፍያ 2800 ብር ብቻ ለ3 ወር ከሚቆይ ነፃ የኦንላይን ልምምድ ጋር 🎁 ከተለመደው የማስተማር ሂደት ወጣ ባለ መልኩ እየተዝናናን እንማማራለን ቋንቋ የመማር passion ካለሽ ትወጂዋለሽ ዛሬውኑ ተመዝገቢ🥰 ምዝገባው የሚቆየው እስከ ግንቦት 30 ድረስ! አድራሻ ሾላ ሱመያ መስጂድ አከባቢ ለመመዝገብ 📞 0988479889 DM @newal11
Показати все...
👍 2
Repost from N/a
Фото недоступне
ምዝገባ 2 ቀን ብቻ ቀረው📍 ከአረፋ በፊት ለ2 ሳምንት የሚቆይ የሂና ስልጠና ሊጀመር ነው በበአል ወቅት እናንተም ፣ ቤተሰቦቻችሁም፣ ልጆቻችሁም ላለመንገላታት ፤ ጊዜያችሁን ወረፋ ከመጠበቅ ቆጥበው የሚያማምሩ የሂና ዲዛይን ለመስራት እና ሰርተው ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ከፈለጉ በዚህ ትምህርት ተጠቃሚ ይሁኑ። ዋጋ- ሂና እና ሜሽ አንድ ላይ 2800 ብር ሂና ወይም ሜሽ ብቻውን 2000 ብር 🤍 2 እና ከዛ በላይ ሆናቹ ለምትመጡ ልዩ ቅናሽ አለን! 📍አድራሻ: ሾላ ሱመያ መስጂድ አከባቢ ወጋገን ባንክ ያለበት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ቦታ ለማስያዝ 👉 +251988116922 🌸 @hasma_fashion 🌸
Показати все...
👍 5
Repost from N/a
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
  • Фото недоступне
በአጭር ጊዜ ስልጠና የሙያ ባለቤት ይሁኑ! የራስዎትን Business ይጀምሩ! 🥰 ምዝገባ ላይ ነን! Henna & mesh አንድ ላይ 2800 ብር ሂና ብቻ መማር ለምትፈልጉ ደሞ 2000 ብር ለመመዝገብ 👉 +251988116922 📍አድራሻ: ሾላ ሱመያ መስጂድ አከባቢ ቀስተ-ደመና ፋብሪካ ፊትለፊት ያለው ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ደውለው ቦታ ያስይዙ። @hasma_fashion || @hasma_fashion
Показати все...
👍 9
Repost from N/a
በትርፍ ሰአታቹ ስራ መስራት የምትፈልጉ እንዲሁም ለመጪው የኢድ በአል ስልጠና ወስዳቹ ወደ ስራ መግባት ለምትፈልጉ!🥳 Henna እና Mesh አንድ ላይ 2800 ብር ስልጠናው የሚቆየው ለ 2 ሳምንት ነው Fashion design 4500 ብር ስልጠናው የሚቆየው ለ 1 ወር ነው 2ቱንም ስልተጠናዎች ስትጨርሱ Certified ትሆናላቹ! የዚ ዙር ምዝገባ የሚቆየው ለ 5 ቀን ነው! በአጭር ጊዜ ስልጠናዎች የሙያ ባለቤት ይሁኑ! ለመመዝገብ 👉 +251988116922 📍አድራሻ: ሾላ ሱመያ መስጂድ አከባቢ ቀስተ-ደመና ፋብሪካ ፊትለፊት ያለው ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ @hasma_fashion || @hasma_fashion
Показати все...
12👍 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.