Dire Dawa Government Communication Affairs Office
Відкрити в Telegram
1 942
Підписники
Немає даних24 години
+97 днів
+6830 днів
Архів дописів
#ዜና /የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ የፖሊስ ጣቢያዎችን ጎበኙ፤ ሕዝባዊ አመኔታን ማጠናከር ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ መሆኑንም ገለጹ
#DGC ጥቅምት 26/2019
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም፣ በአስተዳደሩ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሥር የሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎችን በመጎብኘት የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም፣ የአባላት አደረጃጀትና የአገልግሎት ዝግጁነት ተመልከተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ፣ ምክትል ኮሚሽነሮችና ሌሎች የፖሊስ ተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የፖሊስ ጣቢያዎች ያላቸው አጠቃላይ ቁመና፣ የአባላት አደረጃጀት፣ ለሕዝቡ ተደራሽ ለመሆን ያላቸው ዝግጁነት እንዲሁም ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅና ሕግ በማስከበር ረገድ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ለከንቲባው ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም በድሬዳዋ የተረጋገጠውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማስቀጠል የፖሊስ ተቋሙን ሕዝባዊ አመኔታ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም በፖሊስና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የትብብርና ቅንጅት በአሳታፊነት ማስቀጠል ለሰላምና ደህንነት ዘላቂነት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ገልፀዋል።
በተጨማሪም የፖሊስ ጣቢያዎችን ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ፣ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማቅረብና ለፖሊስ አባላት ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ የማስፋፊያና የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በአጠቃላይ የጉብኝቱ ዓላማ የፖሊስ ተቋሙን የአገልግሎት አቅም ማጠናከር፣ ከሕዝቡ ጋር ያለውን ተዓማኒነትና ትብብር ማሳደግ እንዲሁም በድሬዳዋ ያለውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ መሆኑ ተመላክቷል።
#ዜና / የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
#DGC ጥቅምት 25/2019
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርትና ምርታማነት አቅማቸውን በማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማስፋትና የተኪ ምርትን በማጠናከር ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም ገለጹ።
ከንቲባው በአስተዳደሩ በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶችን እያካሄዱ የሚገኙትን የመስክ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ የተለያዩ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል።
በጉብኝቱም በአስተዳደሩ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች በተኪ ምርት ረገድ እያስመዘገቡ ያሉት ውጤት፣ ለዜጎች የፈጠሩት የሥራ ዕድል እንዲሁም በምርት ሂደታቸው የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ታይቷል።
አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲንቀሳቀሱ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍና ማበረታቻ ከዚህ በበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም በጉብኝቱ ላይ ተጠቁሟል።
የድሬደዋ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም ለአምራች ድርጅቶች ምቹ የሥራ አካባቢ በመፍጠር፣ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመፍታትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የአስተዳደሩን የምርትና ምርታማነት ዕድገት ማፋጠን እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ይህም የሀገር ውስጥ ምርትን ለማስፋት፣ የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ 401 ፋብሪካዎች ያሉ ሲሆን በዛሬው የመስክ ጉብኝት ከተካተቱት ድርጅቶች መካከል ድሬዳዋ ፉድ ኮምፕሌክስ፣ ብራ ኮፊ፣ ሮያል ጁስ፣ አሽረፍ ኘላስቲክ፣ ሀምዳይል ፒኤልሲ፣ ድሬ ፔትሮ ኬሚካል እና አኳ ኡኖ የተጣራ የማዕድን ውሃ ፋብሪካ ይገኙበታል።
በዳግማዊ ፍቃዱ
ፎቶ፦በአገኘሁ ሸዋረጋ
ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DGCOMU
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@Direcommunication
ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB
ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
በላብ እና በጽናት የለመለመችው ኢትዮጵያ
****
በታሪክ፣ በነጻነት እና በጽናት ላይ በኩራት የቆመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ደግሞ የሕዳሴዋን እና የሥራ አቅሟን ፍሬ አፍርታ በዓለም ፊት አዲስ የውበት፣ የብልጽግና እና የከፍታ ታሪክ እየጻፈች ትገኛለች።
የቀደመ ታሪካዊ ግርማዋን ከዘመናዊ የዕድገት ምዕራፍ ጋር በማስተሳሰር የምታደርገው ይህ ሁለንተናዊ የከፍታ ጉዞ፣ የመላው አፍሪካውያን የኩራትና የተስፋ ማዕከልነቷን በአዲስ መልክ ያደሰ ነው።
የዚህ ታላቅ ሀገራዊ ዕይታና እውን እየሆነ የመጣውን ህልም ጥልቅ ሐሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ “ዛሬ ኢትዮጵያ ‘የአፍሪካ ውብ አበባ' ተብላ ብትጠራ፣ እውነታ እንጂ ባዶ ሙገሳ ተደርጎ አይወሰድም” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ይህ አገላለጽ የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና የባህል ጸጋዎቿን ተፈጥሯዊ ድምቀት ብቻ የሚያንጸባርቅ ሳይሆን፣ በጥበብ፣ በጠንካራ እቅድና በሚያስደምም የጋራ ጥረት እውን እየሆነ ያለውን ሁለንተናዊ ሀገራዊ ለውጥ የሚያበስር እውነታ ነው።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት ምልክት፣ የጥቁር ሕዝቦች የትግል ምሳሌ እና የዲፕሎማሲ መነሻ ከመሆኗም በላይ፣ ዛሬ ላይ በአዲስ የሥራ ባህል፣ በፈጠራ፣ በኢኮኖሚ እና በመሠረተ ልማት ግንባታ እያሳየች ባለው ፈጣን እርምጃ የአህጉሪቱ እውነተኛ ውብ አበባ ሆና በመላው አፍሪካ ፊት አብባለች።
“የአፍሪካ ውብ አበባ” የሚለው ድንቅ ሐሳብ በመደመር ዕሳቤ በላብ፣ በሥራና በትጋት በተመዘገቡ ስኬቶች፣ በሕዝቦቿ ኅብረትና በጋራ ጽናት የተረጋገጠ ህያው እውነታ ነው።
ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ ጸጋ፣ ታሪካዊ ቅርስ፣ የመልክአ-ምድር ውበት እና ያልተነካ የሰው ኃይል አስተባብራ በመጠቀም የአፍሪካ የኩራት፣ የብልጽግና እና የውበት ማዕከልነቷን በየቀኑ በተግባር በማረጋገጥ ላይ ትገኛለች። ይህ የተስፋ፣ የውበትና የከፍታ ምዕራፍ የሁላችንንም የተቀናጀ ጥረት፣ የጋራ ርብርብ እና የጽናት ጉዞ አጠናክሮ መቀጠልን የሚጠይቅ ነው።
በየዘርፉ የምናስመዘግበው ሀገራዊ ስኬት፣ የከተሞች እና የገጠር ልማት እንዲሁም የኢኮኖሚ ጥንካሬ ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለዓለም የምታበራው የብርሃንና የጽናት ወገግታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ሲሆን፣ የአፍሪካ ውብ አበባነቷም ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ መሠረት እንዲይዝ ያደርገዋል።
EBC
#ዜና / በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት (PEFA) የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ተካሄደ
#DGC ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የሚካሄደውን የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት (PEFA) ግምገማ አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክና ወርክሾፕ ተካሄደ።
የሕዝብ ፋይናንስ አስተዳደርን ጥራት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቅልጥፍና የሚገመግመው ይህ ዓለም አቀፍ የግምገማ ማዕቀፍ፤ የበጀት ዝግጅትና አፈጻጸምን፣ የገቢና ወጪ አስተዳደርን፣ የሂሳብ አያያዝን፣ የሪፖርት አቀራረብን እና የቁጥጥር ሥርዓትን ይመለከታል።
በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰመድ አህመድ እንደገለጹት፤ ግምገማው በቅርቡ የሚካሄድ በመሆኑ የቀረውን ጊዜ በአግባቡና በተቀናጀ መንገድ መጠቀም ያስፈልጋል። አክለውም ግምገማው የፋይናንስ ቢሮ ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ የአመራር ቁርጠኝነት፣ የተቋማት ቅንጅትና የባለሙያዎች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በበኩላቸው፤ ስልጠናው እንደ መንግስት ያለንን ውስን ሀብትና በጀት በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል።
በፉአድ አሊ
ፎቶ ፦ሰላም አበበ
ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DGCOMU
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@Direcommunication
ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB
ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
#ዜና /የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የ5ኛ የሥራ ዘመን የሴቶች አባላት (ኮከስ) የመክፈቻ ጉባኤ አካሂዷል
#DGC ጥቅምት 24/2019
በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማለት የኅብረሰቡን ግማሽ አካል ማንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን፤ የሰላም፣ የዲሞክራሲ እና የልማት ምሰሶ የሆነውን ኃይል በአግባቡ መጠቀም መሆኑን አስገንዝበዋል።
ባለፉት የሥራ ዘመናት በምክር ቤቱ ውስጥ የነበሩ የሴቶች አባላት ያሳዩአቸው አበረታች ውጤቶችና የተከናወኑ ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት አፈ ጉባኤዋ በቀጣይም ያሉትን ስራዎች በጋራ በማከናወን ክፍተቶችን ለመሙላት ጠንካራ ማዕቀፍና የተናበበ አሠራር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ የ5ኛው የሥራ ዘመን የሴቶች ምክር ቤት አባላት በሕግ አውጪነት፣ በቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም በሕዝብ ውክልና ላይ ያላቸውን አቅም በማሳደግ፤ የሴቶችን የጋራ ድምፅ በማሰማት ለተቋማዊ ውጤታማነት በጋራ እንዲሰራ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም አብራርተዋል።
በመጨረሻም ክብርት አፈ ጉባኤዋ ለጉባኤው መሳካት ሁለንተናዊ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በጉባኤው ላይ ኮከሱን በበላይነት የሚመሩ አመራሮች ሹመት ተከናውኗል።
!
ኢትዮጵያ በመስኖ ስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ተአምር እና የብልጽግና ጉዞ
********
ኢትዮጵያ ልጆቿን አስተባብራና ተፈጥሯዊ ሀብቷን ተጠቅማ ማንኛውንም ፈተና ማለፍ እንደምትችል በመስኖ ስንዴ ልማት ባስመዘገበችው ታሪካዊ ስኬት በተግባር አረጋግጣለች።
በመደመር መንግሥት በተዘረጋው አዲስ የሥራ ባህልና ቁርጠኝነት ያልተነኩ የሀገራችን አፈርና ወንዞች ወደ ታላቅ ሀገራዊ ሀብትነት ተቀይረዋል።
ይህ የለውጥ ጉዞ በ2011 ዓ.ም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንችላለን በሚል አዲስ አስተሳሰብ በ3,500 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረ ሲሆን በ2018 ዓ.ም የምርት ሽፋን 3.7 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል።
በዚህም የምርት መጠኑ መቶ ሺዎችን ተሻግሮ ወደ 149.2 ሚሊዮን ኩንታል ከፍ ያለ ሲሆን ይህም በዝናብ ከሚመረተው ጋር ተዳምሮ የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከመሸፈን አልፎ ለውጭ ገበያ የሚተርፍ ሆኗል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ም/ኃላፊ ድሪባ ገለቴ (ዶ/ር) እንደገለጹት ስኬቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጀምሮ እስከ ታችኛው አመራር እና መዋቀር ድረስ በተደረገ ከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነትና የጋራ አጀንዳ የመጣ ነው።
ለሠላሳ ዓመታት በምርምር ሸልፍ ላይ ተቀምጠው የነበሩ የምርጥ ዘር ዝርያዎች ወደ ማሳ በመውረዳቸው ውጤት መመዝገቡን እና በአሁኑ ወቅት የመስኖ ስንዴ ምርምር በልዩ ፕሮግራም ደረጃ ተቋቁሞ ተቋማዊና ቴክኖሎጂያዊ አቅም መገንባቱን አብራርተዋል።
የዓለም አቀፍ ግብርና ምርምር ማዕከል ከፍተኛ አማካሪ ዘውዴ ቢሻው (ዶ/ር) በበኩላቸው ቀደም ሲል የተተወው ሰፊው የቆላማ አካባቢ ከውኃ ሀብት ጋር በመገናኘቱ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ የማምረት ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማውጣት ከውጭ የምታስገባውን የስንዴ ምርት በሀገር ውስጥ መተካቷ ከኢኮኖሚያዊ ስሌት በላይ የሀገርን ነፃነትና ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ ታላቅ ፖሊሲያዊ ሽግግር መሆኑን ጠቁመዋል።
የስንዴ ተመራማሪ ውለታው ታደሰ (ዶ/ር) እንደሚያስረዱት ደግሞ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት አሁንም በሙሉ አቅሙ አልተጠቀምንበትም።
ያልተገደቡ ወንዞችን በመገደብና ሜካናይዝድ ግብርናን በማስፋፋት አሁን ያለውን ምርት በሁለት እና በሦስት እጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፤ አፍሪካ በየዓመቱ ለስንዴ የምታወጣውን 20 ቢሊዮን ዶላር ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ምቹ የአየር ጠባይና የተፈጥሮ ሀብቷን ተጠቅማ አህጉሪቱን የመመገብ ታላቅ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።
በስንዴ ልማት የተጀመረው ይህ ይቻላል የሚል አስተሳሰብ ዛሬ ወደ ሩዝ፣ በቆሎ፣ አኩሪ አተር እና እንስሳት እንዲሁም ሰብሎች ምርታማነት በመሸጋገር ላይ ይገኛል።
ይህም የውጭ ምንዛሪን በመቆጠብ፣ የወጪ ንግድ ዕድልን በመክፈትና አግሮ-ኢንዱስትሪን በማስፋፋት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያፋጥን ሕያው የመንደርደሪያ መንገድ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
EBC
#ዜና /''የአውሮፓ ህብረት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትምህርትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በቅርበት እንዲሰራ እንፈልጋለን።'' ዶክተር ኡባ አደም የድሬደዋ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት
#DGC ጥቅምት 24/2019
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤምስበርገር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ጉብኝት በማካሄድ፣ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በቀጣይ የትብብር ዕድሎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባ አደም፣ ዩኒቨርሲቲው ሥራ ከጀመረ ብዙ አመታትን ባያስቆጥርም በተከታታይ በሚያከናውናቸው የማሻሻያ ሥራዎች የመማርና የማስተማር ሁኔታውን እያሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል።
በተማሪዎች ቅበላ ቁጥርና በሚሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች ረገድም ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ባለው ትብብር፣ ተማሪዎችና መምህራን በስኮላርሺፕ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑንም ዶክተር ኡባ አስረድተዋል።
በቀጣይም የአውሮፓ ህብረት በዩኒቨርሲቲው የመማርና የማስተማር ሂደት ላይ የበለጠ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በተለይም በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማትና በሌሎች የትምህርት ዘርፎች ዘላቂ ድጋፍ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል።
አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤምስበርገር በበኩላቸው በአውሮፓ ህብረትና በኢትዮጵያ መካከል የረጅም ጊዜ የቆየ መልካም ግንኙነት መኖሩን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የህብረቱ 23 አባል ሀገራት አምባሳደሮች በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን አድርገው እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
ትምህርት የአውሮፓ ህብረት በትኩረት ከሚሠራባቸው ዋና ዋና ዘርፎች አንዱ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ዘርፍ የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ለማድረግ ህብረቱ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
#ዜና /የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ አካሄደ
#DGC ጥቅምት 24/2019
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 4ተኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል።
አስቸኳይ ጉባኤው በምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን አቅራቢነት አጀንዳዎችን በመዘርዘር ተጀምሯል።
በዚህም መሠረት የ4ኛው የስራ ዘመን መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ፅድቋል።
በተጨማሪም የንብረት ታክስ (Property Tax) ደንብ በበጀት ኢኮኖሚ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አማካኝነት ቀርቦ በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ ሊጸድቅ ችሏል።
በዚሁ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች ሹመት በምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ በክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ አቅራቢነት የጸደቀ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ክብርት ወይዘሮ ከሪማ አሊ የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ክብርት ወይዘሮ ሰዓዳ አዋሌ የግብርና ልማት፣ ተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ክብርት ወይዘሮ ሚስራ አብደላ የሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ እንዲሁም ክቡር አቶ ቢቂላ ታደሰ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም የብልጽግና ፓርቲን እና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያካተቱ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢዎችና አባላት እጩዎች ቀርበው ሹመታቸው ፅድቋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የምክትል ፕሬዚዳንቶች ሹመት በአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም አቅራቢነት የጸደቀ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ክቡር አቶ ኢብራሂም ሂርሲ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ክቡር አቶ መሐመድ ኢብራሂም ደግሞ የድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።
በተጨማሪም የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት በከንቲባው አቅራቢነት በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ የጸደቀ ሲሆን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የቦርድ አባላት ሹመትም ፀድቆ 1ኛው አስቸኳይ ጉባኤ ተጠናቋል።
የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፎሮም ኤምስበርገር ድሬዳዋ ለስራ ጉብኝት ተገኝተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም እንዲሁም የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ለአምባሳደሯ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደሯ በድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ የስራ ጉብኝት ቆይታ እንደሚኖራቸው ለማወቅ ተችሏል።
ጉብኝቱ በድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ በአውሮፓ ህብረት መካከል ባሉ የትብብር ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ይጠበቃል።
በዳግማዊ ፍቃዱ
ፎቶ፦አገኘሁ ሸዋረረጋ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሕልውና ምሰሶ፣ የሉዓላዊነት ጽኑ ዋስትና እና የቀጠናው የማይበገር የሰላም ማማ
*******
የአንድ ሀገር መኖር እና አለመኖር የሚወሰነው በመንግሥት ሥርዓት ጽናት እና በሰራዊቱ አጠቃላይ ሉዓላዊ ቆራጥነት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ዑደቶች ውስጥ ዘመናት ተሻግሮ፤ የውጭ ወራሪዎችን እና ሀገር አፍራሽ ኃይሎችን በመመከት ሀገርን ያቆየ ታላቅ የታሪክ ባለቤት ነው።
ይህም ሆኖ የሀገርን ሰላም እና ሉዓላዊነት ለመናድ የተነሱ የውጭ ኃይሎችም ሆኑ ከውስጥ ማኅፀን ወጥተው ከጠላት ጋር ያበሩ አካላት የነደፏቸው ሴራዎች ሁሉ፤ በመከላከያ ሰራዊት የማይበገር ብረት ቆራጥነት ተሰባብረው መቅረታቸውን የዘመናት ታሪክ በድምቀት መስክሯል።
ሰራዊቱ በጦር ሜዳ ባስመዘገባቸው ደማቅ ድሎች የጠላትን ቅስም በመስበር የሀገርን የማይናወጥ ታሪክ በደምና በአጥንቱ አጽንቷል።
መከላከያ ተዳክሟል በሚል ቅዥት የተነሱ አካላት የገጠሟቸው ውድቀቶች፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በእሳት ውስጥ አልፎ እንደተፈተነ ወርቅ ማዕድን የጠራ እና የጸና መሆኑንም በተግባር አረጋግጧል።
ሰራዊቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከማስጠበቅ ባለፈ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተማማኝ የሰላምና የጸጥታ ምሰሶ በመሆን፣ አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን በብቃት በመወጣት የቀጠናው የማይበገር የደህንነት ጋሻ ሆኖ ቆሟል።
የዛሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአየር፣ በምድር፣ በባሕር እና በሳይበር ቴክኖሎጂዎች የተሟላ ሉዓላዊ ኃይል ሆኖ እንዲደራጅ ተደርጓል።
ትናንትን ከነገ ለማስተሳሰር የሚያስችሉ የሎጂስቲክስ፣ የስትራቴጂ፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ሥልጠናዎች በከፍተኛ ደረጃ ተሟልተዋል።
ሰራዊቱ የኢትዮጵያን የውኃ ሀብቶች (የዓባይ ወንዝ እና የቀይ ባሕርን የጂኦፖለቲካዊ ጥቅሞች) ከማስከበር አንፃር ቀን ከሌሊት በመንቃት የሀገራችንን የልማት መሠረቶች በጽናት ጠብቆ እያቆመ ይገኛል።
ለሠንደቅ ዓላማ ክብር እና ለሀገር ነፃነት ሲል ሕይወቱን የሚሰዋ፣ በአእምሮና በአካል የበለጸገ፣ ቴክኖሎጂን ከዕውቀት ጋር አቀናጅቶ ውጊያን በአጭር ጊዜ የሚሰራና የሚጨርስ ብቁ ኃይል ተገንብቷል።
EBC
