HOP Ministry
Відкрити в Telegram
HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
564
Підписники
+524 години
+257 днів
+5930 днів
Архів дописів
564
#Corrie_ten_boom_the_Woman_Who_Hid_Hope
☑️Hid Jews from the Nazis during WWII
☑️Survived a concentration camp
☑️Lost her family but never lost her faith
☑️Chose forgiveness instead of hatred
☑️Inspired millions with her courage
The story of Corrie ten Boom continues on HOP Ministry Telegram Channel.
Join Us:👇
https://t.me/hopministry10
564
“እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።”
— ሉቃስ 11፥28 (አዲሱ መ.ት)
#HOP_Ministry — Hear. Obey. Practice.
በሉቃስ 11:28 መሰረት፦ የእግዚአብሔርን ቃል መስማትን፣ መታዘዝን፣ መኖርን (መተግበርን) መርሁ ያደረገ፤ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ግቡ የሆነ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ነው።
አገልግሎቱ ከሚያካትታቸው ዋና ዋና ይዘቶች መካከል:-
☑️የእግዚአብሔር ቃል ጥናት፣
☑️መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጥሞና ጽሁፎች፣
☑️በየዘመናቱ፣ በአገልጋዮቹ ሕይወት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያሳዩ የተሃድሶ ታሪኮች
☑️የሕይወት ምስክርነቶች
☑️መንፈሳዊ ግለ-ታሪኮች
☑️መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ክርስቲያናዊ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን:
👇
https://t.me/hopministry10
በአንድነት በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እንደግ፤ ለእግዚአብሔር መንግሥት ፍሬ እናፍራ!
564
" #እናንተ_ግን፣ #አብሮአችሁ_ስለሚኖርና_በውስጣችሁ_ስለሚሆን_ታውቁታላችሁ።"
በእኛ ውስጥ ሆኖ፣ በእኛ ውስጥ ኖሮ ራሱን ለሚገልጥልን፣ ትውውቃችን ከውጪ በተነገረንና በምንሰማው ነገር ላይ ብቻ እንዳይመሰረት #በአብሮነቱ፣ ከእኛ ጋር በመኖሩ ሕያውነቱን፣ እውነትነቱን ለሚያረጋግጥልን፣ ለሚያስረግጥልን፤ የርስታችን መያዣ፣ ዋስትናችን ለሆነው ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ይሁን!!
እኛን እንደማንነታችን ቢሆን አይደለም ቤቱ፣ መኖሪያው ለማድረግ ይቅርና ለመጎራበት እንኳ የሚመርጠን አልነበረም፤ እርሱ ግን ማደሪያ መቅደሱ እንሆን ዘንድ ቀድሶ ሊያድርብን ወደደ። " #እናንተ_ግን፣ #አብሮአችሁ_ስለሚኖርና_በውስጣችሁ_ስለሚሆን_ታውቁታላችሁ።" የሚል ምስክርነት፣ ማረጋገጫም በኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጠን።
አሁን #አምላክ_ወዴት_አለ? እያልን ውጭ ውጪውን ስናይ አንባክንም፣ ዝለንም ተስፋ አንቆርጥም። ይልቁንም በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ የሚለው መሠረት ላይ ቆመን፣ ካወቅነው በላይ ልናውቀው፣ ከተጠጋነው ይበልጥ ልንጠጋው እንበረታለን፤ እርሱም እንደ ወገግታ ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል።
የቱንም ያልህ ብንወዳጅና ብንወዳቸው፤ ወዳጅ ያልናቸው የሰው ልጆች ልብ የሚጣልባቸውና የመለዋወጥ ዕድል የሌላቸው አይደሉም። ከዕለታት በአንዱ ቀን የቀን ጎዶሎ ይመጣና በልባችን ላይ ከሰጠናቸው ዙፋን ይወርዳሉ።
ሕያው፣ ከእኛ ጋር ለዘላለም የሚኖር አምላክ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ግን እንጠረጥረው ዘንድ ሰው አይደለምና ታማኝ እንደሆነ ይኖራል፤ በአብሮነቱም በሕይወት ያኖረናል።
ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
¹⁷ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ አብሮአችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።
564
HOP Ministry — Hear. Obey. Practice.
A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives.
Based on Luke 11:28.
Join us: 👇
https://t.me/hopministry10
☑️ Daily Devotionals
☑️ Bible Reflections
☑️ Revival Histories
☑️ Spiritual Biographies
☑️ Faith-Based Storytelling
☑️ Testimonies
☑️ Amharic Translated Christian Literature
564
#A_Glimpse_into_the_Life_of_Praying_Hyde
እስቲ ልጠይቃችሁ ቅጽል ስም ይኖረን ይሆን? ካለን፤ ምናልባት ስለ እኛ የሆነ ነገር ይናገር ይሆናል፡፡ ቅጽል ስሙ እውነተኛ ህይወቱን ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው “ጸሎተኛው ሃይድ” (Praying Hyde) የሰው ልጅ ካለበት ዘርፈ ብዙ ምድራዊ ጥያቄ የተነሳ ወይ ስጠኝ አልያም ግደለኝ በማለት ከአምላኩ ጋር በሚሟገትበት በዚህ ዓለም ላይ ቢኖርም የእርሱ የሙግት ርዕስ ግን ከጀማው ርዕስ ጋር ለየቅል ነበር፡፡
ሰፊውን የህይወት ዘመኑን በጨለማ ስላሉት በመማለድ ያሳለፈው የጸሎት ሐዋርያው “John Hyde” የዘወትር ጩኸት “ #እግዚአብሔር_ሆይ_ነፍሳትን_ስጠኝ_አለበለዚያ_ግደለኝ!!” የሚል ነበር፡፡ በህንድ በነበረው አገልግሎት ወቅት አያሌ ሌሊቶችን በእግዚአብሔር ፊት ማሳለፍ ልማዱ ከመሆኑ የተነሳ የሀገሬው ሰዎች “የማይተኛው ሰው” የሚል ስያሜ የሰጡት የኢሊኖይ ፕሪስባይቴሪያን አገልጋይ ልጅ ጆን ኔልሰን ሃይድ ይሄ ሸክም በልቡ ሊሞላ የቻለው ከአገልጋይ አባቱ እያየ ካደገው ወንጌልን በታማኝነት የመስበክ ትጋት፣ እንዲሁም በምስባክ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቡ መሰዊያ ላይ እግዚአብሔር ወደ መከሩ ሰራተኞችን አብዝቶ እንዲልክ ከሚደረገው ምልጃ የተነሳ ነው፡፡
እውቁ የዌልስ አገልጋይ Seth Joshua በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፡- “ጸሎት ከተዘጋው እልፍኝ በስተጀርባ የሚደረግ ስውር ተግባር ነው፡፡ እጅግ የተካኑት ጉድጓድ ቆፋሪዎች ከእይታ ተሰውረው ወደ ጥልቁ ይወርዳሉ፡፡ በዚህ መስክ ላይ የተሰማሩ አያሌ ሰዎች ናቸው፤ ነገር ግን ራሳቸውን ሰውረውና አጥፍተው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታገሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡"
” ኢየሱስና እርሱ ብቻ!!" ማላጁ ሃይድ እጅግ ሀሴት የሚያደርግበት ነገር ቢኖር #ከኢየሱስ_ጋር_ለብቻው መሆን ነው፡፡ በዚህ ሰው ህይወት ውስጥ ካሉት በጣም አስደናቂ ባህሪያት አንዱ በዚህ ሁኔታ ተደብቆ ለረጅም ጊዜ መቆየት መቻሉ ነው፤ በተለምዶው እንጨት፣ ሳርና ገለባ ለሰው እይታ ቅርብ ሆነው በቀላሉ ሲገኙ፤ ዋጋቸው የከበረው ወርቅ፣ ብርና የከበሩ ድንጋዮች ግን በጥልቅ ውስጥ ስውር ከመሆናቸው የተነሳ በቀላሉ አይገኙም፡፡ እንደዚሁ ጆን ሃይድም ከእግዜር ስውር ሀብቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ የጸሎት ሐዋርያው ገና በለጋ ዕድሜው ነው ሚሲዮናዊ ሆኖ ወደ ህንድ ያቀናው፡፡
ይቀጥላል...
