uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Відкрити в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
912
Підписники
-224 години
-127 днів
+5130 днів
Архів дописів
ኢማሙ አህመድን መሆን ባትችል አቡሀይሰምን ሁን!!! አብዱላህ የኢማሙ አህመድ ልጅ እንድህ ይላል: አባቴን ሁል ጊዜ ""ጌታየ ሆይ አቡ ሀይሰምን ማረው እዘንለት" ሲል እሰማዋለሁ፣አቡሀይሰም ማነው ስል ጠየኩት ኢማሙ አህመድ: አንድ ፊቱን ያላየሁት የገጠር ሰው ነው አለ ከግርፋቴ በፊት በነበረችው ሌሊት ጨለማ እስር ቤት አረጉኝ፣ በጨለማው አንድ ሰው ነካ አረገኝና አንተ ኢማሙ አህመድ ነህ?አለኝ አወ አልኩ ታውቀኛለህ? አለኝ አላውቅህም አልኩት አቡ ሀይሰም እባላለሁ ሌባ ጠጪ ሽፍታ ነኝ በንጉሱ መዝገብ ላይ የሰፈረ በተለያየ ጊዜ አስራ ስምንት ሺህ ግርፋት ተገርፌያለሁ ያን በሸይጣን መንገድ ላይ ሁኘካ ችየዋለሁ አንተ በአላህ መንገድ ላይ ነው ታገስ ያ አህመድ አለኝ!!!!! ከዚያም ታስሬ ግርፋቱ ሲጀምር እያንዳንዱ አለንጋ ጀርባየ ላይ ሲያርፍ የአቡ ሀይሰምን ንግግር አስታውስና ለራሴ አህመድ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ ነህ ፅና እላለሁ።!!!! መናቂቡ ኢማሙ አህመድ ገፅ 450_451 https://t.me/rebizidniielma

👉ፍፁም ሴት አለች⁉️ --------------------- አታስመስይ ራስሽን ሆነሽ ኑሪ ለሆነ ሰው ልዩ ፍጡር ልትሆኝ ትችያለሽ እንጂ በፍፁም ስህተት አልባ ልቶኝ አትችይም። المرأة هي الأساس الذي يقوم عليه المجتمع، فهي الأم، والأخت، والزوجة، والابنة، والصديقة، فهي مربية الأجيال.. ሴት ማለት ማህበረሰቡ የሚገነባበት መሰረት ነች። እሷ እናት፣ እህት፣ ሚስት፣ ሴት ልጅ፣ጓደኛ ብሎም የትውልዶች መሸጋገሪያ ድልድይ ነች። ولها الدور الأكبر في بناء المجتمع وتقدمه، وشاركت في بناء الحضارات منذ القدم وكان لها دور بارز في الحروب، ማህበረሰቡን በመገንባት እና በማሳደግ ትልቁን ሚና አላቸው። ከጥንት ጀምሮ ሥልጣኔዎችን በመገንባት ላይ ተሳትፈዋል።
በጦርነትም ውስጥ ትልቅ ሚና ነበራቸው።
الرجل يعشق بعينيه والمرأة بأذنيها ወንድ ልጅ በአይኑ ሴት ደግሞ በጆሮዋ ትወዳለች ይባላል። 👉በጆሯቸው ስለሚወዱ ነው መሰል.... لا تعرف المرأة قيمة سعادتها مع زوجها إلّا عندما تفارقه.... አንዲት ሴት ከባሏ ጋር ያላትን የደስታ ዋጋ እስክትለየው ድረስ አታውቀውም ይባላል። 👉ይህ ብቻ አይደለም ሴቶች ስኬትም ናቸው። وراء كل رجل عظيم امرأة. ከእያንዳንዱ ታላቅ ወንድ ጀርባ ሴት አለች። وراء كل رجل سعيد امرأة لا تفارق الابتسامة شفتيها. ከእያንዳንዱ ደስተኛ ወንድ ጀርባ በከንፈሮቿ ላይ ፈገግታ የማይለያት ሴት አለች። 👉ይህ ሁሉ ማለት ግን ስህተት አልባ ናችሁ ማለት አይደለም። ብዙ ሴቶች ግን በሆነ ሰው በተፈለጉ ቁጥር ለሁሉም ሰው ፍፁም እንከን አልባ የሆኑ ይመስላቸዋል ይህ ትልቅ #ስህተት ነው። «በሆነ ሰው የተወደድሽው ፍፁም ሆነሽ ሳይሆን የወደደ ሰው አይን መልካምሽን ብቻ እንጂ ስህተትሽ ወይም ድክመትሽ ላይ ስለማያተኩር ነው ገባሽ⁉️» በህይወት ግቡ ላይ የሆነችው ሀሴት፡ በወንድ ልጅ ጀርባ አለችው ልዩ ሴት፡ ይወዳታል እንጂ እሱን ስላልከዳች፡ ፍፁም አይደለችም ከስህተት የፀዳች፡ 👉.....በአንድ ወቅት አንድ ሰው ተጠየቀ⁉️ ፍፁም ሴት አለችን አሉት⁉️ «እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ስለ ፍፁምነት የሚጨነቀው ማን ነው?
ጨረቃ እንኳን ፍፁም አይደለችም።
በሽንቁሮች የተሞላች ናት። ባሕሩ በሚያስደንቅ ሁኔታ ቆንጆ ነው፤ግን ጨዋማና ጥልቁ ጨለማ ነው። ሰማዩ ማለቂያ የለውም፤ ግን ብዙውን ጊዜ ደመናማ ነው። ስለዚህ የሚያምር ነገር ሁሉ ፍፁም ሳይሆን ልዩ ነው። እናም እያንዳንዷ ሴት ለአንድ ሰው ልዩ ልትሆን ትችላለች እንጂ ፍፁም አይደለችም። ስለዚህ "ፍፁም" ለመሆን መሞከርሽን አቁሚ። የማትፈልጊውን በመሆን፤ ያላመንሽበትን ነገር በማድረግ ሌሎችን ለመማረክ አትሞክሪ። «እኔም በዚህ ቋጨሁ» ከውብ ማህፀኗ በምጧ የወጣሁ፡ እስካሁኗ ሰዓት የሷ አይነት ሴት ያጣሁ፡ ግን በህይወቴ ውስጥ ባሳለፍኩት ሁሉ፡ እጂግ ልዩ ፍጡር ሴት ልጅ አለች አሉ፡ ባያስመርጠኝም ፀባይና መልኬ፡ ውብ የትዳር አጋር ባይጠፋም በልኬ፡ ወንድ ልጅ ነኝና ሴት ልጅ ነች ታሪኬ፡ ሐቁን ለመናገር ፈፅሞ አልሰለችም፡ አወ እርግጠኛ ነኝ ፍፁም ሴት የለችም፡ ሁሉም እንድሰማ መልዕክት እየረጨሁ፡ ሀሳቤ ባያልቅም ቃሌን በዚህ ቋጨሁ፡ «ፍፁም ግን ማንም የለም» .....ኑረዲን አል-ዓረብ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

☀️ የአያሙል ቢድ (የነጫጭ ቀናት) ጾም ማስታወሻ! የአላህ መልክተኛ ﷺ በየወሩ 13፣ 14 እና 15ኛ ቀናትን እንድንጾም ይመክሩን ነበር። የዚህ ወር የአያሙል ቢድ ጾም ነገ ይጀመራል፤ የቻለ ይፁም፣ ያልቻለ ደግሞ ሌሎችን በማስታወስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁን! ⇛ አያሙል ቢድ — ሐሙስ (13) ⇛ አያሙል ቢድ — ጁምዓ (14) ⇛ አያሙል ቢድ — ቅዳሜ (15) 🔸 قال ﷺ: «إذا صمت من الشهر ثلاثًا، فصم ثلاث عَشْرَةَ، وأربع عَشْرَةَ، وخمس عَشْرَةَ.» t.me/SleSlkachin

የመስጂድ ውስጥ ልመና ~ ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ ﺃﺻﻞ اﻟﺴﺆاﻝ ﻣﺤﺮﻡ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﺧﺎﺭﺝ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﺇﻻ ﻟﻀﺮﻭﺭﺓ ، ﻓﺈﻥ ﻛﺎﻧﺖ ﺿﺮﻭﺭﺓ ﻭﺳﺄﻝ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﺆﺫ ﺃﺣﺪاً ﻛﺘﺨﻄﻴﻪ ﺭﻗﺎﺏ اﻟﻨﺎﺱ ، ﻭﻟﻢ ﻳﻜﺬﺏ ﻓﻴﻤﺎ ﻳﺮﻭﻳﻪ ﻭﻳﺬﻛﺮ ﻣﻦ ﺣﺎﻟﻪ ﻭﻟﻢ ﻳﺠﻬﺮ ﺟﻬﺮاً ﻳﻀﺮ اﻟﻨﺎﺱ ﻣﺜﻞ ﺃﻥ ﻳﺴﺄﻝ ﻭاﻟﺨﻄﻴﺐ ﻳﺨﻄﺐ ، ﺃﻭ ﻭﻫﻢ ﻳﺴﻤﻌﻮﻥ ﻋﻠﻤﺎً ﻳﺸﻐﻠﻬﻢ ﺑﻪ ﻭﻧﺤﻮ ﺫﻟﻚ ﺟﺎﺯ "ልመና በመሰረቱ በመስጂድም ውስጥ ይሁን ከመስጂድ ውጭ ለአስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር አይፈቀድም። አስገዳጅ ሁኔታ ኖሮ መስጂድ ውስጥ ቢለምን - ማንንም ካላስቸገረ - የሰዎችን ጫንቃዎች መረማመድን ይመስል፣ - በሚያወራው ላይ ካልዋሸ ፣ ማለትም ያለበትን ሁኔታ ብቻ ከጠቀሰ፣ - ሰዎችን በሚጎዳ ጩኸት ካልጮኸ - ለምሳሌ ኸጢቡ ኹጥባ ላይ እያለ መለመንን ይመስል፣ ወይም ዒልም እያደመጡ ካልረበሻቸው ፣ ወዘተ (መለመን) ይቻላል።" [ጊዛኡል አልባብ፣ አሰፋሪኒይ፡ 2/267] በድጋሚ የተለጠፈ = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ውዱ ነብያችን ሲያርፉ በሚስታቸው እቅፍ ውስጥ ሆነው ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሚስት እስከመጨረሻው መንገድ ድረስ የሕይወት ጓደኛ መሆኗን ነው፡፡ ከሷ ውጭ ማን አለህ? እሷስ ካንተ የበለጠ ማን አላት?
ውዱ ነብያችን ሲያርፉ በሚስታቸው እቅፍ ውስጥ ሆነው ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሚስት እስከመጨረሻው መንገድ ድረስ የሕይወት ጓደኛ መሆኗን ነው፡፡ ከሷ ውጭ ማን አለህ? እሷስ ካንተ የበለጠ ማን አላት? ባል ሲታመም ሚስቱ ምን ያህል እንደምትወደው ይገነዘባል፡፡ ሚስት ስትደክም፣ ስትሰበር፣ ስትተክዝ ... ባል ምን ያህል እንደሚያስብላት ትረዳለች፡፡ በማስመሰል ዓለም እየኖራችሁ እውነተኛውን ዓለም አትርሱ፡፡ ለማኅበራዊ ሚዲያው ሰፊ ጊዜ እየሠጣችሁ ማኅበራዊ ኑሮውን አትዘንጉ፡፡ እውነተኛውን ቤት መገንባት ትታችሁ የውሸት ፎቅ አትሥሩ፡፡ በሶሻል ሚዲያ ከሺዎች  በላይ ሰው ይከተለኛል፡፡ በታመምኩ ጊዜ ግን ከጎኔ የምትሆነው ሚስቴ ብቻ ናት፡፡😊

የማይሆን መስሎኝ ያኔ ሲበረታ ሌቱ፤ አይነጋም እያልኩኝ አዘንኩኝ በከንቱ፤ ያኔ መታገሴ ሀዘኔን መቻሌ፤ ለስኬት ዳርጎኛል አወይ መታደሌ። የተወሰደ

«የሌሎችን ወሬ (ንግግር) ወደ አንተ የሚያመጣውን ሰው ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እርሱ የአንተንም ወሬ ወደ ሌሎች ያስተላልፋልና»።
«የሌሎችን ወሬ (ንግግር) ወደ አንተ የሚያመጣውን ሰው ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እርሱ የአንተንም ወሬ ወደ ሌሎች ያስተላልፋልና»።

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ። ነቢዩሏህ ኢብራሂም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰይፍ የተዋጉ ነቢይ ናቸው ፡፡

በነገራችን ላይ...ይህች ዓለም በብዙ ክህደት የተሞላች ነች። ◇ የጠገንካቸው ሰዎች መልሰው ይሰብሩሃል፣ ◇ ያስታመምካቸው ተገልብጠው ያዋርዱሃል፣ ◇ ያበራህላቸው ዞረው ያጨልሙብሃል፣ ◇ እንዲነሱ ብለህ መነሻ የሆንካቸው ተቀይረውብህ አንተኑ ይጥሉሃል፣ ◇ እንባህን ያፈሰስክላቸው ብዙም ሳይቆዩ ያስለቅሱሃል፡፡ አወ!ዐይነ-ሥውር ዐይኑ በተገለጠለት ቅፅበት የሚያደርገው የመጀመሪያው ነገር ዱላውን መወርወር ነው። t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

ምንም ያህል ከመድረሳ ብትርቅ፤ ከሸይኾችህ እግር ብትጠፋም፤ ያኔ ስታወግዛቸው የነበሩ ነገሮች ሁሉ ዛሬም ውግዝ ናቸው። ዘረኝነት ዛሬም ጥምብ ነው። ሽርክና ቢድዓም ዛሬም ያው ናቸው።  ሃሜት ዛሬም የሰው ስጋ ከመብላት እኩል ነው። ሃራም ሁሉ ዛሬም አልተቀየረም፤ ሃራም ነው። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ባለህበት አላህ ይጠብቅህ እንወድኃለን። እናከብርሃለን። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሐፊዘሁላሁ ''ትልቅ ባለውለታችን'' ነው። በተለያዩ ጊዜዎች በሚፅፋቸው ወቅቱን በጠበቁ ፅሑፎቹና በጣፋጭ አንደበቱ በሚያደርጋቸው ሙሐደራዎች በተሳሳቱ አመለካከቶችና ግለሰቦች ላይ በሚሰጣቸው ምላሾቹ ብዙ የተሳሳቱ የጥመት ቡድኖችን አውቀን እንድንርቅ ሰበብ ሆኖናል። አላህ ይጠብቀው። ሙሉ ጤናውን ይመልስለት ብለን ዱዓዕ ከማድረግ ውጪ ውለታውን ችለን መመለስ አንችልም። ብቻ አላህ ይውደደው በጀነትም ይመንዳው። ኡስታዛችንን እንወደዋለን፣ እናከብረዋለን፣ ስንወደው ግን በምክኒያት ነው ፣ በሐቅ በሰለፊያ መንገድ ላይ እስካለ ድረስ እንወደዋለን በምንችለው ነገር ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን ኢንሻአላህ። አረቦች እንዲህ ይላሉ፦ "من لم يستطع الصعود يسب الجبل" ምን ማለት መሰላችሁ " ተራራ ላይ መውጣት ያልቻለ ተራራውን ይሳደባል" ማለት ነው። ለማለት የፈለኩት አንዳንድ የአህባሽ፣ የኢኽዋን እና የለተሞ መንጋዎች የኡስታዛችንን ሀሳብ በመረጃ መሞገት ሲያቅታቸው መሳደብንና ቅጥፈት መንዛትን ተያይዘውታል። በተለይ የለተሞ መንጋ ቅጥፈትን ቁርስ ምሳና እራቱ አድርጎታል። መች በዚህ ብቻ አበቃ! ሱብሀነላህ! ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ታሞ በነበረ ጊዜ አህባሾች እና የለተሞ መንጋዎች አላህ በዛው በወሰደው በማለት ሞቱን ሲመኙለት ነበር። ይህ የሚያሳየው የአህባሽ እና የለተሞ መንጋዎች ምን ያክል ውስጣቸው እንደተቃጠለ ነው። የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብዕር ለመንጋዎች ሚሳይል ሆኖባች እረፍት እና ምቾት ነስቷቸዋል። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የሆነ ፅሑፍ ከለቀቀ ልክ ቦምብ እንደተለቀቀባቸው ነው የሚንቀጠቀጡት። ቃጠሎውን ይጨምርላችሁ ብያለሁ። ደግሞ በጣም የሚገርመኝ የተፃፈውን አማርኛ እንኳን ማንበብ አቅቶት ገልብጦ የሚያነብ ንግግሩን ከአውዱ አውጥቶ አዛብቶ የሚረዳ የለተሞ መንጋ ወንድ ሴቱ ትልቅ ትንሹ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ላይ ተናበው ዘመቻ ሲከፍቱ ማየት ነው። እናንተ ከንቱ የለተሞ ስብስቦች ሆይ! እንዲህ ሲባል አልሰማቹምዴ? "نبح الكلاب لا يضر السحاب" "የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳውም" ሺህ ጊዜ ጧት ማታ ብትጮሁ ነውራችሁን በአደባባይ ከማስወጣት ውጭ ምንም የምትጨምሩ ሆነ የምትቀንሱት ነገር የለም። ምናልባት ጯሂ ሁሉ ተከታይ አያጣምና የናንተ አይነት አስተሳሰብ ያላቸውን muغ ፈሎች ከዙሪያችሁ ተሰባስበው ሊያጨበጭቡ ይችሉ ይኖናል። አንድ ነገር ግን ልንገራችሁ፦ ዛሬ ሰው ላይ እየዋሻችሁና እየቀጠፋችሁ ከሰበሰባችኃቸው ሰዎች ውስጥ በጊዜያዊ ጩኸታችሁ የተታለሉ ማስተዋል የሚችሉ ሰዎች ነገ ላይ ነውራችሁን ሲያውቁ አኝከው ይተፋችኃል። 👉 እስቲ ንገሩኝ! የተውሂድና የሱና ኪታቦችን በማቃጠል ምን አተረፋችሁ? ለኡስታዙ ሞትን በመመኘትስ ምን አይነት ደስታ ተሰማችሁ? ደግሞ የምቀኝነት መጥፎነቱ ባለቤቱን ራሱን መብላቱ ነው።ገጣሚው እንዲህ ይላል፦ (لله در الحسد ما أعدله بدأ بصاحبه فقتله) وقال الشاعر : *اصبرْ على حسدِ الحسودِ  ....  فإنَّ صبرَك قاتلُه النارُ تأكلُ بعضَها  ....  إن لم تجدْ ما تأكلُه ምቀኛን የፀጋ መወገድ እንጂ ሌላ ምንም አያስደስተውም። قال معاوية بن أبي سفيان رضي الله عنهما: (كلُّ الناس أستطيع أن أرضيه إلا حاسد نعمة، فإنه لا يرضيه إلا زوالها)  📜المجالسة وجواهر العلم(3/50) ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን ያለ ምንም ድንበር ማለፍ እንወደዋለን። የሰው ልጅ እንደመሆኑ ሊሳሳት ይችላልና በተሳሳተበት ነጥብ ላይ ግን አንከተለውም። لأنه بشر يصيب ويخطئ وليس بمعصوم. ↪️ ዘመናዊ ሙሪድነታችሁ እንዳይነቃባችሁ ያን የሽማግሌ ተሳዳቢ በዱኒያዊ ጥቅም ሰክሮ እልል በል ሲሉት እንደ ሴት እልል የሚል ዐብዱል ሀማድ አልለተሚ የበቀልና የእልህ ትችቶቹን ስላልተቀበልን ለተራ ወሬዎቹ ግምት ስላልሰጠን የኢብኑ ሙነወር ሙሪዶች ትሉናላችሁ። የእናንተ ሁኔታኮ፦ "رمتني بدائها وانسلت " "በሽታዋን ወርውራበኝ አፈተለከች'' እንደተባለው ምሳሌ ነው። ሸይኻችሁ መርቀን ሲለው ትዝ ያለውን ፉላን ሙብተዲዕ፣ፉላን ዷል ሙዲል፣ ሙመይዕ…  እያለ ሲቀባጥር ከስር ሆናችሁ ያን የከረፋ ጩኸቱን እየሰማችሁ ከማስተጋባት በስተቀረ ለምን ብላችሁ መጠየቅ የማታውቁ كالميت بين يدي" غاسله" አጣቢ ፊት እንደቀረበ ጀናዛ" የሆናቹ ፉጡሮች ሌሎችን ሙሪዶች እያላችሁ ለመወንጀል ሞራሉን ከየት አመጣችሁ!? እናንተኮ እፍረት የሚባል ነገር ስለማታቁ እንጅ አይደለም ሌሎች ላይ አፍ መክፈት ቀርቶ ነውራችሁን ተሸክማችሁ መደበቅ የነበረባችሁ ከንቱ የመንጋ ጥርቅም ናችሁኮ።"ሞኝ ካመረረ በግ ከረረ መመለሻ የለውም" ይባል የለ?! ከራሳችሁ ጋር ተጋጭታችሁ እስከምትናከሱ ድረስ ለጊዜው እንደ ደነበረ በሬ ተራገጡ ተራው የናንተ ነውና።አላህ በሃያት ካቆየን መጨረሻችሁን የምናይ ይሆናል። ያን በዘረኝነት ላይ የቆመ እልህና በቀልን አንግቦ የተነሳ በዲን ሽፋን በመሪነትና በዱኒያ ጥቅማጥቅም የሰከረ የለተሞ መንጋ ኢንሻአላህ መጨረሻቸውን አላህ ያሳየናል። ✍️ አቡ ሰህላ ሙስጠፋ ሰኢድ

" አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት አይቻልም፤ ለማብራራት ብትሞክርም ለዚያ ሰው ምክንያታዊ ላይሆንለት ይችላል፡፡ =

♦️ይሔ ስለ ዑዝር ቢል ጀህል ሸይኽ ሙሐመድ አብዱል ወሀብ ኡዝር እንደሚሠጡ የተጠቀሰበት ማብራሪያ ነው ይቀጥላል 🎙ኡስታዝ አቡ ጁለይቢብ ወደ ቻናል ለመቀላቀል https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin

🌹 ልብ የሚወደውን ለመርሳት ጊዜ ይፈልጋል… አንዳንድ ጊዜ ሰው አንድን ሰው መፈለጉን ያቆመው ስለማይፈልገው ሳይሆን፣ እንደሚፈልገው ልቡን ማሳመን ስለሚያስፈልገው ነው። አእምሮ ነገሩን ቀድሞ ሊረዳ ይችላል፤ “ይህ ሰው አይፈልገኝም፣ መራቅ አለብኝ፣ መቀጠል አለብኝ” ሊል ይችላል። ግን ልብ ያንን እውነት ለመቀበል ጊዜ ይፈልጋል። ምክንያቱም ልብ በቃል ብቻ አይረሳም፤ በትዝታ፣ በልማድ፣ በተስፋና በብዙ ስሜቶች ውስጥ ይኖራል። 🥀 አንድ ሰው አይፈልግህ ከሆነ ሁልጊዜ በአፉ ላይ “አልፈልግህም” ማለት አይጠበቅበትም። ተግባሩ ራሱ መልስ ሊሆን ይችላል። ◆ትደውላለህ… አያነሳም። ◆ትጽፋለህ… አይመልስም። ◆ትቀርበዋለህ… ይርቃል። ◆ለአንተ ጊዜ የለውም፣ ለአንተ መልስ የለውም፣ በሕይወቱም ውስጥ ያለህ ቦታ በተግባሩ እየታየህ ነው። ◆እንደዚህ ሲሆን በተደጋጋሚ መጠየቅ ልብህን ከመጠበቅ ይልቅ የበለጠ ሊያደክመው ይችላል። አንዳንድ ጊዜ መልስ የሚያስፈልገን ከሰውየው ሳይሆን ከራሳችን ልብ ነው። ▶“ለምን አልመለሰልኝም?” ▶“ለምን አይፈልገኝም?” ▶“ምን አጠፋሁ?” ▶“ምን ብሠራ ይቀርበኛል?” ብለን ደጋግመን ከመጠየቅ ይልቅ፣ አንድ ቀን በጸጥታ ራሳችንን፦ ➥“ይህ ሰው በተግባሩ መልሱን አሳይቶኛል፤ አሁን የእኔ ሥራ መልሱን መቀበል ነው” ማለት ያስፈልገናል። ▶ይህ ማለት ወዲያውኑ መርሳት ማለት አይደለም። ▶አንድ ቀን ውስጥ የወደድከውን ሰው አንድ ቀን ውስጥ መርሳት አትችልም። ▶ዛሬ ልብህ ሊያለቅስ ይችላል፤ ነገ ትንሽ ይረጋጋል፤ ከነገ ወዲያ ደግሞ ትንሽ ይበረታል። እንዲህ እያለ አንድ ቀን ትዝታው የሚያሳዝንህ ነገር ሳይሆን ያለፈ ምዕራፍ ይሆናል። 🌿ስለዚህ እራስህን አትውቀስ። “ለምን አልረሳሁትም?” ብለህ ራስህን አትጫን።ልብ የሚወደውን ለመልቀቅ ጊዜ ይፈልጋል። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ውስጥ ራስህን አትጥፋ። ●ለማይመልስልህ ሰው የምትሰጠውን ፍቅር፣ ለራስህ ሰላም ስጠው። ●ለማይፈልግህ ሰው የምትጠብቀውን ጊዜ፣ ለራስህ ሕይወት ስጠው። ●እና የልብህን ባዶነት በሰው ለመሙላት ከመሞከር ይልቅ፣ አላህን አቅርብ። ምክንያቱም አንድ ሰው ከሕይወትህ መውጣቱ ማለት ሕይወትህ አብራ ቆማለች ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች የሚመጡት ለመቆየት ሳይሆን፣ አንድ ምዕራፍ ሊያስተምሩን ነው። እና አንድ ቀን ወደኋላ ስትመለከት፣ 🌹“ያኔ የተሰበረ የመሰለኝ ልቤ፣ በእውነቱ አላህ ከማይጠቅመኝ ነገር እያራቀኝ ነበር” ትላለህ። 🌿 t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asself

🌿 ልባችንን ከሰዎች በመጠበቅ ብቻ አንረጋጋም፤ ከአላህ ጋር በማቀራረብ ነው እውነተኛው ሰላም የሚገኘው። አንዳንድ ጊዜ መፍትሔው ብዙ ማሰብ አይደለም፤ ነገሩን ለአላህ አሳልፎ መስጠት ነው። ሰዎች ሊረዱን ባይችሉም፣ አላህ የልባችንን የማንናገረውን እንኳን ያውቃል። ስለዚህ ልባችንን በጭንቀት አንሙላው፤ በተወኩል እና በዚክር እናሳርፈው።

☕🌿 የቡና ልዩ ጥቅሞች ! 🌿☕ ሸይኽ ዐብደረዛቅ አልበድር ሀፊዘሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ «فَعَلَيْكَ بِشُرْبِ الْبُنِّ فِي كُلِّ لَحْظَةٍ فَإِنَّ بِهَا يَا صَاحِ خَمْسَ فَوَائِدِ» “ስለዚህ ወዳጄ ፣ ቡናን መጠጣትን አትተው፤ በእሷ ውስጥ አምስት ጥቅሞች አሉ” ይላል። ☕ 🌿 ① نَشَاط — ንቃትና ብርታት ይሰጣል ቡና ለአንዳንድ ሰዎች ንቃትን የምትጨምርና ድካምን የምታሳንስ መጠጥ ናት። ጠዋት ላይ የቡናዋ መዓዛ እና ጣዕም ቀኑን በንቃት ለመጀመር ደስ የሚል ጓደኛ ያደርጋታል። 🌿 ② هَضْم ምግብን ለመፍጨት ይረዳል ቡና ከምግብ በኋላ ለአንዳንድ ሰዎች የምግብ መፍጨትን እንደምትረዳ ይነገራል። 🌿 ③ قَطْعُ الْبَلَاغِم — አክታን ለማስወገድ ይረዳል “በላግም” የሚለው ቃል አክታንና በጉሮሮ የሚሰበሰብን ነገር ያመለክታል። ስለዚህ ቡና እነዚህን ለገሮች ለማስወገድ ይረዳል። 🌿 ④ نُورٌ لِلْعَيْن — ለዓይን ብርሃን ይጨምራል ቡና በውስጡ ለዓይን ንቃትና ብርሃን እንደምትሆን ተገልጻለች። በተለይም የጠዋት ቡና ከንቃት ጋር ተያይዞ የሚሰማውን ያን የልዩ ደስታ ስሜት ያስታውሳል። ☕ 🌿 ⑤ قُوتٌ لِعَابِد — ለዓምላኪ ሰው ኃይል ናት ይህ በጣም ውብ የሆነው ክፍል ነው። “ለዓምላኪ ኢባዳ ላይ ላለ ሰው ኃይል ናት” ይላል። ማለትም የቡና መጠጣት እንደ መጠጥ ደስታ ብቻ ሳይሆን፣ ሰውነትን እንዲነቃና ሰውየው በሚፈልገው መልካም ሥራ ላይ እንዲበረታ የሚያግዝ ነገር እንደሆነ ሸይኹ ያቀርባታል። ☕ ቡና ለአንዳንዶች መጠጥ ብቻ አይደለችም፤ የጠዋት አጋር፣ የውይይት ጓደኛ፣ የእንግዳ አቀባበል ምልክት እና የተለያዩ ትዝታዎች አካል ናት። 🌿 “فَعَلَيْكَ بِشُرْبِ الْبُنِّ…” 🌿 ወዳጄ ፣ የቡናዋን ጣዕም ብቻ አትውደድ፤ ከእሷ ጋር የሚመጣውን የጓደኝነት፣ የእንግዳ አቀባበልና የውብ ውይይት ጊዜም ውደድ። ☕ 🌿 ማስታወሻ፦ እነዚህ የተገለጹት ጥቅሞች ናቸው፤ የሕክምና ምክር ወይም ለሁሉም ሰው የሚሰራ የጤና ዋስትና አይደሉም። በተቃራኒው ጉዳት የሚያመጣባቸው ሰዎችም መጠጣት የለባቸውም በተለይ በሀኪም ከተከለከሉ አይጠጡ። እዚህ እያወራን ያለነው ለቡና አፍቃሪያንና ለሚስማማቸው ጥቅም ለምታመጣላቸው ሰዎች ነው። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

☕ ለቡና ወዳጆች ☕ የቡና መጠጥ ለሰውነት አካላት አነቃቂ ነው፤ ጣዕሙም እንደ ስንዴና እንደ ማር የሚያስደስት ነው። በጉዞ ወቅት የዕድሜ ሙሉ አጋርና አጽናኝ ናት፤ መዓዛዋም ሲሰራጭ እንደ ሚስክ መዓዛ ያለ ማንኛውንም ክርክር የማያስፈልገው ደስታ ትሰጣለች። በጠዋት የነፍስ ምኞትና ደስታ ናት፤ በረጋ መንገድ በጊዜዋ ስትመጣ፣ የሚወዳትን ሰው ልብ ታስደስታለች። በችሎታ የተዘጋጀች ቡና ምንኛ ደስ የምትል ናት! የመጣውንም ሆነ ሊጓዝ የተዘጋጀውን እንግዳ ለማክበር የምትቀርብ። በየቤቱ ሁሉ ስሟና በጎነቷ ይነገራል፤ ወዳጅንም ያለ ብዙ ንግግር በመደሰትና በማስደሰት ታስቃለች። “እንኳን ደህና መጣህ!” ትላለች፤ ፈገግታዋም ሁልጊዜ ከአንደበቷ አይርቅም፤ ክብርና መልካም ምግባር ላለው እንግዳም ይህንኑ የአቀባበል ቃል በደስታ ደጋግማ ትናገራለች። በእሷ ላይ ጉድለት የለም፤ ከጉዳትም የጸዳች ናት፤ ስለዚህ ንጹሕ ቡና ጠጣ፤ ከጉዳትም አትፍራ። — ሸይኽ ዘይድ ቢን ሃዲ አል-መድኸሊ رحمه الله 📖 المنظومات الحسان (الديوان المليح)، ص 343. t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَىَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوْقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ ۖ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ ﴿55﴾ [3:55] 👉 አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡