uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Відкрити в Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
902
Підписники
-424 години
-167 днів
+4030 днів
Архів дописів
🎉 አስደሳች ዜና!! ♥️የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) ✍️ የኪታቡ ፀሐፊ፡ አቡ ዐብዱረሕማን አኒስ ብኑ ሷሊሕ 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረ
🎉 አስደሳች ዜና!! ♥️የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) ✍️ የኪታቡ ፀሐፊ፡ አቡ ዐብዱረሕማን አኒስ ብኑ ሷሊሕ 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል ባጂ 🗓 መቼ ይጀምራል? ነሐሴ 4 ፣ ሰኞ ⏰ የዘወትር ፕሮግራማችን ቀናት እና ሰዓት፡ ☑️ ቀናት፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ እና ሰኞ ☑️ሰዓት፡ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ⚠️ሐቂቃ ይህ ኪታብ በተለይም በዚህ ዘመን በድብቅ ወንጀል ለተፈተነ፣ ስማርት ስልኮችና ኢንተርኔት ላመጡት የብቸኝነት ፈተና መፍትሔ የሚሰጥ፣ እንዲሁም ጌታችን አላህ ሁሌም እየተመለከተን መሆኑን በማስታወስ ልብን የሚያነቃቃ ድንቅ ኪታብ ነው! 🔴ትምህርቱ ቀጥታ ስርጭት የሚሰጥበት ቻናል፦🔗
✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1 😬የኪታቡን PDF ለማገኘት:t.me/Sle_qelbachn1/1963

መውሊድ በማን ተጀመረ? በሙዞፈር ወይስ በ“ፋጢሚያ” ሺዐ? ~ የመውሊድ ደጋፊዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። ነገር ግን በነዚህ ሺ0ዎች እንደተጀመረ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ማስረጃዎች በጨባጭ አሉ። ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ። 1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):— በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚይ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡- “የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውዳመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውዳመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ ﷺ ልደት (#መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ የልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁን)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም የልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436] መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዓዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን ﷺ ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዓዙል ሑነፋእ፡ 3/101] ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው። እያስተዋላችሁ! 2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):— ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢይ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡- ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر “ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ ﷺ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ (ዐለይሃ ሰላም) መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን (ዐለይሂመ ሰላም) መውሊድ እና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው።” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219] 3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲይ (821 ሂ.):— ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወራ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ ﷺ መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካለ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካል። [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576] ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው። ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒ'ላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው። ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው። ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ እራሱን ነው የሚያታልለው። ስለዚህ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” ማለት ውሃ አያነሳም። “ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም። በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው። ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “እሱ ጀማሪ ነው” አላሉም። መቅሪዚይ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር። [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚ'ላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት። ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ከሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው። በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው። ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው። አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው። ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም በተጨባጭ አሉ። ያቁት አልሐመዊይን አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው። ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡- “የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው። እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር። ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚመፀውት ነበር። እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃ .ዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር። በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡- ‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ! ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ።’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138] ያቁት አልሐመዊይ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው። በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃዲቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም። ከነቢዩ ﷺ ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም። እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም።

የማለዳ መልእክት (43) ~ ለዒልም እንቅፋት ከሚሆኑ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ቀሪ ማብዛት ነው። ተደጋጋሚ ቀሪ፦ * የዒልምን ጣእም ያሳጣል። * ባለፈን ትምህርት እንዳንቆጭ ይልቁንም መቅረትን እንድንላመ
የማለዳ መልእክት (43) ~ ለዒልም እንቅፋት ከሚሆኑ ሰበቦች ውስጥ አንዱ ቀሪ ማብዛት ነው። ተደጋጋሚ ቀሪ፦ * የዒልምን ጣእም ያሳጣል። * ባለፈን ትምህርት እንዳንቆጭ ይልቁንም መቅረትን እንድንላመድ /'ኖርማል' አድርገን እንድንወስድ/ ያደርጋል። * ከነ ጭራሹ ከዒልም ሰፈር የመራቅን በር ይከፍታል። ስለዚህ ስንፍናችን ጋር ጊዜያዊ እንኳን ቢሆን ወዳጅነት ከመመስረት እንጠንቀቅ። ልማድ ይሆናል። በጊዜ ድክመታችንን እናስተካክል። ዒልምን በመከታተል ላይ ቆራጥ እንሁን። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ፈፅሞ ከዒልም ማእዶች ያለን ተሳትፎ አይቆራረጥ። ዛሬ ቆራጥ ከሆንን የየቀኑ የተጠራቀመች ዒልም በዓመቱ መጨረሻ ትልቅ ክምችት ይወጣታል። ጠብታ ተጠራቅሞ ብዙ ያቁራል። ጠብታ ውሃ ድንጋይ ይበሳል። ፅናት ኖሮን ጥረታችን ዓመታትን ከተሻገረ በርግጠኝነት በአላህ ፈቃድ ጉልህ ለውጥ ይኖረናል። በዚህ አብዛኛው ሰው - አስተማሪውን ጨምሮ - በስሜት፣ በቡድንተኝነት፣ በአስመሳይነት፣ በእልህ፣ በቢድዐ፣ በሞራል ዝቅጠት፣ ... በተለከፈበት ዘመን ከአላህ ጋር እንደ ዒልም ያለ ዋስትና የለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 26 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

መልዕክት አድርሱልኝ 👉መልዕክት አድርሱልኝ ጦሳ ላይ ላለችው፣ 👉ሰወችን በማጥመም ቢዚ ለሆነችው፣ 👉ተይኝ ልማርበት ልሞጥል ኪታቤን፣ 👉በወዳ በወድህ አትወስውሽው ቀልቤን፣ 👉 ሁሌ በክርክር አታድርቂው ልቤን፣ 👉ተምሬ ላሥተምር ዘመድ ቤተሠቤን፣ 👉አላማ አለኝ እኔ ላሳካ ሀሳቤን፣ 👉እኔን ተይኝ በቃ እስኪሳካ ህልሜ፤ 👉ቦታየን አውቄ  ልራመድ እዳቅሜ፣ 👉እውቀት  ልቅሰም ዛሬ ከሁሉ አስቀድሜ፣ 👉አይለፍ ግዜዬ ውድነው ሰአቴ የተሠጠኝ እድሜ፣ 👉ምክር ሰምቻለሁ  ከመሻይኾቸ፣ 👉አለብኝ አደራ ከአስተማሪወቸ፣ 👉እውቀትን እዲቀስም ሁሉን ነገር ትቸ፣ 👉በአደብ እድማር አገቴን ደፍቸ፣ 👉እእህቴአደብ ያዥ አንችም ተመከሪ፣ 👉ሰሰተርቆጠብ ብለሽ ቂራአቱን ቅሪ፣ 👉ሰአትሽ አይባክን ስትከራከሪ፣ 👉#የጀምእያ ሴት እያልሽ መጮኹ በፖስት በኮሜት፣ 👉ፍፁም አይጠቅምሽም አይሆንሽም እውቀት፣ 👉ምን አለሽ እውቀቱ ስለጀምእያ፣ 👉ጥቀሽ ማሥረጃ ከቁርአን አያ፣ 👉ከረሱል ንግግር አምጭ ከሀድሱ፣ 👉መልካም ቀደምቶቸ ምን አሉ ስለሱ? 👉ነዋቂዱል ኢስላም ኡሡሉ ሰላሳ ከተማርሽ  ቃልበቃል፣ 👉ሽርክ የሠራን ሁሉ ከኢሥላም 👉ለማውጣት በአንች ፈህም ይበቃል፣ 👉ያንች ጉድ ብዙ ነው በዚህ መቸ ያልቃል፣ 👉ትቸ ካላለፍኩት ሰአት ይጠይቃል፣ 👉አባትሽ ተስሎ ወደዶሪህ ሲሄድ፣ 👉ለጨሌው ላድባሩ እናትሽ ስታርድ፣ 👉ለለምንዝም አልሽ ያኔ ከተረዳሽ  ተውሂድ ፣ 👉ለምን አታሥረጅም የሀቁን ጎዳና የነብዩን መንገድ፣ 👉ለምን አትሆኒም ለቤተሠቦችሽ መልካም አረአያ፣ ብዬ ስጠይቅሽ ብለሽ መለሽልኝ፦ 👉የዛኔ አልተማርኩም ጃሂላ ነኝ እኔም የእነሡው አምሳያ፣ 👉ስማር ነው ያወኩት ሀቁ ሲብራራልኝ ከቁራአን አያ፣ 👉አታሥተነትኒም አታስቢም ትንሽ? 👉ካንች የተለየ ምን ላይ ነው ጥፋቱ የእናትና የአባትሽ? 👉እህቴ ረጋ በይ ይቀርሻል ብዙ፣ 👉ያለ እውቀት መናገር ከባድ ነው መዘዙ፣ ✍️ ኡሙ ሙቅቢል  ቢንት ሙሐመድ

شرح كتاب ضوابط الجرح والتعديل ( رفع متجدد بإذن الله ) #شرح_كتاب_ضوابط_الجرح_والتعديل_دروس_عام_١٤٤٢هـ_

Repost from ፈዋኢድ
"በሙስጠላሕ አል-ሐዲስ ፈን አንድ ኪታብ እኔ የሰጠሁትን ደርስ በትክክል የሚማር እና ከዚያም ፈተና የሚወስድ ሰው ኢጃዛ ( እሰጠዋለሁ።"ብለዋል ሸይኽ አር-ዚሂይ حفظه الله ሸይኻችን በሙስጠላሕ አል-ሐዲስ ያስተማሯቸው ደርሶች በዚህ ቅደም ተከተል ብትቀሩ መልካም ነው 1. አል-ሙኽተሰር ፊ ሙስጠላሕ አህል አል-አሰር (የሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ ድርሰት)። https://t.me/AliAlrazihi/2759 2. ቱሕፋቱል ሙብተዲ ቢሸርሒ አል-በይቁኒያ (እንዲሁም የሸይኹ ድርሰት)። https://t.me/AliAlrazihi/8664 3. አል-ሙቂዛህ የዘሀቢይ። https://t.me/AliAlrazihi/8945 4. ኢኽቲሳሩ ዑሉም አል-ሐዲስ። https://t.me/AliAlrazihi/9457 5. ኑዝሐቱ አን-ነዘር። https://t.me/AliAlrazihi/5866 6. ደዋቢጡ አል-ጀርሕ ወት-ተዕዲል። https://t.me/AliAlrazihi/3791 7.ሸርሕ ዐሊል አት-ቲርሚዚ – በኢማም ኢብን ረጀብ። https://alrrazihi.al3ilm.net/13237

ስለኢኽዋኖች አካሄድና የበሰበሰ ስለሆነው መንሀጃቸው የተሰጠ ተውጅሀት በኡስታዝ አወል አህመድ መነዮ https://t.me/Multeka_Selefiyin

Repost from N/a
ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  ብዙ  የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ። ጥያቄ 1 💎ተዉሂድ በስንት ይከፈላል?

እኔን ሁሌም የሚገርመኝ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር በእነዚህ ሰዎች ላይ አንዳች ነገር በጻፈ ቁጥር የሚፈጠረው ግርግር ነው። ሁላችንም እንደታዘብነው፣ ኡስታዙ ብዕሩን ሲያነሳ ሁሉም ያለውን የጥላቻ መሳሪያ
እኔን ሁሌም የሚገርመኝ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር በእነዚህ ሰዎች ላይ አንዳች ነገር በጻፈ ቁጥር የሚፈጠረው ግርግር ነው። ሁላችንም እንደታዘብነው፣ ኡስታዙ ብዕሩን ሲያነሳ ሁሉም ያለውን የጥላቻ መሳሪያ እየጎተተ ከአንድ ጉድጓድ ይወጣል። ዱላ ያለው ዱላውን፣ ፍልጥ የያዘውም ፍልጡን ይዞ ለጥቃት ይነሳል። ለ«ወሳኝ ቀን» ብለው በየጉድጓዳቸው የደበቁት ጥላቻ እንዲህ በአደባባይ ይፈሳል! የሚገርመው የታሪክ ግፍ  ይኸው ነው፦ ቢድዓን ለማሰራጨት በሐሰን ታጁ የተጻፈውና ስለ «መውሊድ» የሚከራከረው መጽሐፍ በክብር ተቀምጦ ሳይነካ፤ የቢድዓን አንገት ለመቁረጥና ለብዥታዎች (ሹብሃዎች) በቂ ምላሽ የሰጠበት የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የሱና መጽሐፍ ግን በእሳት እንዲጋይ ተደረገ። አይ በውር ድንብር የሚጓዘው የለተሞ መንጋ! አላህ ወደ ትክክለኛው መንገድ(መንሐጀ ሰለፍ) ይመልሳችሁ።

«የተይሚያ ልጅ» የተይምያ ልጅ ዒልም ያነገሰው ህብረ-ቢድዐን አተራመሰው የሱንናው ጥይት ጥንት የተኮሰው ዘመን ተሻግሮ ዛሬም ጠበሰው ቢድዐ ሲሮጥ ዙፋን ሊወጣ አሸማቀቀው እያቀናጣ «ኢብኑ ተይሚያህ የ
«የተይሚያ ልጅ» የተይምያ ልጅ ዒልም ያነገሰው ህብረ-ቢድዐን አተራመሰው የሱንናው ጥይት ጥንት የተኮሰው ዘመን ተሻግሮ ዛሬም ጠበሰው ቢድዐ ሲሮጥ ዙፋን ሊወጣ አሸማቀቀው እያቀናጣ «ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ» ከተሰኘው የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መፅሃፍ የተወሰደ መፅሀፉን ያላነበባቹህ አንብቡት። ወላሂ! ትጠቀሙበታላቹህ። መጽሐፉ እንዲሁ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በውስጡ በርካታ ቁም ነገሮችንም የያዘ ነው። በተለይ ባለሀብቶች የዚህ አይነት መጽሐፎችን በየመስጂዶች፣ መድረሳዎችና መርከዞች እንደዚሁም በየክፍለ ሀገሩና በየዩኒቨርሲቲዎች እየገዛችሁ ለሙስሊሙ ማህበረሰብና ወጣቶች ብታበረክቱና የብዙዎችን የተሳሳተ ግንዛቤ በመቀየር ረገድ የበኩላችሁን ብትወጡ ወንድማዊ ጥቆማየ ነው። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

خُـــــذ العــــــــلم من الأكابر واترك
أصـــــحاب مقاطـع الآهات والصـــــــرخات والموسيـــــقىٰ في اليوتيوب..!والدعاة الجهــــــــلة..! 👈العلامة ابن باز رحمه الله 👈العلامة الألباني رحمه الله 👈العلامة ابن عثيمين رحمه الله 👈العلامة الفوزان حفظه الله 👈العلامة مقبل الوادعي رحمه الله 👈العلامة اللحيدان رحمه الله 👈العلامة ربيع المدخلي رحمه الله 👈العلامة فلاح مندكار رحمه الله 👈العلامة عبدالسلام بن برجس رحمه الله 👈العلامة الإتيوبي رحمه الله 👈العلامة الجامي رحمه الله 👈العلامة النجمي رحمه الله 👈العلامة زيد المدخلي رحمه الله 👈العلامة عبيد الجابري رحمه الله 👈العلامة عبد المحسن العباد حفظه الله 👈العلامة صالح آل الشيخ حفظه الله 👈العلامة محمد بن هادي حفظه الله 👈العلامة صالح السحيمى حفظه الله .. وغــيرهم من العلـماء و المشايخ المعروفـين بصـحة العـقــيدة عقـيدة أهل السـنَّة والجماعة"وسلامة المنهج "

ونحن كذلك -وإن لم نلقه- نشهد الله على حب الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله. = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

እውነተኛ ወዳጅ << ቢርቅም ቅርብ ነው >>

አቡል ዓስ ሆይ! እኔ ከአንተ ልለይ ነው። ነገር ግን ልቤ ላንተ ባለው ፍቅርና ታማኝነት ላይ እንዳለች ነው የምታልፈው። አላህ ላንተ መልካሙን ይክፈልህ፣ በጥሩ ሁኔታ ጠበቅከኝ፣ ለአባቴም የገባኸውን ቃል ሞላህ..." ይህ የዘይነብ (ረ.ዐ) የመጨረሻ ንግግሯ ነበር።

ይህ ቻናል የተክፊርዮች ቻናል እንጂ የሰለፊዮች ቻናል አይደለም። በስም የሰለፍያን መንሀጅ ስለተመሳሰሉ ብቻ እንዳትሸወዱ! ሰለፊ ነን ስላሉ ብቻ ሰለፊ ናቸው ማለት አይደለም። ብዙ የነሱ ሹብሀ ያልገባ
ይህ ቻናል የተክፊርዮች ቻናል እንጂ የሰለፊዮች ቻናል አይደለም። በስም የሰለፍያን መንሀጅ ስለተመሳሰሉ ብቻ እንዳትሸወዱ! ሰለፊ ነን ስላሉ ብቻ ሰለፊ ናቸው ማለት አይደለም። ብዙ የነሱ ሹብሀ ያልገባቸው ወንድም እና እህቶች የፈትዋ ጥያቄ ለመጠየቅ ብለው እየገቡ ባለማወቅ እዛው እየተመሳሰሉ ነው ያሉት። 👉 ውድ የሰለፍይ ወንድም እህቶች!በመጀመሪያ ደረጃ እውቀት ከማን መውሰድ እንዳለብን ጠንቅቀን እንወቅ። ጥያቄ እኮ ጃሂልም ይመልሳል ግን መልሱ የተሳሳተ ነው ሊሆን የሚችለው።ጥያቄ ለመጠየቅ የሚመልስልን ሳይሆን ትክክለኛ እውቀት ያለው ሰው ነው የሚያስፈልገው። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444