ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
319
Підписники
-124 години
-27 днів
+5430 днів
Архів дописів
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
✍ እናቱን ለሚወድ ብቻ
🎂ደርሰሽ ለጡረታ
የዘጠኝ ወር ቤቴ
ኑሪልኝ እናቴ
የደስታ ማጀቴ
ውስጤ ነሽ አንጀቴ
🍢 እማየ🍢
ችግር አይቅረብሽ ኑሪ በደስታ
ተፈጥሮሽ ልዩ ነው የጀሊል ስጦታ
ሀቅ፣ሽን መጠበቅ ዛሬ ላይ ብረታ
በእጀ ላንከባክብሽ ደርሰሽ ለጡረታ
⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤
🎤 በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ካሳየ
ቻናሏን እናሳድጋት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
🌹 ፈገግ በሉልኝ 🌹
በበፊቱ ግዜ ነው ይባላል። ታሪኩ እናም አራት የገጠር ሰዎች በጀመዓ እየሰገዱ ነበር ከዛም ልክ ሩኩዕ ሲያረጉ አንዱ ወይኔ ወገቤን አለ ሁለተኛው ደሞ የወግብን ነገር አታንሳው ይለዋል። ንግግራችውን የሰማው ሶስተኛ ሰው ሶላት ላይ አይወራም ይላቸዋል ከሁሉም የባሰው አራተኛዉ አንተ ራስህ ሶላት ላይ አኮ ነህ ብሎት እርፍ
አውነተኛ ታሪክ የሆነ ነው።
⚠️ እውነተኛ ሰላም በተውሂድ ውስጥ ነው!
"ሰለፊይ ነህ?" ተብለህ ስትጠየቅ፤ በኩራትና በክብር "አዎ! ሰለፊይ ነኝ፤ በዚህም እኮራለሁ!" ብለህ መልስ። ምክንያቱም ሰለፊይ መሆን ማለት ከነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)፣ ከሶሃቦችና ከቀደምት ደጎች ፈለግ ጋር መሆን ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ ክብርና ጸጋ ነው።
⚠️ ተውሒድ የልብ መረጋጋት ሚስጥር ነው፦ እውነተኛውን የቁርአን ሰላምና የመንፈስ መረጋጋት ማግኘት የምንችለው በተውሂድ ላይ ስንጸና ብቻ ነው። በተውሂድ ላይ ስንሆን የዚህን ዓለም ጭንቀትም ሆነ የቀብሩን ስቃይ የምንጋፈጥበት ጽኑ ምርኩዝ ይኖረናል፤ እሱም አላህ ነው።
⚠️ ሰው በዱንያ ስልቱ፣ በሀብቱ ወይም በሌላ አካል ላይ መመካት የለበትም። ከአላህ ውጪ ያለ መጠጊያ ሁሉ እንደ "በሰበሰ እህል" ወይም እንደ "ሸረሪት ድር" ደካማ ነው። ጽኑ ድጋፍ ሊሆንህ የሚችለው የማይሞተውና የማይለወጠው አላህ
ሱብሃነሁ ወተዓላ ብቻ ነው።
⚠️ የምትሠራው እያንዳንዱ መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከፈለግህ ልብህን ከሪያእ (ለሰው ተብሎ ከሚሠራ ሥራ) አጽዳ። ስራህ ለሰው እይታ ከሆነ፣ ስራው ተቀባይነት አያገኝም፤ ድካምህም ከንቱ ይሆናል። ጥራት ያለው ሥራ በጥራት ከተጠበቀ ልብ ይፈልቃል።
ዛሬ የምንኖርበት መንገድ የነገውን ቤታችንን ይወስናል። ስለዚህ፦
- በተውሂድህ እዘዝ !
- በአላህ ብቻ ተመካ!
- ልብህን ለጌታህ ብቻ ጥርት አድርግ!
ያኔ በዱንያም በአኼራም የማትናወጥ ሰላም ትጎናጸፋለህ። አላህ በሀቁ መንገድ ላይ ያጽናን!
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ተውሒድ 1 ያደርጋል
በምስራቅ በምዕራብ በሰሜን ያላቹህ
እንዲሁም በደቡብ በውጭም ያላቹህ
ሙስሊም ሙስሊማቶች እንደ'ምን አላቹህ
የአላህ ሰላም እዝነት ሁሌ አይለያቹህ
አደራ እወቁልን አንደምወዳቹህ
በያላቹህበት አላህ ይጠበቃቹህ
በውል ተገንዝበን የጠላትን ሴራ
አፋርና ትግራይ ኦሮሞና አማራ
ወላይታና ጋሞ ባንድ ብንጣራ
ሃበሻ እንዲፈካ የተውሂዱ ጮራ
ጨለማው ተገፎ ሱናው እንዲያበራ
አቤት ውበታችን ስንቆም በጋራ
ሲዳማ ሶማሌ ጉራጌ ወላይታ
ሐረሪ ጌዴኦ ከፋ ጉሙዝ ቤርታ
ሀዲያና ጋሞ ኮንሶና ከንባታ
ብሄር ሳይገድበን ወሬና አሉባልታ
መስራት ያስፈልጋል በቀንም በማታ
ተውሒድን ለማድረስ በየሁሉም ቦታ
ሽርክ ተንሰራፍቷል ከተማ እስከ ገጠር
ድሬዳዋም በለው አዲስ አባ ሸገር
መቀሌና አሶሳ ቤንሻንጉል ሀረር
ሰመራና አሳይታ ዲላ ካብሪ ዳሃር
ጅግጅጋና ጅንካ ሽሬ ደብረ ታቦር
ደሴና ወልዲያ እንዲሁም ባህርዳር
ብዙ ኮተት አለ አዲስ ዘመን ጎንደር
ነቀምት ሻሸመኔ ቢሾፍቱና አሰላ
ዶሎ ኦዶ ሀረሪ ናዝሬትም ጋንቤላ
መወገድ ያለበት አለ ብዙ አተላ
ወላይታና አርባ ምንጭ ሀዋሳና ጅማ
ደብረ ማርቆስ አድዋ አክሱምና አዳማ
ብዙ ፍጥረት አለ ተውሒድን ያልተሰማ
አዎ!
ሽርክን አንኮታክቶ ተውሒድን ለማድረስ
ቢድዓን በታትኖ ሱናችን ለማንገስ
እንጣር እንትጋ እስክትወጣ እስትንፋስ
ኩፍር ይከፋፍላል ኢስላም ያዛምዳል
ሽርክ ይለያየናል ተውሒድ ያጣምራል
ቢድዓ ይበትናል ሱና ያስተሳስራል
ቢመርህም ዋጠው ተውሒድ 1 ያደርጋል
✍Abu Imran
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ!
የሚገርመው ነገር፣ አንዳንዶች ስለ ሸሪዓ ጥቃቅን ሕጋጋትና ዝርዝር ጉዳዮች ይጠይቃሉ የተጠሉ ነገሮችን (መክሩሃትን) ሲጠነቀቁ አልፎ ተርፎም ከአንዳንድ የተፈቀዱ (ሙባህ) ነገሮች እንኳ ሲታቀቡ ታያቸዋለህ።
ነገር ግን የዲኑ መሠረት (አስል አድ-ዲን) ላይ ሲደርስ፣ አንዳንዶቹ የተፈጠሩለትን የተውሂድ ምስክርነት (ሸሃዳ) ትርጉም እንኳ አያውቁም። ስለ መስፈርቶቹ (ሹሩጥ) ወይም ስለሚያፈርሱት ነገሮች (ነዋቂድ) ምንም የሚያውቁት ነገር የለም።
በዚህም ምክንያት በትልቁ ሽርክ (አሽ-ሽርክ አል-አክበር) ላይ ወድቀው ታገኛቸዋለህ፤ ወይም የአላህን ስሞችና ባህሪያት የሚያጣምሙ የጀህምያህ እምነት ተከታዮች ናቸው ወይም ደግሞ አላህ በፈጠረው ፍጡር ውስጥ ይሟሟል ወይም ይዋሃዳል (አህሉል ሑሉል ወል-ኢቲሓድ) በሚሉ የጥመት እምነቶች ያምናሉ።
አንዳንዶቹ በኢማን ጉዳይ ወይ ኻዋሪጆች ወይም ሙርጂአዎች ናቸው (ቀድር) ጉዳይም ወይ የፍፁም ነጻ ፈቃድ (ቀደርያህ) ወይም የጅብሪያህ (አስገዳጅነት) አራማጆች ናቸው።
ይህ ሁሉ የሆነው በጃሂልነት (ባለማወቅ) እና ለተውሂድ እምነት (ዓቂዳህ) ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠት ነው!
የአላህ ባሮች ሆይ! በዱንያም በአኺራም ሰላም እንድታገኙና እንድትደሰቱ፡ ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ፣ ከዚያም ተውሂድ!
ሸይኽ ዐብዱሰላም አስ-ሱሐይሚ
ያልበሰለ ደዕዋ
👉በጉራጌው አብሬት ደግሞ በሸከና፤
👉መርሳ አባጌትዬ እንዲሁም በዳና፤
👉በትግራይ ነጃሺ በወሎ ቦረና፤
👉የሸሆቹ ቀብር ሲመለክ በጠና፤
👉ዝም አለ አንደበትህ ህዝብህ እያለቀ፤
👉ተውሒዱን ከሽርኩ እየደባለቀ፤
👉አኽላቅ ትሰብካለህ ጧት ማታ ሰደቃ፤
👉ያላወቀው ወገን በሽርክ እያበቃ፤
👉በመከራው ዘመን ሰው ለዛፍ ተስሎ፤
👉ቃል ለሱ እየገባ ብጣሽ አንጠልጥሎ፤
👉የሞተን ሲማጸን ፈጽምልኝ ብሎ፤
👉ዝም ሲል ገረመኝ አንደበትህ ችሎ፤
👉ተው እንደሱ አይደለም የረሱሎች ጥሪ፤
👉ተውሒድን መስበክ ነው የደዕዋው ጅማሪ፤
👉ግባና ተከተል በረሱሎች ሱና፤
👉ባልበሰለው ደዕዋ ውጤት የለምና፤
✍️ ኡስታዝ አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር ሐፊዘሁላህ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በሀይቅ ከተማ ቢላል መስጂድ የተደረገ አድስ ሙሓደራ
ስለ ሽርክ እና መውሊድ ሰፋ ያለ ማብራሪያ
በሸይኽ አወል አህመድ አልከሚሴ ሓፊዘሁሏህ
ተዉሒድ
وما خلقت الجن والانس الا ليعبدون »
ጋኔንንና ሰውንም ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።
«አል ዛሪያት)):56
ولقد بعثنا في كل امه رسولا ان اعبدوا الله واجتنبوا الطاغوت »
በየህዝቦች ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣኦንታትንም ራቁ በማለት መልእክተኞችን ልከናል። «አል ነህል)) 36
ጌታህም (እንዲህ ሲል አዘዘ )
እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ ። በወላጆቻቹሁም መልካምን ስሩ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው አትገላምጣቸው መልካም ቃል ተናገራቸው ።
ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው ጌታዬ ሆይ በህፃንነቴ (በርህራሄ) እንዳሳደጉኝ እዘንላቸው በል። አል ኢስራእ «23:24))
واعبدوا الله ولا تشركوا به شيئا »
አላህንም ተገዙ በርሱ ምንንም አታጋሩ። አል ኒሳአ «36))
وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيْطَانٍ مَّرِيدٍ
ከሰዎቹም ያለ ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም ሁሉ የሚከተል ሰው አልለ፡፡
