هداية القلوب (የልቦች መሪ)
Відкрити в Telegram
229
Підписники
Немає даних24 години
+177 днів
+1530 днів
Архів дописів
⭕️የአላህን ቃል የአላህን ሸሪዓ
በማስተማር ላይ እና ሰዎችን
በመምከር ላይ ላለን......
ክፍል 1⃣
የአላህን ቃል እና የአላህን ሸሪዓ ማስተማር፣ሰዎችን መምከር፣ወደ አላህ መጣራት.....ጉዳዩ እጅግ ትልቅ ነው፤ደረጃው እና ብልጫውም ግዙፍ ነው፤ወደ አላህ የምንቃረብበት ትልቅ ኢባዳም ነው።አላህም በተከበርው ቃሉ እንዲህ ይላል፦
﴿ وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ﴾
ታዲያ ይህን ትልቅ ኢባዳ ስንፈጽም በርካታ ልንጠብቃቸው እና ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ ነጥቦች አሉ ።
በዚህ ታላቅ እና የተከበረ ጉዞ ላይ ልንጠብቃቸው እና ልንጠነቀቃቸው ከሚገቡ ጥቂት ነጥቦች መካከል፦👇
①ኢኽላስ፦ ወደ አኺራ እና ወደ አላህ ውዴታ የሚደረግ ጉዞ ሁሉ ኢኽላስን ይሻል፤ኒያን ማሳመር እና ኒያ እንዳይበላሽ ዘወትር ማከም እና መንከባከብን ይፈልጋል። ወደ አላህ መጣራት እና ሰዎችን መምከር የተሰኘው ትልቅ ኢባዳ ላይ ደግሞ ኒያን የሚያበላሹ ነገራት እጅግ የበዙ በመሆናቸው ጠንከር ያለ ኒያን የማከም ሂደት እና ኢኽላስን ለመላበስ ዘወትር አላህን ከመለመን ጋር መታገልን ይሻል።
✨ሱፍያን አሰውሪይرحمه الله "ከኒያዬ የበለጠ ለማስተካከል እና ለማከም አስቸጋሪ ሆኖብኝ የታገልኩት ነገር የለም" ይላሉ… አዎ ቀልብ ሁሌ እየተገለባበጠች ብታስቸግርም ስራዋን ሁሉ ለአላህ ብቻ ብላ እንድትሰራ ልናስተካክላት ይገባል።
✨ከእለታት በአንዱ ቀን ሱፍያን አሰውሪይ እና ፉደይል ኢብኑ ዒያድرحمهما الله ተቀምጠው ስለ አኺራ ትውውስ አደረጉ… በስተመጨረሻ ሱፍያን አሰውሪይ- "ይሄን መቀማመጣችን እጅግ የተባረከ እና መልካም መቀማመጥ እንደሆነ አስባለሁ" አለ ይሄኔ ፉደይል- "እኔ ግን ይሄ መቀማመጣችን እጅግ የከፋ እና መጥፎ መቀማመጥ እንዳይሆን እሰጋለሁ" አለው ሱፍያንም በመገረም "እንዴት?" ብሎ ጠየቀው
" አንተ ዘንድ ያለውን ያማረ ንግግር ሁሉ ተጠቅመህ ወደ እኔ አሳምረህ አላቀረብክልኝምን? እኔም እኔ ጋር ያለን መልካም ሁሉ ተጠቅሜ አሳምሬ ወደ አንተ አቅርቤዋለሁ እኔም ላንተ አወራሁ አንተም ለኔ አወራህ አለው
ሱፍያን ይሄን ሲሰማ ጺሙ እስኪረጥብ አለቀሰ እና እንዲህ አለው …( أحياك الله كما أحييتني)
✔️ኒያ መበላሸትን ቀደምቶች ይፈሩት እንደነበረው እና ከዛም በላይ ልንፈራው እና ልንጠነቀቀው ይገባል።ለሰዎች የምንናገራቸውንም ሆነ የምንጽፋቸውን እያንዳንዱን ቃላት የአላህን ፊት ብቻ ልንፈልግበት ይገባል። የእውነት የአላህ ፊት ተፈልጎባት ከእውነተኛ ቀልብ የወጣ ንግግር ከአድማጩ ቀልብ ይገባል… ከእውነተኛ ቀልብ የወጣ ጽሁፍ ከአንባቢው ቀልብ ሰተት ብሎ ይገባል… በረካውም ይበረክታል ለበርካቶችም ጠቃሚ ይሆናል። የአላህ ፊት ሳይፈለግበት የወጣ እያንዳንዱ ቃል ግን በወጣ ቁጥር ቀልብን እያጨለመ እያጠለሸ እና ወደ አላህ ቁጣ እያቀረበ ይሄዳል በረካው ይነፈጋል ጥቅም አልባም ይሆናል (والعياذ بالله)
✨ ለዚህም አንድ ቀን አሊይ ኢብኑ ፉደይል ለአባቱ እንዲህ አለው
"አባቴ ሆይ የሙሃመድ ﷺ ባልደረቦች ንግግር ምንኛ ያማረ እና ጣፋጭ ነው !!!"
አባትም:- " ልጄ ሆይ የነርሱ ንግግር ለምን እንዲህ ያማረ እና ጣፋጭ እንደሆነ ታውቃለህንን? "ብሎ ጠየቀው
ልጅም:- " አይ አባቴ አላውቅም "ብሎ መለሰ
እሱም" እነሱ እያንዳንዱ ንግግራቸውን ሃያል የሆነውን የአላህን ፊት ሲለፈለጉበት ነው" ብሎ መለሰለት
ወደ አላህ የሚጣሩ ቃላትን እየተጠቀምን ወደ ነፍሳችን ከመጣራት እንጠንቀቅ!!!
ኒያን ማስተካከልን አስመልክቶ ኡለማዎች"ኒያን ማስተካከል ስራው ከመሰራቱ በፊት፣ ስራው እየተሰራ እያለ እና ስራው ካለቀ ብኋላ ነው" ይላሉ
ፈገግታ እኛ ጋር
ለወንደምህ ፈገግ ስትል ምን ፈልገህ ነው ይልሀል
ለእናትህ ፈገግ ስትል ምን አጥፍተህ ነው ትልሀለች
ለአባተህ ፈገግ ስትል ብር የለኝም ይልሀል
ለሌላ ሰው ፈገግ ስትል ታውቀኛለህ ይለሀል
ብቻህን ፈገግ ስትል እብድ ነህ ይሉሀል
በቃ ፈገግታ ሚጠቅመው ሞተህ ፈገግ ስትል ነው
"ማሻአለህ በፈገግታ ጌታውን ተገናኘ"
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
ህይወት ሁሌም ወደፊት ትራመዳለች። በየትኛውም መጨረስ ውስጥ የሚፈጠር ሌላ መጀመር አለ። የምታስበው የስኬት ማማ ላይ ላይ ስትደርስ ለሌላ ውጥን መሰላል ታዘጋጃለህ። በህይወትህ ውስጥ አንድ አስጨናቂ ጉዳይ ያልፍና ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ይከሰታል። የምትናፍቀውን ስታገኝ ያልናፈቅከውን ትናፍቃለህ። ሌሊትና ቀን በህይወትህ ውስጥ በማለፍና በመምጣት የሚተካኩትን ያህል ጉዳዮችህ በአንተ ውስጥ ማለቂያም፣ ማረፊያም አይኖራቸውም። ቀኑ ሲደብርህ ሌሊትን ትናፍቅ ይሆናል፣ ሌሊቱን አግኝተህ ስታበቃ ደግሞ ቀኑን ትናፍቅ ይሆናል። ፍጥረተ ዓለሙ ትናንትም ዛሬም በማይቆም እንቅስቃሴ ውስጥ ነው።አንተ ደግሞ የፍጥረተ ዓለሙ አንድ አካል ነህና "አትቁም፣ ወደፊት ሩጥ፣ አሳካ!"።
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ትቶህ የሄደን ይሂድ ተወው። ማን እንደሚጎዳ እናያለን። ስላንተ ግድ የሌለዉን ለሰከንድ እንኳን ጊዜ አትስጠው፣ ሞኝ አትሁን። እንደማይገባው እያወቅክ ከፍ ያረግከው እንደሆን የሰው ልጅ ልኩን ይረሳል።
💬 t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from ስለ ቀልባችን
ዝምተኛ ልቦች…
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፤
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርቆ ብቻ ያስቀራቸው፤
ዝምተኛ ልቦች—ምን ይሆን ቋንቋቸው?!
✅ t.me/Sle_qelbachn1
Repost from ስለ ቀልባችን
⚠️የወጣቱ ችግር… ራስን በራስ ማርካት!
📱የቲክቶክ አድራሻችን፦
🔗 https://www.tiktok.com/@sle_qelbachn1?_r=1&_t=ZS-94vQ2iUC5pY
በህይወታችን ውስጥ ብዙ ሰዎችን እናገኛለን። አብዛኞቹ ግን ይሄዳሉ። ጥቂቶቹ ናቸው በልብህ የስክነቱ ዓለም ውስጥ "ፍቅርም ክብርም" ኖሯቸው የሚቀመጡት። ጥቂቶቹ ልባችን ውስጥ የተለየ ክፍል ይኖራቸዋል። የጊዜ አቧራም አያተናቸውም። የዘመን ለውጥም አይፍቃቸውም።
መልካም ቀን 🎀🎀
ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ፣ አባቷን መሳይ፣ የሴት አይነታ
~
1. አባቷ የፍጡር ቆንጮ የሆኑት ነብያችን ﷺ ናቸው።
2. እናቷ የነብያችን የመጀመሪያ ሚስት፣ በፈተናቸው ጊዜ ከጎናቸው የቆመች፣ ወደ ኢስላም በመግባት ቀዳሚ የሆነችዋ ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ናት።
3. ባሏ አራተኛው ኸሊፋ አንበሳው ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ናቸው።
4. ልጆቿ የጀነት ወጣቶች አይነታዎች የሆኑት ሐሰንና ሑሰይን ናቸው።
5. እሷ ራሷ ደረጃዋ ከፍ ያለ ታላቅ የታላቅ ልጅ ናት።
ፋጢማ
* ከነብያችን ﷺ ልጆች መጨረሻ የሞተች ናት።
* በ24 አመቷ ከነብዩ ﷺ ሞት ከሰባት ወር በኋላ ዱንያን ተሰናብታለች።
* የነብያችን ﷺ ዘር የቀጠለው በሷ በኩል ነው፣ በሐሰን እና በሑሰይን በኩል።
እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፦
أقبَلَت فاطِمةُ تمشي كأنَّ مِشْيَتَها مَشْيُ النَّبِيِّ ﷺ، فقال النَّبِيُّ ﷺ: ((مَرْحبًا يا ابنتي))، ثُمَّ أجلَسَها عن يمينِه -أو عن شِمالِه- ثُمَّ أسَرَّ إليها حديثًا، فبَكَت، فقُلتُ لها: لمَ تَبكِينَ؟ ثُمَّ أسَرَّ إليها حديثًا فضَحِكَت، فقُلتُ: ما رأيتُ كاليومِ فَرَحًا أقرَبَ مِن حُزنٍ! فسألْتُها عمَّا قال، فقالت: ما كُنتُ لأُفشيَ سِرَّ رَسولِ اللهِ ﷺ، حتى قُبِضَ النَّبِيُّ ﷺ فسألتها، فقالت: أسرَّ إليَّ ((أنَّ جِبريلَ كان يعارِضُني القرآنَ كُلَّ سَنَةٍ مَرَّةً، وإنَّه عارَضَني العَام مرَّتينِ، ولا أراه إلَّا حَضَر أَجَلي، وإنَّكِ أوَّلُ أهلِ بَيتي لَحاقًا بي))، فبَكَيتُ، فقال: ((أمَا تَرضَينَ أن تكوني سَيِّدةَ نِساءِ أهلِ الجنَّةِ -أو نِساءِ المُؤمِنين- فضَحِكْتُ لذلك ))
"ፋጢማ እየተራመደች መጣች፤ አረማመዷ ልክ እንደ ነቢዩ (ﷺ) አረማመድ ነበር። ነቢዩም (ﷺ) 'እንኳን ደህና መጣሽ ልጄ' አሏት። ከዚያም በቀኛቸው ወይም በግራቸው በኩል አስቀመጧት። ከዚያም በጆሮዋ ምስጢር ነገሯት፣ አለቀሰች። እኔም 'ለምንድነው የምታለቅሽው?' አልኳት። ከዚያም ደግመው ሌላ ምስጢር ነገሯት፣ ሳቀች። እኔም 'እንደ ዛሬው ለሀዘን ቅርብ የሆነ ደስታ አይቼ አላውቅም!' አልኩ። ምን እንዳሉ ጠየቅኳት። 'የአላህ መልክተኛን (ﷺ) ምስጢር አላወጣም' አለች።
ነቢዩ (ﷺ) ከዚህ ዓለም እስካለፉ ድረስ ምስጢሩን አልተናገረችም ነበር። ከዛ በኋላ ጠየቅኳትና እንዲህ አለች፦
'መጀመሪያ የነገሩኝ ምስጢር፦ 'ጅብሪል በየዓመቱ ቁርአንን አንድ ጊዜ ያቀርብልኝ ነበር፤ ዘንድሮ ግን ሁለት ጊዜ ነው ያቀርብልኝ። ይህ የሚያሳየው መሞቻዬ መቃረቡን ነው። አንቺም ከቤተሰቦቼ ውስጥ ቀድመሽ እኔን የምትከተይ ነሽ' የሚል ነበር፤ በዚህም ምክንያት አለቀስኩ።
ከዚያም ደግመው፦ 'የጀነት ሴቶች አለቃ (ወይም የምእመናን ሴቶች ዋና) በመሆንሽ ደስ አይልሽም?' አሉኝ፤ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሳቅኩ።'" [ቡኻሪይ፡ 3623፣ 3624] [ሙስሊም፡ 2450]
እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዳላቸው ፋጢመህ አቋቋሟም፣ አቀማመጧም፣ ሁሉ ነገሯ አባቷን መሳይ ነበረች። ትቀጥላለች ዓኢሻህ
وكانت إذا دخَلَت على النبيِّ ﷺ قام إليها فقَبَّلَها وأجلَسَها في مجلِسِه، وكان النبيُّ ﷺ إذا دخل عليها قامت من مجلِسِها فقَبَّلَتْه وأجلَسَتْه في مجلِسِها
"እሷ (ፋጢማ) ወደ ነቢዩ (ﷺ) ዘንድ በገባች ጊዜ እሳቸው ተነስተው ይቀበሏታል፤ ይስሟትም ነበር፤ ከዚያም እሳቸው በተቀመጡበት ቦታ ያስቀምጧታል። እንዲሁም ነቢዩ (ﷺ) ወደ እሷ (ቤት) በገቡ ጊዜ እሷ ከመቀመጫዋ ተነስታ ትቀበላቸዋለች፤ ትስማቸውም ነበር፤ ከዚያም እሷ በተቀመጠችበት ቦታ ታስቀምጣቸዋለች።" [አቡ ዳውድ፡ 5217] [ቲርሚዚይ፡ 3872]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 9/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
➤ትችያለሽ ብለው አቅም እየሰጡ
ገና ሳትነሺ ጥለው እየሮጡ
➤የማያጠነክር ስር እየሰደዱ
ልንወዳቸው ስንል ስንቶች ጥለው ሄዱ
➤በይቻላል ዜማ መንገድ እየሰጡ
ልናምናቸው ስንል ስንቶች ጥለው ወጡ
ቀናበይ ቀን አለ ጀጊኒት👑
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
ኒካህ 💍
ኒካህ ማለት ቁልፍ ነው—የርዝቅ ቁልፍ፣ የሰላም ቁልፍ፣ የኢማን ቁልፍ! በአላህ ላይ ተመክቶ፣ ንጹህ ኒያ ይዞ የጀመረው ሰው አላህ በሩን ይከፍትለታል። ድህነትን ፈርቶ ኒካህን የሚርቅ ሰው፣ የኸይር በሮችን ሁሉ በራሱ ላይ እየዘጋ መሆኑን ማወቅ አለበት
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
ረመዳን ላይ እንደነበርንነው ህወታችንን ሁሉ ብንኖረው አኼራን ኢድ ሁኖ እናገኘው ነበር
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
👌 በጣም ደስ የምትል አስተማሪ ነቆራ 👌
👉 የሴትን ልጅ ንፅህና በባሏ ልብስ ታውቀዋለህ .።
ማለትም :- የተተኮሰ ያማረ የነፃ የፀዳ ፏ ያለ ከሆነ በቃ ዝርክርክ ትርክርክ ግደለሽ አይደለችም ስለዚህ የባሏን የልብሱን ንፅህና ትጠብቃለች በሰው ዘንድ ያስታውቃል ። ሲያምር .....❗️
👉 የወንድን ልጆ ወንድነት በሚስቱና በሴት ልጆቹ አለባበስ ታውቀዋለህ ።
ማለትም :- ቅናት ከሌለው የሆነ አልጫ ቢጤ ከሆነ ለሒጃቧ ጣጣ የለውም ። አጭር ጠባብ ጉርድ የለበሰችውን ብትለብስ ደንገጥ አይልም ። ይሔ ወንድ ሳይሆን የርቢ በግ ነው ...❗️
አንተም አንችም በደንብ ገብቷችኋል
እኔ አላልኩም!
እነዚህን ጥያቄና መልሶችን በማስደጋገም ልጆቻቹን ተውሂድን አስተምሩ:
⭕ﺱ :1 ﺃﻳﻦ ﺍﻟﻠﻪ؟
✅ﺝ : ﻓﻲ ﺍﻟﺴﻤﺎﺀ ( ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ) .
⭕ﺱ :2 ﻣﺎ ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ؟
✅ﺝ : " ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻌﺮﺵ ﺍﺳﺘﻮﻯ ".
⭕ﺱ :3 ﻣﺎ ﻣﻌﻨﻰ " ﺍﺳﺘﻮﻯ " ؟
✅ﺝ : ﻋﻼ ﻭ ﺍﺭﺗﻔﻊ ( ﺣﻘﻴﻘﺔ ﻻ ﻣﺠﺎﺯﺍ ) .
⭕ﺱ :4 ﻣﻦ ﺃﻳﻦ ﻧﺄﺧﺬ ﻋﻘﻴﺪﺗﻨﺎ؟
✅ﺝ : ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻭ ﺍﻟﺴﻨﺔ .
⭕ﺱ :5 ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺧﻠﻖ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺠﻦ ﻭ ﺍﻹﻧﺲ؟
✅ﺝ : ﻟﻌﺒﺎﺩﺗﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻻ ﺷﺮﻳﻚ ﻟﻪ .
⭕ﺱ :6 ﻣﺎ ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺧﻠﻖ ﺍﻟﺠﻦ ﻭ ﺍﻹﻧﺲ ﻟﻌﺒﺎﺩﺗﻪ؟
✅ﺝ : " ﻭ ﻣﺎ ﺧﻠﻘﺖ ﺍﻟﺠﻦ ﻭ ﺍﻹﻧﺲ ﺇﻻ ﻟﻴﻌﺒﺪﻭﻥ ".
⭕ﺱ :7 ﻣﺎ ﻣﻌﻨﻰ " ﻳﻌﺒﺪﻭﻥ " ؟
✅ﺝ : ﻳﻮﺣﺪﻭﻥ ﻭ ﻳﻄﻴﻌﻮﻥ .
⭕ﺱ :8 ﻣﺎ ﻣﻌﻨﻰ " ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ " ؟
✅ﺝ : ﻻ ﻣﻌﺒﻮﺩ ﺑﺤﻖ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ .
⭕ﺱ :9 ﻣﺎ ﻫﻲ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﺒﺎﺩﺓ؟
✅ﺝ : ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ .
⭕ﺱ :10 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺃﻋﻈﻢ الذنوب؟
✅ﺝ : ﺍﻟﺸﺮﻙ .
⭕ﺱ :11 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ؟
✅ﺝ : ﺇﻓﺮﺍﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﺎﻟﻌﺒﺎﺩﺓ .
⭕ﺱ :12 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺍﻟﺸﺮﻙ؟
✅ﺝ : ﻋﺒﺎﺩﺓ ﻏﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻊ ﺍﻟﻠﻪ .
⭕ﺱ :13 ﻛﻢ ﺃﻗﺴﺎﻡ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ؟
✅ﺝ : ﺛﻼﺛﺔ .
⭕ﺱ :14 ما ﻫﻲ ﺃﻗﺴﺎﻡ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ؟
✅ﺝ : توحيدﺍﻟﺮﺑﻮﺑﻴﺔ، ﻭتوحيد ﺍﻷﻟﻮﻫﻴﺔ، ﻭتوحيد ﺍﻷﺳﻤﺎﺀ ﻭﺍﻟﺼﻔﺎﺕ .
⭕ﺱ :15 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺗﻌﺮﻳﻒ " ﺗﻮﺣﻴﺪ ﺍﻟﺮﺑﻮﺑﻴﺔ " ؟
✅ﺝ : ﺇﻓﺮﺍﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻲ ﺃﻓﻌﺎﻟﻪ، ﻣﺜﻞ ﺍﻟﺨﻠﻖ ﻭ ﺍﻟﺮﺯﻕ ﻭ ﺍﻟﺘﺪﺑﻴﺮ .
⭕ﺱ :16 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺗﻌﺮﻳﻒ " ﺗﻮﺣﻴﺪ ﺍﻷﻟﻮﻫﻴﺔ " ؟
✅ﺝ : ﺇﻓﺮﺍﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﺄﻓﻌﺎﻝ ﺍﻟﻌﺒﺎﺩ، ﻣﺜﻞ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ﻭ ﺍﻟﺬﺑﺢ ﻭ ﺍﻟﺴﺠﻮﺩ .
⭕ﺱ :17 ﻫﻞ ﻟﻠﻪ ﺃﺳﻤﺎﺀ ﻭ ﺻﻔﺎﺕ؟
✅ﺝ : ﻧﻌﻢ، ﻟﻪ ﻣﺎ ﻭﺻﻒ ﺑﻪ ﻧﻔﺴﻪ ﻭ ﻭﺻﻔﻪ ﺑﻪ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ .
⭕ﺱ :18 ﻣﻦ ﺃﻳﻦ ﻧﺄﺧﺬ ﺃﺳﻤﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﻭ ﺻﻔﺎﺗﻪ؟
✅ﺝ : ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻭ ﺍﻟﺴﻨﺔ .
⭕ﺱ :19 ﻫﻞ ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺗﻤﺎﺛﻞ ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻤﺨﻠﻮﻗﻴﻦ؟
✅ﺝ : ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻻ ﺗﻤﺎﺛﻞ ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻤﺨﻠﻮﻗﻴﻦ ﻓﻲ ﺟﻮﻫﺮﻫﺎ ( ﻭ ﺇﻥ ﺗﺸﺎﺑﻬﺖ ﻣﺴﻤﻴﺎﺗﻬﺎ ﺃﺣﻴﺎﻧﺎ ) .
⭕ﺱ :20 ﻣﺎ ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻻ ﺗﻤﺎﺛﻞ ﺻﻔﺎﺕ ﺍﻟﻤﺨﻠﻮﻗﻴﻦ؟
✅ﺝ : " ﻟﻴﺲ ﻛﻤﺜﻠﻪ ﺷﻲﺀ ﻭ ﻫﻮ ﺍﻟﺴﻤﻴﻊ ﺍﻟﺒﺼﻴﺮ ".
⭕ﺱ :21 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺍﻟﻘﺮآﻥ؟
✅ﺝ : ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻛﻼﻡ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ .
⭕ﺱ :22 ﻫﻞ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻣﻨﺰﻝ ﺃﻡ ﻣﺨﻠﻮﻕ؟
✅ﺝ : ﻣﻨﺰﻝ ﻭ ﻫﻮ ﻛﻼﻡ ﺍﻟﻠﻪ ﺣﻘﻴﻘﺔ ( ﺑﺤﺮﻑ ﻭ ﺻﻮﺕ ) .
⭕ﺱ :23 ﻣﺎ ﻫﻮ ﺍﻟﺒﻌﺚ؟
✅ﺝ : ﺇﺣﻴﺎﺀ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺑﻌﺪ ﻣﻮﺗﻬﻢ .
⭕ﺱ :24 ﻣﺎ ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻋﻠﻰ ﻛﻔﺮ ﻣﻦ ﺃﻧﻜﺮ ﺍﻟﺒﻌﺚ؟
✅ﺝ : " ﺯﻋﻢ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻛﻔﺮﻭﺍ ﺃﻥ ﻟﻦ ﻳﺒﻌﺜﻮﺍ ".
⭕ﺱ :25 ﻣﺎ ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮآﻥ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﻴﺒﻌﺜﻨﺎ؟
✅ﺝ : " ﻗﻞ ﺑﻠﻰ ﻭﺭﺑﻲ ﻟﺘﺒﻌﺜﻦ ".
⭕ﺱ :26 ﻣﺎ ﻣﻌﻨﻰ ﻛﻠﻤﺔ " ﺍﻹﺳﻼﻡ " ؟
✅ﺝ : ﺍﻻﺳﺘﺴﻼﻡ ﻟﻠﻪ ﺑﺘﻮﺣﻴﺪﻩ ﻭ ﺍﻻﻧﻘﻴﺎﺩ ﻟﻪ ﻭ ﺍﻟﺒﺮﺍﺀﺓ ﻣﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭ ﺃﻫﻠﻪ.
እናሰራጨው ..
فكم من يحتاجها وسيتعلم بسببك.!
https://t.me/+SxSGs_sbJnM1NWVk
