(( مركز نور الإسلام للتعلم والتعليم ))Nur Al-Islam Center for Teaching and Learning
Відкрити в Telegram
التعلم والتعليم
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
223
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
+830 днів
Архів дописів
#شباب_اليوم_هدانا_الله_واياكم📝
#ዛሬላይ_ያሉወጣቶች_እነሱንም_እኛንም_አላህይምራን
👈تحليقات غريبة ( القزع ) حراااااااام ⛔
👉ፀጉር አቆራረጣቸው የውጪ ፋሽን የተከተለ⎣ከፊሉን ተቆርጠው ከፊሉን ይተውታል⎦ክል!!!!!ክል ነው⛔
👈سراويل ضيقة ممزقة ( عوراتهم مكشوفة ) حرااااااام ⛔
👉ሱሪያቸው ጠባብ በዛላይ የተቦጨቀ የተቀደደ ፋሽነው እያሉ⎣አካላቸውን የሚወጥር የሚያሳይ⎦ክል!!!!!ክልነው⛔
👈اساور في الأيدي ( تشبه بالنساء ) حراااااااام ⛔
👉በእጃቸው ላይ ጌጣጌጥ አንባር አልቦ ብር የተለያዩ⎣ከሴቶች መመሳሰል ነው⎦ክል¡¡¡¡ክል ነው⛔
👈سلاسل على الاعناق ( تشبه بالنساء) حراااااااام ⛔
👉በአንገታቸው ላይ ሰንሰለት ሌሎች ጌጦች ያረጋሉ⎣ከሴቶች መመሳሰል ነው⎦ክል¡¡¡¡ክል ነው⛔
👈شباب اليوم تشبهوا بالنساء وتشبهوا بالكفار يقلدونهم في كل ما هو سلبي
👉ዛሬ ላይ ያሉ ወጣቶች በሴቶች ይመሳሰላሉ ኩፋሮችን ባለጌዎችን ይመሳሰላሉ በሁለንተናዊ አካሄዳቸው እነሱን ይከተላሉ በመጥፎ እራሳቸውን በሚያሳጣ ነገሮች ሁሉ
#نصيحتي🔰
#ምክር
👈لن اطيل عليك وانت تعلم ما ساقوله لك ان تلك السراويل 👖 التي تلبسها لا يجوز لك ان تلبسها لان هذا فساد ومنكر
👈انت تعلم ان لبسك للسراويل سيظهر عورتك وهذا تشبه بالكفار وهذا الامر والفعل لا يرضي الله لذلك انت بين خيارين ارضاء الناس ام ارضاء الله فاحسن الاختيار
👈 انت تعلم ان هذا اللباس لا يلبسه الا من فقد رجولته ولايلبسه الا المخن
👉በእናተ ላይ ንግግርን አላረዝምም እናንተ ታውቁታላቹ የምናገረውን ነገር ይህ የምትለብሱት ሱሪ👖ጠባብ የተቦጫጨቀ የተቀደደ ሰውነትን የሚወጥር ስትለብሰው ስታወልቀው በትግል በድብድብ አንዳንዴም በፌስታል ካልሆነ አልገባም የሚል ነው ይህ ሱሪ አይፈቀድም ምክንያቱም ብልሹነትን ፈሳድን ያስፋፋል
👉አንተ ታውቃለህ ሱሪ መልበስ ሀፍረተ ገላህን ወጣጥሮ በጉልህ ግልፅ አድርጎ ያወጣል ይህ ደግሞ በካሀዲያን መመሳሰል የፋሲቅ ሰዎች አለባበስ ነው ይህ ተግባር አላህን ማመፅ ነው ሰዎችን ልታስደስት ትችላለህ አላህ ግን አይወደውም አላህ የሚወደውን ከሰራህ ጥሩ ሰርተሀል ጥሩ መርጠሀል
👉አንተ ታውቃለህ ይሄን አለባበስ የሚለብሰው ወንድነቱን የተገፈፈ ሰው ነው ወይም ፆታውን ያጣ ሰው ነው
كن رجلا 🫵 واتق الله ولاتتشبه بغيرك
ጀግና ትክክለኛ ወንድ ሁን🫵🏻አላህን ፍራ በኩፋሮች በፋሲቅ በዱርዬዎች አትመሳሰል
#نسأل_الله_الهداية_لشبابنا
#አላህ_ወጣቶችን_መመራትን_ይስጣቸው
#Abdulሀሚድ
#شباب_اليوم_هدانا_الله_واياكم📝
#ዛሬላይ_ያሉወጣቶች_እነሱንም_እኛንም_አላህይምራን
👈تحليقات غريبة ( القزع ) حراااااااام ⛔
👉ፀጉር አቆራረጣቸው የውጪ ፋሽን የተከተለ⎣ከፊሉን ተቆርጠው ከፊሉን ይተውታል⎦ክል!!!!!ክል ነው⛔
👈سراويل ضيقة ممزقة ( عوراتهم مكشوفة ) حرااااااام ⛔
👉ሱሪያቸው ጠባብ በዛላይ የተቦጨቀ የተቀደደ ፋሽነው እያሉ⎣አካላቸውን የሚወጥር የሚያሳይ⎦ክል!!!!!ክልነው⛔
👈اساور في الأيدي ( تشبه بالنساء ) حراااااااام ⛔
👉በእጃቸው ላይ ጌጣጌጥ አንባር አልቦ ብር የተለያዩ⎣ከሴቶች መመሳሰል ነው⎦ክል¡¡¡¡ክል ነው⛔
👈سلاسل على الاعناق ( تشبه بالنساء) حراااااااام ⛔
👉በአንገታቸው ላይ ሰንሰለት ሌሎች ጌጦች ያረጋሉ⎣ከሴቶች መመሳሰል ነው⎦ክል¡¡¡¡ክል ነው⛔
👈شباب اليوم تشبهوا بالنساء وتشبهوا بالكفار يقلدونهم في كل ما هو سلبي
👉ዛሬ ላይ ያሉ ወጣቶች በሴቶች ይመሳሰላሉ ኩፋሮችን ባለጌዎችን ይመሳሰላሉ በሁለንተናዊ አካሄዳቸው እነሱን ይከተላሉ በመጥፎ እራሳቸውን በሚያሳጣ ነገሮች ሁሉ
#نصيحتي🔰
#ምክር
👈لن اطيل عليك وانت تعلم ما ساقوله لك ان تلك السراويل 👖 التي تلبسها لا يجوز لك ان تلبسها لان هذا فساد ومنكر
👈انت تعلم ان لبسك للسراويل سيظهر عورتك وهذا تشبه بالكفار وهذا الامر والفعل لا يرضي الله لذلك انت بين خيارين ارضاء الناس ام ارضاء الله فاحسن الاختيار
👈 انت تعلم ان هذا اللباس لا يلبسه الا من فقد رجولته ولايلبسه الا المخن
👉በእናተ ላይ ንግግርን አላረዝምም እናንተ ታውቁታላቹ የምናገረውን ነገር ይህ የምትለብሱት ሱሪ👖ጠባብ የተቦጫጨቀ የተቀደደ ሰውነትን የሚወጥር ስትለብሰው ስታወልቀው በትግል በድብድብ አንዳንዴም በፌስታል ካልሆነ አልገባም የሚል ነው ይህ ሱሪ አይፈቀድም ምክንያቱም ብልሹነትን ፈሳድን ያስፋፋል
👉አንተ ታውቃለህ ሱሪ መልበስ ሀፍረተ ገላህን ወጣጥሮ በጉልህ ግልፅ አድርጎ ያወጣል ይህ ደግሞ በካሀዲያን መመሳሰል የፋሲቅ ሰዎች አለባበስ ነው ይህ ተግባር አላህን ማመፅ ነው ሰዎችን ልታስደስት ትችላለህ አላህ ግን አይወደውም አላህ የሚወደውን ከሰራህ ጥሩ ሰርተሀል ጥሩ መርጠሀል
👉አንተ ታውቃለህ ይሄን አለባበስ የሚለብሰው ወንድነቱን የተገፈፈ ሰው ነው ወይም ፆታውን ያጣ ሰው ነው
كن رجلا 🫵 واتق الله ولاتتشبه بغيرك
ጀግና ትክክለኛ ወንድ ሁን🫵🏻አላህን ፍራ በኩፋሮች በፋሲቅ በዱርዬዎች አትመሳሰል
#نسأل_الله_الهداية_لشبابنا
#አላህ_ወጣቶችን_መመራትን_ይስጣቸው
#Abdulሀሚድ
https://t.me/merkeznurilislam
የሰዎችን ገንዘብ እየዘረፉ በሺዎች ሶደቃ ሰጪ ነኝ ከማለት።
አንድት ብርም ብትሆን ከሰዎች ሀቅ መቆጠብ ይበልጣል።
قال مالك بن دينار رحمه الله :
لأن يترك الرجل درهما حراما
خير له من أن يتصدق بمئة ألف درهم .
"المجالسة وجواهرالعلم 5/125"
ማሊክ ቢን ዲናር
(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አንድ ሰው አንዲት የሀራም (የተከለከለች) ድርሀምን ከመውሰድ መቆጠቡ፤ መቶ ሺህ ድርሀም ሰደቃ ከመስጠት ይበልጥ ለእሱ የተሻለ ነው።"
(ምንጭ፦ አል-ሙጃለሳ ወጀዋሂሩል ኢልም 5/125)
https://t.me/merkeznurilislam
አስፈሪ ንግግር ከታላቁ ሰሀቢይ‼
قال حذيفة رضي الله عنه :
أول ما تفقدون من دينكم الخشوع ، وآخر ما تفقدون من دينكم الصلاة ، ورب مصل لا خير فيه ، ويوشك أن تدخل مسجد الجماعة فلا ترى فيهم خاشعاً .
[مدارج السالكين( ١ / ٥١٧ )].
ይህ የታላቁ ሰሃባ የሁዘይፋ ቢን አል-የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ንግግር እጅግ ጥልቅ መልእክት ያዘለ እና እኛ ያለንበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ሁዘይፋ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
"ከዲናችሁ (ከሃይማኖታችሁ) መጀመሪያ የምታጡት ኹሹዕን (አላህን መፍራትና በአምልኮ ላይ መረጋጋትን) ነው።
ከዲናችሁ መጨረሻ የምታጡት ደግሞ ሶላትን ነው።
ብዙ ሶላት ሰጋጆች አሉ፤ ነገር ግን በውስጣቸው ምንም መልካም ነገር የሌለባቸው ።
ለጀመዓ መስጂድ ገብተህ አንድም ኹሹዕ ያለው (ልቡ የተሰበረ) ሰው የማታይበት ጊዜም ይቃረባል።
— [መዳሪጁ ሳሊኪን (1/517)]
https://t.me/merkeznurilislam
👇👇
አላህ ያስተካክለንና የብዝኋኖቻችን አስተሳሰብ በአሁኑ ጊዜ ይሄን ይመስላል።
قال الفضيل رحمه الله :
يا مسكين
أنت مسيء وترى أنك محسن
وأنت جاهل وترى أنك عالم
و أنت بخيل وترى أنك كريم
و أحمق وترى أنك عاقل
أجلك قصير
وأملك طويل
[ سير أعلام النبلاء ٤٤٠/٨
አል-ፉደይል (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንተ ምስኪን! አንተ ጥፋተኛ ሆነህ ሳለህ፤ መልካም ሰሪ እንደሆንክ ታስባለህ።
አንተ አላዋቂ ሆነህ ሳለህ፤ አዋቂ እንደሆንክ ታስባለህ።
አንተ ስስታም ሆነህ ሳለህ፤ ቸር እንደሆንክ ታስባለህ።
አንተ ሞኝ ሆነህ ሳለህ፤ ብልህ እንደሆንክ ታስባለህ።
እድሜህ አጭር ነው፤ ምኞትህ ግን ረጅም ነው።"
— [ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ፣ 8/440]
https://t.me/merkeznurilislam
👇👇
أهم أسباب عدم قبول الحق:
1، الكبر والاستعلاء: رفض الحق استكباراً وتفضلاً على الناس.
2، الحسد: داء كامن يمنع الانقياد للحق إذا جاء من شخص لا يحبه الحاسد.
3، اتباع الهوى: تقديم شهوات النفس وأهوائها على الهدى واليقين.
4، الجهل بالحق: الناس أعداء ما جهلوا، فالجهل بالشيء يؤدي إلى عداوته.
5، التعصب والتقليد الأعمى: التمسك المفرط بعادات الآباء وتقاليد المجتمع.
6، الخوف على الجاه والمال: خشية فقدان المناصب أو المصالح الدنيوية.
7، معاداة الداعي للحق: بغض الشخص الذي يحمل الحق، مما يؤدي لرفض ما جاء به.
8، الصحبة السيئة (بطانة
السوء): الأصدقاء السوء يصدون عن الحق ويشغلون المرء بغيره.
እውነትን (ሐቅን) ላለመቀበል ዋነኛ መንስኤዎች
እውነትን ከመቀበልና ቀጥተኛውን መንገድ (ሲራጠል ሙስታቂም) ከመከተል የሚከለክሉ በርካታ የልብ በሽታዎችና ውጫዊ ተፅዕኖዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡
ኩራትና እራስን ከፍ ማድረግ (አል-ኪብር)፦ ሐቅን በትዕቢት እምቢ ማለትና እራስን ከሰዎች በላይ አድርጎ መመልከት። ይህ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደገለጹት "ሐቅን መግፋትና ሰዎችን መናቅ" ነው።
ምቀኝነት (አል-ሐሰድ)፦ ሐቁ የመጣው ከማይወዱት ወይም ከማይፈልጉት ሰው ዘንድ በሚሆንበት ጊዜ በልብ ውስጥ የሚፈጠርና ለሐቅ እጅ እንዳይሰጡ የሚያደርግ ስር የሰደደ በሽታ ነው።
የስሜት ተከታይ መሆን (ኢቲባዕ አል-ሀዋ)፦ የነፍስን ፍላጎትና ስሜትን ከአላህ መመሪያ (ሁዳ) እና ከእርግጠኛ እውቀት በላይ ማስቀደም።
ስለ ሐቁ አለማወቅ (አል-ጀህል)፦ "ሰው የማያውቀው ነገር ጠላት ነው" እንደሚባለው፤ ስለ አንድ ነገር ያለ እውቀት ማጣት ያንን ነገር እንዲጠሉ ያደርጋል።
ለባህልና ለልማድ መገዛት (አል-ተዓሱብ)፦ የአባቶችን ልማድና የማህበረሰብን ወግ ካለ ምንም ማሰላሰል በጭፍን መከተል (ተቅሊድ)።
ለዝናና ለሀብት መጨነቅ፦ ሐቅን ከተከተሉ የሚገኝን ጥቅማጥቅም፣ ስልጣን ወይም አለማዊ ዝናን እንዳያጡ መፍራት።
የሐቅ ጥሪ አቅራቢን (ዳዒውን) መጥላት፦ መልእክቱን ያመጣውን ሰው በግል መጥላት፣ ግለሰቡን ከመጥላት የተነሳ የያዘውን እውነትም አብሮ ወደ መግፋት ያደርሳል።
መጥፎ ጓደኝነት (ቢጣናቱ-ሱእ)፦ መጥፎ ጓደኞችና የቅርብ አማካሪዎች ሰውን ከሐቅ መንገድ በማሰናከልና በከንቱ ነገሮች በመጥመድ ከመመሪያው መስመር ያስወጣሉ።
https://t.me/merkeznurilislam
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
❌«የኔ ፍቅር... በቃ አሁን ረመዳን ገብቷል፤ ስለዚህ አናወራም፣ አንደዋወልም። ኢንሻአላህ ከረመዳን በኋላ እንገናኛለን!»
💬ይህች አረፍተ ነገር የረመዳን ፆም መግባቱን ተከትሎ በብዙ ወጣቶች ዘንድ የምትሰማ 'የጊዜያዊ ስንብት' ቃል ነች።በነገራችን ላይ ይህ ዓይነቱ ድርጊት ተውበት ሳይሆን፣ ለወንጀል የተሰጠ የዕረፍት ጊዜ ነው የሚባለው።
✔️ምክኒያቱም ወደ አላህ የምናደርገው እውነተኛ ተውበት ተቀባይነት እንዲኖረው ከተቀመጡት መስፈርቶች አንዱና ዋነኛው «ዓዝም» ነው። ዓዝም ማለት ዳግም ወደዚያ ወንጀል ላለመመለስ በልብ የሚደረግ ጽኑ ውሳኔና ቁርጠኝነት ነው። ነገር ግን «ለአንድ ወር ላቁምና ከረመዳን በኋላ እቀጥላለሁ» የሚል ሀሳብ ካለ፣ ገና ከመነሻው እውነተኛ ተውበት አላደረግንም ማለት ነው።
✔️ረመዳን ሲመጣ ሀራም የነበረው ግንኙነት፣ ሸዋል ሲገባ ሀላል አይሆንም። የረመዳን ጌታ የሆነው አላህ የሸዋል፣ የሻዕባን፣ የሙሀረምና የሌሎችም ወራት ሁሉ ጌታ ነው። አላህን መፍራት ያለብን በረመዳን ብቻ ሳይሆን በሁሉም የህይወታችን እስትንፋሶች ውስጥ ነው።
✔«ከረመዳን በኋላ እንቀጥላለን»ብለን ቀጠሮ ስንይዝ፣ ከረመዳን በኋላ በህይወት ለመቆየት ምን ዋስትና አለን? ሞት መቼና የት እንደሚመጣ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው። በሀራም ቀጠሮ ላይ እያለን፣ ወንጀልን በልባችን እያሰብን ሞት ቢመጣስ? በአላህ ፊት በምን ፊት እንቆማለን?
❤️ውድ እህቴ! በአላህ መንገድ ያልመጣ፣ ኒካህ የሌለው ግንኙነት የቱንም ያህል ጣፋጭ ቢመስልም መጨረሻው ፀፀት ነው። ለአንቺ ከልቡ የሚያስብ ወንድ በሀራም መንገድ አያገኝሽም። በአንፃሩም ውድ ወንድሜ፣ የምትወዳትን እህት በሀራም መንገድ እያነጋገርክ የአላህን ቁጣ አታተርፍ። እውነተኛ ፍቅር ማለት የምትወደውን ሰው ከእሳት መጠበቅ እንጂ በጋራ ወደ እሳት መጓዝ አይደለም።
❔ስለዚህ ምን እናድርግ?
ይህ የተባረከ ወር ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ይህን የሀራም ግንኙነት «ለረመዳን ብቻ» ብላችሁ ሳይሆን ―ለአላህ ብላችሁ― ሙሉ በሙሉ አቋርጡት። ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናበቱት። ስልኮቻችሁን ዝጉ፣ ከሀራም የሚያገናኛችሁን መንገድ ሁሉ ጥረጉ።
ሀራምን ነገር ለአላህ ስትሉ ስትተው፣ አላህ ከጠበቃችሁት በላይ የሆነን ሀላል ትዳር፣ የልብ እርጋታን፣ እና በረካን በህይወታችሁ ላይ ያዘንብላችኋል። ንጹህ የሆነው የረመዳን ፆማችሁ በሀራም ቀጠሮ አታበላሹት።
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
*من قواعد السعداء في الحياة:*
*"لا تقارن حياتك بأحد، لا تقارن وظيفتك بغيرك، لا تقارن والديك بغيرك، لا تقارن زوجك بغيرك، لا تقارن أبناءك بغيرك، لا ترتكب ظلما بنفسك وتدخل في باب المقارنات فتهتم وتضيق وتسخط وتعترض على قضاء ربك، وارضَ بما لديك وبما أعطاك ربك=تكن غنيا ولو غيرك أفضل منك"*
በህይወትህ ውስጥ ደስተኛ ከሚያደርጉህ መርሆች መካከል፡
"ህይወትህን ከማንም ጋር አታወዳድር፤ ስራህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፤ ወላጆችህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፤ የትዳር አጋርህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፤ ልጆችህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር። ራስህ ላይ በደል አትፈጽም፤ ወደ ንጽጽር በር በመግባትም አትጨነቅ፣ አትጥበብ፣ አትማረር እንዲሁም በአላህ ውሳኔ ላይ አትቃወም።
ባለህ ነገርና ጌታህ በሰጠህ ነገር ትረካለህ፤ ያኔ ምንም እንኳ ሌሎች ቢስቁብህ እንኳ አንተ ባለጸጋ (ሀብታም) ትሆናለህ።"
መሳሰቢያ‼ ይህ ማለት ማንኛውንም ነገር በማስተካከልና በመልካም ነገር ከሰዎች ተሽለህ መገኘት የለብህም ማለት አይደለም።
https://t.me/merkeznurilislam
የተውሂድ አስፈላጊነትና አንገብጋቢነት‼
قَالَ شَيْخُ الْإِسْلَامِ ابْنُ تَيْمِيَّةَ رَحِمهُ الله :
”ٱلتَّوْحِـــيدُ ٱلتَّوْحِــيدُ يَا إِخْــوَةٌ وَٱللَّهِ لَيْسَ لَنَا عِــزٌ وَلَا رِفْــعَةٌ وَلَا شَـأْنٌ وَلَا صَـلَاحٌ وَلَا فَــلَاحٌ وَلَا نَـجَاحٌ وَلَا نَصْـرٌ وَلَا تَمْكِـينٌ فِي ٱلدُّنْـيَا وَلَا فِي ٱلآَخِـرَةِ إِلَّا بِهذَا ٱلتَّوْحِــيدُ ؛ وَٱللَّهِ لَوْ تَنَفَّـخَتِ الجِـبَاهُ مِنْ كَـثْرَةِ السُّجُـودِ وَدُقَّـتِ العِـظَامُ مِنْ كَـثْرَةِ الصِّـيَامِ وَالقِـيَامِ فَالجَـــنَّةُ حَـــرَامٌ إِلَّا بِهـذَا ٱلتَّوحِـــيدُ“
📓مجموع فتاوى ابن تيمية (٢٣٥/٢٤
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"ወንድሞቼ ሆይ! ተውሂድን (አላህን በብቸኝነት ማምለክን) አጥብቁ፤ ተውሂድን አጥብቁ! በአላህ እምላለሁ! በዚህ በተውሂድ ካልሆነ በቀር በዱንያም ሆነ በአኺራ ለእኛ ምንም ዓይነት የበላይነት፣ ክብር፣ ዝና፣ ስኬት፣ ድልም ሆነ በምድር ላይ መርጋት የለንም። በአላህ እምላለሁ! ግንባሮች ከስግደት ብዛት ቢቆስሉ ፣ አጥንቶችም ከጾምና ከሌሊት ሶላት ብዛት ቢደቅቁ እንኳ፤ ያለዚህ ተውሂድ ጀነት (በማንም ላይ) እርም ናት።"https://t.me/merkeznurilislam
በወላጆቻችን የምንፈፅመው ግፍ እና በደል በልጆቻችን ካይፈፀምብን በፊት
ለወላጆቻችን መልካም ልጆች እንሁን።
📌 قال السفاريني رحمه الله:
✍🏻 قال بعض الحكماء :
من عصى والديه لم ينل السرور من ولده
وعن ثابت البناني قال:
رأيت رجلا يضرب أباه في موضع فقيل
له ما هذا
فقال الأب:خلوا عنه فإني كنت أضرب أبي في هذا الموضع فابتليت بابني يضربني في هذا الموضع.
📖 غذاء الألباب في شرح منظومة الآداب (٣٧٣).
📌 አል-ሰፋሪኒ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
✍🏻 አንዳንዶቹ ጠቢባን እንዲህ አሉ፦ «ወላጆቹን ያመጸ (የበደለ) ሰው፣ ከልጆቹ ደስታን አያገኝም።»
ከጣቢት አል-በናኒ ተወርቶ እንዲህ ብለዋል፦ «አንድ ሰው በአንድ ቦታ ላይ አባቱን ሲደበድብ አየሁና 'ምንድነው የምታደርገው?' ተብሎ ተጠየቀ።
አባትየውም እንዲህ አለ፦ 'ተዉት፣ ይውጣለት! እኔም በዚህ ቦታ ላይ አባቴን እደበድበው ነበር፤ አሁን ደግሞ እኔ በዛው ቦታ ላይ በሚደበድበኝ ልጅ ተፈተንኩ (ተቀጣሁ)።'»
📖 ምንጭ፦ ጊዛኡል አልባብ ፊ ሸርሒ መንዙመቲል ኣዳብ (373)
https://t.me/merkeznurilislam
ወደ ዙሁር ሶላት ስትሄድ የሚወጣህ ላብ በተራዊሕ ሶላት ላይ ከሚፈስህ እንባ ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም ዙሁር ግዴታ ሲሆን ተራዊሕ ግን ሱንና ነው፡፡
ዙሁርን እና ዐስር ሳይሰግዱ ለመግሪብ መንቃት፤ ተኝተው ዉለው ለተራዊሕ እና ለተሀጁድ ሶላት መውደቅ መነሳት ትልቅ መጃጃል ነው፡፡ አንዲት የግዴታ ሶላት መፈፀም ሙሉዉን ረመዷን ከመቆም ይበልጣል፡፡―
ይላሉ ሸይኽ ሙሐመድ ሙኽታር አሽ-ሸንቂጢ።
https://t.me/merkeznurilislam
አሁን ያለንበትን የብዙሀኑን ሰው ባህሪ የሚገልፅ አነጋገር ‼
قال أبو بكر الواسطي - رحمه اللّٰه -:
ابتُلينا بِزَمانٍ ليس فيه آداب الإسلام، ولا أخلاق الجاهلية، ولا أحلام ذوي المروءة.
حلية الأولياء لأبي نعيم (٣٧٢/١٠)
አቡ በክር አል-ዋሲጢ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"የእስልምና ስነ-ምግባር (አደብ) በሌለበት፣ የጃሂሊያ (የጥንቶቹ አረቦች) መልካም እሴቶች በራቁበት፣ እንዲሁም የጨዋ ሰዎች ታጋሽነትና አስተዋይነት በማይታይበት ዘመን ውስጥ ተፈተንን።"
— ሒልየቱል አውሊያ ለአቡ ኑዓይም (10/372)
https://t.me/merkeznurilislam
የቁርአንን መልእክት በአግባቡ እያስተነተን ተቀራነው ለጭንቀቶቻችን ሁሉ መፍቲሄ እናገኛለን።
ልማሳሌ ያክል የሚከተሉትን የቁርአን መልክት እናስተንትን‼ 👇👇
🍂
🌹: علمني القران ....
﴿ ومَا تَسقُطُ مِن وَرقَةٍ إلاّ يَعلمُهَا﴾
فكيف بحالك ..
ودمعة عَينك ..
وألم قلبك ..
بل كيف بسجودك وأنت تناجيه بظلمة الليل يسمعك
🌹: علمني القران ...
{ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا }
عندما يستصعب عليك أي أمر.. حدث نفسك بهذه الآيه فهي حسن ظن بالله ..
🌹: علمني القران ....
ومن يتق الله" هذا شرط..
"يجعل له مخرجاً" هذا وعد ..
"ويرزقه من حيث لايحتسب"
هذه مكافأة..
فحقق الشرط.. لتستحق الوعد.. وتنال المكافأة!
🌹: علمني القران ..
( وأُفوضُّ أمري إلى الله )
إذا تولى الله أمرك هيأ لك الخير وأسبابه ، وانت لاتشعر والدُعاء مفتاح لجميع أبوابه .
🌹: علمني القران ...
(ولاتيأسوا من روح الله)
مهما تكاثرت ابتلاءاتك ومهما اشتدت محنك، ومهما ضاقت عليك الحياة ومهما فقدت أعظم ما ملكت، لا تيأس من كرم الله ولطفه .
🌹: علمني القران ...
( وهو معكم أينما كُنتم )
تكفي هذه الآية لتشعر بطمأنينة قلبك ..
وهدوء نفسك ..
وسكون روحك ..
لا تخف ولا تقلق..
فالله معك في كل حين !
የአረበኛው መልክት ወደ አማረኛ በግርድፉ ሲተረጎም ይሄን ይመስላል👇👇👇
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«ከዛፍ ቅጠል የምትረግፈው እንኳ እርሱ የሚያውቃት ቢሆን እንጂ ሌላ አይደለም።» ቅጠል ስትረግፍ የሚያውቅ ጌታ፤ ያንተን ሁኔታ፣ የዓይንህን እንባ፣ የልብህን ሕመም እንዴት አይረዳውም? ይልቁንም በሌሊት ጨለማ ውስጥ ስታናግረውና በሱጁድ ስትዋደቅ ይሰማሃል።
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው።» ማንኛውም ነገር ሲከብድህና ሲጨንቅህ ለራስህ ይህን አንቀጽ ንገረው። ይህ በአላህ ላይ ያለህን መልካም ጥርጣሬ ይገልጻል።
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«አላህን የሚፈራ ሰው...» — ይህ መስፈርት (ቅድመ ሁኔታ) ነው። «መውጫ መንገድን ያደርግለታል...» — ይህ ደግሞ ቃል ኪዳን ነው። «ካላሰበው በኩልም ሲሳይን ይሰጠዋል...» — ይህ ደግሞ ስጦታው (ሽልማቱ) ነው። ስለዚህ ቃል ኪዳኑ እንዲፈጸምልህና ስጦታውን እንድታገኝ መስፈርቱን (አላህን መፍራትን) አሟላ።
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«ነገሬን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ (እሰጣለሁ)።» አላህ ጉዳይህን ከተረከበልህ፣ አንተ ሳታውቀው መልካም ነገርንና ሰበቦቹን ያመቻችልሃል። ዱዓ ደግሞ የሁሉም በሮች መክፈቻ ቁልፍ ነው።
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።» ፈተናዎችህ ቢበዙ፣ መከራህ ቢበረታ፣ ሕይወት ብትጠበብብህና ያለህን ውድ ነገር እንኳ ብታጣ፤ ከአላህ ቸርነትና ልግስና ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ።
🌹 ቁርዓን እንዲህ አስተማረኝ...
«እርሱ የትም ብትሆኑ ከእናንተ ጋር ነው።» ይህ አንቀጽ ብቻ ለልብህ እርጋታ፣ ለነፍስህ ሰላምና ለውስጥህ መረጋጋት ይበቃሃል። አትፍራ፣ አትጨነቅም፤ አላህ ሁል ጊዜም ካንተ ጋር ነውና‼
https://t.me/merkeznurilislam
ሁላችንም ጥንቃቄ ልናደርግ የሚገባን ወሳኝ ነጥብ።
በተለይ በዚህ በረመዷን ወር‼
قال ابنُ القَيم - رَحِمَهُ الله -:
« قَد جَمَعَ النَّبِيَُ - ﷺ - الوَرَعُ كُلَهُ فِي كَلِمَةٍ وَاحِدة فَقَال :
" مِن حُسنِ إسلامُ المَرءِ تَركُهُ مَا لا يُعنِيهِ ".
فهذَا يَعمُ التَرَك لِمَا لا يَعنِي مِن :
➊ الكَلامِ
➋ والنَّظرِ
➌ والإستمِاعِ
➍ والبَطشِ
➎ والمَشي
➏ والفِكر
وسَائِرُ الحَركَاتِ الظَاهِرَة والبَاطِنَة !!
فَهذهِ الكَلِمَة كَافِيةٌ شَافِيةٌ فِي الوَرَعِ ».
📚مَدارِجُ السَالكِين (٢ /٢١)
የአማርኛ ትርጉም
ኢብኑል ቀይም — አላህ ይዘንላቸውና — እንዲህ ብለዋል፦
«ነቢዩ ﷺ ወረዕን (ጥንቃቄን) በሙሉ በአንዲት ንግግር ውስጥ ጠቅለል አድርገውታል። እንዲህም ብለዋል፦
"የአንድ ሰው የእስልምናው ውበት (ጥራት) የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።"
ይህም የማይመለከቱትን ነገሮች መተውን ሁሉ ያጠቃልላል፦
1, ንግግርን
2. እይታን
3,ማዳመጥን
4. እጅን (ጥቃት ማድረስን)
5, አረማመድን
6. ሀሳብን (አስተሳሰብን)
እንዲሁም ሌሎች ግልጽና ስውር የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ (ያጠቃልላል)!! ይህች ንግግር ለወረዕ (ለጥንቃቄ) በቂና አርኪ ናት።»
📚 መዳሪጁ ሳሊኪን (2/21)
https://t.me/merkeznurilislam
በዚህ በተከበረ ወር ከወንጀል በመራቅ መልካም ስራ በማብዛት እንትጋ‼
_ قال الإمام ابن تيمية رحمه الله :
المعاصي في الأيّام المُفضلة، والأمكنة المُفضلة تغلظ، وعِقابها بِقدر فضيلة الزّمان والمكان.
[ مجموع الفتاوى (١٨٠/٣٤) ]
ሸይኹ አልኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
በታላቅ (በተከበሩ) ቀናት እና በታላቅ ቦታዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (ኃጢአቶች) ክብደታቸው ይበረታል። ቅጣታቸውም እንደ ዘመኑና (እንደ ጊዜው) እና እንደ ቦታው ብልጫ ይወሰናል።"
[መጅሙዕ አል-ፈታዋ (34/180)]
https://t.me/merkeznurilislam
✴️🌙 ሰበር ዜና ... ሰበር ዜና ⤵️
✴️ 🌙 ...*عاجل:
رؤية هلال رمضان في تمير..
وغدا الأربعاء أول أيام رمضان بالسعودية .
📮 ሱዑዲ ላይ ጨረቃ ስለታየች አላህ
ካለ ነገ እሮብ የረመዷን ፆም ጅማሬ ይሆናል
https://t.me/merkeznurilislam
በእውነት ረመዳንን ትጾማለህ!!
አንዳንዶች በዚህ ርዕስ ሊገረሙ ይችላሉ...
ምክንያቱም ሁሉም ሰው ያለምንም ጥርጥር ረመዳንን ለመጾምና ለሊቱን በሶላት ለማሳለፍ በናፍቆት ይጠባበቃል።
በደንብ አውቃለሁ፤
ሁላችሁም ረመዳንን እንደምትጾሙ።
👌 ነገር ግን... የምትጾሙት እውነተኛውን ጾም ነው? ወይስ ዝም ብሎ የተለመደ፣ መንፈስ የሌለውና እንደ ማሽን የሚደጋገም ተግባር (routine) ብቻ?
በዚህ ሐዲስ ላይ አስተውላችኋል?
"ከጾመኞች መካከል ለጾሙ ከረሃብና ከጥም በስተቀር ምንም የሌለው አለ።"
ጾም የምግብና የመጠጥ ብቻ ሲሆን ነገሩ በጣም አደገኛ ይሆናል፤
እውነተኛ ጾም ማለት፦ በልብህ፣ በአካልህና በሕዋሳቶችህ ሁሉ ለአላህ ብለህ መጾምህ ነው።
አይንህ ከሐራም (እይታ) እንዲጾም፤
ጆሮህ ከሐራም (ንግግር) እንዲጾም፤
ምላስህ ከሐራም (ውሸትና ወሬ) እንዲጾም፤
ብልትህ ከሐራም እንዲጾም፤
🌱 ግቡን እስክትመታ ድረስ፦
"አላህን ትፈሩ ዘንድ (ተቅዋ ታገኙ ዘንድ) [ተደነገገላችሁ]።"
ውድ ወንድም እህቶቼ... የምንፈልገው፦
እውነተኛና እውነት የሆነን ጾም እንድንጾም፤
ወደ መልካም ስራዎች (ጣዓት) የሚገፋፋን ጾም፤
ከእርም (ሐራም) ነገሮች የሚከለክለን ጾም እንዲሆን ነው።
https://t.me/merkeznurilislam
*أكثرُ الخلقِ يُصلِحُ حالَهُم مع الفقرِ أكثرَ من الغِنى!*
*قال شيخُ الإسلام الإمام ابن تيمية القيسي رحمه الله تعالى:-
*|[ وفي الحديث:«أعوذُ بك من فتنةِ الفقرِ، وشرِّ فتنةِ الغِنى»*
*والفقرُ: يُصلِحُ عليه خلقٌ كثيرٌ والغِنى: لا يُصلِحُ عليه إلا أقلُّ منهم! ولهذا كان أكثرُ من يدخلُ الجنةَ الفقراء والمساكين لأن فتنةَ الفقرِ أهونُ وكلاهما يحتاجُ إلى الصبرِ والشكر.]|*
*[مجموع الفتاوى (١٤/٣٠٥)]
አብዛኛው ፍጡር (ሰው) ሁኔታው የሚስተካከለው ከሀብት ይልቅ በድህነት ውስጥ ሆኖ ነው!"
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"[በሐዲስ ላይ እንዲህ የሚል መጥቷል፦] «ከድህነት ፈተና እና ከሀብት ፈተና ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ።»
በድህነት (ምክንያት) የብዙ ሰዎች ሁኔታ ይስተካከላል፤ በሀብት ምክንያት ግን ሁኔታቸው የሚስተካከለው ከነርሱ ያነሱ ጥቂቶች ብቻ ናቸው! ለዚህም ነው አብዛኞቹ የጀነት ሰዎች ድሆችና ምስኪኖች የሆኑት፤ ምክንያቱም የድህነት ፈተና (ከሀብት ፈተና) የቀለለ ስለሆነ ነው። ሆኖም ግን ሁለቱም (ድህነትም ሆነ ሀብት) ትዕግስትና ምስጋና (ሹክር) ያስፈልጋቸዋል።"
[መጅሙዕ አል-ፈታዋ (14/305)]
https://t.me/merkeznurilislam
የጁሙዓህ ኹጥበህ ስለሸዕባን ወር መጨረሻ እና ስለ ረመዿን አቀባበል የተዳሰሰበት።
አቡ አህመድ
https://t.me/merkeznurilislam
🌹 ለጋብቻ "እድሜና ቁንጅናን" ብቻ መስፈርት ለሚያደርጉ ወንድሞች የተላከ ወርቃማ ምክር 🌹
*(አላህ የራራላቸው ሲቀሩ እንዚህ ወንዶች ምንኛ በዙ!)*
🛑 "ሚስት አጣሁ" የሚል ምክንያት አታቅርብ!
ወዳጄ ሆይ! መልካም (ሷሊህ) ሴቶችማ እንደ አሸን ፈልተው ነበር፤ ነገር ግን ያንተ መስፈርቶች ከሴቶቹ ቁጥር በላይ በዙ እንጂ!
💡 እስኪ ራስህን ፈትሽ..?
አንዳንድ ወንድሞች (አላህ ይምራቸውና) "መልካም ሚስት (ሷሊሃ) ነው የምፈልገው" ብለው ይሞግታሉ። ነገር ግን ከጀርባ የሚያቀርቧቸው መስፈርቶች አላግባብ የከረሩ ናቸው፡-
👉 "እድሜዋ በጣም ለጋ ትሁን..."
👉 "አይኖቿ እንዲህ ይምሰሉ..."
👉 "ፀጉሯ ቀለሙ፣ ርዝመቱ፣ ልስላሴው..." እያሉ ይቀጥላሉ።
ጉድ እኮ ነው!
ወንድሜ.. አንተ እኮ በዚህ ምድር ላይ በሰው ቆዳ የተፈጠረች "ሁር አል-ኢን" (የጀነት ቆንጆ) ነው እየፈለግክ ያለኸው!
💎 ምክሬን ስማኝ!
የነቢዩን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ዱካ ተከትለህ ለምን "ሱኒያዋን" (ባለ ዲኗን) በመምረጥ አትታደልም? የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለው መክረውሃልና፡-
"ባለ ዲን የሆነችውን ምረጥ፤ እጆችህ አቧራ ይልሱ (ደስታና በረካ ያግኙ)።"
📜 ታላቁ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ፈርኩስ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡-
"በሸሪዓችን ለትዳር አጋር ምርጫ መመዘኛው 'እድሜ' አይደለም፤ መመዘኛው 'ዲን' (ሃይማኖታዊ ጥንካሬ) ነው እንጂ። ለዚህም ማስረጃው ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
*'ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ልትገባ (ልትዳር) ትችላለች፡ ለገንዘቧ፣ ለዘር ክብሯ፣ ለቁንጅናዋ እና ለዲኗ። አንተ ግን ባለ ዲኗን ምረጥ፤ (ይህን ካላደረግክ) እጆችህ አቧራ ይልሳሉ።'*
✨ ትክክለኛዋ ቆንጆ ማናት?
በቁርኣንና በሐዲስ የተወደሰችው 'መልካም ሴት' ማለት ልንመርጣት የሚገባን አይነት ሴት ናት። አላህ እንዲህ ይላል፡-
'መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች፣ አላህ (ሚስጥርን) እንደጠበቀ በሩቅ (ነገር) ጠባቂዎች ናቸው።' (አን-ኒሳእ፡ 34)
እንዲሁም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
*'ሴት ልጅ አምስት (ወቅት ሰላቷን) ከሰገደች፣ ወሯን (ረመዳንን) ከጾመች፣ ብልቷን ከዝሙት ከጠበቀች እና ባሏን ከታዘዘች፤ ከፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።'*
💖 እድሜ መግፋት ለትዳር እንቅፋት አይሆንም!
የአንዲት ሴት እድሜ መግፋት ከእርሷ ጋር ትዳር ላለመመስረት ምክንያት ሊሆን አይገባም። ለዚህም ነቢዩ (ሶ.ሰ) እናታችንን ኸዲጃን (ረ.ዐ) ማግባታቸው የቀጠለ ላንተ በቂ እና ህያው ማስረጃ ነው።
* ♥ እናታችን ኸዲጃ በእድሜ ከነቢዩ በዓመታት ትበልጣቸው ነበር።
* ♥ ነገር ግን ከሰዎች ሁሉ ለሳቸው በጣም ተወዳጅ ሚስት ነበረች።
* ♥ ከሌሎች ሚስቶቻቸው በተለየ መልኩ ልጆችን ያፈሩት ከእርሷ ነው።
* ♥ የሐሰን እና የሁሴን (ረ.ዐ) የዘር ሐረግ የተገኘው ከእርሷ ነው።
ስለሆነም "እድሜ መግፋት"፤ አንዲት ሴት በዲን እንድትተጋገዝህ፣ እንዲሁም አላህ በቁርኣኑ የጠቀሰውን የመረጋጋት (ሰኪና)፣ የፍቅር (መወደህ) እና የእዝነት (ራህማ) ጸጋን በትዳርህ ውስጥ እንዳታገኝ እንቅፋት አይሆንም።
📖 አላህ እንዲህ ይላልና፡-
*"ከነፍሶቻችሁ ለእናንተ ሚስቶችን ወደነሱ ትረጋጉ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉ።"* (አር-ሩም፡ 21)
📚 [ፈታዋ አል-ኡስራህ ቁጥር (296)]
ፀሀፊው ሌላ ነው።
https://t.me/merkeznurilislam
💍 የትዳር ፍሬዎች! 💍
የኔ የሚሉትን ደጋፊና ተቆርቋሪ ታማኝ ወዳጅ ከጎን ያገኙበታል። እሱ ለሷ አሷም ለሱ ከማንም በላይ ጓጊና አዛኝ ይሆናሉና።
« وَمِنْ آَيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَاوَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآَيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ»
« ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህም ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተዓምራቶች ኣልሉ። »
« هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا »
« እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከኣደም) የፈጠራችሁ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው »
የህብረተሰቡም ክብርና ዝርያ ይፀዳበታል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዳስጠነቀቁን
« إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فأنكحوه إلا تفعلوا تكن فتنة في الأرض وفساد كبير …… »
«ዲኑንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ሰው ለጋብቻ ፍለጋ ሲመጣችሁ አጋቡት። ይህ ካልሆነ ግን በምድር ላይ ከባድ የሆነ ፈተናንና ብልሽትን ታሰፍናላችሁ »
قال إِمَامُ الحَرَمَيْنِ أَبِي المَعَالِي عَبْدُ المَلِكِ الجَوَيْنِيِّ -رَحِمَهُ الله
( والنكاح من أسباب زوال الجنون ، كما أن العزبة من أسباب الجنون ) [ نهاية المطلب 12/ 43]
"ላጤነት (ትዳር አለመመስረት) የእብደት መንስዔ እንደሆነው ሁሉ
ማግባት ደግሞ እብደት ከሚወገድባቸው ሰበቦች አንዱ ነው።"
https://t.me/merkeznurilislam
