✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Відкрити в Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
193
Підписники
-224 години
-47 днів
-630 днів
Архів дописів
ቁርኣንን የሓፈዘ ሰዉ መገለጫ ባህሪያት፦
ቁርኣን የሃፈዘ ሰው ትልቅ ሃላፊነት አለበት ምክንያቱም፦
የተሸከመው የአላህን ቃል ነውና፡፡
የሚከተሉትን ባህሪዎች የግሉ
ማድረግ ይኖርበታል፡፡
① ኛ. በሐፈዘዉ ቁርአን ሌሊት ሰላት
ሊሰግድበት ይገባል።
② ኛ. በፆም በዒባዳ መጠንከር አለበት።
③ ኛ. ቁርኣን በሚቀራበት ምላሱ አፀያፊ ነገር ሊናገርበት አይገባም።
④ኛ. በመሐፈዙ መተናነስን አለበት እንጂ
መኩራት የለበትም።
⑤ ኛ. ቁርአኑን የጥቅማ ጥቅም ማሳደጃ
ሊያደርገዉ አይገባም
⑥ ኛ በአጠቃላይ ቁርኣኑ በምላሱ ብቻ
ሳይሆን በተግባሩ ላይ
ሊታይ ይገባል ለሌሎችም አርአያ መሆን ይኖርበታል፡፡
‹የረሱል ባህሪ ቁርአን ነበር› ስትል ባለቤታቸዉ የምእመናን
እናት ዓኢሻ ትናገራለች፡፡
📜ቁርአንን ያለ ሙራጀዓ መሀፈዝ አይቻልም!
- በየቀኑ ያለ ሙራጀዓ እየሀፈዝን ቁርአንን ጨርሰን የሀፈዝነውን መልሰን ለመቅራት ብንሞክር የሀፈዝነውን እረስተነው እራሳችንን እናገኛለን ። ይህ እንዳይፈጠር ሂፍዝን እና ሙራጀዓን በአንድ ላይ ማስኬድ ይኖርብናል ።
ሂፍዝ እና ሙራጀዓን በአንድ ላይ ማስኬድ የምንችልበት ምርጡ መንገድ እንደሚከተለው ይሆናል‥
๏ ቁርአንን 6 ቦታ እንከፍለዋለን ይህም 5ት 5ት ጁዝእ ይሆናል ። በየቀኑ ግማሽ ገፅ እየሀፈዝን ስለሆነ 5 ጁዝእ እስከምንደርስ ድረስ በየቀኑ ከሀፈዝነው 2 ገፅ ሙራጀዓ እናደርጋለን ።
5ት ጁዝእ ላይ ስንደርስ ለአንድ ሳምንት የሂፍዙን ትምህርት አቁመን የሀፈዝነውን በየቀኑ 4 ገፅ እየቀራን ሙራጀዓ እናደርጋለን ። ሙራጀዓ አድርገን ከጨረስን በኋላ የሂፍዙን ትምህርት ጀምረን በየቀኑ ግማሽ ገፅ እየሀፈዝን 4 ገፅ ደግሞ ሙራጀዓ እናደርጋለን ።
10 ጁዝእ ላይ ስንገባ 6 ገፅ ሙራጀዓ ፣ 15 ላይ ስንገባ 8 ገፅ ፣ 20 ላይ ስንገባ 10 ገፅ ፣ 25 ላይ ስንገባ 12 በስተመጨረሻም 30 ላይ ስንገባ በየቀኑ 14 ገፅ ሙራጀዓ እናደርጋለን ።
ቁርአኑን ሀፍዘን ከጨረስን በኋላ ድጋሚ በ10 ጁዝእ 3 ቦታ ከፍለነው የመጀመሪያውን ጁዝእ ብቻ ለ1 ወር ሙራጀዓ እናደርጋለን ። ከጨረስን በኋላ የሚቀጥለውን 10 ፤ ስንጨርስ የመጨረሻውን 10 ጁዝእ ሙራጀዓ እናደርጋለን ።
ይህን አድርገን ከጨረስን በኋላ ልክ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያደርጉት እንደነበረው እስከ እለተ ሞት ድረስ ቁርአንን ሂዝብ ሂዝብ አድርጎ ወይም ለ7 አካፍሎ በየሳምንቱ ማኽተም ነው ። በሀዲስ እንደተዘገበው በመጀመሪያው ቀን ፋቲሃን ጨምሮ 3 ምዕራፍ (በቀራህ ፣ ዒምራን እና ኒሳእ) ይቀሩ ነበር ።
በ2ተኛው ቀን 5 ምዕራፍ (ማኢዳህ ፣ አንዓም ፣ አዕራፍ ፣ አንፋል እና ተውባህ)ን ይቀሩ ነበር ።
በ3ተኛው ቀን 7 ምዕራፍ (ዩኑስ ፣ ሁድ ፣ ዩሱፍ ፣ ራዕድ ፣ ኢብራሂም ፣ ሂጅር እና ነህል)ን ይቀሩ ነበር ።
በ4ተኛው ቀን 9 ምእራፍን (ኢስራእ ፣ ካህፍ ፣ መርየም ፣ ጣሃ ፣ አንቢያእ ፤ ሐጅ ፤ ሙእሚኑን ፤ ኑር እና ፉርቃን)ን ይቀሩ ነበር ።
በ5ተኛው ቀን 11 ምዕራፍ (አሹዐራእ ፣ ነምል ፣ ቀሰስ ፣ ዐንከቡት ፣ ሩም ፣ ሉቅማን ፣ ሰጅደህ ፣ አህዛብ ፣ ሰበእ ፣ ፋጢር እና ያሲን)ን ይቀሩ ነበር ።
በ6ተኛው ቀን 13 ምዕራፍ (ወሳፋት ፣ ሷድ ፣ ዙመር ፣ ጋፊር ፣ ፉሲለት ፣ ሹራ ፣ ዙኽሩፍ ፣ ዱዃን ፣ ጃሲያ ፣ አህቃፍ ፣ ሙሀመድ ፣ ፈትህ እና ሁጁራት)ን ይቀሩ ነበር ።
በ7ተኛ እና መጨረሻው ቀን ደግሞ ከሱረቱ ቃፍ አንስተው እስከ ሱረቱ ናስ ቀርተው ቁርአንን ያኸትሙ ነበር ። በእንደዚህ መልኩ ነው ቁርአንን ጠብቀን መሀፈዝ የምንችለው።
አላህ ያግራልን…
አቡ ሱፍያን
ተውሒድ ሲባል በቃል የሚመሰከር ሸሃዳ ብቻ አይደለም፡፡ በተግባር የሚኖሩት ሕይወት እንጂ፡፡ የሚያሳዝነው ዛሬም ላይ ከአላህ ይልቅ ሸሆቹን፣ጅኖቹን፣ ቆሌዎቹን .. የሚፈሩ ብዙ ናቸው፡፡
ወላሂ ይገርመኛል … ስንቶች ናቸው! አላህን ለማግኘት ብለው ከአላህ የራቁ፡፡ ወደ አላህ የሚደርሱት በሸሆቹ እና በወሊዮቹ በኩል ብቻ መሰላቸዉና የአላህን ሥም አንድም ቀን ሳይጠሩ፣ ወደ አላህም አንድ ቀን እጃቸዉን ሳያነሱ፣ ሸሆቹ እግር ላይ ወድቀው፣ ወሊዮቹ በሚሏቸው በር ላይ ተደፍተው እነርሱን ሲያገለግሉና ሲኻድሙ ኖረው ዱንያን የተሰናበቱ፡፡
ጌታዬን አንተን ከማግኘት ከሚጋርድ ዕውቀት አንተው ጠብቀኝ፡፡
አቡ ሱፍያን
ዘርህ ምንድን ነው⁉️
⇨ፅድት ያልኩ የአማራ ልጅ ነኝ ብሎ ተኩራራ አንደኛው፤
⇨ጥርት ያልኩ የኦሮሞ ልጅ ነኝ ብሎ ፎከረ ሁለተኛው፤
⇨ወርቅ የሆንኩ የትግሬ ልጅ ነኝ ብሎ ተመፃደቀ ሦስተኛው።
ሌሎችም ቀጠሉ።
ፎከሩ፣አቅራሩ፣ተመፃደቁ፣ ተኮፈሱ ከኛ በላይ ሰው የለም አሉ።
.
.
.
ሲታዘባቸው ቆየና የመጨረሻው ልጅ "ምርጦቹ መላእክት የሰገዱለት የምርጥ ሰው ልጅ ነኝ።" አላቸው ።
" ማነው ደግሞ መላእክት የሰገዱለት?" ብለው ግራ በመጋባት ጠየቁት።
" እሱማ አባቴና አባታችሁ፤ እንዲሁም የሁሉም የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ነው" አላቸው
ሁላችሁም የአደም ልጆች ፤ አደም ደግሞ ከአፈር ነው።
አቡ ሱፍያን
በምንለቃቸው ጽሑፎች ውበት አትታለሉ!
" ... እኛኮ! ሚስኪን ሰዎች ነን። ወንጀሎቻችን አላህ ባይደብቅልን ማንነታችን ይጋለጥ ነበር።"
(ኢማሙ አሕመድ)
እህቶች
የምንፈልገውን እየጠበቅን ጊዚያችንን አብከነን ወንጀል ላይ ከመውደቅና ከማይሆን ሰው ጋር ትዳር ከመመስረት ከሞላ ጎደል መልካም ስነምግባርና ጤናማ አቂዳ ያለው ሰው ጋር ሁለተኛም ሶስተኛም አራተኛም ሆኖ ትዳር መያዙ በእስልምና የተወደደ ተግባር ነው።
ግባችን ጀነት ይሁን
ኢብኑል ቀዪም ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"የወሕይን ቅን መመሪያን ያፈነገጠ ሰው በአመለካከቱ መንሸራተት ይገጥመዋል። እንዲሁም በእንቶ ፈንቶ እና በትርኪ ምርኪ አስተሳሰብ አላህ ይፈትነዋል።"
[መዳሪጁ አሳሊኪን (1/311)]
ማን ደፍሮ ይጠጣት??
ማርቆስ ወንጌል 16:16
ትንሿ ብርሌ መላተይን ይዛ
አንድ ብር ብቻ ነች ከሱቅ ስትገዛ
ደቂቃ አያስፈልግ ስታደርግ ጀናዛ።
አውጥተው ሲሰጡት መርዙን ለደርቤ
መድረክ ለቆ ወጣ ፓስተሩ ከአጠገቤ።
ማን ይሞክር ብዬ ደግሜ ብጣራ
የሚጠጣ ጠፍ ሐሞተ ኮስታራ።
በየአደባባዩ እየሱስ እየሱስ እያሉ ሽንጥ ከመገተር
ዛሬም ጀግና ጠፍቷል መርዟን የሚሞክር።
كيف نستقبل رمضان
ረመዳንን እንዴት እንቀበል ?
ዛሬ በመርከዝ አልኢማም አሕመድ ለተማሪዎች የተሰጠ ምክር
ሙሐመድሲራጅ ሙ-ኑር
https://t.me/Muhammedsirage
2⃣0⃣0⃣ ሱረቱል አንከቡት 10-27
የ200ኛ ቀን ደርስ፡
በሸይኽ አብዱሠላም
https://t.me/DessieAnwar
ዲንህ የሱና ኡለሞች በያዙት ልክ ያዘው!!
አንድን ግለሰብ የሚያራምደውን አቋም ብቻ ተከትለህ አትሒድ!!!!
ሌሎቹ የሱና ኡለሞችስ በጉዳዩ ምን አሉ????
ብለህ ጠይቅ
እንደ ግመል ህጻኑም፣ ትልቁም፣ ጃሂሉም ለጉሞ አይጎትትህ
የነዚያን ሰፈር ሰዎች ንቃባቸው!!!!!
አል‐ኢማሙ ዘሀቢ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦
﴿إذا وَقَعَت الفتن لمستك بالسنة ، وألزم الصمت ولا تخض فيما لا يَعْنيك وما أشكل عَلَيْكَ فَرُدَّهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ، وَقِف وَقُل: اللهُ أَعْلَمُ﴾
“ፊትና በሚከሰት (በሚሆን) ግዜ፤ ሱናን አጥበቅህ ያዝ፣ ዝምታን አዘውትር፣ በማይመለከትህ ጉዳይ አትግባ፣ ግራ የገባህን ነገር ወደ አላህና መልዕክተኛው (ወደ ቁርአንና ሀዲስ) መልሰው፣ አላሁ አዕለም (አላህ የበለጠ አዋቂ ነው) ብለህ ቁም።”
ሲየር አዕላሙ ኑበላ፡ 20/142
ዝምድናህን ቀጥል!
ወደ ጌታችን የምንቃረብበት አንዱ መንገድ ነውና!!!
ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰ
ለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اتَّقوا اللهَ، وصِلُوا أرحامَكم﴾
“አላህን ፍሩ ዝምድናችሁን ቀጥሉ።”
ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 869
