uk
Feedback
قناة أبي عبدالله السلفي

قناة أبي عبدالله السلفي

Відкрити в Telegram

منهجنا منهج السلف الصالح هو المنهج الذي سار عليه الصحابة والتابعون نحارب البدع والخرافات

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
197
Підписники
Немає даних24 години
-57 днів
-530 днів
Архів дописів
🚫 እስልምናን ሶስት ነገር ይንደዋል ‼ ↪️ የዓሊም ስህተት ↪️ የሙናፊቅ በቁርኣን መከራከር ↪️ አሳሳች መሪዮች https://t.me/bahruteka
🚫 እስልምናን ሶስት ነገር ይንደዋል ‼ ↪️ የዓሊም ስህተት ↪️ የሙናፊቅ በቁርኣን መከራከር ↪️ አሳሳች መሪዮች https://t.me/bahruteka

‏فيديو من النور الحبشي

💡 ያልሆኑትን ሆኖ ማሳየት ንፍቅና ነው! በየ ሶሻል ሚድያው በየ ቲክቶክ ይሄ ሰው ጥሩ ሰው ነው።ምነው የኔ ወንድም በሆነ ምነው የኔ ባል በሆነ እያላችሁ ምትመኙት ሰው ውጭ ላይ አምሮና ተውቦ ለማሳ
💡 ያልሆኑትን ሆኖ ማሳየት ንፍቅና ነው! በየ ሶሻል ሚድያው በየ ቲክቶክ ይሄ ሰው ጥሩ ሰው ነው።ምነው የኔ ወንድም በሆነ ምነው የኔ ባል በሆነ እያላችሁ ምትመኙት ሰው ውጭ ላይ አምሮና ተውቦ ለማሳየት የሚሞክረው ከበስተጀርባው ግን የቤተሰቦቹ ፀር መጥፎ ሰው ሊሆን ይችላል! ሁሌም መልካም መስሎ የታየን ሁሉ  መልካም እንዳልሆነ ከላይ ባለች የብርቱካን ምሳሌ መገምገም ትችላላችሁ!! ውዷ ሰለፍይ እህቴ ሆይ! በሶሻል ሚድያ ያየሽው ሁሉ መልካም መስሎሽ ዘለሽ ከመግባት ራስሽን ጠብቂ።ያን ውድ እንቁ ሰለፍዩን ወጣት ምታገኝው አላህ በሚወደው ቦታ እና ለዲኑ ወይም ለዱንያው የሚጠቅመው ቦታ ላይ ነው ሚገኘው!! አንተ እንቁ ሰለፍይ ወንድሜ ሆይ! ሚስትን ባሻህ ጊዝዜ  በየ ቲክቶክና በየፌስቡክ ፎቶዋን ምትለጥፈውን ፈሳድን ምታንሰራፋውን ሳይሆን በቤቷ ተሰትራ አንተን ምትጠብቅህ ምረጣት! Telegram channel👇 https://t.me/Abu_Abdullah3633

🌺ካሳለፍሻቸው ጊዜዎች ሁሉ ምርጡ ከቁርኣን ጋር ያሳለፍሽው ነው። •━════✿🍃🌺🍃✿════━• 👇👇👇👇 https://t.me/Abu_Abdullah3633
🌺ካሳለፍሻቸው ጊዜዎች ሁሉ ምርጡ ከቁርኣን ጋር ያሳለፍሽው ነው። •━════✿🍃🌺🍃✿════━• 👇👇👇👇 https://t.me/Abu_Abdullah3633

🎙ቃሪእ ኻሊድ ጀሊል ሱረቱ አል ካህፍ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ሱረቱል  ካፍ    ✅ ከጁመዓ ቀን ሱናዎች ↩️‏ سنن_يوم_الجمعة ➊ الغسل ➋ الطيب ➌ السواك ➍ لبس الجميل ➎ قراءة سورة الكهف ➏ التبكير لصلاة الجمعة ➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ 🔹ገላን መታጠብ 🔹ሽቶ መቀባት 🔹ሲዋክ መጠቀም 🔹ጥሩ ልብስ መልበስ 🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት 🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ 🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد        الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ  اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ https://t.me/AbraribnAwal https://t.me/AbraribnAwal

🚫  የቲክ – ቶክ አደጋ ♻️ ቲክ – ቶክ ማለት በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ሰዎች የተፈተኑበትና ከስነ-ምግባርና ግብነ–ገብነት ያፈነገጠ ትውልድን የሚያጠፋ መርዘኛ ሚዲያ ነው።     🔎 በጣም የሚገርመው ቲክ – ቶክን ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች በፓርላማዎቻቸው አማካይነት እንዲታገድ እያደረጉ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እምነትና መልካም ባህልን የሚያጠፋ ነው የሚል ነው። ምክንያቱ ይለያይ እንጂ ብዙ የምእራብ ሀገሮችም እንዲታገድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።   ➲ በርግጥ እነርሱ እንደአፍሪካዊያን እምነትና ባህልን ይጎዳል በሚል አይደለም የሚጠሉት ይልቁንም ምክንያታቸው ፖለቲካዊ ነው።    ➪ ከማንም በፊት ኢስላም የሰዎችን ዲን፣ ጤና፣ ንብረትና ክብር የሚጎዳን ነገር ይከለክላል። የኢስላም ሸሪዓ ትኩረት ሰጥቶ ከሚጠብቃቸው ነገሮች ዋናውና ትልቁ ዲን ነው። ዲንን የሚጎዳ ማንኛውም ነገር በኢስላም ክልክል ነው።    ➧ ታዲያ እንኳን በመለኮታዊ የህይወት መመሪያ የሚመራ የኢስላም አስተምሮ ይቅርና ጤነኛ አእምሮ ያላቸው ከሀዲያን እንኳን የልጆችን ስነምግባር ያበላሻል የሰዎችን እምነትና መልካም ልማድ አደጋ ላይ ይጥላል ብለው የሚያወግዙትን ቲክ – ቶክ የሱና ሰዎች ነን ከአቋማችን አልተንሸራተትንም እያሉ የሚሞግቱ አካላት ወጣቱን ወደ ቲክ – ቶክ ሲጣሩ ምን ይባላል ‼?       ↪️ አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድርገን። የአደጋው አድማስ በተለይ በሙስሊሞች ላይ እየሰፋ እየሄደ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ። https://t.me/bahruteka

♦️| አዲስ በጣም ወሳኝ የሴቶች ደርስ! 📚 ኪታብ፦ ነሲሐቲ-ሊ'ኒሳእ 📝 አዘጋጅ፦ ኡሙ ዐብዲ'ላህ አልዋ-ዲዒ'የህ 🎙አቅሪ፦ ሸይኽ አቡዘር ሐሰን ኮምቦልቻ 📆 ዘውትር ሐሙስ ከቀኑ 4:00 በኢትዮ
♦️| አዲስ በጣም ወሳኝ የሴቶች ደርስ! 📚 ኪታብ፦ ነሲሐቲ-ሊ'ኒሳእ 📝 አዘጋጅ፦ ኡሙ ዐብዲ'ላህ አልዋ-ዲዒ'የህ 🎙አቅሪ፦ ሸይኽ አቡዘር ሐሰን ኮምቦልቻ 📆 ዘውትር ሐሙስ ከቀኑ 4:00 በኢትዮ 📖 ኪታቡን ለማግኘት፦ "Pdf" 🔴 || በሸይኻችን ቻናል በላይቭ ይተላለፋል፦https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

لمن يتأمل__ ويتفكر ويبحث ___ ويتذكر ዱሮ ዱሮ ስለ ተውሒድ ስለ ሺርክ ስለ ሱና ስለ ቢድዓ በደምብ ይነገር ነበር ዛሬ ዛሬ................. ይሄኮ ነው የደበረን አኺ እኛ በዘመነ አሕባሽ እነ እንትና የጥመት መሪወች ናቸው ብለን በድፍረት እንናገር ነበር እየታሰርንም ቢሆን ጀግኖች ነበር አሁን ግን......

ይችን መፅሀፍ ሁላችሁም አንብቧት በውስጧ ወሳኝ ማስረጃዎችና ሰፋ ያለ ማብራራሪያዎች ስላለባት ትጠቀሙበታላችሁ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ! ቢያንስ አንድ ሰው ለ10 ሰዎችና ከዛ በላይ ሼር ሼር በማድረግ ሀላፊነቶን ይወጡ! 👇 https://t.me/Mistre_ahbashe/4426

💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 🌟 ልዩ የፈትዋ ፕሮግራም ጥሪ 🌟 ​📛 በተለያዩ ዲናዊ ጉዳዮች ላይ      የቀረቡ ጥያቄዎች መልስ      የሚያገኙበት ልዩ የፈትዋ      ፕሮግራም‼️ ✳️ ቀን - መጋቢት 23 (ሮብ) ✳️ ሰአት - ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ 🔺️ መልስ - በሸይኽ ሐሰን ገላው                  ሐሰን (ከባህርዳር) 🔴 ቦታ፦ በአባይ ማዶ ቢላል       መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ 🔗 የግሩፕ ሊንክ፦ https://t.me/bilalmesji 👈 ​❓ ጥያቄ አለዎት? በተለያዩ ሸሪዓዊ ጉዳዮች ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ጥያቄ በቦታችን ሊንክ  @Fetawa_bot በኩል በማንኛውም ሰዓት አስቀድማችሁ መላክ ትችላላችሁ! 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎

​ ፈታዋ በሸይኽ ሀሰን ገላው  (ሀፊዘሁሏሁ ወረዓሁ) ሠኞ  ምሽት የፈታዋ ፕሮግራማቸው ላይ አጠቃላይ ስለዲን ለቀረቡ ጥያቄዎች በቂ፣ ግልፅና አርኪ ምላሾችን ሰጥተውበታል። ​🎧 የሪከርዱ ይዘት፦  ​በቁርአንና በሀዲስ መረጃዎች የተደገፉ አስተማማኝ ምላሾች። ​የልብን የሚያክሙና ለተግባራዊ ህይወት የሚረዱ ማብራሪያዎች። ​📥 እነሆ የሪከርዱ ፋይል! ​ያመለጣችሁ እንድትከታተሉት፣ የሰማችሁት ደግሞ ድጋሚ በማድመጥ እውቀታችሁን እንድታድሱ ተጋብዛችኋል። ​"እውቀትን ለሌሎች ማካፈል ትልቅ ሰደቃ ነው!" > ይህን የኸይር ስራ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ። 💥ማሳሰቢያ :- ጥያቄ ጠይቃችሁ ያልተመለሰላችሁ ወንድም እህቶች ጥያቄያችሁ ተረስቶ እና ተዘሎ ሳይሆን ከጥያቄዎች መብዛት ጋር ተከትሎ ነው የዘገዩት ..ሁሉም ጥያቄዎቻችሁ ደርሰውናል በቅደም ተከተል ይመለሳሉ .እና በሶብር እንድትከታተሉ እናሳስባለን..ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን .. መጋቢት 21 በባህር አባይ ማዶ ሰለፍያ ቢላል መስጅድ

🛑የኢትዮጲያ አህለል አስሱነህ ማህበር (መጅሊስ ) ▪️የኢትዮጲያ አህለል አስሱነህ ማህበር ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ በእምነት ከሚለያቸው ሁሉም የቢደዐህ ስብስቦች በግልጽ መርህና ተግባር በመለየት ትክ
🛑የኢትዮጲያ አህለል አስሱነህ ማህበር (መጅሊስ ) ▪️የኢትዮጲያ አህለል አስሱነህ ማህበር ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ በእምነት ከሚለያቸው ሁሉም የቢደዐህ ስብስቦች በግልጽ መርህና ተግባር በመለየት ትክክለኛውን የጧቱን እስልምና ስያስተምር እነ ለብዙ መሻይኾችና ዱዓቶች ሚናቸውን የመለየትና ግልፀኝነት መርህ ያደረገ የደዕዋህ እንቅስቃሴ እንዲከተሉ ምክንያት(ሰበብ) ሆነዋል ። ጀዛቸውን አላህ እጥፍ አድርጎ ይመንዳቸው ። 👌ሐቂቃ እነዚህ የባህርዳር መሻይኾች ለሐበሻ ሰለፊዮች ተመዩዝ ምን እንደሆነ በተግባር ያሳዩ ብርቅዬ ምሳሌዎቻችን ናቸው ። በዛ በጨለማው ዘመን ብዙ ውጣውረድ አሰልቺ  የክርክር መድረኮችን በጽናት አልፈው በመጨረሻም ከሱፊዮችና ከእኽዋኖች መጅሊስ  አንድ አይደለንም ብለው ለመንግስት መሰረታዊ ልዩነት እንዳለን በመግለፅ የራሳችንን መጅሊስ የቋቋሙልን ታገዮቻችን ስለመሆናቸው አፌን ሞልቼ እናገራለሁ ። 👌በዛ ለይ በሰለፊዮች መካከል የአንድነትን የመከባበርን ፣ የመተባበርን ፣ የመተዛዘን፣ የመተናነስን እነ የመቻቻልን ምንነት በተግባር ያሳዩን ግንባር ቀደም አርአያ ናቸው። ✏️ለሐበሻ ሰለፊዮች የሚለው ነገር ቢኖር የሐገራችንን እነዚህን ብርቅዬ መሻይኾች በማክበር በእያንዳንዱ ችግሮቻችን እያማከርናቸው የሰለፊያ አስተምሮ በሰለፊያው መጅሊስ ውስጥ እንድናስኬድ እነ የእኽዋኖችን መጅሊስ ሙሉ በሙሉ መለየት ይኖርብናል ።     👌መሻይኾቻችን ጠንካራ ቁመና ያለውን ተቋም መስርተውልናል የምናከብራቸው የሰለፊያ አባቶቻችን ናቸው። በሐበሻ ምድር ተመዩዝ በተግባር ምን ማለት እንደሆነ የሚገባህ የነዚህን መሻይኾች የደዕዋህ አጀማመር እነ አሁን ለይ የደረሱበትን የሰለፊየህ ደዕዋህ ደረጃ  ስትረዳ ነው።

+1
فَتْحُ رَبِّ الْبَرِيَّةِ فِي كَشْفِ شُبُهَاتِ التَّكْفِيرِيَّةِ {{ የፍጡራን ጌታ የሆነው  የአላህ መክፈትና  ማብራራት፤    የተክፊርዮችን  ((( ሙስሊሞችን ያለ መስፈርት  ከእስልምና የሚያሶጦ ቡድኖችን)))  ብዥታና  ውዥንብር  በማጋለጥ }} ~ የተክፊርዮች  ብዥታ የተብራራበት ነው!!! ~ ስለ ኡዝ ቢል ጀህል ማብራሪያ አለበት!!! ~ ስለ ኡዝር ቢተዕዊይል ማብራሪያ አለበት!!! ~ ሁጃ እንዴት መቆም እንዳለበት ማብራሪያ አለበት!!! 🎤  الشيخ محمد حياة الولوي الهروي حفظه الله تعالى 🎤 በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት አል ወለዊይ አል ሀረዊይ ( አሏህ ይጠብቃቸው) الحلقة الثالث ክፍል ሶስት https://t.me/SheikMohmmedHyatHara

ብቻሽን ስለሆንሽ የግድ ሰዉ ያስፈልገኛል ብለሽ ከማይመጥንሽ ጋር ለመግጠም አትልፊ የሚመጥንሽን እስከምታገኝ ዱዓ እያደረግሽ አርፈሽ ተቀመጭ በአላህ ላይ ሙሉ የሆነ የቂን እርግጠኝነት ይኑርሽ አላህ ለ
ብቻሽን ስለሆንሽ የግድ ሰዉ ያስፈልገኛል ብለሽ ከማይመጥንሽ ጋር ለመግጠም አትልፊ የሚመጥንሽን እስከምታገኝ ዱዓ እያደረግሽ አርፈሽ ተቀመጭ በአላህ ላይ ሙሉ የሆነ የቂን እርግጠኝነት ይኑርሽ አላህ ለሁሉም ነገር ገጣሚዋንና ተስማሚዋን ያደረገላት ቢሆንጂ ዝብሎ አልፈጠራትም።

ይደመጥ! 🎙ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ረምዛን ሀፊዘሁሏህ የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል የሚከተለዉን ሊንክ ይጠቀሙ! ↘️↘️↘️↘️↘️↙️↙️↙️↙️↙️ https://t.me/Abu_Abdullah3633

      👉  ደማችን ቢፈስም ነፍሳችን ቢጠፋም ሐቅ እንናገራለን ! በአላህ ይሁንብኝ!  በአላህ ይሁንብኝ !  ከቢዳዓ ኪታቦች ሁሉ እንደ ሰይድ ቁጥብ ኪታቦች አይነት የጥመት ኪታብ አላየሁም ። በሰማያትና ምድር ጌታ እምላለሁ ( የሰይድ ቁጥብ ኪታቦች) ቢዳዐን ከሁሉ ጫፉ ሰብስቧል ። ከቢዳዓ መሰረቶች ህያው ያደረገው ቢሆን እንጂ የተወዉ የለም ። ሙስሊሞች ሆይ በነፍሳችሁና በልጆቻችሁ አላህን ፍሩ ( ከቢዳዐ ተጠበቁ) ። https://t.me/bahruteka

የኛዎቹ ኮተታም ሱፍያዎች ከዚህ ከኦርቶዶክስ ስርአተ አምልኮ ኮርጀው የመሰረቱትን የሶደቃ ስርአት፣ “ከክርስትና ጋር አመሳስላችሁታል” እንዳይባሉ የኦርቶዶክሱን 12ኛ ቀን፣ 14ኛ ቀን በማድግ፣ 80ኛ ቀንን በመዝለል፣ የስድስት ወሩን (የመንፈቁን) የአራት ወር በማድረግ የተወሰኑ ለውጦችን አድርገዋል፡፡ ወይም ድግሞ መጀመሪያ ላይ በደንብ መኮረጅ ስላልቻሉ ወይም ኩረጃ ያካሄዱበት ሰነድ ከግእዝ ፅሁፍ ጋር ስለተቀላቀለ ተምታቶባቸውም ሊሆን ይችላል፡፡ አሏህ በተከበረው ቁርአኑ፣ በበቀራህ ምእራፍ፣ አንቀፅ 118፤ “ልቦቻቸው (በክህደት) ተመሳሰሉ” ይለናል፡፡ በዚሁ ምእራፍ፣ አንቀፅ 208 ላይ፣ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስልምና ውስጥ ጥቅልል ብላችሁ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና” ይላል፡፡ እዚህ ላይ ይህን የሶደቃ ስርአት የሚተገብሩትን ብቻ ሳይሆን፤ ታቦት የሚሸኙትን፣ ፈንዲሻ ቆልተው፣ በጳጉሜ ውሀ ታጥበው፣ በግ አርደው… የእነሱን በአል የሚያከብሩትን ሁሉ ጨምራችሁ አስቡት፡፡ አሏህ በተከበረው ቁርአኑ፣ የእስራኤልን ልጆች በተመለከተ እንዲህ ይላል፡- “የወይፈኑንንም (የአምልኮት) ውዴታ - በክህደታቸው ምክንያት - በልቦቻቸው ውስጥ ተጠጡ፡፡ ‘አማኞች እንደሆናችሁ፣ እምነታችሁ በእርሱ የሚያዛችሁ ነገር ከፋ!’ በላቸው፡፡” አሁን ከሁሉም በላይ ዋናው ጥያቄ፣ የሱፍያ ሼሆች “ከእንዲህ አይነቱ ቅሌት ውስጥ እንዴት ገቡ?” የሚለው ነው፡፡ የድሮዎቹ ቢሳሳቱ፣ የዘመናችን ሱፍያዎች “ለምን በዚህ ተራራ የሚያክል ስህተት ውስጥ እንደ ተዘፈቁ መቀጠልን መረጡ?” የሚለው ነው፡፡ “ሼህ፣ አሊም፣ ዳኢ፣ ኡስታዝ…” እየተባለ በየኢኽዋኑና ሙመይኡ መስጂድ፣ መጅሊስና ሶሻል ሚድያ ላይ የሚጋፋው ሁሉ ለምን አፉን ለጎመ?” የሚለው ነው፡፡ ሀቁን ከተናገሩ፣ የሚሊየን ሚሊየኖች ያሉበትን የሱፍያውን ህብረተሰብ መንካት ይሆንባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሀብታቸው፣ የስልጣናቸው፣ የክብራቸው… ምንጭ እንዲደርቅባቸው ምክንያት ሊሆንባቸው ይችላል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከክርስትና ተኮርጆ የመጣውን መውሊድን ማውገዝ ተስኗቸው’ኮ ነው ያሉት፡፡ አንዳንዶቹም - በተቃራኒው - እሱን በማንቆለጳጰስ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ ሀያሉ አሏህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡- “እነዚያ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ፣ ከአሏህም መንገድ የሚያግዱና መጣመሟን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው፡፡” ከዚህ ፅሁፍ አላማ አንፃር ጉዳዩን ገድበን ማየት ግድ ይለናልና ይህ የሶደቃ አፈፀፀም እንዴት የብዝበዛ ስርአት (System of exploitation) እንደሆነ ብቻ በማየት እናጠቃለው፡፡ አንድ ሰው ሲሞት፣ በሞተበት አመት ውስጥ ቤተሰቦቹ በተለያዩ ጊዜዎች (በሶስት ቀኑ፣ በሁለት ሳምንቱ፣ በአርባ ቀኑ…) አምስት ሶደቃዎችን ያዘጋጃሉ፡፡ ከዚያ በኋላ በያመቱ አንድ ሶደቃ መደገስ ግዳቸው ነው፡፡ አንድ አባዋራ ወይም ቤተሰብ ቢያንስ አንድ የሞተ ቅርብ ዘመድ ይኖረዋል፡፡ አመታዊው ሶደቃ ደግሞ ያለ ገደብ በየአመቱ መደረግ ያለበት ነው፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ሙስሊም አባዋራ - አቅም እስካለው ድረስ - በአመት አንድ ጊዜ ሶደቃ መደገስ አለበት፡፡ እናስ ይህ “ህግ” የሶደቃን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የወጣ ለመሆኑ የሚያጠራጥር ምን ነገር አለ? የሱፍያ ሼሆች የምግብ ዋስታናቸውን ለማረጋገጥ የዘየዱት አምልኮ ለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንስ ነገር አለ? የሱፍያ ሼሆች የብዝበዛ ስርአታቸውን እንዲህ አድርገው ነው የዘረጉት፤ እንዲህ አድርገው ነው ስለእምነቱ እውቀት አልባ የሆነውን ህዝበ ሙስሊም በብዝበዛ ሰንሰለታቸው ተብትትበው የያዙት፡፡  ዘመድ የሞተበት ሰው አቅም እያለው ሶደቃ ለማዘጋጀት ዳተኝነት ካሳየ፤ አንዱ የአካባቢው ነዋሪ የሟቹን ስም በመጥቀስ፣ ለሟቹ ቅርብ ዘመዶች እከሌን “ዛሬ በህልሜ አየሁት” በማለት ያወራል፡፡ ብዙ ጊዜ ትርክቱ የሚያሳዝንን ገለፃ ያካትታል - የተቀዳደደ ልብስ ለብሶ፣ ባዶ ሰሀን ይዞ፣ ከስቶና ጠቋቁሮ፣ ከሌሎች ሰዎች ምግብ ሲለምን… የመሳሰሉ፡፡ በህብረተሰቡ ጭንቅላት ውስጥ የኮተታሙ ሱፍያ ሼሆች የቀረፁት የዚህን መሰሉ ትርክት ትርጓሜ፣ “ሟቹ ሶደቃ ፈልጎ ነው” የሚል ነው፡፡ ስለዚህ አቶ የቅርብ ዘመድ ወደ ሶደቃ ዝግጅት ዘው ነዋ… ይህ የሶደቃ ስርአት ቢድአ (ከክርስትና የተወሰደ፣ በቁርአንና በሀዲስ ማስረጃ የሌለው ሶለዋት የሚባልበት፣ ያሲንን ጨምሮ ቁርአን የሚቀራበት፣ ዱአ የሚደረግበት) ከመሆኑም በላይ፣ የተወሰኑት ክንውኖች (ለምሳሌ ሶለዋቱና ዱአው) በሽርክ ቆሻሻ የተበከሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም በእውናዊውም ሆነ በህልማዊው የሶደቃ ቅስቀሳ ውስጥ የሸይጧን ውትወታና ጉትጎታ የራሱን ሚና አሳምሮ መጫወቱ አይቀሬ ነው፡-   “እነዚያ፣ ለእነርሱ ቅኑ መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት፣ ሰይጣን ለእነርሱ መመለሳቸውን (ንፍቅናቸውን) አስዋበላቸው፤ (አሏህ) እነርሱንም (እድሜያቸውን በማስረዘም) አዝዘናጋቸው፡፡” (ሙሀመድ፣ 25) ይህን ከኦርቶዶክስ ክርስትና ተኮርጆ ስራ ላይ የዋለውን የሶደቃ ስርአት አለመተግበር፤ የሞቱ ሰዎች ዱንያ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ እንዲቆጡ እንደሚያደርጋቸው፣ ከዚያም አልፎ ዱንያ ላይ ያሉ ሰዎች ላልታሰበ ቅጣት ወይም መቅሰፍት (ድርቅ፣ ርሀብ፣ ወረርሽኝ…) ሊዳርጉ እንደሚችሉ የሚያምኑ ሱፍያዎች ሁሉ አሉ፡፡ ጋሼ ይመርን ጨምሮ የሰፈራችን ሰዎች በየግላቸው ከሚደግሱት ሶደቃ በተጨማሪ፣ ሁሉንም የዳውዶ ሙስሊሞች የሚያካትት አንድ አመታዊ ሶደቃ “ለአምዋቶች” በማለት ይደግሱ ነበር - ድግሱ ቢቀር አምዋቶች እንደሚቆጡና የሆነ አደጋ (ድርቅ፣ ርሀብ፣ ወረርሽኝ…) እንደሚደርስባቸው በመፍራት፡፡ ወደ ዳውዶ ስልክ በመደወል እንዳረጋገጥኩት፣ ይህ አመታዊ ሶደቃ አሁንም ድረስ አለ - በመጠኑ መልኩን ቀይሮ፡፡ የሱፍያን ኮተታኮተት ተገን አድርጎ በያሲን ቂርአትም ሆነ በሶደቃ ስም በተዘረጋው የብዝበዛ ስርአት (System of exploitation) እስከ መቼ ነው እንዲቀጥል የሚፈቀድለት? ይህ የብዝበዛ ስርአት፣ ህዝበ ሙስሊሙን ከመበዝበዝ አልፎ፣ ከነቢድአና ሽርኩ ላይ እንደ ወደቀ ወደ አኼራ እንዲጓዝ እያደረገው እያለ፤ የሱፍያ፣ የሙመይእና የኢኽዋን ዳኢዎች፣ ሼሆችና አሊሞች እስከ መቼ ነው አፋቸውን ለጉመው የሚቀመጡት? እስከ መቼ ነው የአሏህና የመልእክተኛውን (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) አደራ ከአሮጌ እቃ እንደቆጠሩት የሚኖሩት? በበቀራህ ምእራፍ፣ በአንቀፅ ቁጥር 159፣ አሏህ እንዲህ ይላል፡- “እነዚያ ከአንቀጾችና ከቅን መምሪያ ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁ፤ እነዚያን አሏህ ከእዝነቱ ያርቃቸዋል፤ (አሏህ ከእዝነቱ እንዲያርቃቸው) ረጋሚዎችም ይረግሟቸዋል፡፡” በዶክተር ጀማል ሙሐመድ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة