uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

Відкрити в Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
669
Підписники
+224 години
+47 днів
+230 днів
Архів дописів
​የሰሜን ምስራቅ (ደሴ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል! ​የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) የሰሜን ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማእከል በሆነችው በደሴ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል። ​ይህ ታላቅ ጉባኤ በአጠቃላይ ከ23 ከተሞች እና ከ34 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ወጣቶችን፣ መሪዎችንና አገልጋዮችን (Associates) ያገናኘ ስትራቴጂካዊ መድረክ ነበር። የተሳታፊዎቹ ስብጥርም የሚከተለውን ይመስላል፦ ​▪️ ከሰሜን ወሎ ዞን፦ አለማጣ፣ ሙጃ፣ መርሳ እና ወልድያ ▪️ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፦ ሰሃላ-ሰቆጣ ▪️ ከደቡብ ወሎ ዞን፦ ውጫሌ፣ ማርዬ፣ ጎልቦ፣ ደሴ፣ ኩታበር፣ ተንታ፣ ጊምባ፣ ከለላ፣ ጃማ፣ ወረኢሉ እና ሰኞ ገበያ ▪️ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞን፦ ሃርቡ፣ ከሚሴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ አንጾኪያ-መኮይ፣ አጣዬ-ኤፌሶን እና የግሼ ራቤ ▪️ ከአፋር ክልል፦ ሎጊያ እና ሰመራ ​📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦ በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) የቃል ጥናት አድርገናል። በተጨማሪም የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናዎች እና አገልግሎት ተኮር ውይይቶች ተካሂደዋል፦ 🔹 አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership) 🔹 አካዳሚያዊ ብቃት (Academic Excellence) 🔹 የህይወት ቅድስና (Purity) 🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method) ​ቀጣይ ርምጃችን፦ በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ይህንኑ ጉባኤ ይዘን ወደ ሌሎች ክልሎች እናመራለን! 📍 በሰሜን ምዕራብ፡ ባህር ዳር 📍 በምዕራብ፡ ነቀምቴ ​በባህር ዳር እና በነቀምቴ ለሚካሄዱት ለእነዚህ ጉባኤዎች በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን! ​የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) ​@suethio #LeadershipSummit2018 #Dessie #ደሴ #StudentLeaders #YouthEmpowerment #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

photo content
+7

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+8

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+8

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+1

photo content
+9

photo content
+9