SU|ኤስዩ
Открыть в Telegram
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
669
Подписчики
+224 часа
+47 дней
+230 дней
Архив постов
669
የሰሜን ምስራቅ (ደሴ) ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በጌታ ጸጋ ተጠናቋል!
የኢትዮጵያ ቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማሕበር (SUE) የሰሜን ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ ማእከል በሆነችው በደሴ ከተማ ያስተናገደው የ2018 ዓ.ም የክልላዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሪዎች ጉባኤ (SUE-RHLS) እጅግ በተባረከ ሁኔታ በስኬት ተጠናቋል።
ይህ ታላቅ ጉባኤ በአጠቃላይ ከ23 ከተሞች እና ከ34 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ወጣቶችን፣ መሪዎችንና አገልጋዮችን (Associates) ያገናኘ ስትራቴጂካዊ መድረክ ነበር። የተሳታፊዎቹ ስብጥርም የሚከተለውን ይመስላል፦
▪️ ከሰሜን ወሎ ዞን፦ አለማጣ፣ ሙጃ፣ መርሳ እና ወልድያ
▪️ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፦ ሰሃላ-ሰቆጣ
▪️ ከደቡብ ወሎ ዞን፦ ውጫሌ፣ ማርዬ፣ ጎልቦ፣ ደሴ፣ ኩታበር፣ ተንታ፣ ጊምባ፣ ከለላ፣ ጃማ፣ ወረኢሉ እና ሰኞ ገበያ
▪️ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞን፦ ሃርቡ፣ ከሚሴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ አንጾኪያ-መኮይ፣ አጣዬ-ኤፌሶን እና የግሼ ራቤ
▪️ ከአፋር ክልል፦ ሎጊያ እና ሰመራ
📖 የቃል ጥናት እና ሴሚናሮች፦
በነበረን ቆይታ "ተልዕኳዊ ህይወት ፡ ተልዕኳዊ ህብረት" በሚል መሪ ሐሳብ (በ1ኛ ቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ) የቃል ጥናት አድርገናል። በተጨማሪም የተማሪዎችን አቅም በሚገነቡ ርዕሶች ዙሪያ ስልጠናዎች እና አገልግሎት ተኮር ውይይቶች ተካሂደዋል፦
🔹 አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)
🔹 አካዳሚያዊ ብቃት (Academic Excellence)
🔹 የህይወት ቅድስና (Purity)
🔹 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ (Bible Study Method)
ቀጣይ ርምጃችን፦
በቀጣዩ ሳምንት ደግሞ ይህንኑ ጉባኤ ይዘን ወደ ሌሎች ክልሎች እናመራለን!
📍 በሰሜን ምዕራብ፡ ባህር ዳር
📍 በምዕራብ፡ ነቀምቴ
በባህር ዳር እና በነቀምቴ ለሚካሄዱት ለእነዚህ ጉባኤዎች በጸሎት እንድታስቡን አደራ እንላለን!
የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ)
@suethio
#LeadershipSummit2018 #Dessie #ደሴ #StudentLeaders #YouthEmpowerment #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት
