uk
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Відкрити в Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
2 480
Підписники
+724 години
+3147 днів
+35230 днів
Архів дописів
የኤልጂ (LG) ስማርት ቲቪዎች ተጠቃሚዎችን በምስጢር ይሰልላሉ የሚል ከፍተኛ ክስ ቀርቦባቸዋል። ታዋቂ የቴክኖሎጂ መርማሪዎች (Gamers Nexus እና Level1Techs) ባደረጉት ጥናት፣ የLG ቲቪዎች ጠፍተው ባሉበት (Standby) ጊዜ ሳይቀር የሰዎችን የድምፅ ንግግር እንደሚቀዱ እና በቤት ውስጥ ያሉ ሌሎች ስልኮችንና ኮምፒውተሮችን ያለፈቃድ እንደሚቃኙ ይፋ አድርገዋል። ይህ የተሰበሰበ መረጃ ለማስታወቂያ ኩባንያዎች ይሸጣልም ተብሏል። ምን ይሄ ብቻ ..... የLG ኩባንያ ባወጣው መግለጫ የድምፅ ስርቆት ክሱን በፍፁም አልቀበልም በማለት አስተባብሏል። ነገር ግን በቤት ውስጥ ያሉ ሌሎች መሣሪያዎችን የመቃኘቱ ተግባር እውነት መሆኑን አምኖ፣ ይህ አሠራር ቲቪው ከሌሎች ስልኮች ጋር በቀላሉ እንዲገናኝ የሚያግዝ የተለመደ የቴክኖሎጂ አሠራር ነው ሲል ተከላክሏል። ድሮም አላምናቸውም ነበር .... 🤔

የ ኮክሰን ሙሉ የ x መልእክት:- " ​I resigned from Anthropic today. I spent the last three years doing pretraining research at both OpenAI and Anthropic. Neither company is acting responsibly. They are racing straight to self-improving superintelligence and gambling with our lives. More thoughts below. ​Do not underestimate the power of this technology. These will soon be superhuman systems that can hack anything, revolutionize any field overnight, and acquire real power and resources. We have all witnessed the progress in each of these domains, and progress is not slowing. ​The people building AI earnestly believe that it could kill us all by the end of the decade. This is not a marketing stunt. If anything, many executives and senior researchers will couch their phrasing in the press to sound sensible - but I hear the same people express fear privately. No other human activity poses this level of danger. ​A common response is "if they truly believe this, why are they still building it?" At OpenAI, many have not deeply internalized the civilizational stakes. At Anthropic, the stakes are well-understood, but they are locked in a race to get there first - they believe no one else will act responsibly, so they must do it themselves, despite the risk. ​Accepting this race and entering the "endgame" is a hubristic gamble that should not be launched from a private company's Slack. Attempting to speedrun alignment should require extraordinary confidence that there are no better trajectories available. ​I am optimistic about the potential for coordination. Warning shots like the Hugging Face attack have made pacing agreements between U.S. labs more viable. I don't feel like we're on track to prevent a global race, which may require costly actions such as a temporary ban on improving model capabilities. ​If you are a lab researcher, I urge you to consider what the next few years will actually feel like. Do you want to kick off a superintelligent RL run without a rigorous understanding of its mind? Should you put your head down because "it's happening anyway" - or take this moment... "

በቅርቡ ከ Anthropic የለቀቁት የቀድሞው ከፍተኛ የ AI ተመራማሪ ጃኮብ ኮክሰን (Jacob Coxon) በዚህ ሳምንት በ X ገባቸው ለይ ባሰፈሩት መልዕክት ፣ "መሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በሰው ልጅ ህይወት ላይ አደገኛ ቁማር እየተጫወቱ ነው" ሲሉ አስጠነቀቁ! ​ባለፉት 3 ዓመታት በ OpenAI እና Anthropic ውስጥ በከፍተኛ የቅድመ-ስልጠና (pretraining) ምርምር ላይ የቆዩት እኚህ ባለሙያ ፣ ሁለቱም ኩባንያዎች በኃላፊነት ስሜት እየሰሩ እንዳልሆነ ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፣ በላቦራቶሪዎቹ ውስጥ የ AI ቴክኖሎጂውን እየገነቡ ያሉ በርካታ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂው እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ እንደሚችል በቁም ነገር ያምናሉ። ነገር ግን ፣ OpenAI የጉዳዩን አደገኝነት በበቂ ሁኔታ ስላላስተዋለው ፣ Anthropic ደግሞ "እኛ ቀድመን ካላደረስነው ሌሎች በኃላፊነት አይሰሩትም" በሚል እምነት ፣ ሁለቱም ራሱን ወደሚያሻሽል "ልዕለ-ብልህነት" (Superintelligence) በከፍተኛ ፍጥነት እየተሽቀዳደሙ ይገኛሉ። ​ "ይህ የሽያጭ ማስታወቂያ ስልት አይደለም ፤ ብዙ ስራ አስፈፃሚዎች እና ከፍተኛ ተመራማሪዎች ፍርሃታቸውን በግላቸው ሲገልጹ እሰማለሁ" የሚሉት ኮክሰን ፣ በላቦራቶሪዎች መካከል የእድገት ፍጥነት ስምምነት ወይም ጊዜያዊ እገዳ ካልተጣለ ዓለም አቀፋዊው ውድድር አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል አሳስበዋል። በጣም የሚደንቀው ደግሞ የ Anthropic ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳሪዮ አሞዲ በኮክሰን ሀሳብ መስማማቱ ነው። የAlን እድገት እንቀንሰው በማለት ከሳም አልትማን ጋር የተለዋወጡትን ሀሳብ ትናንት ሼር ማድረጌ አይዘነጋም! በነገራችን ላይ የ AI Risk እንደ ቀላል መታየት የለበትም ብዬ አምናለሁ በአለም አቀፍ ደረጃ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ ፣ ክትትል፣ ትብብር ያስፈልጋል። Al እስከምን መሄድ አለበት የሚለውም መወሰን አለበት ፤ የ AI ላብራቶሪዎች ፍተሻ እና ጥብቅ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ! በድጋሜ የ AI ጉዳይ አቅልለን ማየት ይቁም ባለፈውም ብያለሁ ብዙ ጊዜ እያወራን ያለነው ጥቅሙን ብቻ ነው!? እናንተስ ምን ሀሳብ አላችሁ? ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ 👇 https://t.me/miftahcode ​#AI #ArtificialIntelligence #Anthropic

photo content

Vibe Coding ምን እንደሆነ እየተነጋገርን ነው እንቀጥላለን .... ቆይ ግን .. 🤔 አንድ የሀገሬ ወጣት ምንም የኮዲንግ ልምድ ያልነበረው እና Al የፈጠረለትን እድል ተጠቀሞ ወይም በትክለኛ አጠራሩ Vibe Codingን ተጠቅሞ የሆነ ቢዝነስ ተቋም ችግርን የሚፈታ እና በትክክል የሚሰራ Aplication አዘጋጅቶ ቢያቀርብ እና ምርቱን ወደ ገበያ አውጥቶ ገንዘብ ማግኘት ቢጀምር ምን ክፋት አለው? ምንድን ነው ስህተቱ? ምንስ ያበሳጫል? እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እኛ ሀገር እኮ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ገና እኮ ነው ገና ..... የዲጀታል ክህሎት ደረጃችንን የምታዩት ነው። አይደለም the whole ማኅበረሰቡ ሶሻል ሚዲያ ላይ ያለው ፣ ስማርት ፎን የያዘው ብዙሃኑ በቅጡ መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት የለውም። የሶፍትዌር ልማት ዘርፍ እንዲያድግ ከተፈለገ ይህ ባህላችን ማደግ አለበት ፤ ብዙ በክህሎት የበቁ በተግባር የተፈተኑ ደቨሎፐሮችም መፈጠር አለባቸው። ከዘመኑ ቴክኖሎጂ እድገት እና የገበያ ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ እና አብረው የሚሄዱ ብዙ ወጣቶች ያስፈልጉናል! የዘርፉ ማነቆ ይሄ ብቻ አይደለም ሌላ ጊዜ በሰፊው እዳስሰዋለሁ። በVibe Coding የሚገቡ አዳዲስ ወጣቶች ገበያውን አያጣብቡትም ይልቁኑ ህዝቡ ቴክኖሎጂን እንዲለምድ፣ የሶፍትዌር ፍላጎት እንዲጨምር እና የቴክኖሎጂ ባህላችን እንዲያድግ ያደርጋሉ። ወደዚህ ለሚመጡ ያለኝ ምክር ዛሬ እውቀት ማግኛ መንገዱ ሰፊ በመሆኑ ጎን ለጎን ጊዜ ሰጥታችሁ መሰረታዊ እውቀቱን ብትማሩ የበለጠ ውጤታማ ትሆናላችሁ። በጥቅሉ ዘርፉ ካደገ ለሁላችንም ይበቃል! ችግሩ አለማደጉ ነው አትበሳጩ እኔ ብቻም አትበሉ ፣ የቴክኖሎጂ ለውጦችንም ካለን ስራ ጋር አጣጥሞ መሄድ ያስፈልጋል ለማለት ነው። ቴሌግራም ቻናሌን መቀላቀል ለምትሹ 👇 ↗️ https://t.me/miftahcode

Vibe coding የፈጠረው አብዮትን ሼር ማድረግህ "የሶፍትዌር ልማት ገበያውን ይገድለዋል" ነው እያለ ያለው። እውነት ገበያውን ይገድለዋል? እኔ ሼር ባላደርገውስ የተደበቀ ነው?
Vibe coding የፈጠረው አብዮትን ሼር ማድረግህ "የሶፍትዌር ልማት ገበያውን ይገድለዋል" ነው እያለ ያለው። እውነት ገበያውን ይገድለዋል? እኔ ሼር ባላደርገውስ የተደበቀ ነው?

😲 "AIን ሰከን እናድርገው?!" — ምናልባት በህልማችን ይሆናል! 😂 ይህ የSam Altman እና የDario Amodei የ(X)ትዊተር ልውውጥ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። Dario Amodei "የA
😲 "AIን ሰከን እናድርገው?!" — ምናልባት በህልማችን ይሆናል! 😂 ይህ የSam Altman እና የDario Amodei የ(X)ትዊተር ልውውጥ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። Dario Amodei "የAIን ፍጥነት ሰከን ልናደርገው ይገባል፣ 3 የውሳኔ ሃሳቦችንም አዘጋጅቻለሁ" ሲል... Sam Altman ደግሞ "እውነትህን ነው Dario! እኛም በቅርብ ሳምንታት በዚሁ ጉዳይ ስንመክር ነበር፣ ገለልተኛ ገምጋሚዎችንም እንመድባለን" ብሎ ሲመልስ ያሳያል። ምንም እንኳን በAI Safety ዙሪያ የሚደረገው ውይይት ከባድ ቢሆንም፣ ሁለቱ የኢንዱስትሪው ግዙፍ መሪዎች በአንድ ጊዜ ፍጥነታቸውን ሰከን ለማድረግ መስማማታቸው የሚያሳየው የ X ገፅ ልውውጣቸው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። እስኪ እናውራበት ፤ የAI ኩባንያዎች በእውነት ፍጥነታቸውን ሰከን ያደርጉ ይሆን ወይስ የቴክኖሎጂው ውድድር ሊቆም አይችልም? 🤔👇 የቻይናን ግስጋሴስ እንዴት ያሰክኑታል? አብረን እናያለን! 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚና አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode

ዲጂታል ዓለሙ የሰጠንን እድል እስከምን ድረስ ተጠቀምንበት? ትምህርት፣ ቢዝነስ፣ አዳዲስ ክህሎቶች... ዛሬ በቤታችን ቁጭ ብለን ማግኘት የምንችላቸው እድሎች ወሰን የላቸውም። ​ለምሳሌ እኔን ብትወስዱ ይህንን የዲጂታል ዓለም ዕድል ተጠቅሜ ፣ ለ6 ዓመታት በብዙ ፈተናዎችና ተስፋ አለመቁረጥ ውስጥ አልፌ በአሜሪካው University of the People (UoPeople) በኮምፒተር ሳይንስ የባችለር ዲግሪዬን ተመረቅኩ! ​ ዛሬውኑ የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰዱ — ኢንተርኔት ማህበራዊ ሚዲያ መጎብኛ ብቻ ሳይሆን ህይወት መቀየሪያ መሳሪያም ነው! ቴሌግራም ቻናላችንን ማግኘት ለምትፈልጉ 👇https://t.me/miftahcode

እዚህ ገጽ ላይ የምታዩት እያንዳንዱ ነገር... ​ብዙ ጊዜ ሶሻል ሚዲያ ስናስብ መረጃ ማጋራት ወይም ቁጥር (ተከታይ) መሰብሰብ ብቻ ሊመስለን ይችላል። ለእኔ ግን ይህ ገጽ ከዚያ በጣም የላቀ ዓላማ አለው! ​እዚህ የምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፡ ↗️ ​እውቀትና ሃሳብ የምንለዋወጥበት ዲጂታል ካፌ ነው፣ ↗️ ​አዳዲስ የቴክኖሎጂ እና AI እድሎችን አብረን የምንቃኝበት መድረክ ነው፣ ↗️ ​የጋራ ማህበረሰብ (Community) እና ኔትወርክ የምንገነባበት መስመር ነው! ​አላማዬ Followers መሰብሰብ ሳይሆን፣ እውነተኛ እሴት (Value) መፍጠር እና አብረን ማደግ ነው። ​እናንተስ በዚህ ገጽ ላይ በብዛት ምን አይነት ውይይቶች እና ይዘቶች እንድናበዛ ትፈልጋላችሁ? አስተያየታችሁን ኮመንት ላይ አጋሩኝ👇 ቴሌግራም ገፃችንን ለምትፈልጉ ⤵️ https://t.me/miftahcode

በተራ የንግግር ቋንቋ (NL) ብቻ እና ምንም ኮዲንግ ሳያውቁ ሙሉ የዌብ አፕሊኬሽን (Web App) በቀጥታ በብሮውዘርዎ መሥራት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ይህ "Vibe Coding" ይባላል። ነገር ግን ለAI የደንበኝነት ምዝገባ የሚጠየቀው ክፍያ ውድ ሊሆን ይችላል። ያለ ምንም የኮምፒውተር ሶፍትዌር (IDE) በቀጥታ በዌብሳይት ላይ ብቻ በነፃ መሥራት ከፈለጉ፣ ከታች የተዘረዘሩት 3 መሣሪያዎች በቀን የሚሰጡት ነፃ ዕድል (ቶክን) ጋር ለስራችሁ ወሳኝ ምርጫ ናቸው። የመጀመሪያው Bolt.new ሲሆን፣ በአንድ ቀን ረጅም ሰዓት ተቀምጠው ለሚሠሩ ሰዎች ምርጥ ምርጫ ነው። በቀን እስከ 300,000 ቶከኖች (በወር እስከ 1 ሚሊዮን) በነፃ ይሰጣል። በአንድ ከሰዓት ውስጥ ከ10 እስከ 15 ተከታታይ ትዕዛዞችን (Prompts) በመስጠት ሙሉ የፊትና የጀርባ (Full-stack) ፕሮቶታይፕ በአንድ ጊዜ ማጠናቀቅ ያስችላል። 🔗: https://bolt.new/ ሁለተኛው v0 by Vercel ደግሞ በጣም ማራኪ የሆነ የዌብሳይት ዲዛይን እና ንጹህ ዘመናዊ ገጽታዎችን (UI) ለመሥራት ወደር የለውም። ይህ መሣሪያ በቀን 7 የትዕዛዝ መልዕክቶችን በነፃ የሚፈቅድ ሲሆን፣ በየ24 ሰዓቱ የሚታደሱትን እነዚህን ዕድሎች በመጠቀም የዌብሳይትዎን የፊት ገጽታ በጥራት ማሳመርና ማስተካከል ይችላሉ። 🔗: https://v0.app/ ሦስተኛው Lovable.dev የውሂብ ጎተራ (Database) ያላቸውን ሙሉ ዌብሳይቶች በጥራት ለመሥራት አስደናቂ መሣሪያ ነው። በቀን 5 የባውንድ ክሬዲቶች (Build Credits) ብቻ ስለሚፈቅድ፣ ትልቅ ፕሮጀክትን በአንድ ጊዜ ከመሥራት ይልቅ በየቀኑ በጥንቃቄ እና በጥቂቱ እያሳደጉ ለአንድ ሳምንት ለሚሠሩ ሰዎች ተመራጭ ነው። ለነፃ ተጠቃሚዎች የሚሆን ጠቃሚ ምክር⤵️ ፕሮጀክታችሁ እያደገ ሲሄድ AI ሙሉውን ኮድ በየጊዜው ማንበብ ስላለበት የተሰጣችሁን ነፃ ዕድል በፍጥነት ይጨርሳል። ስለዚህ ሁሌም እንደምለው ትዕዛዛችሁን ግልጽ እና አጭር አድርጉ! በዚህ ሳምንት ምን ለመሥራት አቅደዋል? የሞከራችሁት እንዴት አገኛችኋቸው? ኮሜንት ላይ ያጋሩን! 👇 ከወደዱት ሼር ያድርጉት ↗️ 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode

✨ በኮዲንግ ዓለም ውስጥ አዲስ አብዮት፦ Vibe Coding! ምናባችሁን ወደ እውነታ ለመቀየር አሁን የኮድ መስመሮችን በረጅሙ መደርደር አያስፈልጋችሁም። እስኪ አስቡ አንድ ወጣት ደቨሎፐር በስክሪኑ
✨ በኮዲንግ ዓለም ውስጥ አዲስ አብዮት፦ Vibe Coding! ምናባችሁን ወደ እውነታ ለመቀየር አሁን የኮድ መስመሮችን በረጅሙ መደርደር አያስፈልጋችሁም። እስኪ አስቡ አንድ ወጣት ደቨሎፐር በስክሪኑ ፊት ተቀምጦ ለረጅም ሰዓታት እና ቀናት በሺህ የሚቆጠሩ የኮድ መስመሮችን እየፃፈ ሲታገል ይታያችሁ—አሁን ግን ሁኔታው ተቀይሯል። በ Vibe Coding አሠራር፣ የፈለጋችሁትን አፕሊኬሽን ወይም የዌብ ገጽታ በራሳችሁ/ በሰውኛ ቋንቋ (Natural Language) ቃላት አብራርታችሁ ለኤአይ (AI) ትነግሩታላችሁ ፤ ኤአይ ደግሞ ሐሳባችሁን ወዲያውኑ ወደሚሠራ ሶፍትዌር ይለውጠዋል። የእናንተ ድርሻ መሪ መሆን፣ ውጤቱን መፈተሽ እና ፍጹም እስኪሆን ድረስ ከኤአይ ጋር እየተነጋገራችሁ ማሻሻል ብቻ ነው! ይህ አዲሱ የቴክኖሎጂ ማዕበል የሶፍትዌር ልማትን ሙሉ በሙሉ እየቀየረው ነው፤ እናንተስ በዚህ አዲስ አሠራር ለመሞከር ዝግጁ ናችሁ? ለ Vibe coding የሚያገለግሉ ነፃ ቱሎችንስ ትፈልጋላችሁ? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አካፍሉን ! 👇 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚና አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode #VibeCoding #ArtificialIntelligence #TechInnovation #SoftwareDevelopment #MiftahTech

አንትሮፒክ (Anthropic) የተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ተቋም፣ የየመኑ ሁቲ አማፂያን የክሎድ (Claude) ሞዴሉን ለሚሳይል ቴክኖሎጂ ልማት ሲጠቀሙበት እንደነበር ይፋ አደረገ። ተቋሙ
አንትሮፒክ (Anthropic) የተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ተቋም፣ የየመኑ ሁቲ አማፂያን የክሎድ (Claude) ሞዴሉን ለሚሳይል ቴክኖሎጂ ልማት ሲጠቀሙበት እንደነበር ይፋ አደረገ። ተቋሙ ባወጣው የደኅንነት ሪፖርት መሠረት፣ ከታጣቂ ቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸው የጦር መሣሪያ መሐንዲሶች የኤአይ ሥርዓቱን በመጠቀም ለሦስት የተለያዩ የሚሳይል ፕሮግራሞች የሚሆን የሶፍትዌር መሪ መቆጣጠሪያ ለመሥራት ጥረት አድርገዋል። ይህ የየመኑ ቡድን የክሎድ ሞዴል ላይ የተቀመጡትን የደኅንነት ማጣሪያዎች ለማለፍ ጥያቄዎቹን "ለሕጋዊ የመከላከያ ምርምር" እንደሚጠቅሙ በማስመስል ሲያቀርብ እንደነበር ተገልጿል። ይሁን እንጂ አንትሮፒክ ለወራት የዘለቀውን ይህንን አደገኛ እንቅስቃሴ ደርሶበት አካውንቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማገዱንና ማቋረጡን አስታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋሙ በሰሜን የመን ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን መቋረጡን አልጀዚራ የዜና ወኪል አስነብቧል! በተጨማሪም ተቋሙ ከዚሁ የሁቲ ሙከራ ጋር በተያያዘ ከሩሲያ እና ከቻይና በመነሳት በኤአይ ቴክኖሎጂ የታገዙ ስድስት የተለያዩ የሳይበር እና የጦር መሣሪያ ልማት እንቅስቃሴዎችን አክሽፌያለሁ ብሏል። ይህ ክስተት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ደኅንነትና ቁጥጥር ዙሪያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ቅርብ ጊዜ ክሎድ Al ትልቅ አቅም አለው ብያችሁ ነበር ፣ አሜሪካ የኢራን ከፍተኛ አመራሮችን ላይ ጥቃት ስትሰነዝር ይሄው ቴክኖሎጂ ተጠቅማ እንዲነበር ሪፖርቶች ወጥተዋል። ከደህንነት ጋር በተያያዘ ያላቁ የ Anthropic Al ሞዴሎች በአሜሪካ ፍርድ ቤት መታገዳቸው ይታወቃል። የተመረጡ ሀገራት ላይ እንዳይሰራ የሚከለከል ጭምር ነበር። 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode

Prompt engineeringን በሚገባ እንድንረዳ የሚረዱን ሶሥት + 1 ድንቅ PDF መጽሐፍት ከወደዱት ሼር ያድርጉት ↗️ 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode

+3
Prompt engineering Author: Lee Boonstra

Vibe Coding ምንድን ነው እንዴት ይሰራል? 👇 Click me

ያለፈውን ዓመት ስህተቶች እንደ Bug ፈልገን አርመን ፣ ያተረፍናቸውን ልምዶች ደግሞ እንደ Feature አጠናክረን አዲሱን ዓመት እንጀምራለን። ገና ያልተጻፈውን የ365 ቀን ነጭ ወረቀት በምርጥ ታሪኮች፣ በትልልቅ ስኬቶች እና በታላቅ ደስታ እንሙላው። 🌼🌼🌼 ​አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የዕድገት እና የስኬት ዓመት ይሁንልን! 🌻

2018 ታሪክ ሆኗል፤ 2019 ደግሞ ገና ያልተጻፈ ነጭ ወረቀት ነው፤ በጥሩ ታሪክ እንሙላው!

Thank you! #New_milestone@miftahcode ❤️
Thank you! #New_milestone@miftahcode ❤️

በኢትዮጲያ የዘመን አቆጣጠር ዛሬ የ2018 የመጨረሻዋ ቀን! ያረብ ... እዚህ ሀገር ላይ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ ፣ ጥላቻ ስልችቶናል! ጥላቻ ጫፍ ረግጦ እርስ በርስ እያገዳደለን ይገኛል ፤ ኑሮውምንም አልቻልንም አጎብጦናል😥 ፤ የሚንገዳገድና የወደቀውም መአት ነው። 🌼🌼🌼 ያረብ ...🤲 ቀጣዩን አዲስ አመት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እንዲሁም መልካም የምንሰማበት ፤ አቅማችን የሚጎለብትበት አድርግልን! አሚን

ስህተታችንን እንደ ውድቀት ከመቁጠር ይልቅ፣ እንደ አዲስ ማንቂያና ወደ ታላቅነት መሸጋገሪያ ድልድይ ልናደርገው ይገባል።
ስህተታችንን እንደ ውድቀት ከመቁጠር ይልቅ፣ እንደ አዲስ ማንቂያና ወደ ታላቅነት መሸጋገሪያ ድልድይ ልናደርገው ይገባል።