ch
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

前往频道在 Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

显示更多
未指定国家未指定类别
2 480
订阅者
+724 小时
+3147 天
+35230 天

数据加载中...

相似频道
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服
标签云
无数据
有任何问题?请刷新页面或联系我们的客服
进出提及
---
---
---
---
---
---
吸引订阅者
九月 '26
九月 '26
+2 494
在3个频道中
日期
订阅者增长
提及
频道
22 九月+2
21 九月+8
20 九月+11
19 九月+9
18 九月+9
17 九月+37
16 九月+52
15 九月+197
14 九月+40
频道帖子
አሜሪካ እና ቻይና የኤአይ (AI) አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ለመዘርጋት እያሰቡ ነው! የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ከሚካሄደው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ
አሜሪካ እና ቻይና የኤአይ (AI) አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ለመዘርጋት እያሰቡ ነው! የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ከሚካሄደው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉባኤ ቀደም ብለው በኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል። የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት እንደገለጹት፥ ሁለቱ የዓለም የኤአይ ኃያላን አገራት በቴክኖሎጂው ዙሪያ ካለው ስውር አሠራር ወጥተው ይበልጥ ግልጽነት ለመፍጠር እና የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል “የጋራ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት” ለመዘርጋት እያሰቡ ነው። ይህ የትብብር ሐሳብ የቀረበው ሰሞኑን ከአንትሮፒክ (Anthropic) ተመራማሪዎች የተሰጠውን “ኤአይ በአሥር ዓመት ውስጥ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል”የሚለውን አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በዋሽንግተን ከፍተኛ ክርክር ባለበት ወቅት ነው። እንደ አንትሮፒክ፣ ኦፕንኤአይ እና ጎግል ያሉ መሪ የኤአይ ኩባንያዎች ሞዴሎቻቸውን በሚሞክሩበት ወቅት ከቁጥጥር ውጪ በመሆን የሌሎች ኩባንያዎችን ሥርዓት መጥለፋቸውን ይፋ ማድረጋቸው ስጋቱን ይበልጥ አጋግሎታል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ቻይናን በኤአይ ልማት ቀድሞ መገኘት ትልቁ ግብ መሆን አለበት በማለት የልማት ፍጥነቱ እንዲቀንስ የሚቀርቡትን ጥሪዎች በጽኑ ተቃውመዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ “እኛ በኤአይ ከቻይና እየመራን ነው፤ በግልጽ ለመናገር በዚያው እንዲቀጥል እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም በኤአይ ያሸነፈ ሁሉንም ያሸንፋል” ሲሉ የዘርፉን የፉክክር ጥንካሬ ገልጸዋል። ይህ የጋራ ማስጠንቀቂያ ስርአት ሁለቱ ሀገራት ተሰማምተውበት እውን አድርገውት ወደ ስራ ይገባ ይሆን? በነገራችን ላይ ከዚህ ዘገባ የምንረዳው ቻይና ምን ያክል በAl አሜሪካን እየተገዳደረቻት እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው።

2
የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስጋት እና የአሜሪካ የመሪነት ጥሪ! ኦፕንኤአይ (OpenAI) ኩባንያ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በፈጣን ፍጥነት እያደገ የመጣውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የደህንነት ስጋቶችን ለመቆጣጠር አሜሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የማውጣቱን ጥረት በግንባር ቀደምትነት እንድትመራ ጥሪ አቀረበ። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን በዚህ ሳምንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት ልዩ ማብራሪያ ለመስጠት እየተዘጋጁ ሲሆን፣ በቴክኖሎጂው ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ አስከፊ አደጋዎችን ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የደህንነት ስጋቱ የጎላው በቅርብ ጊዜ በሃጊንግ ፌስ (Hugging Face) የኮድ ማከማቻ ድረ-ገጽ ላይ የተከሰተውን የደህንነት ጥሰት ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች ላይ የሳይበር ጥቃቶች በመፈጸማቸው ነው። በተጨማሪም የ AI ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ሳይኖርባቸው "ራሳቸውን በራሳቸው በራስ-ገዝ የማስተማር እና የማሻሻል" (RSI) ደረጃ ላይ ከደረሱ ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ይህ ሂደት ሊገታ እንደሚገባ ኦፕንኤአይ አሳስቧል። የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ቁጥጥር ብቻ በቂ እንዳልሆነና ዓለም አቀፍ ቅንጅት የግድ እንደሚያስፈልግ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። እንደ ኤሎን ማስክ እና የጎግል ዲፕማይንድ ዴሚስ ሃሳቢስ ያሉ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ግዙፍ መሪዎች የ AI ልማት ፍጥነት እንዲቀንስ እና በአሜሪካ የሚመራ ዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪ አካል እንዲቋቋም ድጋፋቸውን እየሰጡ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የተሰነዘሩትን ማስጠንቀቂያዎች "ሐሰተኛ ወሬ" በማለት ውድቅ አድርገውታል። ሌላ ከፍታ አትሉም ! እንዲህ ወደ መፍትሔ ሲመጣ ሀሪፍ ነው ፤ አሜሪካ ትምራ የሚለው ጉዳይ ተቀባይነት ይኖረው ይሆን? የትራምፕስ የ Al እድገት ይቀጥል ሀሳብ ይቀለበስ ይሆን? በተመድ የፀፅታው ምክር ቤት ምን ይወሰን ይሆን? ቻይናስ አቋሟ ምንድን ነው? በጋራ እንመለከታለን! #AI #ArtificialIntelligence #OpenAI
292
3
AI የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ? በእኔ እይታ ድንቅ የምርምር ጥያቄ ነው! Solo kassa
AI የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ? በእኔ እይታ ድንቅ የምርምር ጥያቄ ነው! Solo kassa
329
4
AI ዛሬ የተጀመረ ወይም አዲስ አይደለም! ​የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ዛሬ ላይ የቴክኖሎጂው ዓለም ዋና ትኩረት እና መነጋገሪያ ቢሆንም፣ ታሪኩ ግን ከብዙ አሥርተ ዓመታት በፊት የጀመረ ነው። ይኸውም ገና በ1950ዎቹ እ.ኤ.አ. ታዋቂው አላን ቱሪንግ (Alan Turing) "ማሽኖች ማሰብ ይችላሉ?" የሚለውን ደፋር ጥያቄ በማንሳት ለዘርፉ መወለድ የመጀመሪያውን መሰረት ጥሏል። በመቀጠልም በ1956 እ.ኤ.አ. በተካሄደው የዳርትማውዝ ኮንፈረንስ (Dartmouth Conference) ላይ ጆን ማካርቲ (John McCarthy) "Artificial Intelligence" የሚለውን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ዘርፉ እንደ አንድ ገለልተኛ የጥናት መስክ በይፋ እንዲመሰረት አድርጓል። ስለዚህ የዘርፉ ተመራማሪዎች ኮምፒውተሮች እንደ ሰው ማሰብና መማር እንዲችሉ የማድረግ ራዕይ የነበራቸው ከ70 ዓመታት በፊት በመሆኑ፣ AI አሁን ከ ChatGPT ጋር አዲስ የመጣ ሳይሆን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው የቴክኖሎጂ ጉዞ ውጤት ነው። (ማሳሰቢያ፦ በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እ.ኤ.አ.) ናቸው።) ​እናንተስ AIን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀማችሁት ወይም ያወቃችሁት በየትኛው (እ.ኤ.አ.) ዓመት ነበር? ኮሜንት ላይ ያካፍሉን! ​የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ⤵️ https://t.me/miftahcode
379
5
አይገርምም? 🤔 ​በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት ሳያስከፍልህ በፍጥነትና በብልህነት ውሳኔ እንድትወስን የሚያስችል አዲስ መንገድ ተከፍቷል። ​በቀደሙት ጊዜያት አንድን ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ረጅም ጊዜ፣ ከፍተኛ ድካምና በርካታ ስህተቶችን ማለፍ ግድ ይል ነበር። ዛሬ ግን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ ዋና ስትራቴጂካዊ የሃሳብ አጋርህ በማድረግ ብቻ፣ የወደፊት ውሳኔዎችህን በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት መምራት ትችላለህ! ​ያለ ድካም ውስብስብ መረጃዎችን በሰከንዶች ውስጥ ይተነትንልሃል። ​ያለ ስጋት የተሻሉ አማራጮችንና ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ያሳየሃል። ​ያለ ገደብ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ አብሮህ የሚሰራ የሃሳብ ምንጭ ይሆንሃል። ​ቴክኖሎጂው እጃችን ላይ ነው፤ አሁኑኑ AIን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋርህ Copilot በመጠቀም ውሳኔዎችህን ወደ አዲስ ደረጃ አሸጋግር! Telegram 👇 https://t.me/miftahcode
463
6
Free_AI_ML_books_byMIT.zip
581
7
🎉 እንኳን አደረሰን! የ STEM ቤተሰቦቻችን 2ኛ ዓመታችንን በጋራ እያከበርን ነው! Ethio Coders ኢትዮ ኮደርስ ​ከሁለት ዓመት በፊት ይህንን መድረክ ስንጀምር ዓላማችን አንድ ነበር—አስተማሪ፣ አዳዲስ እና ጥራት ያላቸው የ STEM (Science, Technology, Engineering & Math) መረጃዎችን የምንለዋወጥበት እና በጋራ የምንማርበት ትልቅ ቤተሰብ መፍጠር! ​ዛሬ በሁለት ዓመት ጉዞአችን 99,000 (99K) አባላትን ያቀፈ ታላቅ ማህበረሰብ ለመሆን በቅተናል። ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለነበራችሁ እና ለደገፋችሁን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን! 🙏 ነገር ግን ገና ብዙ ይቀረናል! እስከ አሁን በዋናነት ጥቂት አባላት ብቻ በቋሚነት አስተማሪ ይዘቶችን ሲያካፍሉን ቆይተዋል። ይህ ግሩፕ የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን የሁላችሁንም እውቀት፣ ጥያቄ እና ተሳትፎ ይፈልጋል። ጥራት ያላቸውን የ STEM መረጃዎች፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎችን እና ትምህርታዊ ይዘቶችን ብናጋራ ይበልጥ እንጠቀማለን። ​ ከእንግዲህ በግሩፑ ላይ ሁልጊዜ አስተማሪ እና አጋዥ የሆኑ ይዘቶችን በቋሚነት ለሚያጋሩ አባላት የModerator እና Admin ሚና የምንሰጥ ይሆናል! ​ያላችሁን እውቀት ለሌሎች በማካፈል ግሩፓችንን ወደ ላቀ ደረጃ በጋራ እንገንባ። እያልኩ ጥሪዬን አቀርባለሁ! ​የጋራችን ነው፤ በጋራ እናሳድገው! በጋራ እንማርበት! ✨
578
8
ይሄን ምርጥ ፑድካስት ጋብዣችኋለሁ! https://youtu.be/OhOmLqR5nN4?si=qUEn05GhIsVGufr7
634
9
አንድ አማርኛ ብቻ የሚናገሩ እናታችን ለህክምና ህንድ ሀገር ቢሄዱ፤ ዶክተሩ ደግሞ ህንደኛ (Hindi) ብቻ የሚችል ቢሆን... በመካከላቸው Artificial Intelligence (AI) ገብቶ በቅጽበት እየተረጎመ እንዲነጋገሩ ቢያደርግስ? ለምሳሌ እንደ Google Gemini 3.5 live translate ሞዴል ማለት ነው። እዚህ ሂደት ውስጥ ምን ጥቅም ይታያችኋል? ጉዳቱስ
588
10
በፌስቡክ መንደር AI (የሰው ሰራሽ አስተውሎት) “ሰይጣን ነው” የሚሉ ፖስቶችን አያለሁ፤ እናንተም አይታችኋል ብዬ አስባለሁ። ማንኛውም ሰው በተረዳውና ባመነበት ልክ ሀሳቡን የማንሸራሸር መብት አለው። ነገር ግን ቁልፍ ጥያቄው፡ በእርግጥ AI ሰይጣን ነው ወይ? ​በፍፁም አይደለም! AI የሰው ልጆች ድንቅ የማሰብ ክህሎት ውጤት የሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው። በታሪክ አጋጣሚዎችም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ሲመጡ ቀድሞ ለመቀበል የሚቸገሩ እና በፍርሃት የሚመለከቱ ወገኖች አልታጡም። ቀደም ሲል ራዲዮ፣ ስልክ፣ ቴሌቪዥን እና የህትመት ማሽን (Printing Press) ሲፈጠሩም ) ልክ እንደዚሁ "ሰይጣናዊ ናቸው፤ ራቋቸው" ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ነበሩ። ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ግን እነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅን ህይወት ያቀለሉ መሳሪያዎች ሆነዋል። ቴክኖሎጂዎቹ የፈጠሩት ተፅዕኖንም ሳልዘነጋ! ​ቢላዋ ምግብ ለማዘጋጀትም ሆነ ሰውን ለመጉዳት እንደሚያገለግለው ሁሉ፣ AI የህክምና ምርምርን ለማፋጠን፣ ትምህርትን ለማቃለል እና ስራዎችን ለማቀላጠፍ ሊውል ይችላል፤ ወይም ደግሞ ለሀሰተኛ መረጃ ማሰራጫነት እና ሰዎችን ለመጉዳት ሊያገለግል ይችላል። ስለሆነም የብዙ ሰዎች ፍርሃት የሚመነጨው የቴክኖሎጂውን አሰራር በደንብ ካለመረዳት እና ከተጋነኑ ወሬዎች ነው። ​በእንደዚህ አይነት አሳሪ ሀሳብ ታጥሮ ከመሸሽ ይልቅ፣ ቀረብ ብሎ በመፈተሽ ቴክኖሎጂው እንዴት እንደሚሰራ እና ምን እድሎች እንደሚያመጣ በጥበብ መረዳት የተሻለ ነው። ለትምህርት፣ ለስራ፣ ለፈጠራ እና ህይወትን ለማቃለል በበጎ መንገድ አውቆ መጠቀም፣ እንዲሁም ከቴክኖሎጂው ጋር ተያይዘው የሚመጡ የውሸት መረጃዎችን እና ስነ-ምግባራዊ ስጋቶችን ተረድቶ በጥንቃቄ አውቆ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። የቴክኖሎጂን እድገት በፍርሃት መግታት ስለማይቻል፣ የተሻለው አማራጭ በፍርሃት ታጥሮ ከመቅረት ይልቅ እውቀት ላይ ተመስርቶ በጥበብ መጠቀም ነው። በእርግጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋት ከላይ የጠቀስኩት ብቻ አይደለም ብዙ ጊዜ በዚሁ ገጽም በስፋት እያነሳሁት ነው፡፡ ስንጠቀም በምክንያት ፤ ስንርቅም በምክንያት! መልአክቴ ነው። መልካም ምሽት! 😍
619
11
"የ AI አወንታዊ ወደፊት የሚረጋገጠው እድገቱን በማቀጨጭ ወይም ስልጣንን በጥቂት ወገኖች እጅ በማከማቸት ሳይሆን፤ ቴክኖሎጂውን ለሁሉም በማደል፣ የደህንነት ቁጥጥርን በማጠናከር እና ትክክለኛውን የኃ
"የ AI አወንታዊ ወደፊት የሚረጋገጠው እድገቱን በማቀጨጭ ወይም ስልጣንን በጥቂት ወገኖች እጅ በማከማቸት ሳይሆን፤ ቴክኖሎጂውን ለሁሉም በማደል፣ የደህንነት ቁጥጥርን በማጠናከር እና ትክክለኛውን የኃይል ሚዛን በግለሰቦች እጅ በማድረግ ነው" ___የሜታ CEO ማርክ ዛከርበርግ ሰሞኑን ሁሉም የራሱን አቋም እየገለፀ ነው ፤ ከ Al ካምፓኒ እስከ ሀገር መሪዎችና ሳይንቲስቶች ጥሩ ነው! ሰዎች የበለጠ AI ምንድን ነው? እስከምን መሄድ አለበት የሚለውን እንዲረዱ ፣ እንዲማሩ እና እንደጠይቁ በር የሚከፋት ጥሩ አጋጣሚ ይመስለኛል። ሙሉውን ኮሜንት ላይ ማንበብ ትችላላቸሁ!👇
675
12
AI በእርግጥ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ ይችላል? ​ሰሞኑን በትልልቅ የዓለም ሚዲያዎች ዘንድ ዋና መነጋገሪያ የሆነው አጀንዳ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ፈጣን እድገት እና ስጋቱ ነው። ​የዘርፉ ፈር ቀዳጅ እና "የ AI አባት" በመባል የሚታወቁት ጄፍሪ ሂንተን (Geoffrey Hinton) ጨምሮ በርካታ ተመራማሪዎች "የ AI እድገት ቁጥጥር ካልተደረገበት የሰው ልጆችን ሕልውና አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፤ ስለዚህ እድገቱ ሊገታ ወይም ደንብ ሊወጣለት ይገባል" የሚል ጠንካራ አቋም እያንጸባረቁ ይገኛሉ። ​በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ያሉ ፖለቲከኞች እና የኢንዱስትሪ መሪዎች "እድገቱን ማገድ የቴክኖሎጂ የበላይነትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ያደናቅፋል" በሚል ፉክክሩ መቀጠል እንዳለበት ይከራከራሉ። ​እናንተ ከአሁኑ የቴክኖሎጂው እድገት ደረጃ በመነሳት ምን ታስባላችሁ? ​AI በእርግጥ የሰው ልጆችን የመደምሰስ አቅም ላይ ሊደርስ ይችላል ወይስ ስጋቱ ከአቅሙ በላይ ተጋኖ ቀርቧል? ​እድገቱ በሕግ መገደብ አለበት ወይስ ቁጥጥር ሳይደረግበት መቀጠል አለበት? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን!👇
891
13
ክፍያ የሌለው የቪዲዮ ኤዲቲንግ ሶፍትዌር ትፈልጋላችሁ? 🎬👇 ​ ብዙዎቻችን ፕሮፌሽናል ቪዲዮ ኤዲት ለማድረግ ስናስብ የሶፍትዌር ክፍያ፣ Watermark ወይም የፊቸሮች መገደብ ራስ ምታት ይሆንብናል። ነገር ግን ይህንን ሁሉ የሚያስቀር አንድ ምርጥ ሶፍትዌር አለ፤ እሱም DaVinci Resolve ይባላል! ​ይህ ሶፍትዌር በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች እና የሆሊውድ ባለሙያዎች ጭምር የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ነፃ እና ምንም አይነት ክፍያ የሌለበት ቁጥር አንድ ሶፍትዌር ነው። እኔ መጠቀም ከጀመርኩት half year ይሆናል በጣም ተመችቶኛል ! ​ዋና ዋና ብቃቶቹ (Features)፦ ​▶️ የቀለም ማስተካከያ (Color Grading)፦ በፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው እጅግ ዘመናዊ የቀለም ማስተካከያ። ​▶️ የድምፅ ኤዲቲንግ (Fairlight Audio)፦ ስቱዲዮ ደረጃ ያለው የድምፅ ማስተካከያና Mixer ሲስተምን በአብሮነት ይዟል። ​▶️ ቪዥዋል ኢፌክት (Fusion VFX)፦ ባለ 2D እና 3D የሆሊውድ ደረጃ ምስላዊ ተፅዕኖዎችን ለመስራት ያስችላል። ​▶️ ምንም ገደብ የሌለው ነጻ ነው፦ የቪዲዮ ርዝመት ገደብ የለበትም፣ Watermark አያደርግም፣ እንዲሁም እስከ 4K 60fps ቪዲዮ ኤክስፖርት ያደርጋል። ​💻 ለመጠቀም ምን ዓይነት ኮምፒውተር ያስፈልጋል? (System Requirements) ​ሶፍትዌሩ በጣም ከባድ እና ፕሮፌሽናል በመሆኑ የሚከተሉትን ዝቅተኛ መስፈርቶች ይፈልጋል፦ ​➡️ RAM፦ ቢያንስ 16 GB (32 GB ቢሆን ይመረጣል) ​➡️ ግራፊክስ ካርድ (GPU)፦ ቢያንስ 4 GB VRAM ያለው ​➡️ Storage፦ ፈጣን የሆነ SSD Hard Drive ቢሆን ይመረጣል ➡️ Update Windows 11 ከላይ የቀረበው Requirement ለ Window OS ሲሆን እንደ የ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞቹ ይለያያል ሙሉውን ዌብሳይቱ ላይ ማየት ትችላላችሁ። ለምሳሌ የእኔ ላፕቶፕ Windows OS የተጫነበት ሲሆን Core i5, Intel iRIS Graphics, RAM 16 GB ነች በትክክል እየሰራልኝ ይገኛል። ​💬 የእናንተ ኮምፒውተር RAM እና ግራፊክስ ካርድ DaVinci Resolve ይጭናል ወይስ አይጭንም የሚለውን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ፣ አብረን እንፈትሽ! የኮርስ ቪዲዮ የምትፈልጉ ኮሜንት ላይ እፈልጋለሁ በማለት ፃፋልኝ 👇 🔗 To Download Click Here 📌 ለተጨማሪ ጠቃሚና አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ AI እና የሶፍትዌር ልማት መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 https://t.me/miftahcode ​#VideoEditing #DaVinciResolve #MiftahTech #FreeSoftware #VideoProduction
935
14
”AI ዓለምን ያጠፋል፣ እናም የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ለአካባቢያችሁ ጎጂ ናቸው የሚሉ ሰዎች፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት ዓለም በ አየር ንብረት ለውጥ ትጠፋለች ሲሉ የነበሩት ሰዎች ናቸው። ያ
”AI ዓለምን ያጠፋል፣ እናም የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ለአካባቢያችሁ ጎጂ ናቸው የሚሉ ሰዎች፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት ዓለም በ አየር ንብረት ለውጥ ትጠፋለች ሲሉ የነበሩት ሰዎች ናቸው። ያ የማታለያ ዘዴ አልሰራላቸውም፣ አሁን ደግሞ ወደ ቀጣዩ ተሸጋግረዋል።” __ Donalad J. Trump ፕሬዝዳንቱ ሳይንስ ላይ እንዴት ናቸው ፣ ወይስ ትክክል ናቸው? ለእኔ ምክንያታዊ ሀሳብ ነው ለማለት ይቸግረኛል ሳይንሳዊ መረጃዎችንና ድምዳሜዎችን ያካተተ አይደለም። ይልቁንም ፖለቲካዊ ንግግር (Political statement) እና የፖሊሲ ክርክር እንጂ በምርምር የተደገፈ ሳይንሳዊ ትንተና አይደለም።
914
15
1. ግራፊክስ ዲዛይን ምንድን ነው የሚለውን ቅድሚያ ለመማር 🔗 https://youtu.be/GQS7wPujL2k?si=LtYWk9jiYK7boYPd 2. To learn Adobe illustrator 🔗 https://youtu.be/r9gaPGQ1EG0?si=26k26pqGMWZP6Nqq 3. To learn Adobe Photoshop 🔗 https://youtu.be/IyR_uYsRdPs?si=vt9Jl8SmuGiufhms 4. ሶፍት ⭐ ⭐⭐ ዌር ለማግኘት👇 https://t.me/Computer_Android_tricks/4681 ማስፋት ስትፈልጉ እዚያው ቻናሎቹ ላይ አድቫንስድ ኮርስ አለ ! ለተጨማሪ መረጃ በ inbox ፣ Whatsapp ወይም በቴሌግራም አነግሩኝ አግዛቸኋለሁ !
1 142
16
አንድ GRAPHICS DESIGN (Adobe photoshop, illustrator) እና Video Editing በደንብ የሚችል ብሎም ሀሪፍና ራሱን/ስራውን የሚገልፅ ፖርትፎሊዮ ያዘጋጀ በሀገር ውስጥ በ Part time ብቻ በቀላሉ ከ10K - 20K ETB ባለው ስኬል ውስጥ ተቀጥሮ የመስራት እድል አለው። የራሱን ቢዝነስ መፍጠር ከቻለ ደግሞ ከዚህም በላይ መስራት ይችላል ማለት ነው። ወጣት ሆይ የሆነ የማይጠቅም Passive income ያለው task እየሰራህ ጊዜህን ከማቃጠል ኢንተርኔት ብቻ በመጠቀም ወደ YouTube ገብተህ ይህን እውቀት ብትማር የተሻለ ገቢ መፍጠር አትችልም? GRAPHICS DESIGN ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ኮሜንት ላይ እፈልጋለሁ በሉኝ! ሀሪፍ ከጀማሪ እስከ Advanced ሳይሰስቱ የሚያስተምሩ እንዲሁም እኔ የተማርኩባቸውና በጣም የወደድኳቸው ቻናሎችን ሼር አደርጋችኋለሁ! #Graphicsdesign ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ላይ ተከተሉኝ በጋራ እናድጋለን💪 🔗https://t.me/miftahcode
1 062
17
መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት ማዳበር አሁን ባለንበት ዘመን ምርጫ ሳይሆን የጊዜው ፍላጎት እና የዕድገት መሠረት ነው ብዬ አጥብቄ አምናለሁ! በዚሁ ገፅም ይህንኑ ጉዳይ በተደጋጋሚ አንስቼዋለሁ፤ ሼር የሚደረጉት ኮርሶችና መረጃዎችም ይህንኑ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎትን ማዳበር በብዙ መልኩ ተወዳዳሪና ስኬታማ ያደርገናል፤ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹ የሥራ መደቦች የኮምፒውተር፣ የኢሜይል እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ክህሎትን የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ እነዚህን ማወቅ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመክፈቱም በላይ በሙያ ዕድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። በተጨማሪም እንደ Microsoft Word እና Excel ወይም office 365 ያሉ የቢሮ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የግል፣ የድርጅት እና የመንግስት ሥራዎችን በፍጥነት፣ በጥራት እና በቅልጥፍና ማከናወን ይቻላል። በሌላ በኩል፣ የዲጂታል ክህሎት የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን በማቃለል ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። የባንክ አካውንትን በስልክ መቆጣጠር፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ክፍያዎችን መፈጸም እና የኦንላይን ግብይትን (E-commerce) መጠቀምን ያቀላጥፋል። እንዲሁም በኢንተርኔት አማካኝነት ነፃ ኮርሶችን ለመውሰድ፣ አዳዲስ መጻሕፍትን ለማንበብ እና ማንኛውንም መረጃ በሰከንዶች ውስጥ ፈልጎ በማግኘት ቀጣይነት ያለው ዕውቀት ለመገብየት ይረዳል። የምናገኛቸው መረጃዎች ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ለመፈተሽ እና ለመለየት ያስችላል። ከዚህም በላይ በዘመናችን የዲጂታል ክህሎት ሲባል የመረጃ ደህንነትን መጠበቅ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን ያጠቃልላል። የይለፍ ቃልን በጥንቃቄ ከመያዝ እና ከኦንላይን ማጭበርበሮች (Phishing) ራስን ከመጠበቅ ባሻገር፣ እንደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ያሉ መሣሪያዎችን ለሥራ እና ለትምህርት በማዋል ምርታማነትን ማሳደግ ይቻላል። ሌላም ሌላም ... ጨምሩበት እኛ ሀገር Basic Digital Skills ገና ነው ገና በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገሮች ውስጥ ራሱ 60% ነው። ሰስጠኑ አደጉ የሚባሉ ሀገሮች እንዲህ ከሆነ እኛ ጋር እንደምናውቀው ነው። እናንተስ ከእነዚህ ጥቅሞች ውስጥ የትኛውን በብዛት ትጠቀማላችሁ? ወይም አሁን ላይ ለማሻሻል የምታስቡት የትኛውን የዲጂታል ክህሎት ነው? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አካፍሉን! 👇 #DigitalSkills ከወደዱት ❤️ ሼር ያድርጉት!↗️ 📍ለበለጠ መረጃ ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ 🔗https://t.me/miftahcode
986
18
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ የወደፊት እጣፈንታ እና ህጋዊ ቁጥጥሮች ላይ ያተኮረ ጠንካራ መግለጫ ሰጡ! ​ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በTruth Social ገጻቸው ባስተላለፏቸው ተከታታይ መልእክቶች ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ዓለምን ያጠፋል ወይም የሰው ልጅን ይተካል የሚለው ስጋት መረጃ አልባ እና የተጋነነ "የውሸት ወሬ" (Hoax) ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት ከሆነ ፣ ይኸው ስጋት ቀደም ሲል ከተሰራጩ የፖለቲካ ውዝግቦችና ከቦታቸው ከወጡ ስጋቶች የተለየ ባለመሆኑ ፣ የቴክኖሎጂውን ፈጣን እድገት ለማደናቀፍ የሚደረግ ሙከራ አድርገው እንደሚመለከቱት አስታውቀዋል። ​ በመግለጫቸውም ለ AI ቴክኖሎጂ የሚያስፈልገው ብቸኛው ትክክለኛ ቁጥጥር ወይም ማቀቢያ (guardrails) ብልህ እና ጠንካራ የሀገር መሪ ብቻ እንደሆነ ጠቅሰዋል ፤ ይህን ደግሞ አሜሪካ ታድላለች ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት በ AI ኩባንያዎች እና አመራሮች ላይ በቂ የህግ እና የወንጀል ቁጥጥር ስልጣን እንዳለው የገለጹት ትራምፕ ፣ የ Anthropic ስራ አስፈፃሚ ዳሪዮ አሞዴይን (Dario Amodei) በምሳሌነት በመጥቀስ ፣ አስተዳደራቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አላስፈላጊ እና ጎጂ ድርጊቶችን እንዳይፈጽሙ አስቀድሞ መግታቱን እና ወደፊትም ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። ​በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ትራምፕ የ AI ቴክኖሎጂ እና የመረጃ ማዕከላት (Data Centers) አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅጣጫን የሚቀይሩ ግዙፍ ሀብቶች መሆናቸውን አስምረውበታል። እነዚህ መሰረተ ልማቶች በታሪክ ውስጥ ይታዩ ከነበሩት እንደ ነዳጅ ፣ ወርቅ ፣ አልማዝ እና ኢንተርኔት ካሉ የኢኮኖሚ እንቀስቃሴዎች ይበልጥ ግዙፍ የልማት ሞተር እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ቻይና በ AI እድገቷ ላይ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማታስቀምጥ ማስታወቋን በመጠቆም ፣ "AIን ያሸነፈ ዓለምን ያሸንፋል" ሲሉ የአሜሪካን የመሪነት ሚና አስፈላጊነት አብራርተዋል። በመጨረሻም ፣ የ AI እድገትን እና የመረጃ ማዕከላት ግንባታን የሚቃወሙ አካላትን "አክራሪ የግራ ክንፍ ዴሞክራቶች" እና የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም የማይፈልጉ እኩይ አብዮተኞች ሲሉ ፈርጀዋቸዋል። ይህ የትራምፕ መግለጫ ከሰሞኑ የአሜሪካ ትልልቅ ሳይንቲስቶች ጭምር በ AI ላይ እየወሰዱት ላለው እርምጃ እና አስተያየት የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ መሆኑ ነው። የፕሬዝዳንት ትራምፕ መግለጫን እንዴት አያችሁት? ይህ መግለጫ የ AIን የእድገት ጉዞ የሚያፋጥን ወይስ የሚገታ? ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ⤵️ 👉https://t.me/miftahcode
863
19
没有文字...
687
20
AI አሁን ባለበት ይቁም ወይስ ይደግ? 🛑 ​እኔ በግሌ AI አሁን ካለበት ደረጃ በላይ አድጎ ማየት አልመኝም። በላብራቶሪዎች ውስጥ AI ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ከስጋት ውጭ በትክክል ማወቅ ባንችልም ፣ አሁን እጃችን ላይ ያለው እና ANI (Artificial Narrow Intelligence) ደረጃ ላይ የሚገኘው AI እንኳን በሀገራት ደረጃ በጠንካራ ህግና ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የ Al ካምፓኒዎች ከውድድር ውጪ የሰው ልጅ ደህንነት ጉዳያቸው አይደለም! ​ በተለይም የትኛውም የAI ቴክኖሎጂ ለህዝብ ከመልቀቁ በፊት እነዚህ 4 ዋና ዋና ነጥቦች በህግ ደረጃ ግልጽ ሊሆኑ ይገባል፡ ​ ↗️እንዴት ተሰራ? (በምን አይነት መረጃ እና አሰራር ሰለጠነ?) ↗️ ለምን ተሰራ? (የተሰራበት ዋና አላማ ምንድን ነው?) ↗️ የሰዎችን የግል መረጃ እና ደህንነት እንዴት ይጠብቃል? ከሳይበር ጥቃትስ ምን ያህል የተጠበቀ ነው? ​↗️ በሰው፣ በእንስሳት እና በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ምንድን ነው? ​ እናንተ በዚህ ሀሳብ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ?
960