Genesis Within
Відкрити в Telegram
Thoughts • Life • Everything in between — Literary Works — ◇ Genesis Z.◇ Because a person's life isn't one-dimensional 😉
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
248
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-130 днів
Архів дописів
I was dangerously close to naming names here 😮💨
—^—^—^—^—^—^—^—^—^—
Forward it here since there are a bunch 😭😭
As a channel, we needed to look like those channels doing this ... Hope you’re not tired of them.😂😂
Repost from N/a
https://www.myinstants.com/en/index/et/
Trending sounds store 🤟
If there's any tiktoker here
በቁመት መመካትእናንት ቁመተ-ለግላጎች ሆይ፤ በምድር አጫዋቾች ላይ ልባችሁ ስለምን ይታበያል? በአንድ ወቅት አጥሮ የነበረ፣ በጊዜ ሂደት ረዝሞ ክንድ ሲያዘረጋ አይተናል። ደግሞም በርዝመቱ የሚስተካከለው ያልነበረው፣ ጊዜ ሚዛን ነውና ባልንጀሮቹ በልጠውት ሲገኙ ተመልክተናል። (በገዛ መስፈርታችሁ ሰፍራችሁ ራሳችሁን ለፈረጃችሁ፣ ወይም ደግሞ በእርግጥም በአንጻራዊነት ሆናችሁ ለምትገኙ...😁) ይህ ለውጥ ሁልጊዜ የማይከሰት ቢሆን እንኳ፣ “ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም” የሚለው ብሒል ለዚህ ጉዳይ አይነተኛ ማሳያ ነው ። በሁለቱ ጫፎች (በረጃጅሞችና በአጭሮች) መካከል የምንገኝ እኛ "መካከለኛዎቹ"፤ በሁለቱም ጎራ ያላችሁ ወገኖች በመግባባትና በመከባበር እንድትኖሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ይህ ጽሑፍ ከግፉዓን ጎን የቆመ ቢመስልም፣ ዋና ዓላማው ግን መካሰስና መተራረብ ቀርቶ ሁሉም በሰላምና በፍቅር እንዲኖር መሻት መሆኑ ይሰመርበት።😌 (ከህይወት ተሞክሮ የተቀመረ ቁም ነገር አዘል መጣጥፍ 😅😅😅) #PressRelease @GenesisSpeaks
ዛሬ ማንን እንዳገኘሁ አታምኑም! 😁
"ምን ልሁንልሽ… ምን ትሆኚልኝ?"
ለማታውቋቸው፣ እኚህ ሰው በቲክቶክ መንደር ታዋቂ ሰው ናቸው። ለበዓል እረፍት ብዬ ወደ ደብረ ብርሃን ባመራሁበት አጋጣሚ እኒህን ትልቅ ሰው አገኘኋቸው! ለካስ የዚያው አካባቢ ሰው ኖረዋል፤ atleast እኔ ያገኘኋቸው እዛው ነው። በጣም የሚገርም አጋጣሚ ነበር።
እኔ ቀድሜ ሰላም አልኳቸው፤ እሳቸውም በፈገግታ የታጀበ ሞቅ ያለ ሰላምታ መለሱልኝ። ከቤተሰብ ጋር ባልሆን ኖሮ ፎቶ ተነስተን እልክላችሁ ነበር! 😭😭 እሳቸው ግን አድናቂዎቻቸው እንደበዙ ስለተረዱ መሰለኝ፣ ለቤተሰቦቼ ሁሉ በመደዳ ነበር ሰላምታ የሰጡት። የሚገርመው ግን ቤተሰቦቼ "ታውቃቸዋለህ እንዴ?" ብለው እስኪጠይቁኝ ድረስ ማንነታቸውን አላወቁም ነበር። እኔም የቲክቶክ ዝነኛ መሆናቸውን ስነግራቸው ተደነቁ።
በውነቱ ... እንኳን ለበዓል መጣሁ! እንኳንም ዛሬ class አልነበረ! 😅
It was such an unexpected encounter.#GuessWhoIRanInto @GenesisSpeaks
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ፣ ሚዳቋ ጸለየች... ‹‹አውጣኝ! አውጣኝ!›› አለች፣ ለፈጠራት ጌታ። ነብሩም ተርቦ፣ ወደ አምላኩ ቀርቦ፣ ሚዳቆዋን አይቶ፣ አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ፣ ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ። የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ፣ ጸሎታቸውንም ሰማቸው ፈጣሪ፤ አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት፦ ‹‹እሩጠሽ አምልጪ ከበረታው ጠላት።›› ነብሩንም አለው፦ ‹‹እሩጥ ተከተላት፣ ምግብህ አርገህ ብላት።›› ሚዳቆዋ ስትሮጥ፣ ከነብር ለማምለጥ፤ ነብሩም ሲከተላት፣ ሆዱን ሊሞላባት። ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ፣ ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ፤ ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር፣ ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር። ‹‹አውጣኝ›› ያለው ወጥቶ፣ ‹‹አብላኝ›› ያለው በላ፤ ሳይጸልይ ያደረው ከርከሮ ተበላ!https://telegra.ph/ሳይጸልዩ-ማደር-04-13 #StoryTime @GenesisSpeaks
